cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው። 📞 0974163424 ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1 ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ። ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)

Show more
Advertising posts
54 821Subscribers
-524 hours
-527 days
-34330 days
Posts Archive
206👍 140🥰 37🙏 27🕊 16👏 4
➕➕ የእግር እብጠት➕➕ 🖲 ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣ 🖲 ለወራት የሚቆይ ተቅማጥ ፣ የጉበት ችግር፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና የልብ ድክመት ሲኖር፣  ከተለያዩ ተጓዳኝ ምልክቶች ጋር ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል። 🖲 እብጠቱ በኩላሊት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ፣ በእግር ላይ እብጠት ከመጀመሩ በፊት፣ የአይን ዙሪያ እብጠት ይኖራል 🖲 በልብ ህመም ምክኒያት የሚመጣ የእግር እብጠት፣ እንደ ደረጃው ራስ መሳት፣ አቅም ማነስ፣ ሳል እና አየር ማጠር ሊኖረው ይችላል 🖲 የእግር እብጠት በጉበት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ ደሞ፣ ሆድ ማበጥ እና የአይን ቢጫ መሆን ሊከሰት ይችላል። 🖲 አንዳንዴ ደሞ፣ የከፋ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታም፣ አንድ ሰው ላይ የእግር እብጠት ሊያጋጥም ይችላል። 🖲 ለምሳሌ፣ ነብሰጡር ሴት ላይ እርግዝናው እየገፋ ሲሄድ፣ ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል፣ 🖲 ውፍረት የሚታይበት ሰው በቀን ውስጥ ረጅም ሰአት የሚቆም ከሆነም፣ እግር ሊያብጥ ይችላል። 🖲 አብዛኛውን ግዜ እድሜያቸው ከ 50 በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ፣ ከደም ስር ድክመት ጋር በተያያዘ ሁኔታ፣ ሁለቱም እግር ላይ እብጠት ሊፈጠር ይችላል። ⭕️ ታዲያ አንድ ሰው ላይ የሚታይ የእግር እብጠት ፣ በምን ምክኒያት እንደመጣ እንዴት መለየት ይቻላል 👉የእግር እብጠትን በተመለከተ ከነህክምናው ሰፋ ያለ መረጃ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ። ▶️የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/KeBT-mfwqiQ
Show all...
👍 179 51🥰 22🙏 21🤩 13
262🙏 112👍 59🥰 29👏 16👌 9🕊 9🎉 8🤩 6
ዶ/ር ሐይለልዑል ለሚሰራው ድንቅ የበጎ አድራጎት ስራ ድምፅ እንሁነው።
Show all...
👍 22 2🙏 2
ዉድ ተከታዮች ዛሬ እገዛቹ ያስፈልገኛል በፌስቡክ የስራ ፈጠራ ዉድድር ተዘጋጅቷል ።በዉድድሩ ተሳታፊ ስለሆንኩኝ ከታች ባስቀመጥኩት ሊንክ እየገባችሁ "አንዴ እናዉራ" የሚለዉ ምስል ላይክ 👍 በማድረግ ይምረጡ አመሰግናለሁ🙏 👇👇👇 https://www.facebook.com/100002028524680/posts/pfbid02n9vd4WoU6biznHeXBFcu4DvEmrRCgMcxwVmQQU4tfMcsAb5maWnudgTS7gESQ2YHl/?app=fbl
Show all...
👍 89👏 4
➕➕ የነርቭ ህመም ➕➕ 🖲የነርቭ ህመም፣  በአንድ የህመም ምልክት ብቻ የሚገለፅ ህመም አይደለም፣ እንደ ቦታው እና እነደ ነርቭ ጉዳቱ ደረጃ፣ በተለያየ አይነት የህመም ምልክቶች ይገለፃል። 🖲መቆጥቆጥ፣ ማቃጠል፣ መለብለብ ፣መደንዘዝ ፣መዛል ፣ እና ከአቅም ማጣት ጀምሮ እስከ ራስ መሳት ድረስ ሁሉ ያሉ የህመም ምልክቶች ፣በነርቭ ህመም ተጠቂዎች ሊገለፁ ይችላሉ። 🖲ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ፣ አንዳንዴ፣ በህክምና እንኳን መመለስ ስለማይቻል ፣ ብዙ ሰዎችን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ይዳርጋል። 🖲ጉዳቱ አነስተኛ ከሆነ ደሞ፣ እንደ ተጎዳው ነርቭ  እና፣ ጉዳቱን እንዳስከተለው በሽታ፣ በህክምና ፣ ወደነበረበት መመለስም ይቻላል። 🖲አንድ ሰው ላይ፣ ባጋጣሚ ከሚደርስ አደጋ አንስቶ በቂ ክትትል በሌላቸው ስር ሰደድ በሽታዎችም ጭምር የነርቭ ህመም ሊጀምር ይችላል። 🖲አንድ ጤናማ ሰው ላይ ያለ የነርቭ አካል አፈጣጠር በአቀማመጡ በሁለት ይከፈላል፣  ማእከላዊ የነርቭ አካል እና ውጫዊ የነርቭ አካል። 🖲ማእከላዊ የነርቭ አካል ማለት፣ አይምሮ እና ሀብለ ሰረሰር ናቸው። ውጫዊ የነርቭ አካሎች ደሞ፣ ከአይምሮ እና ከ ሀብለ ሰረሰር የሚነሱ የነርቭ መስመሮች ናቸው። 🖲አይምሮ ውስጥ ያሉ የነርቭ ህዋሶች በከፍተኛ ደረጃ ሲጎዱ ራሳቸውን መልሶ የማደስ ብቃታቸው አነስተኛ ስለሆነ አይምሮ ላይ የሚደርስ ጠንከር ያለ የነርቭ ጉዳት ሲኖር ዘላቂ ለሆነ ወይም በህክምና ለማይመለስ የአካል ጉዳት ሊዳርግ ይችላል። 🖲ከአይምሮ እና ከሀብለሰረሰር ውጪ ያሉ የነርቭ መስመሮች ደሞ፣ እንደ ጉዳት ደረጃቸው ራሳቸውን የማደስ የተወሰነ አቅም አላቸው። 🖲አብዛኛውን ግዜ፣ ቀለል ያለ እና መካከለኛ የጉዳት ደረጃ የደረሰባቸው ከሆነ በግዜ ሂደት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያገግሙ ይሆናሉ። 🖲ነገር ግን፣ አንዳንዴ እነዚህ የነርቭ መስመሮች ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ከሆነ፣ ጉዳቱ የነርቭ መስመሮቹ ራሳቸውን ከሚያድሱበት አቅም በላይ ስለሚሆን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ሊዳርጉ ይችላሉ። 🖲የነርቭ ህመም በተለያዩ አደጋዎች እና የውስጥ ደዌ በሽታዎች ምክኒያት ሊከሰት ይችላል፣ የነርቭ ህመሙ በአደጋ ምክኒያት ሲጎዳ፣ ነርቩ ሊጨፈለቅ፣ በከፍፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊቆረጥ ይችላል። 🖲ስርሰደድ በሽታዎችን ተከትለው የሚመጡ የነርቭ ህመሞች፣ ለምሳሌ፣ የስኳር በሽታን ተከትሎ የሚመጣ የነርቭ ህመም፣ ከእይታ ድክመት ጀምሮ እንደ ደረጃው በብዙ መንገድ ሊገለፅ ይችላል፣ 🖲ነገር ግን አብዛኛውን ግዜ ፣ ከጉልበት በታች በሁለቱም እግር ላይ የሚሰማ የመለብለብ እና የማቃጠል ስሜት በተለይ ከመሀል እግር ጀምሮ ወደላይ ከፍ እያለ የሚሄድ የህመም አይነት ይሰማቸዋል። 🖲ከዚህ ውጪ ፣ ለምሳሌ፣ በአልኮል ጥገኝነት፣ በቫይታሚን ቢ እጥረት፣ በመመረዝ፣ በታይሮይድ ህመም እና በተለያዩ ኢንፌክሽኖችም ጭምር የሚመጡ ሌሎች አሳሳቢ የሆኑ የነርቭ ህመም አይነቶችም አሉ። ⭕️የነርቭ ህመምን በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ፣ የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ!! 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/ASL4flPnaU4
Show all...
👍 105 35🥰 23🙏 16
13
254👍 74🥰 31🙏 30🤩 4
➕➕ቋቁቻ ➕➕ 🖲 ቋቁቻ እና ጭርት ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፣ ነገር ግን፣ ሁለቱም  የተለያየ ዝርያ ባለው ተህዋስ የሚፈጠሩ የቆዳ በሽታዎች ናቸው፣ 🖲 ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም፣ ጭርት ከሆነ ግን ከሰው ወደሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት ወደሰውም ጭምር በንክኪ መተላለፍ ይችላል። 🖲 ቋቁቻን የሚያስከትለው ተህዋስ፣  አንድ ጤናማ ሰው ቆዳ ላይ፣ ምንም አይነት ቋቁቻን ሳያስከትል ፣ ልከኛ በሆነ መንገድ በተፈጥሮ የሚኖር ተህዋስ ነው፣በህክምናው malassezia ተብሎ ይጠራል። 🖲በተለያዩ ምክኒያቶች ፣ይህ ተህዋስ ከልክ ባለፈ መልኩ ቆዳ ላይ ማደግ ሲጀምር እና የላይኛውን ቆዳ ሲያጠቃ፣ በቦታው ላይ ቋቁቻን ይፈጠራል። 🖲 ይህ ቋቁቻን የሚያስከትል ተህዋስ፣ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት ቢሆንም፣ ነገር ግን፣ አንድ ሰው ላይ ቋቁቻን ሊፈጥሩ የሚችሉት በዋነኝነት 3 አይነት ዝርያዎች ናቸው። እነዚህ ዝርያዎች፣ አንድ ሰው ቆዳ ላይ ፣ ቋቁቻን የሚያስከትሉበት የተለያየ ምክኒያት አላቸው፣ 👉 ወዛም የሆኑ ሰዎች፣ ሞቃታማ ቦታ የሚኖሩ ከሆነ እና ፣ የንፅህና ጉድለት ካላቸው 👉ዘይታማ ቅባቶችን ቆዳ ላይ አዘውትሮ በመቀባት 👉የአንድ ሰው የበሽታ መከላከል አቅም ሲቀንስ 👉እንደ ደርሞቬት ፣ቤትኖቬት፣ ቤታሴት የመሳሰሉትን መዳኒቶች ፣ ከሀኪም ትእዛዝ ዉጪ ለረጅም ግዜ አዘውትሮ በመቀባት 👉ጥራታቸውን ያልጠበቁ እና ፊትን የሚያቀሉ ክሬሞችን ማዘውተር የመሳሰሉት፣ አንድ ሰው ላይ በተደጋጋሚ ግዜ ቋቁቻ እንዲወጣ የሚያደርጉ ምክኒያቶች ናቸው። 🖲 ቋቁቻ በቆዳ ላይ ሲወጣ፣ ነጣ ያለ ወይም ደሞ ጠቆር ያለ ገፅያን ሊይዝ ይችላል፣ አብዛኛውን ግዜ ደሞ፣ ከሌላው የሰውነት ክፍል ይልቅ፣ ወዝ በበዛበት የቆዳ ክፍል ላይ የመውጣት ባህሪ አለው። 🖲 ፊት ላይ የሚወጣ ቋቁቻ ፣ አብዛኛውን ግዜ በአዋቂዎች ላይ የተለመደ አይደለም፣ ነገር ግን፣ ካዋቂዎች ይልቅ አንዳንዴ የልጆች ፊት ላይ ሊያጋጥም ይችላል። 🖲 ቋቁቻ መሆኑን ለመለየት ፣ አንድ ሰው ከታጠበ በኋላ ምንም አይነት ቅባት ሳይቀባ፣ ቋቁቻው በወጣበት ዙሪያ ያለውን ቆዳ በመለጠጥ ፣ወይም ደሞ ፣ቋቁቻው ሲታከክ፣ አመድ የመምሰል ገፅታን ይሰጣል። 🖲 እየከሰመ ያለ ቋቁቻ ሲሆን ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ አመድ የመምሰል ባህሪ ላይኖረው ይችላል። ⭕️ታዲያ ቋቁቻን ለማጥፋት የሚያስፈልገው መዳኒት ምንድነው? በቤት ውስጥ ቀምሞ መጠቀም የሚቻል ውህድስ አለ? 🔴የቋቁቻ ህክምናን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለው። ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ። 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/44WovKjIg_E
Show all...
👍 125 38👏 7💯 6
👍 4 3
➕➕ መጥፎ የአፍ ጠረን ➕➕ 🖲 ጠዋት ላይ ብዙ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ መጥፎ የአፍ ጠረን ያጋጥመዋል። 🖲 ከ 85 በመቶ በላይ የሚሆነው መጥፎ የአፍ ጠረን፣  በድድ በጥርስ እና በአፍ ዙሪያ ባለ ችግር ይጀምራል። 🖲 ከዛውጪ የሳይነስ ፣የቶንሲል፣ የሳምባ ፣ የጨጓራ እና  እንዲሁም፣ የጉበት እና የኩላሊት ድክመትን ጨምሮ በተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች ምክኒያት፣ አንድ ሰው ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊጀምር ይችላል። 🖲 መጥፎ የአፍ ጠረን በህክምናው( Halitosis) በመባል ይታወቃል። 🖲 ይህ ችግር በተለያየ እድሜ ክልል ሊጀምር ይችላል፣ እንዲሁም ደሞ ፣ እድሜ እየገፋ ሲሄድ፣ አንድ ሰው ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚከሰትበት እድል እየጨመረ ይሄዳል። 🖲 አንድ ሰው ፣በህክምና የተረጋገጠ ፣ምንም አይነት መጥፎ የአፍ ጠረን ሳይኖረው፣ ነገር ግን፣ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳለው በማሰብ ብቻ ወደህክምና የሚመጣ ከሆነ፣ የስነልቦና ችግር እንዳለ ያመላክታል። 🖲 ይህ አይነቱ ችግር ሲኖር በህክምናው (Delusional halitosis) በመባል ይታወቃል 🖲 በተፈጥሮ ወይም በተጓዳኝ በሽታ ምክኒያት፣ አንድ ሰው ላይ በህክምና የተረጋገጠ መጥፎ የአፍ ጠረን ሲኖር ደሞ፣ በህክምናው (Genuine halitosis) በመባል ይታወቃል 🖲 ምንም አይነት የጥርስ እና የድድ ችግር ሳይኖር፣ ወይም ደሞ ምንም አይነት ተጓዳኝ የውስጥ ችግር በሌለበት ሁኔታ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚፈጠር ከሆነ ተፈጥሮአዊ ሊሆንም ይችላል። 🖲 ይህ አይነቱ ችግር በህክምናው (Phyisiological halitosis) በመባል ይታወቃል፣ ይህ የሚመጣበት ሁለት አይነት ምክኒያት አለው 👉 የመጀመሪያው፣ በአንድ ጤናማ ሰው አፍ ውስጥ፣ በተፈጥሮ የሚኖሩ ጥቃቅን ተህዋሶች ፣አንድ ሰው ከተመገበ በኋላ በምላስ እና በጥርስ መሀል የሚቀር ጥቃቅን የምግብ ትርፍራፊን ወደ መጥፎ ጠረን ወዳለው ተረፈ ምርት ሲቀይሩት ነው። 👉 ሌላው ምክኒያት ደሞ ፣የምራቅ መጠን እና የምራቅ ዝውውር መቀነስ ነው፣ በአፍ ውስጥ በቂ የምራቅ መጠን የማይኖር ከሆነ ፣በአፍ ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ተህዋስያን ፣ አፍ ውስጥ የቀረ ምግብን የበለጠ እንዲያብላሉ ስለሚያስችላቸው፣ መጥፎ የአፍ ጠረንን ይፈጥራሉ። 🖲 አንድ ሰው እርግጠኛ የሆነ መጥፎ የአፍጠረን እንዳለው ለማወቅ በሀኪም እገዛ ፣ወይም ደሞ በቤት ውስጥ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ማወቅ ይቻላል። 👉 ለምሳሌ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ የሚል ሰው፣ ለ 12 ሰአት ያህል ምንም አይነት ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች ሳይመገብ እና ለ 6 ሰአት ያህል ጥርስ ሳይቦረሽ ፣ የእጁን ጀርባ አንድ ግዜ በመላስ በምራቁ ካረጠበ በኋላ፣ ምራቁ ሲደርቅ በቦታው ላይ ያለ መጥፎ ጠረን መኖሩን ማረጋገጥ ነው። 👉 ሌላው ደሞ ፣ ንፁህ መጥረጊያን በመጠቀም፣ ምላስን በመፈግፈግ እና ፣ ወይም ደሞ፣ በጥርስ መሀል በሚገባ ገመድ ፣  ወይም dental flos በመጠቀም ፣የጥርስ መሀልን ፈግገፍጎ ገመዱ ላይ መጥፎ ጠረን መኖሩን አሽትቶ በማረጋገጥ ነው። 🔴 መጥፎ የአፍ ጠረንን የሚያስከትሉ በሽታዎችንን እና ህክምናቸውን በተመለከተ፣ እንዲሁም በቤት ውስጥ መደረግ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ በ 🚩 YouTube🚩 ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አስቀምጫለሁ። ❤️የሚቀጥለውን ማስፈነወጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ፣ መልካም ግዜ። 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/6stDN6haWac
Show all...
👍 146🙏 39 35
13🙏 5👍 4
⭕️⭕️ ውድ ተከታታዮቼ ከላይ የላው ሊንክ አልሰራ ካለ ለመምረጥ ይሄኛውን መጠቀም ትችላላችሁ፣ አመሰግናለሁ 👇👇👇 https://tiktokcreativeawards.com/
Show all...
👍 104 43👌 12🥰 1
ውድ የቻናላቺን ተከታታዮች Tik talk creative awaerd ላይ ለ dr seife vote እንስጥ
Show all...
👍 129 13🙏 1
🔴 ውድ ተከታታዮቼ፣ በኢቶፒያ የመጀመሪያው የ tiktok award ምርጫ እየተኪያሄደ ይገኛል፣ በመሆኑም በህክምናው ዘርፍ እጩ ሆኜ ስለቀረብኩ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ፈቃዳችሁ ከሆነ እንድትመርጡኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ። ☝️ከላይ ያስቀመጥኩት ምስል እንዴት እንደምትመርጡ የሚያሳይ ነው፣ ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ ዶ/ር ሰይፈ ወርቁ 👇👇👇👇👇👇 https://tiktokcreativeawards.com/vote/
Show all...
👍 221 69🥰 30🙏 28
➕➕የተረከዝ ህመም➕➕ 🖲 የተረከዝ ህመም ሁሉ፣ አንድ አይነት በሽታ ነው ማለት አይደለም 🚩 🖲የውስጥ እግር ማቃጠል እና መቆጥቆጥ ሲኖር አብዛኛውን ግዜ የስኳር በሽታ ምልክት ነው የሚል ስጋት በታካሚዎች ላይ ይስተዋላል፣ 🖲ምንም እንኳን የስኳር በሽታ የነርቭ ጉዳትን ከማስከተል ጋር ተያይዞ የእግር ህመምን ቢያስከትልም ፣ነገር ግን፣ የውስጥ እግር እና የተረከዝ ህመም በተደጋጋሚ ግዜ ሲያጋጥም ፣እንደ ህመሙ አይነት እና ባህሪ የተለያየ  አይነት መንስኤ አለው። 🖲ለምሳሌ፣ ብዙ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም አንድ የተረከዝ ህመም አይነት አለ በህክምናው ( Plantar Faciitis ) በመባል ይታወቃል፣ 🖲አብዛኛውን ግዜ ፣ሰዎች በዚህ ህመም ሲጠቁ በየህክምና ተቋሙ ይመላለሳሉ። 🖲ነገር ግን፣ ይህን አይነቱን የተረከዝ ህመም፣  ያለ መዳኒት ፣በቤት ውስጥ በሚደረግ ቀላል እንቅስቃሴ ብቻ ማዳን የሚቻልበትም መንገድም አለ። 🖲ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች፣ አብዛኛውን ግዜ ጠዋት ላይ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ፣ወይም ደሞ ረዘም ላለ ግዜ እረፍት አድርገው ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ፣ ከስር ተረከዛቸው ላይ ፣የውጋት ስሜት ይሰማቸዋል። 🖲አንዳንዴ የህመም ስሜቱ ከበድ ያለ ሲሆን፣ ከተረከዝም አልፎ እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ የሚደርስ የውጋት ስሜት ይኖራል። 🖲በዚህን ግዜ ታዲያ፣ እግርን ማንቀሳቀስ የውጋት ስሜት ስለሚፈጥር ፣ በተቀመጡበት አንኳን እግርን እንደልብ ለማንቀሳቀስ ያስቸግራል፣ እንደውም ብዙ ሰዎች በህመማቸው ግዜ፣ ቁርጭምጭሚታቸው ላይ እብጠት እንዳለ ያህል ይሰማቸዋል፣ 🖲በተለይ ደሞ ፣ጠዋት ላይ ከአልጋ ሲወረድ፣ ሙሉ እግር መሬት ሲነካ ህመሙ ስለሚብስ፣ በእንቅስቃሴ ግዜ፣ የማስነከስ ባህሪ ሊኖረው ይችላል፣ 🖲ወይም ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ ፣ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች፣ ህመሙን ለመቋቋም ሲሉ፣ ጠዋት ጠዋት ላይ ተረከዝን መሬት ሳያስነኩ በጣታቸው መራመድን ይመርጣሉ። 🖲ታዲያ፣ የተረከዝ አጥንት ላይ ከሚደርስ አደጋ አንስቶ፣ የቁርጭምጭሚት፣ የጡንቻ እና የጅማት አካሎችን የሚያጠቃ ችግር ሲኖር ፣የውስጥ እግርን እና፣ የተረከዝ ህመምን ይፈጥራል። 🔴የተረከዝ ህመም አይነቶችን እና ከተረከዝ ጅማት ቁጣ የተነሳ የተረከዝ ህመምን በቤት ውስጥ ማከም የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ። 🔴ከታች ያለውን አድራሻ ተጭናችሁ መመለክት ትችላላችሁ፣ መልካም ግዜ። 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/4vBtJmJ0De4
Show all...
👍 134 54🙏 11🏆 6🥰 5👏 2
👏 6
➕➕ የወገብ ህመም ለሚያስቸግረው➕➕ 🖲 የወገብ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ ሀኪምጋ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ የወገብ ህመም ያለበት ሰው ላይ፣ አንዳንድ ተጨማሪ  ምልክቶች ከታዩ፣ በቶሎ ህክምና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። 🖲 የዲስክ መንሸራተት ብቸኛው የወገብ ህመም አምጪ በሽታ አይደለም፣ የአከርካሪ አጥንት፣ የጡንቻ ፣ የነርቭ እና የውስጥ ደዌ ህመሞችም፣ የወገብ ህመምን ሊፈጥሩ ይችላሉ 🖲 አንድ ሰው ላይ ፣የወገብ ህመም መኖሩ ብቻ ሁልግዜ አሳሳቢ ችግር ነው ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ አንዳንድ ግዜ ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች፣ የወገብ ህመሙ አደገኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው 🖲 የወገብ ህመም እንደቆይታ ግዜው በ 4 አይነት መንገድ ይከፈላል፣ ማለትም፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምት በታች የቆየ ከሆነ የአጭር ግዜ የወገብ ህመም ወይም ( acute back pain) ተብሎ ይጠራል። 🖲 ወይም ደሞ፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምንት እስከ 3 ወር ድረስ የቆየ ከሆነ ፣( subacute back pain) ተብሎ ይጠራል: ሲተረጎም፣ ከፍያለ ደረጃ ያለው  የአጭር ግዜ የወገብ ህመም እንደማለት ነው። 🖲 የወገብ ህመሙ ፣3 ወር እና ከዛ በላይ የቆየ ከሆነ፣ (chronic back pain) ወይም ስር የሰደደ የወገብ ህመም እንደሆነ ያመላክታል። 🖲 ከዚህ ውጪ ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም፣ በመሀል ለተወሰነ ግዜ እረፍት እየሰጠ የሚመላለስ እና ለረጅም ግዜ የሚቆይ የወገብ ህመም ያጋጥማቸዋል፣ 🖲 ይህ አይነቱ የወገብ ህመም በህክምናው (recurrent back pain ) ተብሎ ይጠራል ወይም ተመላላሽ የወገብ ህመም ማለት ነው። 🖲 የወገብ ህመምን በዚህ መልኩ በቆይታ ግዜው መከፋፈል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክኒያት፣ የወገብ ህመም መንስኤ የሆነውን በሽታ ለመለየት እና ትክክለኛውን ምርመራ እና ህክምና ለመስጠት ታስቦ ነው። 🖲 ምክኒያቱም፣ ከ 30 በላይ የሚሆኑ የበሽታ አይነቶች፣ የወገብ ህመም ስሜትን የመፍጠር አቅም ስላላቸው ማለት ነው 🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ ከ 6 ሳምንት በታች የሚቆይ የወገብ ህመም በቀላል ህክምና ወይም በቀላል የህመም ማስታገሻዎች ብቻ የሚድን ሆኖ ይገኛል። 🖲 80 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚያጋጥመው የወገብ ህመም አይነትም፣ ይሄው አጭር የግዜ ቆይታ ያለው የወገብ ህመም ነው፣ ከነዚህ ውስጥ፣ 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በ 6 ሳምንት ውስጥ ሲሻላቸው ይታያል። 🖲 የወገብ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው ታዲያ መቼ ነው? አንድ ሰው በራሱ ላይም ሆነ፣ በቤተሰብ አባል ላይ የሚታይ የወገብ ህመም ሲያጋጥመው ፣ሀኪም ጋር ከመምጣቱ በፊት ምን ማድረግ አለበት? ሙሉውን መረጃ በቪዲዮ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ በመጫን በቀጥታ መመልከት ይችላሉ። መልካም ግዜ። 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/t0uvR99J0MQ
Show all...
➕➕ መጥፎ የመሀፀን ፈሳሽ ➕➕ 🖲 እድሜያቸው ያልደረሰ ሴቶች ወይም ልጆች ላይ፣ ከዚህ በፊት ያልነበረ የመሀፀን ፈሳሽ ከታየ፣ ምናልባት ጥቃት ደርሶባቸው ፣ወይም ደሞ ባእድ ነገር በመሀፀናቸው ገብቶ ሊሆን ይችላል። 🖲 ለአቅመ ሄዋን የደረሱ ሴቶች ላይ የሚታይ የመሀፀን ፈሳሽ ሁሉ የአባላዘር በሽታ ምልክት ነው ማለት አይደለም። 🖲 ምንም አይነት የግብረ ስጋ ግንኙነት ኖሩዋት የማታውቅ ሴትም ጭምር፣ መጥፎ የመሀፀን ፈሳሽ ሊያጋጥማት ይችላል፣ ምክኒያቱም፣ ካባለዘር በሽታ ውጪ ያሉ በሽታዎችም መጥፎ የመሀፀን ፈሳሽን ሊፈጥሩ ይችላሉ። 🖲 ጤናማ የመሀፀን ፈሳሽ መጥፎ ጠረን የለውም፣ ይዘቱ እና መጠኑ ግን የተለያየ ሊሆን ይችላል። 🖲 አንዳንድ ሴቶች ላይ፣ ጤናማ ያልሆነ የመሀፀን ፈሳሽ ኖሮ እንኳን የህመም ስሜት ላይኖራቸው ይችላል፣ አንዳንድ ሴቶች ደሞ፣ መጥፎ የመሀፀን ፈሳሽ አጋጥሟቸው ከታከሙት በኋላ፣ በድጋሚ ሲመለስባቸው ይታያል። 🖲 ተደጋግሞ የሚመጣ መጥፎ የመሀፀን ፈሳሽ፣ ምክኒያቱ ታውቆ ካልታከመ፣ አንዳንዱ በሽታ ላለመፀነስ ችግርም ሊያጋልጥ ይችላል። 🖲 ምክኒያቱ በምመርመራ ታውቆ ህክምና ሲሰጥ ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ ችግሩ በቀላሉ የሚፈታ ሆኖ ይገኛል። 🖲 ጤናማ የሆነ የመሀፀን ፈሳሽ፣ ተፈጥሮአዊ የሰውነት ጠረንን ከመያዝ ውጪ፣ ከወትሮው የተለየ እና መጥፎ የሆነ ጠረንን አይፈጥርም፣ ⭕️ በይዘቱም ሆነ በመጠኑ ያልተለመደ የመሀፀን ፈሳሽ የሚታይ ከሆነ፣ ⭕️መጥፎ ጠረንን የሚፈጥር የመሀፀን ፈሳሽ እና ብልት አካባቢ የሚያሳክክ ከሆነ፣ ⭕️ በግንኙነትም ሆነ ሽንት በሚሸናበት ግዜ የህመም ስሜትን የሚፈጥር ከሆነ፣ 👉 የመሀፀን ፈሳሹ ከተጓዳኝ የጤና ችግሮች የመጣ መሆኑን የሚያመላክት ይሆናል ማለት ነው። 🖲 ባባላዘር በሽታ ምክኒያት የመጣ የመሀፀን ፈሳሽ፣ በግንኙነት ስለሚተላለፍ፣ ለሷም፣ ለወንድ ጓደኛዋም ህክምና ማድረግ ግዴታ ነው። 🖲ነገር ግን፣ መጥፎ የመሀፀን ፈሳሹ የተፈጠረው፣ በሌላ የመሀፀን በሽታ ምክኒያት ከሆነ ደሞ፣ ለሷ ብቻ የሚሰጠው ህክምና በቂ ይሆናል ማለት ነው። ⭕️መጥፎ የመሀፀን ፈሳሽን ስለሚፈጥሩ በሽታዎች የያንዳንዳቸውን ምልክት እና ህክምናቸውን በተመለከተ በሰፊው YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። ⭕️ይህንን link ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/noWhPrK8n6o 🛑ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉  @LEKETERO ወይም 👉 @Apointment1 ተጭነው ስም እና ስልክ በማስቀመጥ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። እናመሰግናለን
Show all...
➕➕ የፀጉር ቀለም ➕➕ 🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ አንድ ሰው የፀጉር ቀለምን የሚጠቀምበት አንደኛው ምክኒያት፣ ያለግዜው የሚመጣ ሽበትን ለመሸፈን ነው። 🖲ያለግዜው የሚመጣ ሽበት ደሞ፣ በጣም ጥቂት ከሚባሉ የጤና ችግሮች በስተቀር፣ አብዛኛውን ግዜ በተፈጥሮ የሚመጣ ሁኔታ ነው። 🔴 እርጉዝ ሴት የፀጉር ቀለም መቀባት ትችላለች እንዴ? ለካንሰር በሽታ አጋላጭ የሆነው የፀጉር ቀለምስ የትኛው ነው? 🖲 ከአንድ የፀጉር ዘለላ ተፈጥሮአዊ ክብደት ውስጥ ፣97 % የሚሆነው የፀጉር ይዘት፣ ቀለም አልባ ተፈጥሮ ነው። የፀጉር ቀለም፣ የተቀረውን 3 % ብቻ የሚሆነውን የክብደት ድርሻ  ይይዛል። 🖲 ታዲያ፣ ምንም እንኳን ተፈጥሮ ለፀጉር ቀለም ያደለው ክብደት በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ከስነውበት አንፃር በማህበረሰብ ዘንድ የሚሰጠው  ድርሻ ግን ቀላል የሚባል አይደለም 🖲 የአንድ ሰው ተፈጥሮአዊ የፀጉር ቀለም፣ አብዛኛውን ግዜ ከ ሁለት መሰረታዊ የተፈጥሮ ቀለሞች የተገነባ ነው። እነዚህ ቀለሞች፣ በህክምናው " eumelanin "እና  "pheomelanin " በመባል ይታወቃሉ። አንዳንድ ሰው ላይ   "oximelanin " በመባል የሚታወቅ ሶስተኛ የቀለም አይነት ሊኖር ይችላል። 🖲 አንድ ሰው፣ ምንም አይነት ተጓዳኝ የጤና ችግር ሳይኖርበት በተፈጥሮ ብቻ የመጣ ሽበትን ግዜያዊ በሆነ መልኩ ለመቀነስ ካሰበ፣ ሁለት አይነት አማራጮችን መጠቀም ይችላል። 🖲 አንደኛው መንገድ፣ የሽበት መጠኑ 10 % እና ከዛ በታች ከሆነ፣ ሽበቱን መንቀል ይቻላል። ወይም ደሞ የዛ ሰው የሽበት መጠን ከ 10 % በላይ ከሆነ፣ የፀጉር ቀለምን መጠቀም ሌላኛው አማራጭ ነው 🖲 ሽበትን ለመሸፈን፣ ወይም ለማቅለም የተዘጋጁ የፀጉር ቀለሞች፣ በሁለት አይነት መንገድ ፀጉሩን ሊያቀልሙት ይችላሉ፣ 👉 አንደኛው መንገድ፣ የፀጉሩን ዘለላ የላይኛውን ሽፋን ብቻ በቀለም በመሸፈን ሲሆን፣ 👉 ሁለተኛው መንገድ ደሞ፣ ቀለሙ ከፀጉር ዘለላው ውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ በማድረግ ነው። 🖲 ፀጉር ውስጥ ሳይገቡ የፀጉሩን ሽፋን ብቻ የሚያቀልሙት የፀጉር ቀለሞች፣ ግዚያዊ ቀለሞች ናቸው፣ በተደጋጋሚ ግዜ በመታጠብ ግዜያቸውን ጠብቀው ከፀጉር ላይ ይነሳሉ። 🖲የፀጉር ዘለላው ውስጥ የሚገቡት ቀለሞች ደሞ፣ በቋሚ መልክ የተዘጋጁ ቀለሞች ናቸው፣ ማስለቀቂያ ኬሚካሎችን በመጠቀም እና ፀጉሩን በመቁረጥ ካልሆነ በቀር፣ ፀጉሩን በተደጋጋሚ ግዜ በማጠብ ብቻ ቀለሙን ማስለቀቅ አይቻልም። ▶️በዚህ መሰረት ታዲያ፣ አራት አይነት የፀጉር ቀለሞችን ገበያ ላይ ታገኛላችሁ ⭕️ስለነዚህ የፀጉር ቀለም አይነቶች እና አንዳንዶቹ ቀለሞች የሚያስከትሉትን የጎንዮሽ ጉዳት በተመለከተ አጠር ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። ⭕️ለመመልከት ከፈለጋችሁ የሚቀጥለውን አድራሻ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/kpcAbBIFXmk መልካም ግዜ።
Show all...
hi
Show all...
➕➕የዓይን ዙሪያ ጥቁረት➕➕ 🖲 የዓይን ዙሪያ ጥቁረት፣ አብዛኛውን ግዜ በቀላሉ የሚጠፋ ጥቁረት አይደለም 🖲አንዳንዴ ፣እንደ ጥቁረቱ ይዘት እና እንደ መጣበት ምክኒያት ህክምና ሲደረግ፣ አንዳንዱ ሙሉበሙሉ የሚጠፋ፣ አብዛኛው ደሞ፣ በከፊል ወይም በመጠኑ ብቻ የሚደበዝዝ ሆኖ ይገኛል። 🖲ምክኒያቱም፣ በዓይን ዙሪያ ያለ ቆዳ ከሌላው ቆዳ የበለጠ ስስ ከመሆኑ የተነሳ፣ ቆዳው ላይ የሚፈጠር ጥቁረት አብዛኛውን ግዜ ከቆዳው ስር ስለሚጠራቀም ነው። 🖲 የዓይን ዙሪያ ጥቁረት፣ አራት መነሻ መሰረቶች አሉት፣ የመጀመሪያው በዓይን ዙሪያ ላይ ያለው ቆዳ ፣ በተፈጥሮም ሆነ  በተለያዩ ምክኒያቶች ቀለሙ ከልክ ያለፈ ሆኖ ሲገኝ ነው። 🖲 ሁለተኛው መነሻ መሰረት ደሞ ፣ከቆዳው ስር ያሉ ደም ስሮች ገነው በሚታዩበት ግዜ ነው። የዚህ አይነቱ ሁኔታ፣ በተለይ ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች፣ በዓይናቸው ዙሪያ ያለው ቆዳ የሳሳ ይሆንና አንዳንዴ በዙሪያው ያለው ደምስር ጎልቶ ሲወጣ በዓይናቸው ዙሪያ ጥቁረትን ሊፈጥርባቸው ይችላል። 🖲 ሶስተኛው መነሻ መሰረት ፣ በዓይን ዙሪያ የሚፈጠር እብጠት ወይም መሰርጎድ ሲኖር ፣ በቦታው ላይ የሚፈጥረው ጥላ የዓይን ዙሪያ ጥቁረት ሆኖ ሊታይ ይችላል። 🖲 አራተኛው እና የመጨረሻው ምክኒያት ደሞ፣ አንድ ሰው ላይ እነዚህ ሶስት መነሻ መሰረቶች ተደራርበው በሚከሰቱበት ግዜ ነው። ለምሳሌ፣ በዓይን ዙሪያ ገኖ የሚታይ ደምስር ያለበት ሰው፣ በተጨማሪም የዓይን ስር እብጠት ወይም መሰርጎድ ሲኖረው የጥቁረቱ መነሻ የተደራረበ ይሆናል ማለት ነው። 🖲 ታዲያ፣ አንድ ሰው የዓይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ መጀመሪያ የዓይን ዙሪያ ጥቁረቱ የተፈጠረው ከተጓዳኝ የቆዳ ችግር አለመሆኑን ሀኪም ጋር ቀርቦ ማረጋገጥ አለበት። 🖲 ማድያትም ሆነ፣ ማንኛውም ቁጣን የሚፈጥር የቆዳ ችግር ካለ፣ ጥቁረትን የሚጀምር እና የሚያባብስ ምክኒያት ስለሚሆን ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል። 🖲 ከዛ ውጪ፣ እንደ እንቅልፍ ማጣት፣ ከፍተኛ የህይወት ጫና መኖር፣ የአልኮል መጠጦችን ከልክ ባለፈ መልኩ መጠጣት፣ እና፣ ራስን ለከፍተኛ የፀሀይ ጨረር ማጋለጥ የመሳሰሉ ምክኒያቶች፣ የአይን ዙሪያ ጥቁረትን የሚያባብሱ ናቸው፣ 🖲 ለዚህም ሲባል፣ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ፣ በቂ እረፍት እና በቂ ውሀ መጠጣት፣ እንዲሁም ደሞ፣ ወደፀሀይ ሲወጣ ዓይንን በአግባቡ የሚሸፍን የፀሀይ መከላከያ መነፅሮችን መጠቀም ያስፈልጋል። 🖲 በተጨማሪም፣ ከተቻለ፣ የሚኒራል ይዘት ያላቸውን፣ ለዓይን ዙሪያ ቆዳ የተዘጋጁ የፀሀይ መከላከያ ክሬሞችን ብቻ መጠቀም እና ፀሀይ ላይ ከ ሁለት ሰአት በላይ መቆየት ግዴታ ከሆነ ፣ ደግሞ መቀባት ያስፈልጋል 🖲 ከዛ ውጪ፣ የአይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ የሚረዱ ፣በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ የተለያዩ ክሬሞች አሉ። እነዚህ ክሬሞች ያላቸው አቅም እና ውጤታማነታቸው ከሰው ሰው የተለያየ ነው። 🖲 ታዲያ፣ አብዛኛውን ግዜ፣ የዓይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ ሲታሰብ፣ አንድ ክሬም ብቻ መጠቀም ያንን ያህል አጥጋቢ ለውጥን አያስገኝም። በተለያየ መንገድ ጥቁረቱን ለመቀነስ እንዲያስችል ከ አንድ በላይ ክሬሞችን መጠቀም ተመራጭ ነው። 🔵 ስለነዚህ ክሬሞች አይነት እና አጠቃቀማቸውን በተመለከተ፣ የበለጠ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ። 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/8weptclRps4
Show all...
➕➕የፀጉር ቅባት ➕➕ 🖲የትኛውም የፀጉር ቅባት ፣ ከተፈጥሮ ውጪ የፀጉር ርዝመትን አይጨምርም። ነገር ግን፣ እንክብካቤ የጎደለው ፀጉር ጥንካሬውን ስለሚያጣ ከእድሜው በፊት ይሰባበርና የፀጉርን ርዝመት ያሳጥራል። 🖲 አንዳንድ ሴቶች፣ ለፀጉራቸው እንክብካቤ፣ ከቅባት ይልቅ ቅቤ መቀባትን ይመርጣሉ። አንዳንድ ሴቶች ደሞ፣ ቅቤ የሚፈጥረውን መጥፎ ጠረን በመጥላት እና የቀለጠው ቅቤ ፊታቸውን ሲነካ ስለማይወዱ፣ ቅቤ ከመቀባት ይልቅ የፀጉር ቅባትን ይመርጣሉ። 🖲 አንድ ሰው፣ ውብ የሆነ የፀጉር ገፅታ እንዲኖረው መጀመሪያ የፀጉሩን ተፈጥሮአዊ ባህሪ ማወቅ አለበት። 🖲 የፀጉሩን አይነት ባማከለ መልኩ በቂ የሆነ የፀጉር እንክብካቤ ሲኖር እና ፣ፀጉር ልከኛ በሆነ መንገድ የሚዋብ ከሆነ ጥንካሬውን እና ውበቱን እንደጠበቀ መቆየት ይችላል። 🖲 በቂ እንክብካቤ የሌለው ፀጉር ፣ ለማስዋብ ሲባል ከልክ ባለፈ መልኩ  የሚንገላታ ከሆነ፣ ፀጉሩ በግዜ ሂደት በቀላሉ የሚበላሽ እና በተፈለገው መንገድ ለማስዋብም አስቸጋሪ እየሆነ ይሄዳል። 🖲 ፀጉር በተፈጥሮው አንዴ ከተበላሸና ፣ተፈጥሮአዊ ገፅታውን ካጣ በኋላ፣ የተበላሸውን የፀጉር ከመቁረጥ ውጪ፣ ፀጉሩን በቋሚነት ወደነበረበት ገፅታው ለመመለስ የሚያስችል የፀጉር ቅባት የለም። 🖲 ነገር ግን፣ የተበላሸው ፀጉር ከተቆረጠ በኋላ፣ ከስር በአዲስ መልክ የሚበቅለውን ፀጉር ተፈጥሮአዊ ገፅታውን ሳይለቅ ለረጅም ግዜ እንዲቆይ የሚረዱ የተለያዩ የፀጉር ቅባቶች አሉ። 🖲 አንድ የፀጉር ቅባት፣ ለፀጉር እንክብካቤ ተመራጭ የሚሆነው፣ የፀጉርን ዘለላ በደምብ የማራስ ባህሪ ሲኖረው እና የፀጉሩን ተፈጥሮአዊ ይዘት የሚያጎላ ሆኖ ሲገኝ ነው። 🖲ገበያ ላይ የተለያዩ የፀጉር ቅባት አይነቶች ይገኛሉ፣ ከምርቶች ውስጥ ለአፍሪካዊ ፀጉር ተስመማሚ የሚሆኑት የተፈጥሮ እና የመአድን ዘይት መጠናቸው ከፍ ያሉ ቅባቶች ናቸው። 🖲ገበያ ላይ የፀጉር ዘይቶች ለብቻቸው እንዲሁም ከተለያዩ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ጋር ተቀላቅለው ለተጠቃሚው ይቀርባሉ። 🖲 አብዛኛውን ግዜ በተጠቃሚዎች ዘንድ የሚታወቁት፣  የ Olive Oil እና Shea Butter ናቸው። እነዚህ ቅባቶች ሁለቱም ለአፍሪካዊ ፀጉር እንክብካቤ ጠቃሚ ናቸው። በተለይ Shea Butter, ከርዳዳ ፀጉር ላለው ሰው የፀጉርን እርጥበት እና ወዛማ ገፅታን ይጠብቃል። 🖲 ከነዚህም ውጪ፣ እንደ Coconut Oil, Jojoba Oil, Argan Oli, እና Tea Tree Oil የመሳሰሉ ለአፍሪካዊ የፀጉር አይነት ተመራጭ የሆኑ ቅባቶችም አሉ። 🚩 ስለነዚህ ቅባቶች ጠቀሜታ እና አይነታቸውን በተመለከተ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አቅርቤያለሁ። 🚩የሚቀጥለውን Link በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ ። 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/H2ALiwlnXH0
Show all...
🙏 ለጤና ባለሙያዉ እንድረስለት 🙏 🔹ከታች የምትመለከቱት ወንድማችን ተሾመ አበራ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በደምቢ ዶሎ ከተማ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን  እዛው በማጠናቀቅ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመሄድ በህብረተሰብ ጤና ት/ት ክፍል በጥሩ ዉጤት ተመርቆ ህብረተሰቡን እያገለገለ ለተወሰነ ጊዜ ቢቆይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት እንደቀድሞዉ መስራት አልቻለም። 🔹በአካባቢው ባለ ሆስፒታል ቢታከምም ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እና ወደ አማኑኤል ሆስታፒል ሪፈር ቢፃፍለትም ወላጅ እናቱ ብቻቸውን በመሆናቸው እሱን ለማሳከም ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል ። 🔸አቅማችንሁ በፈቀደ መጠን በእናቱ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት እጃችሁን እንድትዘረጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን። # 1000527420265(CBE-አያሉ) ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ:: ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ
Show all...
➕➕ የፀጉር እንክብካቤ (Shampoo & Conditioner)➕➕ 🖲 የፀጉር እንክብካቤ ፣ የፀጉር ንፅህናን ከመጠበቅ ይጀምራል። 🖲ፀጉር ከቆዳ በበለጠ መልኩ በተለያዩ ምክኒያቶች ሊቆሽሽ ይችላል፣ ደረቅ ፀጉር እርስ በእርሱ ሲፋተግ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ስለሚያጠራቅም፣ በቀላሉ ብናኝን የመሳብ አቅም አለው። 🖲በተጨማሪም የራስ ቅል ቆዳ ፍርፋሪ ፣ከፀጉር ስር የሚመነጭ የተፈጥሮ ወዝ እና ላብ ከልክ ያለፈ ሲሆን፣ እንዲሁም ለፀጉር ውበት በምንጠቀማቸው፣ ዘመናዊ እና ባህላዊ ቅባቶች ምክኒያት ፀጉር በቀላሉ ሊቆሽሽ ይችላል። 🖲ታዲያ፣ ፀጉር ሲታጠብ፣ ከትኩስ ውሀ ይልቅ፣ በመጠኑ ለብ ያለ ውሀን መጠቀም ተመራጭ ነው ። ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ማበጠር ደሞ፣ የፀጉርን ሰበቃ ስለሚጨምር ፀጉር ከልክ በላይ ሊሳሳብ እና ሊሰባበር ይችላል። 🖲 ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ለማበጠር ከተፈለገ፣ ለዚህ ተብለው የተዘጋጁ ለየት ያሉ ኮንዲሽነሮችን መጠቀም ያስፈልጋል። 🚩 ስለነዚህ ምርቶች በቪዲዮው ላይ አይነታቸውን አብራርቻለሁ። 🖲ፀጉር ላይ የምንጠቀማቸው ሳሙናዎች፣ ጥንካሬያቸው፣ የፀጉሩን አይነት ያማከለ ካልሆነ፣ የፀጉር ቅርፊትን እና የፀጉር ተፈጥሮአዊ ወዝን ከልክ ባለፈ መልኩ ስለሚያነሱ፣ ፀጉርን ሊያገረጡና ውበቱን ሊያሳጡት ይችላሉ። 🖲በተለይ ጨዋማ የሆነ ወይም ፣የጉድጓድ ውሀ ባለበት ቦታ የሚኖር ሰው፣ ለፀጉር ንፅህና፣ የገላ ወይም የልብስ ሳሙናን ባይጠቀም ተመራጭ ነው። 🖲ከዛ ይልቅ ፣ እንደ ፀጉሩ አይነት በተለያየ ጥንካሬ የተዘጋጁ የፀጉር ሻምፖዎችን መጠቀም ይመረጣል። 🖲ገበያ ላይ 11 አይነት የፀጉር ሻምፖዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። እነዚህ ሻምፖዎች በውስጣቸው የሚጨመርባቸው ግብአት፣ የተጠቃሚውን ትኩረት ለመሳብ ሲባል፣ ከፋብሪካ ፋብሪካ ወይም ከምርት ምርት የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። 🖲ነገር ግን፣ የትኛውም ፋብሪካ ቢሆን፣ አንድን ሻምፖ ለገበያ ሲያቀርብ፣ በዋነኝነት 5 የዲተርጀንት አይነቶችን ይጠቀማል። 🖲ከነዚህ ውስጥ፣ አንድን ሻምፖ ጠንካራ የሚያስብለው፣ በውስጡ በሚይዘው የ ሰልፌት አዘል ዲተርጀንት ፣አይነት እና መጠን ይሆናል። 🖲 ስለተለያዩ የሻምፖ እና የኮንዲሽነር አይነቶች፣ እንዲሁም የትኞቹ ምርቶች ለየትኛው የፀጉር አይነት ተስማሚ እንደሆኑ፣ በቪዲዮው ላይ በምስል የታገዘ መረጃ አስቀምጫለሁ። 🖲 ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ፣ ቪዲዮውን መመልከት ይችላሉ   👇👇👇 https://youtu.be/5lX5lmp2u9Q
Show all...