cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Venue

መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር! : መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

Show more
Advertising posts
2 149Subscribers
+224 hours
+107 days
+3830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ላጥ ላጥ እያልን ስንሄድ የምናይ ነው ኮ ምንመስለው... ለማንኛውም በዝናብ እየተራመድን ብናልፋችሁ ለምን ዘጋችሁኝ አይባልም😑 ሲጀመር እንዲህ ነው የሚታየን😂 (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13
Show all...
😁 4
እባክዎትነ በአረንጓዴ የተሰመረባቸውን ይመልከቱ🙄 @Venuee13
Show all...
🥰 3
በአዲስ ፅሁፍ እስከምንገናኝ ድረስ ለሁላችሁም መልካሙን ተመኘሁ። ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏
Show all...
1
#ኡራዝ_ቪ (አብዱልሀኪም ሰፋ) ሁለት ወደ ኋላ: አንድ ወደፊት! 7/9/16 እንደ አላህ ፍቃድ መነበብ ይጀምራል። : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
🔥 4
* ቅንፍ * አብዱልሀኪም ሰፋ ( ክፍል ሰባት) : የአደጋውን ሂደት የሚከታተሉ መርማሪዎች በእለቱ ከነበሩት ሰዎችና በአቅራቢያ አደጋውን የተመለከቱትን ሰዎች ቃለ መጠይቅ እያደረጉላቸው ነው። ከተጠያቂዎቹ መካከል አንዲት ሴት በእምባ እያስደገፈች ምሬቷን ትገልፃለች " እኛ መንግስት ባለበት ሀገር ውለን መግባት አልቻልንም … ህ…እ… ባለቤቴ ከሞተ አሁን ልጆቼን ምን ላደርጋቸው ነው???… ንገረኝ እስቲ !!! እናንተ ይህንን ለወሬ ማጣፈጫ ብላችሁ መዝግባቹ ከመሄድ በዘለለ ምን ትፈይዱልኛላቹ???… ትራፊክ ፖሊሶቹ መኪናውን አጀቡት እንጂ ምን ያረጉት ነገር አለ…ህ…እ… " እያሉ እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው " ምንም ላታመጣ አታስለፍልፈኝ… ፍትህ… ሰማህ አደል !!!… እያንዳንዱን ይዛቹ ፍትህ አሰጡኝ ፍትህ… ዎ…ይ… ኧረ !!!…የሰሚ ያለህ ዎ…ይ " እያሉ ከቅድሙ ይበልጥ አምርረው ለቅሷቸውን ቀጠሉ። መርማሪ ፖሊሱ መናገር አቅቶት መዝገቡን አጣጥፎ ተነሳ። : : ጀሚል በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው። የሀሽሽ ደንበኝነቱን አጥቷል በዛ ላይ የዛሬውን አደጋ ሁሉም ለየት ያለ ትኩረት ስለሰጠው አሳስቦታል። ከምንንም በላይ እቤቱ ያዘጋጀው የነበረው መጠነኛ ሀሽሽ እንዳይገኝበት ሰግቷል። ይህን ሁሉ በሰመመን እያሰላሰለ ሲሻለው ምን ማድረግ እንዳለበት ያስባል። ሆስፒታል የተጠራበት ምክንያት በውል ባይረዳም ማወቅ ግን ፈልጓል። ቶሎ አገግሞ ወደ ነበረበት መመለስ ጓጉታል ይህ ግን ከደረሰበት ጉዳት አንፃር በቀላሉ የማገገሙ ነገር ጊዜ ይወስዳል። : : የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በለቅሶ ሲያቀልጡት የነበሩ አንዲት እናት የፈሩት አልቀረም ልጃቸውን በሞት ተነጥቀዋል። አንዱ ልጃቸው ደግሞ በሞትና በህይወት መሀል እየታገለ ነው። እኚህ እናት በምድር ላይ አሉኝ ከሚሏቸው ሁለት ነውጠኛ ልጆቻቸው መካከል አንዱን አጥተው አንዱን ፈጣሪ እንዲያተርፍላቸው መቀነታቸውን አጥብቀው በእምባ ታጅበው ልመናቸውን እያደረሱ ነው። ፑል ቤት ከነበሩት ልጆች መሀል በተነሳው ፀብ ምክንያት ሳሚ ያገኘውን የፑል ስቲክ ( ዱላ) አንስቶ የመታው ልጅ የእኚህ እናት ልጃቸው ነበር። ገና ያልጠና ወጣት የ 9 ኛ ክፍል ተማሪ ነበር። ያለ እድሜው ከእድሜው በላይ ተንጠራርቶ ቁማር በሚባል ትብታብ ተጠፍንጎ ለእናቱም ሳይረባ ሀዘንና ቁጭት አከናንቧቸው መኖር ሳይጀምር ይቺን ዓለም ተሰናበታት። በአደጋው ወቅት አደጋው እንደተፈጠረ ዶክተሮቹ ወደ ጀሚል የደወሉት በአጋጣሚ ሳይሆን ከኪሱ አውጥተው የተመለከቱትን ዋሌት ፎቶ በስልኩ ላይ ከተመዘገበው ስልክና ፎቶ ተመሳስሎ ስላገኙት ነበር። እንደዛ ሆስፒታሉን በዋይታና ለቅሶ ሙሾ የሚያወርዱት የጀሚል እናት ወይዘሮ ሸምሲያ ናቸው። : : ሳሚ ተጣልተው ከነበሩት ልጆች መሀል የመሞቱን ዜና ሲሰማ ልቡ በፍረሀት ራደ። በተኛበት የሚያደርገው አሳጥቶት ጭንቅ ጥብብ ይላል። " ወይኔ ሳሚ በቃ ልታሰር ነው ማለት ነው???… አሁን ምናባቴ ላደርግ ነው??? አምላኬ አደራህን ከጉድ አውጣኝ " እያለ ከራሱ ጋ ይሞግታል። በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ዘብጥያ መውረዱን ሲያስብ ያንገሸግሸዋል ። " እድሜ ልኬንማ እስር ቤት አልማቅቅም !!! የመጣው ቢመጣ ምንም ነገር አድርጌ ማምለጥ አለብኝ " ይላል። በሀሳቡ ውስጡን እያጀገነው አካሉን ግን ወኔ መስጠት ከብዶት መልሶ ተስፋ ይቆርጣል። " እንደዚ ሆኜ እንኳን አንድ ሰው ሊጠይቀኝ አይመጣም??? ውድ ጓደኛዬ የምለው ቢንያሚን እንኳ የታል??? ሁሉም ባዶ!!! የገዛ ወላጆቼ የጨከኑብኝ ጓደኛዬ ባያዝንልኝ አይገርመኝም " እያለ መልሶ በራሱ ሀሳብ ውስጥ ይገባል። ከሳሚ ጋር ሲጣሉ የነበሩት ቀሪዎቹ ሶስት ወጣቶች ዱካቸው ጠፍቷል። የቀረው ብቸኛ ሰው ሳሚ ብቻ ነው። ዶክተሮቹ የሆነውን ሁሉ ለፖሊሶቹ ሪፖርት ስላደረጉ ፖሊሶች የሳሚን መንቃት ብቻ ነው የሚጠባበቁት። ሳሚ መንቃቱን ለጊዜውም ቢሆን ዶክተሮቹ ወከባ ላይ ስለነበሩ አላስተዋሉትም። ምንም አይነት ቃል ላለመተንፈስ ወስኗል። : : ቢንያሚን እጅግ በጣም ብዙ ደም ፈሶታል። የሲቃ ድምፅ እያወጣ ከአይኖቹ እንባውን ያወርዳል። ከህመሙ በላይ የእናቱ ወይዘሮ ሳሚያ፣ የወይዘሮ ሰብለ እንዱሁም የትንሿ ሰመር ሁኔታ ጨንቆታል። በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ። " ቅና ከእማዬ ጋር ነኝ " የሚለው የሰመር ንግግር እየተመላለሰ ልቡን በፍርሀት ያርደዋል። እንደ ገደል ማሚቱ እያስተጋባ " ቅና ከእማዬ ጋር ነኝ " የሚለው ንግግር ጆሮው ላይ ያስተጋባል። አካሉ ፈዟል አይኖቹ ብቻ የውስጡን ህመምና ፍርሀት ይናገራሉ። እዛው አጠገቡ ከፈን የለበሰ ሰው ሲመለከት ሰውነቱ ራደ። አንዳች ፍርሀት ውስጡን ተቆጣጠረው። የማጣት ስጋት፣ የብቸኝነት ንፋስ በውስጡ ይነፍሳል። ደም ያጨቀየው ፊቱ ከአይኖቹ የሚወጣው እንባ የፊቱን ደም እያጠበ ደም ያነባል። : : ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ወከባው አልተረጋጋም። የመገናኛ ብዙሀን ወሬውን እያራገቡት ስለነበር ትልቅ ትኩረት አግኝቷል። የሰውን ቀልብ የገዛው ደሞ በነዚህ ሬድዮ ጣቢያዎች ተከሽኖ የወጣው መረጃ ነው። " በዛሬው እለት በመዲናችን አዲስ አበባ በሳርቤት ገብርኤል አካባቢ ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደርሷል። የዚህ አደጋ መንስኤ እስካሁን በውል ባይታወቅም ጠጥቶ ማሽከርከር እና አላግባብ ፍጥነትን ጨምሮ ማሽከርከር ሊሆን እንደሚችል እንዳንድ የውስጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአደጋው እለት እያንዳንዱ ድርጊት የተቀረፀ በመሆኑ በመርማሪ ፖሊሶች ዘንድ የተለየ ትኩረት ተስጥቶታል። ይህም የአገራችንን ሰላምና ልማት ለማደናቀፍ በተደራጁ ግብረ ሀይሎች የተፈፀመ ድርጊት ሊሆን እንደሚችል ዋና ሪፖርተራችን ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአደጋው ወቅት 4 የሞት 3 ከባድና 8 ቀላል አደጋዎች ተመዝግበዋል። ከሟቾች መካከል አንዲት በእድሜ ያልደረሰች ነገ ሀገሯን ትረከባለች ተብሎ ተስፋ የተጣለባት ታዳጊ ልጅ ህይወቷ አልፏል። መኪናውን ሲያሽከረክሩ የነበሩ ሹፌሮች እና አንዲት እናት ከሟቾች መካከል እንደሚገኙበት ሪፖርተራችን ዘግቧል። ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን ይስጥልን ሲል የሬድዮ ጣቢያችን ሀዘኑን ይገልፃል። " ( ተፅናንተን ከእረፍት ቡሀላ እንቀጥለዋለን ያው ሆስፒታልም ግር ግር በዝቶ የለ እንደዛ ይሻላል ) April 2018 : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
👍 2😢 2
* ቅንፍ * አብዱልሀኪም ሰፋ ( ክፍል 6) : የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጋዜጠኞችና በፖሊሶች ተከቧል። ሰው በደቦ የመጣ እስኪመስል ድረስ እየተንጋጋ እየመጣ ሆስፒታሉን ወሮታል። የሚሆነውን ሁሉ ሲቀርፁ የነበሩት ወጣቶች የቀረፁትን ምስል በየ ማህበራዊ ድረ ገፆች በትነውታል። ስራ ያጡ የመገናኛ ብዙሀን ጋዜጠኞች የደረሳቸውን መረጃ የራሳቸውን ወሬ ማጣፈጫ ቅመም ጨምረው በማስታወቂያ አጅበው ዲስኩራቸው ላይ ተጥደዋል። : : የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዶክተሮች ከወትሮው በተለየ መልኩ በስራ ተወጥረዋል። በመኪና አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ህይወት ለመታደግ ከላይ ታች ጠብ እርግፍ እያሉ በህክምናቸው ተወጥረዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ በእጅጉ ተዋክበዋል። : : ሳሚ ከነበረበት መንቃት ቢችልም በህመሙ ሰበብ ሰውነቱን እንደልቡ ማንቀሳቀስ ተስኖት አይኑን ባለበት እያንከራተተ አልፎ አልፎ የሚሆነውን ከመስማት ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረውም። ከሱ ጋር ተጎድቶ የመጣውን ወጣት እጅግ በጣም ብዙ ደም ፈሶት የወጣውን ደም ለመተካት ተመሳሳይ የደም አይነት አጥተው ዶክተሮቹ ህይወቱን መታደግ ሳይችሉ ህይወቱ አልፏል። : : ፖሊሶች የአደጋውን መነሻ ሰበብ እያጣሩ ነው። የዛሬው የመኪና አደጋ የብዙሀኑ መነጋገርያ ሆኗል። በመገናኛ ብዙሀን ተመልካቾችና አድማጮች ሳይቀር እየተቀባበሉት የእለቱ የመወያያ ርዕስ ሆኗል። በአደጋው ወቅት ከእያንዳንዱ ሰው የተገኙ መረጃዎች በጥንቃቄ ተመዝግበው ተይዘዋል። ይህንን የሚከታተል ልዩ ሀይል ተመድቦ ሁሉንም መከታተል ጀምሯል። አደጋው እያንዳንዱ የተፈጠረበት ቅፅበት ተቀርፆ በመቀመጡ መርማሪ ፖሊሶች ዘንድ ተራ የመኪና አደጋ ብሎ ለማለፍ የሚያስችል ድፍረት አጥተዋል። በተደራጁና ሆነ ተብሎ የተደረገ ሴራ ነው የሚለው ሚዛን ደፍቷል። : : የተጎጂ ሰዎች ቤተሰቦች ሆስፒታሉን ድብልቅልቁን አውጥተውታል። በዋይታና ለቅሶ ሙሾ ያወርዳሉ። ይህንንም እያንዳንዱን ድርጊት ሁሉም እየታዘበ ይቀርፃል። የአንዲት እናትን ግን ለቅሶ ማንም ችሎ ለማስቆም ድፍረት አላገኘም። እየተነሱ ይፈርጣሉ። ሊያባብሏቸው የሚመጡትንም ማንኛውም ሰው አልሰማም ብለዋል። የእናትነት አንጀታቸው ከወትሮው ዛሬ ተፈትኗል። ብቸኛ መሆንን የሰጉ የሚመስሉ እኚህ እናት ብሶታቸውን በእምባ ይናገራሉ። የአደጋውን ዝርዝር መረጃ አግኝተው የሞቱትንና የተረፉትን ለማወቅ ጭንቅ ጥብብ ብሏቸው የእንባ ጎርፍ ያወርዳሉ ። : : ዶክተሮቹ ሁለት ነፍሶችን ለማትረፍ የተቻላቸውን ያህል እየጣሩ ነው። ከአደጋው ተጎጂዎች መካከል አንድ ሰው ሰውነቱ በድን ሆኖ በተከደኑ አይኖቹ ስር የእንባ ዘለላዎች ይወርዳሉ። ሁለቱ ተጎጂዎች በድን ሬሳ ሆነዋል ። በአጠቃላይ በትራፊክ ፖሊሶች በወጣ መረጃ መሰረት 4 የሞት፣ 3 ከባድና 8 ቀላል አደጋዎች ተመዝግበዋል። ( እስቲ ይታከሙና መረጃ ከሰጡን የሚሆነውን እናያለን ) April 2018 : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
👍 2
የሚወደድ... የሚበላ... የሚሸተት... የሚያቅፉት አይነት ... እንዲህ ያለ ሲያገኙ🌼... እንዲህ ለወዳጅ ያካፍሉታል(ልባም ሰው ቢሆኑ ደግሞ...ማካፈልም ሳይሆን ሙሉውን ይሰጡትም ነበር)... ተወደዱልኝ... ቆንጆ እጣናም እሁድ🌼! (ነጃት ሐሰን) የረሳሁት ደግሞ... ይህንን መፅሀፍ አንብቡ። : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
6👍 5🔥 2
ጥያቄ ከነጃት ሰውን እናንተ ዘንድ ቅርብ አድርጎ የሚያቆየው ፡ ንፁህ መውደድን መስጠት ስለቻላችሁ ብቻ ነው? : @Venuee13
Show all...
5
የስቃይ ምሬት ለቃል እያነሰ። ከገላ ቁስል የልብ ባሰ። እንደው ላመል ነው የላይ ላይ ኑረት የልብን ስቃይ መች የያል ፍጥረት? አ… አ… ልቤን! [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
😢 13👍 2 1
* ቅንፍ * አብዱልሀኪም ሰፋ ( ክፍል አምስት) : የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዶክተሮች አንድ የስልክ ጥሪ ደርሷቸዋል። ለሳሚ ከተደወሉ ስልኮች መካከል አንዱ ነበር። ተነጋግረው በፍጥነት እንዲመጣ ነግረውት ስልኩ ተቋረጠ። የሁለተኛው ታማሚ የጤና ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። የልብ ምቱ እየደከመ የመተንፈስ አቅሙም አየቀነሰ ነው። ዶክተሮቹ የ ኦክስጅን መተንፈሻ አፉ ላይ ገጥመው ይሯሯጣሉ። ሳሚ ቀስ በቀስ ነቃ። ፑል ቤት እንዳለ ነበር የሚያውቀው ነገር ግን ራሱን ሆስፒታል ውስጥ አፉ ላይ የመተንፈሻ ኦክስጅን አንግቶ ተመለከተ። እንዳሰበው ግን ቀላል አልነበረም አናቱ በመትረየስ የተመታ እስኪመስለው ድረስ ህመሙ አይኖቹን ከማንቀሳቀስ በዘለለ ለአንገቱ እንኳ እድሉን አልሰጠውም ። : : ቢንያሚን እናቱን ወይዘሮ ሳሚያ ከሆስፒታል ይዞ እየተመለሰ ነው። ወይዘሮ ሳሚያና ወይዘሮ ሰብለ ከትንሿ ሰመር ጋር ከኋላ ወንበር ተቀምጠዋል። ሰመር እና ወይዘሮ ሰብለ ከዳር እና ዳር ሆነው ወይዘሮ ሳሚያን አጅበዋል። ቢንያሚን ከሹፌሩ አጠገብ ገቢና ቁጭ ብሏል። አንገቱን ወደ ኋላ ጠምዝዞ ከትከሻው ሰበር ብሎ እናቱን ወይዘሮ ሳሚያን ይመለከታል። የሰመር የማያርፉ እጆች አሁንም ሳይቦዝኑ ወይዘሮ ሳሚያን እየኮረኮሩ ያስቋቸዋል። ቢንያሚን እንዲህ ሲፈነድቁ አይቶ የቅድሙ ሀዘን ትዝ ይለዋል። ፈጣሪውን እያመሰገነ የሚሆኑትን ለመቅረፅ ስልኩን አወጣ። ስልኩ የመዓት ያልተሳኩ ጥሪዎች እና በተደጋጋሚ የተደወለ ስልክ ተመልክቶ መልሶ መደወል ጀመረ። " ሄሎው… " ጤና ይስጥልኝ …" " አቤት ማን ልበል …? " እባክዎ አሁኑኑ ወደ ጥቂር አንበሳ ሆስፒታል ይድረሱ…" " ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለምን? ማለቴ ምን ተፈጥሮ ነው ??? " " ሳሙኤል ሀይሉ የተባሉ ሰው በድንገት ታመው ሆስፒታላችን የድንገተኛ ክፍል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ነው እና ወደዚው መጥተው እንዲከታተሏቸው አሁኑኑ ይድረሱ " ቢንያሚን ምንም መናገር አቅቶት ዝም ብሏል። ስልኩን ቀስ በቀስ ከጆሮው ማሸሽ ጀመረ። ወይዘሮ ሳሚያ " የኔ ውድ ምን ተፈጥሮ ነው ጥቁር አንበሳ ስትል ሰማሁ " ወድያው ዝምታውን አሸንፎ " የትምህርት ቤት ልጆች ናቸው ዛሬ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህሙማንን እንጎብኝ ሲሉኝ ድንገት መሆኑ አስደንግጦኝ ነው። " " አይ ኸይር( ጥሩ) ነው ታማሚን መጠየቅ አላህ ይወደዋል ሂድ እንዳትቀር " አሉ ወይዘሮ ሳሚያ። ወድያው ሰመር ቀበል አርጋ " እንዴ እማ እኔን ጥሎኝ? " አለች። " አንቺማ ጥለሺኝ ካልሄድሽ በስተቀር እኔማ ትቼሽ አልሄድም! " አለ ቢንያሚን። " እማ እንደውም አሌድም ካንቺ ጋ ነው ምሆነው… ቅ…ና ከማዬ ጋ ነኝ " አለች ሰመር። ወይዘሮ ሰብለ ተገርመው " ወቸው ጉድ …" ይላሉ። ሁሉም እየተሳሳቁ ወደ ቅድሙ ጨዋታቸው ተመለሱ። ያቺ ትንሽዬ ላዳ በሳቅ እና ደስታ ታጅባ ወደ ካርል አደባባይ ሳትደርስ አንድ መስመሩን የሳተ መኪና በፍጥነት ተንደርድሮ ከፊታቸው ገባ። : : ጀሚል ሹፌሩን የቱንም ያህል በፍጥነት ቢነዳው " አፍጥነው ፍጠን ፍጠን …" ማለቱን አላቆመም። መንገድ ላይ የነበሩ ትራፊክ ፖሊሶችን ሳይቀር ጥሶ እየሄደ ነው። የትራፊክ አባላቶቹ እየተከተሉት ነው ተጨማሪ የሰው ሀይልም ደውለው ከፊት ለፊት መንገድ እንዲጠብቁ አዘዋል። የትራፊኮቹን ውጥረት ለማንገብ ከበፊቱ ይበልጥ ፍጥነቱን ጨምሮ መንዳቱን አላቆመም። ሳር ቤት አደባባይ አልፎ በመቻሬ ሜዳ በኩል እየጋለበ ነው። ትራፊኮቹ ከፊት ለፊት ለሚገኙ አባላት በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ደጋግመው በመገናኛ መረባቸው ያስጠነቅቃሉ። መሀል አደባባይ እጥፍ ብሎ ፊት ለፊት ወደ ቀለበት መንገድ ከሚያስወጣው መንገድ ፖሊሶቹ እየከነፉ መጥተዋል። ጀሚልን ይዞ እየገሰገሰ የሚሄደው መኪና ሹፌር አንዴ ጥሶ የመጣውን ትራፊክ እንዲሁም እየተከተሉት ያሉትን ሲያይ ውጥረቱ ጨመረ። ለመቆም ማሰቡ አማራጭ ሆኖ ከቅጣት ስለማያስጥለው ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ መሄዱን ቀጥሏል። ካርል አደባባይ ጋ ሲደርስ ከፊት ለፊት ቀለበት መንገድ መውጫው ጋር ያሉትን ፖሊሶች ሽሽት ይሄድበት ከነበረው ትቶ ተቃራኒውን ይዞ በደመነፍስ በሚመስል አይነት ወደ ታች ነዳጁን ረግጦ ይዟል። ከፊት ለፊት የነበሩ መኪናዎች በሚመጣው መኪና ፍጥነት ተረብሸው እነሱም መንገዳቸውን ስተው የሳርቤት ገብርኤልን መንገድ " ፒፕ…ፒ……ፕ " በሚል ሞገደኛ ድምፅ አቅልጠውታል። ሁሉም መንገድ እየለቀቁ ወደ ዳር እየወጡ ይላተማሉ። ውጥረቱ ከደቂቃ ደቂቃ እየጨመረ ነው። ፍርሀት እና እልህ እጅንና እግርን ከማዘዝ አልቦዘኑም። የነበረው የትራፊክ ፍስት በዛች ጠባብ አስፋልት የጉንዳን ሰራዊት መስሎ መኪናው ሁሉ ዋይታውን እያሰማ ነው። ሰው የፈጣሪ ቅጣት አለ ተብሎ የማይደነግጥ ሁሉ ቁጭ ብድግ እያለ ዋይታውን አድምቆታል። ታሪክ መስራት የተሳናቸው ወጣቶች ስልካቸውን ጥደው ለተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ታዋቂ ለመሆን ታሪክ ይሆናል በማለት ይቀርፃሉ። መንገዱ እየተዘጋጋ ሲመጣ ሹፌሩ የመኪናውን ፍሬን ረግጦ ወደ ውስጥ ታጥፎ ለማምለጥ አሰበ ። የመኪናውን ፍሬን ረግጦ ለመታጠፍ ሲሞክር ከፊት ለፊቱ ከነበረው መኪና ጋር ተላተመ። : ( የባሰ አታምጣ ነው ሚባለው… የባሰ ነገር ካልመጣ አይቋረጥ) April 2018 : @Venuee13 @Vennuee13
Show all...
👍 4