አንድሮሜዳ🇪🇹
Open in Telegram
ይህ ቻናል ዘመናዊ ASTRONOMI ከ ጥንታዊ ስነ ፈለክ ጥበብ አጣምሮ የያዘ ፣ ስለ ሰማዩ ምስጢር የሚዳስሱ መጸሐፍትን ከአቡሻህር እስከ universe books እንዲሁም ከምድር እስከ ጠፈር ፣ከሜርኩሪ እስከ ዩራኖስ፣ከፕሮክሲማ ሴንታወሪ እስከ ቪዋይ ካኒስ ማጆሪስ ፣ከ ሰለጠኑ ፍጡራን አስከ UFO ፣ከብላክ ሆል እስከ ዋይት ሆል... ማወቅና ማግኘት ለሚሻ እንሆ.. #አንድሮሜዳ
Show moreEthiopia14 313The category is not specified
1 095
Subscribers
No data24 hours
+47 days
+2230 days
Posts Archive
1 095
ጅግጅጋUniversity
አድራሻ ❓
📚 ጅግጅጋ ሱማሊያ ክልል የሚገኝ አንጋፋ የሆነ ዮኒቨርሲቲ ሲሆን በኢትዮጵየም ተወዳዳሪ ዮኒቨርሲቲ ነው ።
የአየሩ ሁኔታ ❓
📚 የመጀመሪያውን ሴሚስተር ይበርዳል ፤ ቀላል የማይባል አቧራ አለ ፤ አየሩ ትንሽ እስኪለመድ ይከብዳል (ይበርዳል ) ፤ ሁለተኛ ሴሜስተር ላይ ግን ሞቃታማ ነው፥ በጣም ሞቃታማ ነው ፤ ቀላል ልብሶች መያዝ ግድ ነው ፤ መርጦም(ሽርጥ) ብይዙም አይከፋም ። ከሚያዚያ በኋላ ዝናባማ ነው እናም በዝናብ ወቅት ወደ ውጭ ወጥቶ ምግብ ምናምን መመገብ ትንሽ ሊከብድ ስለሚችል ማለት በጣም ጭቃ ስለሚሆን ላያስኬድ ይችላል ። ጭቃው ከግቢ ውጭ እንጂ ግቢ ውስጥ አያሳስብም ስለዚህ ግቢው ውስጥ በሚገኙ ላውንቾች (ምግብ ቤቶች ) ምናምን መጠቀም አማራጭ ነው ።
የካንፓሶች ብዛት ❓
📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሁለት ናቸው ።
-------> Main campus
------->referral campus
📚 የካንፓሶቹ አብዛኛው ፊልድ ይሰጣል ፤ አንጋፋ የሆነ ግበ ነው ከሜዲሲን እስከ agri ምንም አይቀረውም ።
የትምህርት ጉዳይ ❓
---> ብዙዎች እንደሚያስቡት ቀላል አይደለም ።
---> ፍሬሽ አስተማሪዎች ምናምን ከሆኑ ብዙም አያካብዱም ።
---> ለማንኛውም ችከላ ግድ ነው ። 3ላይብረሪዎች አሉ ። ለችከላ Main ፤law and FB መጠቀም ይቻላል ።
📚medicine ተማሪዎች እስከ ዘንድሮ ድረስ ፍሬሽ ላይ main campus ነበር ሚማሩት nxt ግን ከመጀመሪያ አመት ጀምሮ ሪፈራል ግቢ ሊመድቡ ይችላሉ ።
የካፌ ምግብ ❓
📚 በተማሪዎች ካፌ ዜርfore (ስጋ) በሳምንት አራት ቀን ሲሆን ቀናቶቹም ፦ ማክሰኞ ፤ሀሙስ ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ናቸው ። ቀሪዎቹን ሶስት ቀናት ድንች ወጥ እና መኮረኒ ፤ እራት ደግሞ ሽሮ፣ድንች ወጥ እና ክክ ይገኛል።
ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓
📚ከግቢ ውስጥ ያሉ ምግብ ቤቶች ብዙም እንጀራ የላቸውም አብዛኛው ተምጋቢ ሱማሌ ስለሆነ mostly የሱማሌ ባህል ምግብ ይቀርባል ፤ ከከተማ ለመጣ ሰው ካፌ ብቸኛ አማራጭ ነው ፤
ውሃ ፤ መብራት ፤ WIFI ❓
📚 ሌላው ለፍሬሽ ትንሽ አስቸጋሪው የውሃው ነገር ነው
፤ ዉሃው እስኪለመድ ይከብዳል ማለት ጨዋማ ነው
፤ ብዙ ጊዜ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመብራትና የውሃ መጥፋት ችግር የለብንም በተለይ የመብራት ችግር አይታሰብም ፤ WIFi ግን ችግር አለ ፤ በጣም አዛ ነው ።
የሽንት ቤት ጉዳይ ❓
📚 አሪፍ ነው ምርጥዬ ባይባልም ፤ በአንፃራዊነት ጥሩ የሚባል ነው
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
ሰመራ UNIVERSITY
አድራሻ ❓
📚 ሰመራ በአፋር ክልል የምትገኝ ዮኒቨርስቲ ነች ።
የአየር ሁኔታው ❓
📚 በጣም ሞቃታማ ነው ስለዚህ ከበድ ያለ ብርድ ልብስ ፈፅሞ አያስፈልግም ይህም ማለት ግን ምንም አይነት አንሶላ አያስፈልግም ማለት አይደለም መጀመሪያ ሴሚስተር ላይ ቀለል ያሉ አንሶላዎች ያስፈልጋችኋል ።
የካንፓሶች ብዛት ❓
📚 ግቢው አንድ ብቻ ነው ምንም branch የለውም።
✅ በግቢው የሚሰጡ ኮሌጆች እንደሚከተለው ተገልጿል ፦
1.College of engineering and technology
1.1 Chemical Engineering
1.2 Electrical Engineering
1.3 Civil Engineering
1.4 Mechanical Engineering
1.5 Construction Technology & Management (CoTM)
1.6 Water resource & irrigation engineering
2. College of business and economics
2.1 Accounting
2.2 Management
3.college of health science
3.1 Bsc.nursing
3.2 midwifery
4.College of Agriculture
4.1 Narm
4.2 RDA
4.3 Horticulture
.
.
.
.
.
5.College of Computational science
5.1 Biology
5.2 Chemistry
5.3 Statistics
5.4
6.Language and literature
እና ሌሎችም
📚 ማህበረሰቡ በጣም ጨዋ እና ሠው ወዳድ እንግዳ ተቀባይ ነው ።
የካፌ ምግብ ❓
📚 እንደ ማንኛውም ዮኒቨርስቲ ያን ያክል አስደሳች የሚባል አይደለም ፤ የሚቀርቡ ምግቦች ምሳ ላይ ሻል ይላሉ በተረፈ ትንሽ ከበድ ይላል ።
ከካፌ ምግብ ውጪ ያሉት❓
📚 መጀመሪያ ላይ እንደገባችሁም ቢሆን Non-cafe መመዝገብ ትችላላቹ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ጋ አይቻልም ።
የረብሽ ሁኔታ ❓
📚በተረፈ ግቢያችን ከሀገሪቱ ዩንቨርሲቲዎች አንፃር ሲታይ ሰላማዊ ግቢ ነው። የፍቅር ሀገር ነው ።
ውሃ ፥ መብራት፤ WIFI ❓
📚 መብራት አሳሳቢ አይደለም ከነ አይጠፋም ፤ ውሃ እና WIFi በቂ ባይኖንም ለማቅረብ ይሞከራል ።
ሽንት ቤት ❓
📚 የትም ግቢ ካለው አይለይም የፀዳ ባይባልም ፤ ለመጠቀም ያክል ይሆናል ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
WELKITIE UNIVERSITY
አድራሻ ❓
ደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ትገኛለች ። ከአዲስ አበባ የ85 ብር መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል ከተመሰረተ 10 አመቱን አስቆጥሯል ፤ በ 2004 ነበር የተመሰረተዉ ።
የአየር ሁኔታ ❓
📚 አየሩ አሪፍ የሚባል ነው ግን መጀመርያ አከባቢ ይሞቃል ፤ ለሴቶች ጥላ ነገር መያዝ ይኖርባቹሃል ትንሽ ፀሃዩ ያቃጥላል ።
የካንፓሶች ብዛት ❓
📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎችሁለት ብቻ ናቸው ። እነርሱም textile and main ይባላሉ ።
♨ textile ግቢ ከተማ ዉስጥ ያለ ሲሆን በውስጡም
🌻Textile
🌻Garment and
🌻 designing( exam አለው በፈተና ነው የሚገባው ። )
✅MAIN ግቢ ፦
📚 ከከተማዋ የ10 ብር ትራንስፖርት ሲሆን ጉብሬ የሚባል SUB CITY ቦታ ላይ ይገኛል ፤በዉስጡ ያሉት ዲፓርትመንቶች ደሞ ፦
👉Engineering and Technology
✍civil
✍chemical
✍ Electrical
✍food process
✍HWRE(water)
✍mechanical
✍ cotm
✍architecture (ፈተና አለው በውድድር ነው ሚገባው..!)
⚠️ Note ፦
▶ምህንድስና ክፍል ላይ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በጣም አሪፍ ነው ።
👉computer science
✍Software
✍ CS (computer science)
✍IS( Information system)
✍IT( Information technology)
👉 social science
✍midwifery
✍ nursing
✍FB
✍Law
✍Psychology ...
👉social/natural comptitional
✍ Mathematics
✍Sport
✍ Physics
Health
HO ..
🏩Medicine --> እስካሁን ግን በህክምና አላስመረቀም ገና ተቀብሎ በማስተማር ላይ ነው ።
የካፌ ምግብ ❓
📚 ምሳ ላይ በሳምንት ሶስት ቀን ዜrፎr (ስጋ ጣል ጣል) አለ ፤ አትክልትም አለ ግን ብዙም አይነፋም ፦
🍛ምስር ፣
🍳 ክክ እና
🍲 አሪፍ ሽሮ የምሳ ምግቦች ናቸው ።
ቁርስ ደግሞ ፦ ፍርፍር ፤ ሩዝ እና ቅንጬ ይቀርባል ።
ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓
📚ግቢ ውስጥ 3 ላዉንቾች (ምግብ ቤቶች) አሉ ፤ ዋጋቸዉም
🍥በያይነት 13-15
🍥ፓስታ በሱጎ 13
🍥ፓስታበአትክልት 13-15 ነው ፤ በጣም ተመጣኝ ነው ። Non ካፌ ተማሪዎች ኩፖን ከገዛቹህ 12.5-13.5 ነው ።
☕ቡና 2.5
☕ሻይ 1.5
☕ቀሽር 3
☕ስፕሪስ 3
⚠️ Note ▶
📚ካፌ ላይ ጨጓራ ምናምን ላለባቹህ ልጆች special ቡፌ አለ ከክሊኒክ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ከሆነ ያበደ ምግብ ይበርብላችሀዋል ።
የግቢው ክሊኒክ ❓
📚 ክሊኒክ በመሻሻል ላይ ቢሆንም እንደማንኛውም ግቢ ደስ የማይል ነገር አለው ፣ ከፓራስታሟል የተሻለ ኪኒን የላቸውም ።
ውሃ ፤ መብራት እና WIFI ❓
📚 ውሃ በፈረቃ ይለቀቃል ካልተለቀቀ ላውንች አካባቢ እንደልብ ስለሚገኝ ጣጣ የለም ፤ መብራትም አይጠፋም ፤ WIFi ትንሽ አዛ ነው ፤ ይሻሻላል የሚል ነገር አለ ።
ሽንት ቤት ❓
📚 ግቢው በዚ ላይ ችግር አለበት ደስ አይልም ፤ ይደብራል ፤ ማሻሻል ያለበት ነገር ነው ።
የዶርም ሁኔታ ❓
📚 ዶርምም ብዙም አያስደስትም ግን የብዙዎቹ ግቢዎች ችግር ስለሆነ ምንሞ አይደረግም መቻል ነው ።
የዕቃ ስርቆት ❓
📚 ግቢ ዉስጥ እና በዙሪያው አስፈሪ ነገር የለም ። ሰላማዊ ከተማ ነው ።
ሀይማኖታዊ ተቋማት ❓
📚 እንደሌሎች ግቢዎች ሃይማኖታዊ ተቋማት በቅርቡ ስለሚገኙ ምንም ዓይነት ጭንቅ እንዳይሰማቹህ ፤ እንደሙዳችሁ አለ ።
ማሳሰቢያ ❗️
⚠⚠⚠⚠⚠⚠ℹ
📚 በነገራችን ላይ ግቢው ዲሲፕሊን ላይ በጣም ሃርድ ነው medicine በተቀበል በ መጀመርያው አመት 16 medicine ተማሪዎችን አባሯል ፤ በዲሲፕሊን ምክንያት ማለት ነው ፤ እንዲሁም ሊመረቅ ሳምንት የቀረዉም ልጅ አባሯል እና ተማሪዎች ግድ ጸባያቸዉን ማስተካከል አለባቸዉ በተልይ ድብድብ ፤ጫት ፤ሲጋራ ምናምን ከባድ penalty አላቸው ። ሌላ ደሞ አንዳንድ ፍሬሽ ተማሪዎች ሊጠነቀቁ የሚገባቸዉ ነገር ጫት በብዛት ስላለ እንዳይሸወዱ ፤ በተለይ ጉብሬ ግቢ የሚደርሳቹህ ተማሪዎች በርጫ በበርጫ ስለሆነ ሀገሩ እንዳትዘናጉ ለማለት ነው ።
N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
© ካምፓስ
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
◦•●◉✿[ Dilla University ]✿◉●•◦
ዲላ ዩኒቨርስቲ ከአድስ አበባ 360ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን
👉የአየሩ ሁኔታ ሚካበድ ሙቀት የለም ግቢው በጣም አርንጓዴ ነው ግን ከግቢው ውጪ ፀሃይ አለ፤በተወሰነ መልኩ ሞቃት ነው ለመልመድ ግን አይከብድም
በውስጡ ያሉ ግቢዎች፡ ሶስት
Techno: Engineering, CS
Main :agree, physics... and
Tena gbi: social...
ትምሮ በጣም አይከብድም ግን እንድታጠኑ በትንሹ ለማጨናነቅ ይሞክራሉ ፤ በተረፈ እንደማንኛውም ግቢ ካልቸከልክ ትጫራለህ
👉የምግብ ቤቶች ዋጋ ባንፃራዊነት በጣም አሪፍ ና ተመጣጣኝ ነው ዋጋ 15–17 ብር ነው
👉የቡና ዋጋ ከ 3–5 ብር ነው በጣም አሪፍ የጨፌ ቡና ዲላ ይገኛል☕☕☕☕
👉የካፌ ምግብ ብዙም አይደለም፤ ከግቢ ውጭ ግን አሪፍ ምግብ ቤቶች አሉ ከ13ብር ጀምሮ🍚🍟🍔🍕🍜
👉ፍርፍር በጣም ርካሽ ነው🍜🍜🍜🍜
👉ሙዝ የአንድ ብር አምስት ፍሬ 🍌🍌🍌
👗👟👞🎩👗👕👡👠👢👕👖🎒👔👚👘👚
👌 ያው ኑሮ በ ዲላ ርካሽ ነው የተለያዩ ኮንትሮባንድ እቃዎች ይገኛሉ
💍ልብስ እና ጫማም በጣም ርካሽ ነው
ባጠቃላይ ትወዱታልቹህ
ውሃ መቼም አይጠፋም
ሻወር 24 ሰዓት መጠቀም ይቻላል፤ ዋን ለሜ ምንጭ እያለች ዲላ የውሃ ችግር አይታሰብም።
N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
©ዘ ካምፓስ
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
🏢 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 🏬
አድራሻ....❓
💬 በኢትዮጽያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛል ።
የአየር ሁኔታ ...❓
💬 የመጀመሪያዎቹ ወራቶች መጠነኛ ብርዳማ ሆነው ወደ ኋላ ላይ ግን ሞቃታማ የአየር ንብረት አለው ።
የካንፓሶች ብዛት ❓
📚 በጣም ብዙ ማለትም አስራ ሰባት ይደርሳሉ ። እያንዳንዱ ካንፓስ የተለያየ ፊልድ ይሰጣል ።
ያሉት ካንፓሶች ፦
6 ኪሎ ፣
5 ኪሎ ፣
4 ኪሎ ፣
ሜክሲኮ ፣
ልደታ ፣
18 ማዞሪያ
ጥቁር አንበሳ ( hospital)
ቃሊቲ ፤
ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ፤
ላምበረት ......ካንፓሶችን ያካትታል ።
በካንፓሶች የሚሰጡ ፊልዶች ❓
🏠6 kilo
💡 ለሶሻል ተማሪዎች ብቻ የሶሻል ዘርፍ ትምህርቶችን ይሰጣል ።
🏠5 kilo
💡 ለኢንጂነሪግ ( Software , electrical , biomedical , mechanical , civil , chemical ..የሚሰጥበት ካንፓስ ነው ።
✅ biomedical engineering ከሚሰጥባቸው ጥቂት ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው።
🏠4 kilo
💡 በዚ ካንፓስ computer science እና computer engineering ይሰጣል ።
🏠 18 ማዞሪያ
💡 የሜዲሲን ዘርፎች በ Other health የሚካተቱትን ይሰጣል ።
🏠 ጥቁር አንበሳ
💡 ይህ ካንፓስ አንጋፋ ሲሆን በውስጡም የMedicine ኮርስን ይሰጣል ፤ ተማሪዎች አፓረንትም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይወጣሉ ።
🏠 ላም በረት
💡 በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ አተኩሮ የሚሰራ ካንፓስ ነው ፤ AASTU የሚገኝበት ሲሆን APPLIED እና Enginering ኮርሶችን ይሰጣል ።
🏠ልደታ
💡በልደታ ካንፓስ የሚሰጡት ፊልዶች architecture ፤ cottom ፤ urban plannig እና የመሳሉትን ያካትታል ።
🏠 ሜክሲኮ
💡 ይህ ካንፓስ የcommerce ግቢ ነው ። ( marketing management , business administration, management የሚሰጥበት ካንፓስ ነው ።)
🏠 ሰፈረ ሰላም
📚 የጤና ዘርፍ ግቢ ነው ፤ ሜዲስን ነርሲንግ እና የመሳሰሉት ወደ ጥቁር አንበሳ 3ተኛ አመት ላይ ከመሄዳቸው በፊት የማሩበት ግቢ ነው ።
🏠 ቢሾፍቱ ካንፓስ
📚 AAU ደብረዘይት ላይ Veterinary medicine & Science collage አለው ። ደብረዘይት ነው የሚገኘው ካንፓሱ በጤና እና ሳይንስ ዘርፍ ይሰጣል ..!
💬ለኢንጅነሪግ ተማሪዎች ፧
➡ የdrawing መሳሪያዎች መያዝ አለባችሁ
➡ Mathematics and Mechanics Statics guide books ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው ።
የካፊው ምግብ ❓
📚 ምግቡ ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ከሌሎች ዮኒቨርሲቲዎች የተሻለ ነው ፤ በተለይ ደግሞ ሰፈረ ሰላም ካንፓስ ደስ የሚል ነው ።
በሳምንት ውስጥ ካፌ የሚሰጡ ምግቦች ዝርዝር ስኬጁል ❓
📚 ከሌሎች ዮኒቨርስቲዎች የተለየ አይደለም ቁርስ ፍርፍር ፤ ሩዝ ፤ ሻይ በዳቦ ፤ ስልስ ይቀርባል ፤ ምሳ እና እራት በሳምንት 2-3 ቀን ስጋ ምሳ እና እራት ይኖራል ፤ ሽሮ ፤ ምስር ፤ አታክልት የመሳሰሉት ምግቦች ይቀርባሉ ። (በፎቶ የምግቡን ጥራት ማየት ይቻላል)
ከካፌ ውጪ ስለሚገኙ ምግቦች እና ዋጋቸው ❓
📚 ከሌሎች ግቢዎች የተለየ አይደለም ነገር ግን 4 ኪሎ ግቢ ምግብ ከሚታሰበው በላይ ቅናሽ ነው ። ዋጋቸው ከታች ተቀምጧል ...!
ቀላል ምግቦች ፓስታ ፍርፍር... etc 20 -30 ብር
ከባድ ምግቦች እንቁላል ፤ ስጋ ..etc 30-50 ብር
ሻይ እና ቡና ...etc 2-4 ብር ይሆናል ።
የሎከር ነገር ❓
📚 ሎከር በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ በዶርም ውስጥ አንድም የሚሰራ ሎከር ማግኘተ ይከብዳል ። አብዛኛው ተበላሽቷል አይሰራም ።
ውሃ ❓
📚ውሃ በተደጋጋሚ ይጠፋል ፤ በተለይ ደሞ የዕረፍት ቀናት ለአንድ ሰዓት ብቻ ተለቆ ይቆማል ፤ ከተማዋ ላይ የውሃ እጥረት ስላለ ግቢ ውስጥም የተለየ ነገር የለም ..!
...ሽንት ቤት ...❓
📚 እንደ ካንፓሶቹ ቢለያይም አብዛኛው ግን በጣም አሪፍ የሚባል ነው ፤ በተለይ 4 ኪሎ በየቦታው ይገኛል ፤ የሚያስከፋ ነገር የለውም ሻል ያለ ነው ።
በግቢው ስላለ የዕቃ ስርቆት፦! ❓
📚 እንደካንፓሶቹ ቢለያይም ግርግር ፤ ረብሽ የሚባል ነገር ስለሌለ የስርቆት ነገር በጣም rare ነው ፤ ቸልተኛ ካልሆነ ስርቆቶ ብዙ የሚያሳስብ ነገር አይደለም ።
የሃይማኖታዊ ተቋማት ፦ ❓
📚 በብዙዎቹ ካንፓሶች በአቅራቢያቸው መስኪድ እና ቤተስኪያን ስላለ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን ለመከውን አያዳግትም ።
📚ተጨማሪ መረጃዎች በፎቶ እና ድምፅ የተቀመጡ ለማግኘት የድምፅ መረጃ ወይም የፎቶ መረጃ የሚለውን በተን ይጫኑ ።
📚 በተጨማሪም ሌሎች መረጃዎች ማወቅ እና መጠየቅ ከፈለጋችሁ ተጨማሪ የሚለውን በመጫን የዮኒቨርሲቲው ዌብሳይት እና ሬጅስትራል ስልክ የተማሪ ተወካዮች ሰልክ እንዲሁም የነባር ተማሪዎች መወያያ ግሩፖችን አቅርበንላቹሃል።
N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
©ዘ ካምፓስ
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
JIMMA UNIVERSITY
አድራሻ ❓
📚 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከሆነችዉ ከአድስ አበባ ደቡብ ምዕራብ በኩል የሚትገኝ ሲሆን ከአድስ አበባ እስከ ጅማ 390 km አከባቢ ነዉ።
የአየር ሁኔታ ❓
ሞቃታማ ፥ ከአዳማ እና ከመሰል ሞቃት ሃገሮች ለሚመጡ ተማሪዎች ሙቀቱ ምንም ዓይነት ተጽእኖ የለውም እንዲያውም ሊበርዳቸው ይችላል፤ በግልባጩ ደግሞ ከብርዳማ አከባቢ ለሚመጡ ተማሪዎች የሙቀቱ መጠን ከፍ ያለ ይሆንባቸዋል ።
ለማንኛውም ቀለል ያሉ ልብሶችን ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው።
ስለ ዮኒቨርስቲው ❓
📚 ድሮም ጀምሮ የፍቅር ከተማ ተብሎ በሚጠራዉ በጅማ ከተማ የሚገኝ አንጋፋና ለኑሮም ሆነ ለትምህርት ከየትኛዉም ዩኒቨርሲቲ የተሻለ ነዉ ብለን የሚናስበዉ ዩኒቨርሲቲ ነዉ። ጅማ ታርካዊና አንጋፋ በሆኑ በንጉስ አባጅፋር ታርክ የታወቀች ከተማ ስትሆን ዩኒቨርሲቲዉ ለከተማ ብዙም ሳይርቅ በከተማ ዉስጥ ነዉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ይገኛል። ሌላዉ እና በጣም ደስ የሚል ታርካዊ ቦታ ቢኖር ንጉስ አባጅፋር ቤተመንግስት የሚገኘዉ ከዋናዉ ግቢ ብዙም ሳይርቅ መገኘቱ ነዉ። ለጉብኝት በፈለጋችሁ ጊዜ ሁለ መዝናናት የሚያስችል ቦታ ነዉ። በጅማ ዩኒቨርሲቲ በጣም የሚያማምሩ ህንፃዎች ከመኖራቸዉ ባሻገር ለመማርም በጣም ምቹ የሆኑ ህንፃዎች ናቸዉ። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በጣም በፍጥነት እያደገች ትገኛለች።
የካንፓሶች ብዛት ❓
📚 በጅማ ዩኒቨርሲቲ አራት Campus ያለ ስሆን ከቅርብ ጊዜ በኋላ አንድ አድስ campus ስራ ይጀምራል ተብሎ ይገመታል። የአራቱ campuses ስማቸዉም እንደሚከተለዉ ነዉ፦
✅# ዋና ጊቢ ( Main campus)..
በዋና ግቢ የሚገኙ ኮሌጆች ፦
# ጤና እንስቲትዩት
# ህግና አስተዳደር ኮሌጅ
# የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ
#ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ እና
# ስነ ባህሪ ኮሌጅ ናቸዉ።
✅ ቤኮ ኮሌጅ ( College of business& economics) ከዋናዉ ግቢ ትንሽ የሚርቅና በመካከላቸዉ ትልቅ መንገድ ያለ ስሆን ዋናዉንና ቤኮ ግቢዉን የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ይገኛል። ከዚህ የተነሳ የዋና ግቢ ተማርዎችም ሆነ የቤኮ ( college of business& economics ) ተማርዎች በድልድዩ በኩል ያለምንም መንገድ ችግር ይመላለሳሉ።
✅# የቴክኖሎጂ ግቢ የእንጂነርግ ተማሪዎች እና የcomputer science ግቢ ሲሆን ለመማርም ለመኖርም ምቹና በጣም አስደናቂ የሆኑ ህንፃዎች ያሉበት ግቢ ስሆን በመጀመሪያ ጊዜ የህንፃዎችን አሰራር ያዬ ሰዉ እዉነትም ይህ ህንፃ የእንጂነሮች ስራ ነዉ ብሎ ከማድነቅ ወደኋላ አይልም። የቴክኖሎጂ ግቢ ከዋናዉ ግቢ የ 5 ብር መንገድ ስሆን ከጅማ ከተማ ከመርካቶ የ 3 ብር መንገድ ነዉ።
✅4# የግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ፦ የሚገኘዉ ከቴክኖሎጂ ግቢና ከዋና ግቢ መሃል ይገኛል። የግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ከዋናዉ ግቢ የ5ብር መንገድ ስሆን ከመርካቶ የ3 ብር መንገድ ነዉ። (በታክሲ)
📚በእያንዳንዱ ግቢ አንደኛ አመት ተማሪዎች ይመደባሉ ፤ የጂማ ዩኒቨርሲቲ ብሎኮች በጣም የሚያማምሩ ናቸው ። ትምሮ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ትንሽ ከበድ ሊልባቹህ ስለሚችል በግቢው ምቾት እንዳትታለሉ ።
የካፌ ምግብ ❓
የምግብ ነገር ከሌሎች ግቢዎች በሚመጡ ተማሪዎች የተመሰከረለት ነው። የግቢ ካፌ በጣም ተስማሚ ከመሆኑ የተነሳ non ካፌዎች ቁጥር አናሳ ነው ።
ምግቡ Normal ነው አንዳንድ ምግቦች ሊደብሩ ይችላሉ በተለይ ለፍሬሽ ቢሆንም ግን ጨጓራ ምናምን አይነካም።
ከካፌ ውጪ ስላሉ ምግቦች ❓
📚በካፌው በተጨማሪ ግቢ ውስጥ እና ከግቢ ውጭ ያሉ ብዙ አማራጮች አሉ። ከግቢ ውጭ ያሉ ብዙ ምግብ ቤቶች አሉ ፥ በአይነትም በጥራትም አሪፍ የሚባሉ። በጣም የሚገርማቹህ ውድ የሚባልው ምግብ 3p ብር ነው ።
🎯 ፓስታ ፣ አይነት ፣ ሽሮ ምናምን ከግቢ ውጭ 20ብር ሲሆኑ ግቢ ውስጥ ደግሞ 25 ብር ናቸው።
🎯 ሻይ ሁለት ብር ሲሆን ቡና ደግሞ 3 ብር ነው። ለነገሩ ብዙም አይገርምም ሀገሩ ጅማ እኮ ነው በቡናማ አይታሙም። ከግቢ ውጭ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ማግኘት ይቻላል፤ 🍌 ሙዝ ፣ ብርቱካን፣ አቩካዶ ምናምን ነፍ ነው ፤ ሌላም የተለያዩ ጁስ ቤቶች ይገኝሉ ፥ ጁስ 15 ብር ነው ።
ውሃ መብራት እና WIFI ❓
📚 የብዙ ግቢዎች ችግር የሆነው የውሃ ጉዳይ ነው፤ ውሃ ጅማ ውስጥ ለአንድ ቀን ጠፋ ማለት ኒዎርክ መብራት ጠፋ ማለት ነው። የውሃ ችግር ጅማ ውስጥ የለም ማለት ይቻላል እንዳያሳስባቹህ ግን ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም አይባልም ግን በዛ ቢባል ለአንድ ቀን ነው ።
መብራት ኖርማል ነው አንዳንዴ ብቻ ይጠፋል ፤ WIFI ለክፉ አይሰጥም አሁን ላይ መሻሻል እያሳዮ ነው ።
📚 በተረፈ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ቀዳሚ ከሚባሉት ዩንቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም በመሆኑ ብዙ አስቸጋሪ ነገር አያጋጥማችሁም ።
የሽንት ቤት ❓
📚 በብዙ ግቢዎች እንደተለመደው ትንሽ የሚያስቸግር ነገር ቢኖረውም ከብዙ ካንፓሶች የተሻለ ነው ።
N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
©ዘ ካምፓስ
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
ድሬዳዋ university፦
አድራሻ ❓
📚 በድሬደዋ ከተማ የምትገኝ ፍቅር ነሆነች ዮኒቨርስቲ ነች ።
የአየር ሁኔታ ❓
📚 ሞቃታማ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ፦ ወፍራም ብርድልብስ አያስፈልግም ፤ አንሶላ እና አልጋ ልብስ በቂ ነው፤ የመጀመሪያዎቹን አራት ወራት ትንሽ ሊበርድ ይችላል ፡ ግንቦት ላይ ምናምን ግን በጣም ሞቃት ነው።
የካንፓስ ብዛት ❓
📚 ድሬ አንድ ግቢ እና ሶስት መግቢያ መውጫ በር ያለው ሲሆን ሁሉም filed of study እዛው ነው የሚሰጠው ሌላ ቅርንጫፍ የለውም ።
🎯 በተጨማሪም ሶስት ላይብራሪ ያለ ሲሆን እነሱም፦
🏩 Tecno
🏩 Main
🏩 Fb/keranyo
✅ የሚሰጡ ፊልዶች በጥቂቱ ፦
🌐IOT
🌐FBE
🌐other social science
🌐Computitional science
🌐Fashion design
🌐Architecture
🌐 Engineering
🗻Engineering fileds
1 mechanical
2 electrical
3 chemical
4 civil
5 textile
6 cotm
7 food
8 industrial
9 survey
📚 arcthicure and Medicine መግባት ለምትፈልጉ መግቢያ ፈተናና የEntrance ውጤትም ይታያል።Software engineering የለም ።
📚 FB ( faculty of business) total social fileds House of medicine ፤ ሁሉንምhealth science ያጠቃልላሉ ።
📚 Architecture and Fashion design መግባት የምትፈልጉ የመግቢያ ፈተና ስላለው እዛያሉ ሲኒየር ተማሪዎችን ስለፈተናው ኢንፎ ብትጠይቁ አሪፍ ነው ። Marketing መግባት ለምትፈልጉ ደግሞ ድሬ ላይ ልብስ ጫማና ምግብ ቅናሽ ነው ።
የካፌ ምግብ ❓
📚 ድሮ አዛ ነበር አሁን ግን በጣም ምርጥዬ ሆኗል ፤ በቃ ኢትዮጵያ ውስጥ አሪፍ ከሚባሉት አንዱ ነው ።
ኀከካፌ ምግብ ውጪ ❓
📚ምግብ ቤቶች ብዙም ውድ አይባሉም አሪፍ ነው።
🎯 ፍርፍር 11-15ብር
🎯 ፓስታ 13/15ብር
🎯 ድንች ለብለብ/ሰላጣ 11ብር
🎯 በአይነት...--------12ብር ከግቢ ውጭ 25ብር
🎯 ቡና 4ብር ------------6 /7 ከግቢ ውጭ
🎯 ሻይ 1.5 or 2---------3/4 ከግቢ ውጭ
ሌላውም fair ነው ።
ዶርም እና ሽንት ቤት ❓
🎯 የዶርም እና የሽንትቤት ነገር አስደሳች አይደለም
ስለ ግቢው ሁኔታ ብዙ ደስ የሚል ነገር አትጠብቁ ፤
በጣም አስጠሊ ነው ።
የትምህረት ሁኔታ ❓
📚የትምህርት አሰጣጡ ምናምን በጣም አሪፍ ነው፥ ላይፉም ሙድ አለው ብቻ እናንተ ኑ ፤ የድሬ ሰዎችም ሲበዛ ፍቅር ናቸው ይህን ስትመጡ ትመሰክራላችሁ ።
የዕምነት ቦታ ❓
📚መስጂድ እና ቤተ-ክርስቲያንም በግቢው አቅራቢያ ስለሚገኝ ይበልጥ ትወዱታላቹህ ።
የረብሽ ጉዳይ ❓
📚 አልፎ አልፎ አንዳንድ አለመረጋጋቶች ይከሰታሉ ፤ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ወደ መስጂዶችና ውደ ቤተ- ክርስቲያናት በመሄድ ራሳቸውን ከአላስፈላጊ እንግልትና ከፌደራል ዱላ ይከላከላሉ ። በአመት አንዴም ሁለቴም ግርግር አይጠፋም ።
የዕቃ ስርቆት ❓
📚 ወደ ድሬ ስትመጡ መጀመሪያ ቀጥ ብላቹህ ወደ ግቢ ግቡ ፤ ፍሬሽ ተማሪዎች ሲመጡ በየመንገዱና በመናሀሪያ በተለይም በታክሲ(ባጃጅ) ላይ ምናምን የናንተን መፍዘዝ ready ሆነው የሚጠብቁ ብዙ ሌቦች አሉ። አሸዋ ገራሚ የዝርፊያ ቦታ ነው በተለይ ጫማ ምናምን ለመግዛት ስትሄዱ ፤ ሰባተኛ፡ ማታ ማታ walk ለማድረግ ስትፈልጉ ፤ seido፡ ቀን ላይ እነዚህን ሰፈሮች በጥንቃቄ ማለፍ ይኖርባቹሃል ። በተለይ ስልክን ገንዘባችሁን ተጠንቀቁ...!
ጫት እና ድሬ ❓
🌲 ድሬ ከተማ ላይ እንደምታቁት ጫት ከምግብ በላይ አንገብጋቢና በጣም ወሳኝ ምግብ ነው ሆኖም ግን ለግቢ ተማሪዎች ጫት ስለማይመከር ለቅምሻም ቢሆን እንዳትሞክሩ። እመኑኝ የድሬ ጫት ከጥፍጥናው የተነሳ ሱስ ያሲዛል(አሉ)....!
የውሃ እና መብራት ጉዳይ ❓
📚ውሃ እና መብረት አያሳስብም ጨቅ ነው ። ትንሽ WIFI ነው እንጂ አዛ የሚያደርገው....!
N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
©ካምፓስ tip
━━━━━━━━━━━━━━━
Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@androethiop
@androethiop
1 095
❗️ ይሰውረን .....Thingዎች😂 ......❗️
📚 ግቢ በጣም አሪፍ ነገሮች የምታሳልፎበት ነው ። በዛውም ልክ ብዙዎች ካለመረዳት ህይወታቸው የሚበላሽበት ነው ። በግቢ መጥፎ ነገሮች እና ባይደርሱብን ባንደርስባቸው የምንመኛቸው ጉዳዮች እንዳስሳለን🙌 ።
💡 ዘ... መጫር 😭
📚 የምትጫረው ዝም ተብሎ አይደለም ህግ ካላከበርክ ነው😄 ። በቃ ከአስተማሪ የምትጣለ ከሆነ ...በየሜዳው ከሴት ጋር የምትልከሰከስ ከሆነ ና ፕሮክተሮቹ ካገኙ😩 ....ግርግር አስነሳለሁ ካልክ😕 ...ሴት አስተማሪዎችን የምታስቸግር ከሆነ 😏....ሱሳሱስ ይዞ ገብቶ መጦዝ🙄 ....ወይ ከዶርም ልጆች ጋር ፒስ ከሌለህ 😴....ትጫራለህ ...ካንፓስ በነጥብም ላሽ ልትባይ ትችያለሽ😔 ። ከመጫር ይሰውራቹሁ ነገር ግን የመጫር መነሻዎችን አውቃችሁ ብትጠነቀቁ መልካም ነው😉 ።
💡 ዘ ....ማርገዝ😇
📚 ሴቶችዬ እንደው አላስችል ብሎ ጭን መክፈት ግድ ከሆነ ቢያንስ መከላከያ አትርሱ(ይሄ ልጅ ምንድነው የሚያወራው እንዳትይ😂 ዩኒቪርስቲ ከዚህ የባሰ የማታውቂው ስንት ጉድ አለ ለራስሽ ነው አሁን ማንበብሽን ቀጥይ😘)...ማርገዝ በጣም አስጠሊ ነው ። የጋሽ እንትና ልጅ ተማሪ ቤት ሄዳ ልጅ ታቅፋ መጣች ይባልልሻል🤯.....ህይወትሽ በሙሉ ነው ሚበላሸው እሱ ምን አለበት ሆዱ አያብጥ ፤ አይነፋ🤭 .......አበስገበርኩ ራሷ ሳታድግ ልጅ ... ወቸውጉድ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ.....አንቺ ጨለልሽ ይሄን ስትሰሚ😭...ካረገዛችሁ ተበላቹሁ በቃ ( አስወርዳለሁ ) ሌላ ጣጣ ውስጥ ...ላይፍ ሃርድ ነው ። አንድ ሰሞን ደሞ ፈተና ካለፋችሁ F ራሱ የማይሰጡ "ገገሙ" ቲቸሮች ስላሉ ትባክናላቹሁ 🙌። ታነቁ ታነቁ ነው የሚላችሁ ። ባካችሁ ህይወታችሁ እንዳይበላሽ ከፈለጋችሁ ...ፍቅር እንኳን ብትጀምሩ ተጠንቀቁ ...ሴቶች ሆዳቹ አበጥ ሲል ጠርጥሩ ቦርጭ እያላቹሁ ጉድ እንዳትሆኑ በኃላ ከምትታነቁ🤗 ... በመጨረሻም በመጀመርያ ግን ጥንቃቄ ። ማንም ከህልምሽ እንዳያሰናክልሽ❤
💡 ዘ ...ሃንግ
📚 ግቢ ሳይዘረፉ መምጣት ተኣምር ነው ። በቃ ወይ ስልክ ወይ ላፕቶት ወይ ልብስ ወይ መጀመርያ ላይ በሶ .....ብቻ የሆነ ነገር ሳትደረጉ አትመጡም😂 ። ስልክ ግቢ ውስጥ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል መሸት ሲል ከክላስ ወይ ላይብረሪ ወደ ዶርም መንገድ ላይ ጭለማ ተገን ተደርጎ ወይም ለሽረሽር ወጥታቹ ወደ ካንፓስ ስትመለሱ ግቢ አከባባቢ ቆመው የሚጠብቁ እነ አቶ ግብዳ BODY አሉ😤 ። ዶርምም ሱሱስ የምትጠቃቀም ሰውዬ ካለች ሲጠርባት መንጩ ሊላቹሁ ይችላል ። ልብስ አስጥታቹሁ የምትወዷትን አንድ ያለቻችሁን ማጣትም ብርቅ አይደለም 😭። በግርግር ግዜ ለመሸሽ ጫካ ከገባችሁ ስልካችሁ ሰታቹ ነው የምታልፎት ። ፍሬሽ የሆናቹ ሰሞን ሰው አትመኑ ፥ ወደ ጫካም ለማየት ብላችሁ አትሂዱ ......ፍሬሽ ሲገባ የአየር ሰዓት ነው ብዙ ጀዋል ይሰረቃል ready ሆነው ነው ሚጠብቋቹሁ ..በር ሳትዘጉ ደሞ እንቅልፍ እንዳይወስዳቹሁ ከፍታቹሁ እንዳትሄዱ ...ዘው ብለው ያገኙትን ይዘው ነው የሚወጡት ......ተጠንቀቁ🫡 ..!
💡 እመት ....ሱስ😶 .....!
📚 ሱስ በካንፓስ መጠንቀቅ ያለባቹሁ ነገር ነው😯 ። ሱሰኞች ለገንዘብ ሲሉ ፍሬሾችን ለመከተብ ይጥራሉ ። በምትወዱት ይዢቹሃለሁ ሱስ የሚባል ነገር ለFUn እያላቹሁ ለፍሬንዶች ብላቹሁ ..ለጥናት ምናምን እንዳትሞኩሩት😷... ራሳችሁን የሲኦል ደጃፍ ነው የምታገኙት ...ሱስ ካለብህ ስልክን ሸጠህ ጫት ትቅምበታለህ 🤧...ከዛ መዝረፍ ትጀምራለህ ትምህርት ይረሳሃል ...ግዜ ካላቹሁ ክበብ ምናምን ተሳተፎ ከሱሰኛ በ billion miles መራቅ ነው🤲 ። ዘመናችሁን ወይኔ ካንፓስ ነው የሚያስብሏቹ ። ጠንቀቅ ነው ።
💡 ጋሽ ...ራስን ማጥፋት🫷 ...!
📚 ብዙ ቴንሽናሞች ፈተና ውጤት ሲበለሽባቸው መታነቅ ከፎቅ መፈጥፈጥ ይቀናቸዋል🥶 ። ለምን የF መኣት ...የ incomplete መኣት አይደረደርም ... ሁሉም ሲቀር ይቀራል ምንም ሁኑ በቃ ...ሞታቹሁ ሲኦል ከምትገቡ ግን ይሻላል ። በቻላችሁ ሰግጣችሁ ለውጤት ስሩ🙂 .. ነገር ግን ግሬድ ተበላሽቷል ብላቹሁ ገመድ መግዛት 😱...በረኪና መጠጣት የፋራ ነው የምር ። ፏንቃ ያዘኝ ብላችሁ😨 አትጃጃሉ ስትፈልግ ገደል ትግባ ሲቀጥል አንተ ሮሚዮ ነህ ለሷ ብለህ ምትሞተው🤦♂️..አ.ት.ጃ.ጃ.ል ....ካልሞትኩ ወፍ .....ህንድ በትምህርት ጭንቅት (ቴንሽን) ምክንያት ከፎቅ በመፈጥፈጥ በአለም አንደኛ ነች ። ህንዶች ለዛ ብለው የሰሩት ያበደ ፊልም አለ ። Three Edits (ሶስቱ ደደቦች ..) ልታዮት የሚገባ የአሚር ከሃን ፊልም ነው ጋበዝኳቹ🤗 ። ስለ ትምሮ ያላቹሁ አመለካከት ይቀየራል ፊልሙን ፈልጌ በቻናሉ እለቀዋለሁ ። የምር ትምህርት ሳትጀምሩ እዮት😄 ።
💡 አጅሬ ....ፖለቲካ 😳...
📚 ካንፓስ የካፌ ካልሆነ በቀር ...ሰልፍ ስታዮ ...ቀነኒሳ እንዳይቀድማቹሁ አርጋቹሁ ሩጡ 🏃♂️። ለምን የሴት ልጅ ግርዛት ይቁም ...የሚል ሰልፍ አይሆንም አትሳተፎ🤫 ....በምን ፍጥነት ተቀይሮ አንገታችሁን እንደሚገርዝላቹ አታውቁም😂 ....ከፓተሊካ ራቅ ነው ። ጀዋር .....ኮ ....ምን አገባኝ🙄 .... አብይ....ምንአገባኝ 😊.....ምርጫ ምን አገባኝ 🤗...... ሆሆ ከዚኛው ትሪሊየን ማይል ነው መራቅ ያለባቹሁ .....ይሄ ሞት ቅርብ የሆነበት ሰፈር ነው ። ወገብ አገዳችሁን ፤ ጥርሰ ፍንጭታችሁ ነው ሚሏቹሁ😄 ....ከሞትማ ራቅ ነው ። ግቢ የሰውነት አቋማችሁን እንጂ የፓለቲካ አቋማችሁን ለራሳቹሁ ራሱ እንዳትናገሩ🙏 .....ኤርፎን ያዙ ልክ ወሬው ፓለቲካ ሲሆን ጆሮዎኣቹ ላይ የምትሰኩት🤗 ...ከፓለቲካ የጩባውን ዘፈን ነው ሚሻላችሁ😂 ።
💡 ዘ.....መጣላት 😡
📚 ካንፓስ በፍፁም ጫማ መለካካት የሌለብን ማስቀየም የሌለብን ሰዎች አሉ🤗 ። የመጀመርያው ከLocal ጋር ነው ማለትም ጎንደር ልጅ ሆነው ጎንደር የተመደቡ ሀገራቸው የሆነ🤫 .....በቃ ሀገሩን ስለሚያቁት አሳራችሁ ነው ሚያበሏቹሁ ከማ ጋር እንደምትሳፈጡ እወቁ🙃 ። ቢናገራቹሁም ቻል ረብሽ በተነሳ ቁጥር ደብቁኝ ከማለት ይሻላል ። ሌላው ዶርም ሜት ነው ። የዶርም ልጆች ምንም ጠባይ ቢኖራቸው አትቀያየሙ LOVE ግድ ነው😇 ። ከተቀያየማቹሁ እቃ ሊያዘርፋችሁ ምናምን ይችላል ። ዶርም ነቆራ ካለ ለማረፍም አይመችም☺️ ....አትጣሉ በምንም። proctor ("ጠባቂዎችን) በፍቅር ያዙ ይጠቅማቹሃል🥰 .... ከአስተማሪም እንዳትጣሉ ....ለሴት ብላቹሁ ሌላ ሙዱ ውስጥም እንዳትገቡ😅 ..20ሺ ሌሎች አሉ ኣ ምን በወጣቹሁ ትጣላላችሁ ....!መርጣችሁ ነው የምታፎነቅቁት😍 ...አብሽር in millions መሆናችን ለዚህ ነው ሚጠቅመን😘(የገባው ገብቶታል😉..!)
via-abel🧑🎤
1 095
🥂 ታላቅ መልዕክት ለፍሬሾች እና ለሪሜዲያል ተማሪዎች....!
💊ግቢ በየትኛውም ሰዓት ብትደርሱ ስለሚያስተናግዷቹህ በጭራሽ ቤርጎ እንዳትከራዩ ፤ በተለይ ከሩቅ ቦታ የምትመጡ ተማሪዎች ግቢው ስለሚረ'ዳቹህ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳትዳረጉ ፤ ስርቆትም ሊኖር ስለሚችል ለብቻቹህ ከሆናቹህ ቤርጎ ባትከራዩ ፒስ ነው(በተለይ ሴቶች)
💊ከብዙ ወከባዎች ለመትረፍ ከፈለጋቹህ አንድ ቀን ቀደም ብላቹህ ግቢ ግቡ ማለት ግቢው በ29 ከጠራ እናንተ በ28 ግቡ ያስጋባችኋል ፤ ቀደም ብሎ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም የሚሉት ሳክስ ነው ፤ቀደም ብላቹህ ከመሄዳቹህ በፊት ግን ነባር ተማሪዎችን ለማንኛውም አናግሩ ።
💊ሻንጣ እንዳይቀያየርባቹህ የናንተን ሻንጣ የምትለዩበት መለያ ምልክት ይኑራቹህ ፤ ብዙ ሻንጣ ሊኖር ስለሚችል በስህተት እንዳይቀያየር (ለክፉም ለደጉ ግን ስልክ ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ አስፍሩበት በወረቀትም ቢሆን....!)
💊ግቢ በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚኖር ባለፈው የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ይዛቹህ እንዳትመጡ ፤በስህተት ካመጣቹህ በር ላይ ይቀሟቹሃል ።
የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ቅርብ ቦታ አስቀምጡ ማለት ሻንጣ ውስጥ አታርጉት ፤ በር ላይ ቅድሚያ ስለምትጠየቁ ሁሉንም ዶክመንቶች በእጃቹህ ለመያዝ ሞክሩ ።
💊ወንዶች ፀጉራችሁን ከልክ በላይ አታሳድጉ ቀለምም አትቀቡ ፤ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ ፀጉር ምናምን ሊባል ስለሚችል በተቻላቹህ ያህል እይታ ውስጥ የሚያስገባ የፀጉር style አይኑራቹህ(ምቺ ያስመታቹሃል....!)
💊ሴቶች አለባበስ ላይ ወጥ አትርገጡ ፤
አንዳንዶቻቹህ ለትምሮ የምትሄዱ እስከማትመስሉ ድረስ ትራቆታላቹህ ፥ የምር አይነፋም ይብራብሽ እርድናም አይደለም ( ለነገሩ ግቢ በር ላይም አይፈቱሽም ጥበቃዎች...!)
💊ግቢ ስትገቡ ፀባያችሁ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ትዕግስተኛ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ከማንም ጋር ብትጣሉ ካለምንም ማስተዛዘኛ የመባረር እድላቹህ ይሰፋል ።
💊የጥላቻና የዘረኝነት ንግግሮችንም ይሁን አመለካከቶችን በፈጠራቹህ ጌታ ይሁንባቹህ እንዳትጠቀሙ ፤ የማንንም ስብዕና የሚነካ ንግግር በስህተት እንኳ እንዳትናገሩ ።
💊 ግቢ ውስጥ ማንንም እንዳትንቁ ፤ ከየትኛውም ከተማ ልትመጡ ትችላላቹህ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ ግን እኩል ናቹህ ማለትም አትበላለጡም።
1 095
🥂 ታላቅ መልዕክት ለፍሬሾች እና ለሪሜዲያል ተማሪዎች....!
💊ግቢ በየትኛውም ሰዓት ብትደርሱ ስለሚያስተናግዷቹህ በጭራሽ ቤርጎ እንዳትከራዩ ፤ በተለይ ከሩቅ ቦታ የምትመጡ ተማሪዎች ግቢው ስለሚረ'ዳቹህ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳትዳረጉ ፤ ስርቆትም ሊኖር ስለሚችል ለብቻቹህ ከሆናቹህ ቤርጎ ባትከራዩ ፒስ ነው(በተለይ ሴቶች)
💊ከብዙ ወከባዎች ለመትረፍ ከፈለጋቹህ አንድ ቀን ቀደም ብላቹህ ግቢ ግቡ ማለት ግቢው በ29 ከጠራ እናንተ በ28 ግቡ ያስጋባችኋል ፤ ቀደም ብሎ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም የሚሉት ሳክስ ነው ፤ቀደም ብላቹህ ከመሄዳቹህ በፊት ግን ነባር ተማሪዎችን ለማንኛውም አናግሩ ።
💊ሻንጣ እንዳይቀያየርባቹህ የናንተን ሻንጣ የምትለዩበት መለያ ምልክት ይኑራቹህ ፤ ብዙ ሻንጣ ሊኖር ስለሚችል በስህተት እንዳይቀያየር (ለክፉም ለደጉ ግን ስልክ ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ አስፍሩበት በወረቀትም ቢሆን....!)
💊ግቢ በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚኖር ባለፈው የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ይዛቹህ እንዳትመጡ ፤በስህተት ካመጣቹህ በር ላይ ይቀሟቹሃል ።
የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ቅርብ ቦታ አስቀምጡ ማለት ሻንጣ ውስጥ አታርጉት ፤ በር ላይ ቅድሚያ ስለምትጠየቁ ሁሉንም ዶክመንቶች በእጃቹህ ለመያዝ ሞክሩ ።
💊ወንዶች ፀጉራችሁን ከልክ በላይ አታሳድጉ ቀለምም አትቀቡ ፤ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ ፀጉር ምናምን ሊባል ስለሚችል በተቻላቹህ ያህል እይታ ውስጥ የሚያስገባ የፀጉር style አይኑራቹህ(ምቺ ያስመታቹሃል....!)
💊ሴቶች አለባበስ ላይ ወጥ አትርገጡ ፤
አንዳንዶቻቹህ ለትምሮ የምትሄዱ እስከማትመስሉ ድረስ ትራቆታላቹህ ፥ የምር አይነፋም ይብራብሽ እርድናም አይደለም ( ለነገሩ ግቢ በር ላይም አይፈቱሽም ጥበቃዎች...!)
💊ግቢ ስትገቡ ፀባያችሁ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ትዕግስተኛ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ከማንም ጋር ብትጣሉ ካለምንም ማስተዛዘኛ የመባረር እድላቹህ ይሰፋል ።
💊የጥላቻና የዘረኝነት ንግግሮችንም ይሁን አመለካከቶችን በፈጠራቹህ ጌታ ይሁንባቹህ እንዳትጠቀሙ ፤ የማንንም ስብዕና የሚነካ ንግግር በስህተት እንኳ እንዳትናገሩ ።
💊 ግቢ ውስጥ ማንንም እንዳትንቁ ፤ ከየትኛውም ከተማ ልትመጡ ትችላላቹህ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ ግን እኩል ናቹህ ማለትም አትበላለጡም።
1 095
የጂኒየስነት ሚስጢር ክፍል 1
🥰ውዶቼ ቀለሜ ትሆኑ ዘንድ የማውቀውን ላካፍላችሁ ?( ታዲያ ይህ የግል ልምዴ እንጂ የፈጣሪ ቃል አይደለም)
🏈ከምን ልጀምር 😊 አዎ በክፍል ውስጥ ስላለው ሁኔታዬ ላውጋችሁ ። በተቻለ መጠን ከፊት ለመቀመጥ ሞክራለሁ ። ይህም ሙሉ ትኩረቴን መምህሩና ሰሌዳው ላይ እንዳደርግ ስለሚረዳኝ ነው ። ( በርግጥ አጭር ስለሆንኩም ነው ። 😅 አትሳቁኣ ) ይህ ካልሆነም መምህሩን ፊትለፊት የማይበት ቦታ ነው ምቀመጠው ። ብዙውን ነገር ምጨርሰው እና ምሰበስበው ክፍል ውስጥ ስለሆነ ልክ መምህሩ ማስረዳት ሲጀምር ብዕሬን አስቀምጬ አይን አይኑን እያየሁ እከታተላለሁ አዳምጣለሁ😄 ። ያው ነገር በአይን ይገባል አይደል የሚባለው ?። ይህ ብቻ ሳይሆን መምህሩ እየተከታተልኩት እንደሆነም እንዲያውቅ አደርጋለሁ😊
ሲገባኝ ራሴን ነቀንቃለሁ ። አታምኑኝም እንጂ ሳይገባኝ ራሱ እጄን ማውጣት አሊያም መጠየቅ ሳይጠበቅብኝ ከመምህሮቼ ጋር ያለቋንቋ እንግባባለን😉 ። ምንም እንኳን መምህሩ ጥሩ ባያስተምርም ሳልንቅ እሰማዋለሁ coz ከክላስ ስመለስ እንዳጠና የሚያነሳሳኝ ክላስ ውስጥ የተማርኩት ስለሆነ ነው✨ ።
🏈ከክላስ ስወጣ ለጥናት የሚመቸኝ ቦታ ላይብረሪ ነው ። ከመፅሀፉ ውጪ ምንም ስለሌ አንብቡ አንብቡ የሚል ነገር አለው ለኔ ።
😭 በርካታ ሰዓታትን ቁጭ ብሎ ማንበብ አልችልም ። ሊገባኝና ልረዳ በምችልበት እንዲሁም አእምሮዬ ንቁ በሚሆንበት ሰዓት ግን በደንብ አነባለሁ😘 ። በመሀል በየ30 ወይም 40 ደቂቃው እረፍት ወስዳለሁ ወይም ሌላ ከት/ት ውጪ ያለ ነገር አነባለው ። አንዱ ሰብጀክት ሲደብረኝ ወደሌላው ቶሎቶሎ እገላበጣለሁ ።
አብዛኛዎቹ ጓደኞቼ ትምህርት ላይ እስከዚህም ናቸው እና በተቻለ መጠን ህልሜንና ጓደኞቼን አላጋጫቸውም😉 ከሚያጠናው ጋር አብሮ ማጥናት መዝናናት ካለብኝ ፈታ ከሚያረገኝ ልጅ ጋር ማውራት😄..አለቀ cool መሆን ግድ ነው ከሚመጣው ሁሉ ጋር አብረው ካበዱ ውድ አንባቢዬ እመኑኝ እድገቶትን ገና አልጨረሱም😂
🥰ፍቅር ምናምን እየተባለ ደሞ ጎበዝ ተማሪ መሆን አይቻልም እና በዚህ ጉዳይ አትጃጃሉ ጎበዝ ተማሪ ለመሆን ሞክሩ..ሁሉም ሰው ከሱ የተሻለ ሰው ይፈልጋልና ራስን በእውቀት መገንባት ግድ ነው😘..ወንድሜ ንቃ አንቺም
🏈 ሳላነሳው የማላልፈው እና የመጨረሻው ነገር ጥያቄ የመስራትን ጥቅም ነው💊 ። ማንበብ ብቻ ዋጋ የለውም ። ጥያቄ ስትሰሩ የጠያቂዎቻችሁን አዕምሮ ታነባላችሁ ትረዱታላችሁ ። ባጠናችሁት ክፍል ላይ እንዴት እና ምን ሊጠይቁ እንደሚችሉ ፣ እንዴት ሊሸውዱ እንደሚችሉ እና በጠቅላላው ፈተና አውጪዎች ምን እንደሚፈልጉ ትረዳላችሁ 😉። ጥያቄዎቹን ትለምዷቸዋላችሁ ። ታዲያ ጥያቄ ስትሰሩ ምንም ላትመልሱ ትችላላችሁ ። ራሳችሁን ስትገመግሙትም ምንም እንዳላነበባችሁ ሊሰማችሁ ይችላል ። ነገር ግን ደጋግማችሁ መስራታችሁን አቷቋርጡ ።
🤲 በመጨረሻ አንድ ሚስጥር ሹክ ልበላችሁ ። በተደጋጋሚ ጥያቄ የምትስቱበትን ት/ት ፈተና ላይ በደንብ ትሰሩታላችሁ ። ስለዚህ ተስፍ አትቁረጡ ። (ጨረስኩ መሰለኝ 😅? )
ክፍል 2 ይቀጥላል😊
1 095
😄እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🍂?
🏈 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።
🍫አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።
🥰አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።
ስለዚህ እንዴት እናብብ🥺
🏈የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም😄።
🏈ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ
🍫 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።
🏈መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።
🖤የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።
🏈ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።
🏈የጊዜ አጠቃቀም
🍫ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።
🏈 አለመሰልቸት
🍫ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።
🏈ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።
🍫ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።
🍷 Google
🏈ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ🥂።
😊
1 095
Repost from TEKA TECH SOLUTION
👩💻 How to Apply:
Show us your skills! Send your resume and examples of your work to contact@tekacreative.com / t.me/tekatech_service Let your creativity shine!
1 095
Repost from TEKA TECH SOLUTION
🚀 Exciting Opportunity at TEKA TECH Solution! 🌐
TEKA TECH Solution is looking for talented individuals ready to make their mark in the world of digital innovation! If you have expertise in Graphic Design, skills in Content Creation, or proficiency in CMS Design & Development, we want to hear from you! 💡
🌟Priority for Female Applicants!
We believe in diversity and empowering women in tech. If you're passionate about digital creativity, we invite you to apply! 🚺✨
🔍 What we're looking for:
- Graphic Design expertise 🎨
- Content Creation skills 📝
- CMS Design & Development proficiency 💻
👩💻 How to Apply:
Show us your skills! Send your resume and examples of your work to contact@tekacreative.com / t.me/tekatech_service Let your creativity shine! ✨
🌈 Why Join TEKA TECH Solution?
- Be part of a dynamic team shaping the future of digital solutions 🚀
- Priority consideration for female applicants, fostering diversity and inclusion 🌐
- Opportunities for growth and skill development 💪
📩 Application Deadline: 16/11/2023
📢Spread the world! Share this post with someone who fits the bill or tag them in the comments. Let's build a diverse and innovative team together! 🌟
#JobOpportunity #GraphicDesign #ContentCreation #TEKATECHSolution #WomenInTech 🚀
1 095
ጥያቄ 2
🤔መጀመሪያ ግቢ ስንደርስ ማን ጋር ነው ምንገናኘው ?
📢 ግቢ በር ላይ ከመኪና ኦር ከታክሲ እንደወረዳቹህ በመጀመሪያ የምታገኙት እንኳን ደህና መጣቹህ የሚል ፈገግ ያለ ፊት ነው ። ( like አስጌ ዴንዴሾ )
❗️እዚህ ጋር መርሳት የሌለባቹህን ላገጠጠላቹህ በሙሉ ሻንጣ እንዳትሰጡ በተለይ መናሀሪያ የምትወርዱ ከሆነ በጣም ተጠንቀቁ አንገታቸው ላይ or ደረታቸው ላይ ባጅ ያጠለቁ እሱንም የዩንቨርሲቲው ማህተም ያለበት መሆኑን ቼክ አርጉ አንዳንድ ከተሞች ላይ በጣም የተደራጁና ረቀቅ ያሉ ሌቦች ስለሚኖሩ be take care.
🔆የትኛውም ግቢ አዲስ ተማሪዎች በሚገቡበት ቀን በር ላይ የተለየ ዝግጅት በማድረግ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ።
❗️ ማንኛውም ተማሪ የያዘውን ሻንጣ ከፍቶ ሳያስፈትሽ እግሩ ወደ ግቢ አይገባም ።
ከፍተሻው በተጨማሪ ግን ሁሉም ተማሪ የዶርምና ብሎክ ቁጥር ማወቅ አለበት እሱም ከግቢ ውጭ ወይም ግቢ ውስጥ ይለጠፋል አንዳንዶች ግቢዎች ደግሞ ዌብሳይት ላይ አስቀድመው ይለቃሉ like AAU እንዳደረገዉ።
የብሎክና ዶርም ቁጥራችሁን ካወቃቹህ ጓዛችሁንም ካስፈተሻቹህ በኋላ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ ዶርም ነው ።(ነባር ተማሪዎች ብሎክ ድረስ ይሸኟቹሃል)
ብሎካቹህ ጋር ስትደርሱ ground ላይ የብሎክ ሃላፊው(ፕሮክተር) ቢሮ በመስኮት በኩል ዶርም ቁጥራችሁን፣ ስም፣ phone number እና ፎቶ በመስጠት ፈርማቹህ የዶርም ቁልፍ ትቀበላላቹህ ።( ቁልፍ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ አንድ የዶርም አባል ብቻ ነው ከተቀደማቹህ ቁልፍ የተሰጠውን ዶርሜት ስልክ ቁጥር ተቀብላቹህ መደወል ነው)
🔆ዶርም ስትገቡ የመጀመሪያ ሰው ከሆናቹህ ያሻችሁን አልጋና ሎከር መርጣቹህ የመያዝ ሙሉ መብት አላቹህ😎 ። ደስ ካላችሁም ትራስ ምናምን መቀያየር ችቡድ ሰባራ ከሆነ እሱንም መቀየር... ብቻ በዶርሙ ላይ የተመቻችሁን የግል ንብረት ማሽከርከር ትችላላቹህ coz ማንም በቦታው ላይ የለምና🤷 ።
❗️ከተቀደማቹህ ግን ከቀደማቹህ ሰው ጋር ሳትጋፉ ያገኛችሁትን ....
አደራ ግን እንዳትጨቃጨቁ
🔆ሌላው ዶርም ስትገቡ አንሶላና ትራስ ጨርቅ ምናምን ሳትጠቀሙ ጋደም ማለት ቢያምራቹህ እንኳ እንዳተኙ coz ፎከታም🙈 ትሆኑብኛላቹህ(biology ላይ የተማራችሁትን አትርሱ fungus+virus)
🔆የዶርም ጣጣችሁን ከጨረሳችሁ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ register ይሆናል (በስራ ሰዓት ብቻ)
አመሻሽ ላይ ግቢ ከደረሳቹህ ለምዝገባ ስለማትደርሱ የዶርማችሁን ጣጣ ለመጨረስ ሞክሩ ለምዝገባው አታስቡ በነገታው መመዝገብ ትችላላቹህ ።
📢ምዝገባ ቦታ ላይ ያለው process
መጀመሪያ ክላሰር ወረቀት ትገዙና የሚሰጣችሁን ፎርም ትሞላላቹህ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኦሪጂናሉንና ኮፒውን ትጠየቁና ኦሪጂናሉ ይመለስላቹሃል ። ፎቶም ትጠየቃላቹህ
በሌላ መስኮት ደግሞ ID ምናምን ታወጣላቹ ከዛ ትንሽ ትንቀዋለሉና ትጨርሳላቹህ
🔆Above ሁለት ሺህ ተማሪ ምናምን በአንድ መስኮት ስለሚስተናገድ በጣም መጨናነቅ ይኖራል ቻል ማድረግ ነው ።
♦️ምዝገባ ከጨረሳቹህ መታወቂያ ከተቀበላቹ ዶርም ሂዳቹ ደስ ካላቹህ ተገልብጣቹህ ለጥ ማለት ትችላላቹህ ።
አንዳንድ ግቢዎች ላይ መጨናነቁ በከፊል ሊቀንስ ይችላል ።
አንዳንዶች ጋር ደግሞ ባስ ይላል
ተማሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ይሆናል register ላይ ግን እንደፍሬሽ አይንከራተቱም ID ማሳደስ ብቻ ሌላው ነገር በሙሉ ተመሳሳይ ነው ።
🖊Muja እንደጣፈው በ አንድሮሜዳ Channel የቀረበ
📌Share and Support Us.🙏📌
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Join us 👇👇
📌||| - @androethiop
1 095
ጥያቄ 3⃣
❓ለአንድ ለዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪ በተለይም ለfresh stud በወር,...ምን ያክል ገንዘብ ያስፈልጋል..?
📢 የመጀመሪያዎቹን ሳምንታት ወጪ ሊበዛበት ስለሚችል እንደ አቅሙ ሳይጋነን የተወሰነ ብር ቢይዝ አሪፍ ነው ( የብሩን መጠን መናገር አልችልም coz እንደአጠቃቀማችን ስለሚለያይ)
🏧 ብር ለምን ለምን ያስፈልገናል ግቢ ውስጥ?
▪️ የካፌ ምግብ ለቀናት ላይለመድልን ስለሚችል ...
▪️ አንዳንድ የዶርም መገልገያዎችን በመዋጮ ለመሸመት
▪️ ኮፒ ምናምን
▪️ሻይ ቡና ለማለት
ወዘተ...
⚠ ለሴቶች ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነባር ሴት ተማሪዎችን ጠይቁ
ለነን ካፌ ተማሪዎች የሚያስፈልጋቹህ ብር እንደየግቢዎቹ ስለሚለያይ ምደባ ከወጣ በኋላ በተከፈተላቹህ ግሩፕ በመግባት ወይም ነባር ተማሪዎችን በመጠየቅ መዘጋጀት ትችላላቹሁ።(cost አንዳንድ ግቢዎች በሴሚስተር ስለሚወጣና የምግብ ቤቶች ዋጋም ስለሚለያይ ብዬ ነው)
🖊Muja እንደጻፈው በ ቀለሜ Channel የቀረበ
📌Share and Support Us.🙏📌
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Join us 👇👇
📌||| - @adroethiop
1 095
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ።😊
በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Website: https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot
1 095
University ያለፉቹ ተማሪዎች ምደባ ወቷል... እምቢ ያላቹ ወይም እስካሁን ድረስ የት ዩኒቨርስቲ እንደተመደባቹ ያላወቃቹ ልጆች comment sr "me" እያላቹ ፃፉ እኔ በ inbox አዋራችኋለው id number ትልኩልኝ እና እኔ እሞክርላችኋለው እስካሁን የ 3 ሰው ማየት ችለናል..
