cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ! . ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤ ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Show more
Advertising posts
9 623
Subscribers
-224 hours
-107 days
-2630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በመጨረሻም. . . . ከአራት መንፈቀ-ዓመታት በላይ የለፋሁበት ሦስተኛው መጽሐፌ በትናንትናው ዕለት በተዘጋጀው የሊቀ-ቀንበር የወግ ድግስ ላይ ይፋ ኾኗል። ምናባዊ-ልቦለዶች(fantasies) በብዛት ያካተተው ይኽ ሥራ በቅድመ-ክፍያ የሚገዙትን ሦስት መቶ ሰዎች ይጠብቃል። በትናንትናው መድረክ የተወሰኑ ሰዎች አስቀድመው በመግዛት ወደ ህትመት ቤት የሚያደርገውን ጉዞ አስጀምረውታል። ሦስት መቶ ሰዎችን እንደማላጣ ተስፋ በማድረግ እነሆ በማህበራዊ ገጾችም ላይ ይፋ አድርጌዋለሁ። የአንዱ መጽሐፍ ዋጋ 500 ብር ብቻ ነው! 1000413125654 -Feysel Mohammed የገዛችሁ ስክሪንሾት በማድረግ ላኩልኝ መጽሐፉ እንደታተመ በቅድሚያ ለእናንተ ይሠጣል! #ሰንባች . @huluezih @huluezih
Show all...
ብዙ ብዙ ማለት እፈልጋለሁ...አሁን ግን አልችልም። ጅማሮው ላይ የተገኛችሁልኝ ሁሉ ውለታችሁ አለብኝ። ድጋፋችሁን ወድጄዋለሁ፣ መኖራችሁ ቀና እንድል አድርጎኛል። ክበሩልኝ!🙏
Show all...
እስካሁን ግን ስንቶቻችሂ ናችሁ ቲኬት የገዛችሁት? ማበረታታት ላይ እንዴት ናችሁ?🙄
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የቲኬት ሽያጭ ተጀምሯል! 🎫 . በጉጉት የሚጠበቀው የሊቀ-ቀንበር የወግና የመዝናኛ ድግስ የመግቢያ ቲኬቶች ለገበያ ቀርበዋል። ቲኬቶቹ የት ይገኛሉ? 1. ቤተል ሚስተር ኮፊ፣ ፋሚሊ ታወር 4ኛ ፎቅ 2. ዋልያ ቡክስ (4 ኪሎ ኢክላስ ህንጻ) 3. the hungout cafe (አዶት ሲኒማ ህንጻ ground ላይ) . ባሉበት ኾነው ቲኬቱን በሞባይል ባንኪንግ ለመቁረጥ :- 1000413125654 Feysel በዚህ አካውንት በመቁረጥ ስክሪንሾቱን የዝግጅቱ ዕለት መግቢያ ላይ እያረጋገጡ መታደም ይችላሉ። . የቲኬቱ ዋጋ:- መደበኛ :- 200 ብር ቪ.አይ.ፒ:- 300 ብር . መሠናዶው የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 ብስራተ-ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው አዶት ሲኒማ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሔዳል። . @huluezih @huluezih
Show all...
ና! . (#ፈይሠል_አሚን) . ና ወደ አምላክህ! ተጠጋ ከደጁ! ምን አጥተህ ታውቃለህ፣ ከዚያ ለምለም እጁ?! ከአዱኛው ግርዶሽ፣ከማይከስመው ጣጣ፤ ከእልፍ ሕዝብ መሐል. . . አንድ "ሰው" ስታጣ፣ አምላክህ ብቻ ነው የመዳንህ ዕጣ፤ እንደ ሰው አይልህም. . . "ለጥቅሙ ሲል መጣ!" . @huluezih @huluezih
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን ክብደቱ ጅማሬው ላይ ነው። ሲጀመር ከጥቂት ወዳጆችህና ቤተሰቦችህ ውጪ ከጎንህ ላይቆሙ ይችላሉ። ነገ የምትደርስበት ሥፍራ ዛሬ ላይ ለማንም አይታይ ይኾናል። ለዚያ ነው....በምትተማመነው ነገር ቁማር መጫወት ግድ የሚኾነው። እነሆ የመጀመሪያ ቁማሬ😁 . የአዳራሽ የቀን እና ሌሎችም ከባድ ውሳኔዎች መዘግየትን ፈጥሯል። እንደምታስተዋውቁልኝና እንደምትመጡ ተስፋ አደርጋለሁ። there is stg special.
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በቅርብ ቀን በመድረክ ላይ እንገናኛለን! እስከዛ ድረስ ባላችሁ የሶሻል ሚድያ አካውንቶች በማስተዋወቅ እንድትቆዩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ!🙏 . @huluezih @huluezih
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
. . . of the day!😎
Show all...
የሙዓዚኑ ድምጽ! . (#ፈይሠል_አሚን) . ምቹ ፍራሼ ላይ. . . ስክነት አልሰፈረም፤ ከላባው ትራሴ፣ ከሐር መከዳዬ፣ሰላም አልነበረም! እጋላበጣለሁ! . ልብ ወደ አምላኩ አዘውትሮ ሲያምጽ፣ ከመስጊድ ተሰማኝ የሙዓዚኑ ድምጽ! "ጸሎት ከእንቅልፍ ይሻላል" እያለ ደጋግሞ ይጣራል! . ሳይጸልይ ያነጋው ልቤ አመጸኛው፣ ድርብርብ ኩኔነው ፊትስ መች አስተኛው? . ከሁለት አንድ አጥቶ፣ እንዲህ ከመቀጣት፤ መጸለይ ይሻላል እንቅልፍም ከማጣት! . መልካም ጁምዓ!❤ . @huluezih @huluezih
Show all...
አንቺና ጨረቃ.mp31.31 MB