cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

@Greatmissiontube(ታላቁ ተልዕኮ)✍✍✍✍✍

Great mission with out great comitment geat omission/ታላቁ ተልዕኮ.....For any comment find @millionpaul

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
227Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from Dr. Tesfaye Robele
major cult - ዐበይት መናፍቃን ተስፋዬ ሮበሌ 1994 ዓ.ም Tesfaye Robele 2001
Show all...
በመስቀል ላይ የተጋገረው እንጀራ እግዚአብሔር አንድያ ልጅ አለው። በክበበ መለኮት ከአብ ጋር ባለው ኅብረቱ ወልድ ተብሎ የሚጠራ። እርሱ በኵር፥ የኹሉ ራስና ጌታ ሊኾን የተገባው የኹሉ ወራሽ ነው። መላለሙ በእርሱ ስለ እርሱ ተፈጥሯል (ቈላ. 1፥15-17)። የእግዚአብሔር አብ የባሕርዩ ምሳሌና የክብሩ ነጸብራቅ የኾነው አንድያ ልጅ ከአብ ጋር በተካከለ አምላካዊ ክብር ኗሪ ነው (ዕብ. 1፥3)። በአባቱ ክብር መኖር ባሕርይው እንጅ ትሩፋቱ አይደለም። ከዘላለም እስከ ዘላለም “በዕቅፉ የሚኖረው” አንድያ ልጅም አባቱን ገልጦታል(ዮሐ. 1፥18)። “አብ ወልድን ይወደዋል” (ዮሐ. 5፥20)። የሚያደርገውንም ኹሉ ያሳየዋል። ከሰማያት በመጣ ድምፅ “የምወደው ልጄ እርሱ ነው” ብሎ ዐውጆለታል (ማቴ. 3፥17፤ 17፥5)። አንድያ ውድ ልጅ። ይኽን አንድ በሉ። በሌላ በኩል፥ እግዚአብሔር ለአዲስ ልደት በሚኾን መታጠብና የመንፈስ መታደስ የዋጃቸው የጸጋ ልጆች አሉት። እነዚህ ልጆች የልጁን መልክ እንዲመስሉ (ሮሜ 8፥29) ወስኖ በአድኅኖት ሥራው የተቤዣቸው ሲኾኑ፥ ውሉዳነ-ጸጋ ይባላሉ። እነርሱ በዳግም ልደት ብርሃን ከጨለማ ተነጥቀውና የማደጎ ልጅነትን ተቀዳጅተው ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት ፈልሰዋል (ቈላ. 1፥14)። ልጆች በመደረጋቸው ክብር ምክንያት ብርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናቸው (ገላ. 4፥7)። እግዚአብሔር አብ እነዚህንም ልጆቹን ይወዳቸዋል (1ዮሐ. 4፥10)። ስለ ወደዳቸውም የእርሱ ልጆች የመኾን መብትን አቀዳጅቷቸዋል (ዮሐ. 1፥12)። የተወደዱ ልጆች (ኤፌ. 5፥1)። ይኸን ደግሞ ኹለት በሉ። አንድና ኹለት እንዴት ተዛመዱ? እግዚአብሔር ዓለሙን ስለ ወደደ አንድያ ልጁን ስለ ብዙኀን መዳን ለመስቀል ሞት አቀረበው። ፍቅር የኾነው አምላክ ለወደደው ዓለም አንድ ልጁን ሰጠ (ዮሐ. 3፥16)። አንድያ ልጅም ስለ ብዙ ልጆች ራሱን ቤዛ ለማድረግ ነፍሱን ገበረ (1ዮሐ. 3፥16)። በኀጢአታቸው እንዳይጠፉ ደሙን አፈሰሰላቸው (ኤፌ. 1፥7)፤ ስለ እነርሱ ርግማን ኾኖ ሊቤዣቸው ለመስቀል ሞት በመታዘዝ መዳናቸውን ፈጸመ (ዕብ. 2፥10)። “አንዱ ስለ ኹሉ ሞተ” የማለትን ምሥጢር አተመ (2ቆሮ. 5፥14)። አንድያ ውድ ልጅ ስለ ብዙኀን የሚዋጁ ኀጢአተኞች የማስተሰረያ መሥዋዕት ኾነላቸው (ሮሜ 3፥21-26)። የእርሱ ሥጋ አንድ ጊዜ ስለ እነርሱ ቀርቧልና ለዘላለም ተቀደሱ (ዕብ. 10፥10)። አዎ፥ አንዱ ስለ ኹሉ ሞተ! በሞቱ ሞታቸውን ገደለ (ዕብ 2፥14-15)። አንድያ ልጅ በመስቀል ተዘርቶና ብዙዎችን አፍርቶ በክብር ተነሣ (ኢሳ. 53፥10፡ 12፤ ዮሐ. 12፥24)። አንዱ ስለ ኹላችን ሞተ። እንግዲህ፥ ልብ በሉ፤ ይኸ ኹሉ የኾነ እግዚአብሔር ትርፍ ልጅ ኖሮት አልነበረም። ለመዳናችን የተሰጠው አንድያ ልጅ እንጂ ከብዙ አቻዎቹ መካከል የነበረ ወኪል አይደለም። የሞተልን ትርፍ ልጅ ሳይኾን አንድዬ ራሱ ነው። እግዚአብሔር በአንድ ልጁ ሕይወት በሕይወታችን ተካፈለ። ፍቅሩን ገለጠ። ፍቅሩን ለእኛ የገለጠልን ስለ ፍቅር ረቂቅ ቅኔና መወድስ በማመስጠር አይደለም። በእርሱ ዘንድ ፍቅር ግስ እንጂ ስም ብቻ አይደለም። በግብር የተገለጠ ነው። እግዚአብሔር ዓለሙን ወደደ። ዓለሙን ስለ ወደደ ልጅ ሰጠ። የፍቅሩም ዳር ድንበሩ “አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ” (ዮሐ. 3፥16) የበረታ ኾነ። ይህ በሌላ ጐኑ ምን ያሳየናል? እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን የወደደበት ፍቅር ታላቅነት ከመታወቅ የማለፉን ድንቅ ይመሰክራል። እግዚአብሔር ወዶናል። ሲወደንም በዓለም ውስጥ ያለነው እኛ ብቻ ያለን ያህል በኾነ ፍቅር ሲኾን፥ ፍቅሩ ወደር አልተገኘለትም። የእኔ ኀጢአተኛው የመዋጀቴ ዋጋ የዓለም መድኀኒት የአንድዬ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን የሚያህል ኾነ። ቅዱስ አውግስጢኖስ፥ “God loves each of us, as if there were only one of us” እንዲል። ይህም የተደረገልን በእኛ መልካምነት አልነበረም። “ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቶአልና፤ … ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና፥ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ 5፥7-8)። እነሆ፥ ከዘላለም ጥፋት እንድተርፍ ትርፍ ልጅ ሳይኾን አንድያ ልጁ የሞተልኝ ኀጢአተኛ ነኝ። እኔም፥ ከእኔ ትልቅነት ሳይኾን ከሞተልኝ ጌታ ታላቅነት የተነሣ የእግዚአብሔር ልጁ እንጂ ትርፍ እንግዳው አይደለሁም። ማሟያ ሳልኾን በአብ የተመረጥሁ የልጁ ሥራ ውጤት ነኝ። ክብር ለዘላለም ለስሙ ይኹን! ተወደጆች ሆይ፥ በዚህ በኀጢአቱ ግሳንግስ ታፍኖ እያቃሰተና ሕመሙ ጠንቶበት እያጣጣረ በሚገኝ ድኩም ዓለም ውስጥ ልናውጀው የሚገባ እውነት ይዘናል። እውነተኛው አምላክ ከዓለሙ ሕመምና ሥቃይ የራቀ አይደለም። ይልቅስ ወደዚሁ ዓለም መጥቶ የዓለሙን ሕመም በገዛ አካሉ የተካፈለ፥ ቍስሉንም የተሸከመ አምላክ አለው ማለት አለብን። “እያልን ያለነው” ይላል ኤን. ቲ. ራይት፥ “እግዚአብሔር ዓለሙን ስለ ወደደው አንድ የኾነ ሰውዬ ላከለት” የሚል መልእክት አይደለም፤ ይልቅ፥ “እግዚአብሔር ዓለሙን ወድዷልና የሚወድደውን አንድያ ልጁን ሰጠለት” የሚሰኝ የታላቁን መቈረስ የምሥራች ነው። እግዚአብሔር በልጁ በኩል ለገዛ ራሱ ዓለም ተቈርሶ ታደለ። ታላቁ የሕይወት እንጀራ፥ በቀራንዮ ላይ በደሙ ተዘራ። ልብ በሉ! "የእኛ መሠረታዊው ችግራቸን ኢኮኖሚያዊ ቢኾን ኖሮ፥ እግዚአብሔር ኢኮኖሚስት ይልክልን ነበር። ችግራችን መዝናኛ ቢኾን ኖሮ፥ እንዲሁ አዝናኝ የሕዝብ አጫዋች ወይም ምርጥ ተዋናይ በላከልን ነበር። ታላቁ አስፈልጎታችን ፖለቲካዊ መረጋጋት ቢኾን ኖሮ፥ ፖለቲከኛ ይልክልን ነበር። የሚያስፈልገን ታላቁ ነገር ጤና ቢኾን ኖሮ፥ ሐኪም ይልክልን ነበር። ነገር ግን፥ ታላቁ ችግራችን በኀጢአታችን ምክንያት ከእርሱ ተለይተን መጥፋታችን፥ አስፈሪው ዐመፃችንና ሞታችን ነበርና እግዚአብሔር መድኅን ላከልን" ይላል ዲ. ኤ. ካርሰን። አዎ፥ ዓለምን የሚያድነው መድኀኒት ተልኮልናል። አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ እንደ ተቀኘው፥ “በኹለት አኽያ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው መድኀኒት ዓለምን አዳነ።” ፍቅር ተገለጠ። ፍቅሩ ጫፍ ደርሶ የተገለጠው በቀራንዮ መስቀል ላይ በመቈረሱ ነበር።“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም” (ዮሐ. 15፥13) በማለት ያወጀው ለታይታ አልነበረምና የሕይወት እንጀራ በመስቀል ላይ ተጋገረ። “ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው” (ዮሐ. 6፥51) እንዳለው አደረገ። “የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ. 1፥29፡36) ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል። ተቈርሶም ታድሏል። መውደዱ በሥጋው መቈረስ ደመቀ፤ ለእኛ ያለው ፍቅሩ በደሙ መፍሰስ ታተመ። በቍስሉ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተጨባበጥን። በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር፥ በምድር ለሰው ልጅ ሥምረት ኾነ (ሉቃ. 2፥14)። እነሆ፥ ዐዲስ የወዳጅነት መንገድ ተከፈተ። ከእግዚአብሔርም ጋር ኾነ ከሰው ጋር እንታረቅ ዘንድ የመድኀኒት እንጀራ በቀራንዮ መስቀል ተቈረሰ። እነሆ ቅረቡ፥ መስቀል ላይ የተጋገረውን የሕይወት እንጀራ ብሉ። በሕይወትም ትኖራላችሁ። የታመነው ምስክር ክርስቶስ ራሱ “የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይኾናል” (ዮሐ.6፥57) ብሎናል። መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን
Show all...
ስሑትና አሳች ትርጕማን የ1980ዎቹ የኢኦተቤ/ክ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም የመጀመሪያውም እንደገና የታተመውም የሄደበት የአተረጓጐም ስልት የሚደንቅም የሚያስደነግጥም ነው። ትርጕም ከምንጭ ወደ ተቀባይ ይፈስሳል እንጂ ከተቀባይ ተነሥቶ ወደ ምንጭ ቋንቋ አይሄድም። በዚያ ትርጕም ውስጥ እንዲህ የተደረጉ በጣም ብዙ ቢኖሩም አንድ ሦስት ምሳሌዎች ብቻ እንይ። አንደኛ፥ ቲቶ 1፥5 ሽማግሌ የሚለውን ቄስ ወይም ቀሳውስት ብለው በመለወጥ በግርጌ ማስታወሻ፥ #የግሪኩ #ሽማግሌዎች #ይላል።’ ብለው ጽፈዋል። ከየትኛው ነው የተረጐሙት ማለት ነው? ግሪኩ ይህን ካለ፥ ግሪኩ የግርጌ ማስታወሻ አማርኛው ዋና መሆኑ ነው ማለት ነው? አማርኛ ከግሪኩ መብለጡ ነው ማለት ነው? የግሪኩ ሽማግሌ ያለውን የአማርኛ የቀደሙት ተርጓሚዎችና ሊቃውንትም ሽማግሌ ያሉትን በኋላ የመጣው ተርጓሚ ሊለውጥ ድፍረትን ከወዴት አገኘ? ስሑት ትርጕም። ሁለተኛ ምሳሌ፥ ይህኛው ወደ ምንጩ ወደ ግሪክም፥ ወደ ጎን ወደ ግዕዝም የሚሄድ ነው። ማቴ. 5፥6 ‘ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ’ የሚለውን፥ በመጀመሪያ ‘በግዕዙ፥ ‘ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ’ የሚል የግርጌ ማስታወሻ ተጽፎለታል። በቀጣዩ ደግሞ፥ ‘በግሪኩ፥ ‘ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ ይላል’ ተብሎ የግርጌ ማስታወሻ ተቀምጦለታል። እውነት ይላል? የትኛው ግዕዝ እንደሚል አልተገለጠም። ታትሞ የተሰራጨው የግዕዝ አዲስ ኪዳን፥ ‘ብፁዓን እለ ይርኅቡ ወይጸምኡ ለጽድቅ።’ ይላል። ጽድቅን እንጂ ስለ ጽድቅ አይልም። ወደ ግሪኩ ስንመጣም ስለ ጽድቅ ይላል? አይልም። ታዲያ ለምን ተባለ? ምናልባት ስለ ጽድቅ ሲባል ወይም ለመጽደቅ ሲባል ወይም ጽድቅን ለማግኘት ሲባል መራብና መጠማትን ለማስተማር ይመስላል። በማመን ሳይሆን በመከራና በጉስቍልና ለመጽደቅ የሚደረግ ጥረትን ትክክለኛ ለማስመሰል ያልተባለው እንደተባለ የተደረገ ነው የሚመስለው። ስሑት ትርጕም። ሦስተኛ፥ ሮሜ 8፥34 ‘ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።’ የሚለውን፥ ‘ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ኢየሱስ ነው።’ ካሰኙት በኋላ በግርጌ ማስታወሻ፥ #ግሪኩ #የሚማልደው #ይላል።’ ብለዋል። ማለቱን አምነው ግን ለውጠውታል። ከሌላ ቋንቋ ጋር ተስተያይቶ፥ ለምሳሌ፥ እንግሊዝኛው ወይም ጉራግኛው እንዲህ ይላል ቢሉ አንድ ነገር ነው። ዋናው የተጻፈበት፥ ኦርጅናሌው፥ ‘ግሪኩ እንዲህ ይላል’ ብሎ ያ የምንጩ ቋንቋ ያላለውን መተርጐም ስነ ጽሑፋዊ ወንጀል ነው። መንፈሳዊ ዕብለቱን ትተን። አዲስ ኪዳን የተጻፈው እኮ ሲጀመርም በግሪክ ነው። በግሪክ እንደዚያ ካለ፥ በምን ምክንያትና ሥልጣን ነው እኛ፥ ‘የግሪኩ የሚማልድ ይላል፤ እኔ ግን ይፈርዳል ብዬዋለሁ።’ ወይም፥ ‘የግሪኩ ሽማግሌ ይላል እኔ ግን ሊቅ፥ ሊቃናት፥ ቄስ፥ ቀሳውስት፥ ቀሲስ ብዬዋለሁ።’ ወይም፥ ‘የግሪኩ ጽድቅን ብሏል፤ እኔ ግን ስለ ጽድቅ ብያለሁ።’ የምንለው? ይህ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን፥ ድፍረትም ብቻ ሳይሆን፥ የትርጕም ሕግን መተላለፍ ብቻም ሳይሆን፥ አላዋቂዎችን የማሳት የአሳችነት አካሄድ ነው። የኑፋቄ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፤ ትልቅ እርምጃ! መጽሐፍ ቅዱሳችንን በአክብሮት እንማረው፤ ትርጕሙም፥ አተረጓጎሙም፥ ትርጓሜውም ጤነኛ ሆኖ እንጠብቀው። ዘላለም ነኝ።
Show all...
Repost from Zelalem Mengistu
መልእክተ ይሁዳ
Show all...
በጸሎት ቤት ውስጥ የገጠመን ነገር ከጸጋ ውጪ የተለያዩ ነገሮችን መለማመድ የጀመርንበት ጊዜ ነበር፤ መንፈሳዊ የሚመስል ግን ትክክለኛ ባልሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ውስጥ ገባን። ስሁት ትምህርት ውስጥ ተዘፈቅን፤ ትምህርቱ በጣም ትዕቢተኛ ነው የሚያደርገው:- - ሰው መንፈስ ነው - ትንንሽ እግዚአብሔር ነን - ኀጢአት የሚባል የለም - መጸለይ አያስፈልግም፤ ሕይወታችን ራሱ ጸሎት ነው፤ ቀኑን ሙሉ እየጸለይን ነው የምንውለው። የሚል ስሜት ውስጥ ገባን:: መንበርከክ አቆምን። የእግዚአብሔርን ቃል በጣም አንብበን ስለ ነበር በምንፈልገው መንገድ እየተረጎምን እንደ ፈለግን እንናገራለን። ቤተ ክርስቲያንን ማወክ ጀመርን። በዚህ ጊዜ ከቤተ ክርስቲያን ተጠራሁና መሪዎች አነጋገሩኝ። እኔም ያንን ትምህርት ማቆም እንደማልፈልግ ተናገርሁ። ከቤተ ክርስቲያን ለተወሰነ ጊዜ ገለልተኛ ሆንኩ። ቤተ ክርስቲያን አካባቢ አልሄድም ነበር። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ከእኛ መካከል አብዛኛዎቹ ጫት ቃሚ ሆኑ። ወደ ኋላ ያፈገፈጉ ጥቂት የሚባሉ አልነበሩም። የተለያየ የሃሰት አሠራር ውስጥ የገቡ ነበሩ። እግዚአብሔር ረድቷቸው ደግሞ እንደገና በምሕረቱ ብዛት ወደ ቤቱ የተመለሱ ከአጥፊው ጥፋት የተረፉም ነበሩ። እንግዲህ ከተረፉት መካከል አንዱ እኔ ነኝ። አንድ ቀን ተኝቼ በእንቅልፌ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በጸሎት ጓድ ውስጥ የሚያገለግል ዘለቀ የሚባል ወንድም በህልሜ ሲጸልይልኝና አጋንንትን ከእኔ ውስጥ ውጣ እያለ ሲጸልይልኝ እኔም ስጮኽ አየሁ። ስባንን ላብ አጥምቆኛል፤ በጣም ደንግጬ ተመልሼ ተኛሁ። ጠዋት በር ተንኳኳ በሩን ስከፍተው በሕልሜ ያየሁት ዘለቀ በር ላይ ቆሟል። ምንም አላለኝም። በህልሜ ስላየሁት ደነገጥሁኝ። “እንዴት መጣህ?” ስለው፣ “ንስሐ ትገባለህ ወይስ አትገባም?” አለኝ። ደንግጬ ሕልሜን ማሰብ ጀመርኩኝ። ቀጥሎም:- “አለበለዚያ አጋንንት ይገባብሃል” አለኝ። እዚያው ተንበርክኬ ጸለየልኝና ንስሐ ገባሁኝ፤ እግዚአብሔር አምላክ በባርያው አሳረፈኝ። ወደ አገልግሎቴና ወደ ቤተ ክርስቲያን በንስሐ ተመለስሁ። እንደዚህ ዐይነት ልምምዶች ውስጥ ያላችሁ የእኔ ሕይወት ትምህርት ይሁናችሁ። ሕይወት ቀልድ አይደለም። በእግዚአብሔር እውነት መደራደር የለባችሁም። እኔ እንዳስተዋልሁት የስህተት ትምህርቶች ሰውን እልኸኛና ደረቅ ያደርጋሉ። “እኔ ብቻ አውቃለሁ” እና “እኔ ብቻ ትክክል ነኝ” የሚል ፅንፍ ውስጥ ይገባሉ። ክርስቶስን እንዳትመስሉ ከሚያደርጓችሁ፣ ትሁትና ገር እንዳትሆኑ ከሚከለክሏችሁ ትምህርቶች ልትጠነቀቁ ይገባል።   (ኬፋ ሚደቅሳ፤ ኑሮ ሲኖር፣ ገጽ 63-65።)
Show all...
ፍቅር ፍቅር እደዚ ነው እኔ አይቸዋለሁ፡ ብዙ ንብረት ነበር ባባቴ ቤት ሳለሁ፡ ጥጋቤ በዛና ከዛ ከሞቀው ቤት፡ አባቴን በትእቢት እዲህ ተናገርኩት፡ በላ ድርሻየን ስጠኝ ራሴን ልቻልበት፡ እሂን መጠየቄ የለብኝም ስተት፡ አሁን ስጠኝና ቶሎ ልሂድበት፡ አባቴ በኔ ላይ እጂጉኑ ቢያዝንም፡ ኧረ የድርሻየን አልከለከለኝም፡ ወጣሁ ካባቴ ቤት ከሞቀው ጓዳየ፡ በገንዘብ በሀብት በራሴ ታብየ፡ ያላዩትን ሀገር ናፋቂ ሆኩና፡ የምታምር መስሎኝ አለም ስትለኝ ና፡ ገዘቤን በተንኩት ውርሴ መና ቀረ፡ ሰውም በኔ ስራ እጂጉን አፈረ ፡ ድህነት ወረሰኝ እጂግ ተጓሳቆልኩ፡ እኔም ከራሴ ጋ እዲሁ ተማከርኩ፡ እዴው ባባቴ ቤት ተመልሸ ብሄድ፡ እደልጂነቴ ባይኖርም መወደድ፡ ልጂነቱ ቀርቶ እደ ባርያው ልሁን፡ ኧረ ይሻለኛል ናፈኩኝ ያቺን ቀን፡ አባቴ ሲያየኝ ገና ከሩቁ፡ የቆሸሸውን ልብስ ቶሎ አውልቁ፡ የደለበውን ለልጀ ረዱ፡ የጠፋው ልጀ ተመለ ሰልኝ፡ እያለጮኸ በይኖቹ እያየኝ፡ ታዲያ ፍቅር ከዚ በላይ አለ፡ በደልን ሳይቆጥር ባለም ላይ ያየለ፡ በደሌን ሳይቆጥር እዲህ የወደደኝ፡ የሰማዪ አባቴ ስሙ ይክበርልኝ፡፡ ❤️ፍቅር በደልን አይቆጥርም!
Show all...