cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Tesfaye Robele

ተስፋዬ ሮበሌ (ዶ/ር) ሥነ መለኮት እና ፍልስፍና ያጠና ባለ ጥልቅ እውቀት አቅብተ እምነት ነው። ሥነ መለኮትን እና ፍልስፍናን ለመማር ከፈለጉ ይቀላቀሉን። ይህ ቻናል የራሱ (የዶክተር ተስፋዬ) አይደለም፤ ነገር ግን እኛ መውደዳችንን ለመግለፅና ሰው ሁሉ የእርሱን ጽሑፍ ወይም ቪድዮ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ካለን ፍላጎት የተከፈተ ነው። Ethiopia No: +251923439161 @chereGC

Show more
Advertising posts
4 511
Subscribers
+1324 hours
+507 days
+24930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዛሬ የተወለድሁበት ቀን ነው! የብዙዎች እንኳን አደረሰህ ደርሶኛል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ! ”እነዚህ፣ እኔ ለወንጌል ለመሟገት እዚህ እንዳለሁ ስለሚያውቁ፣ በፍቅር ይህን ያደርጋሉ“ ፊልጵስዩስ 1 ፥16 NASV በእግዚአብሔር ጸጋ ይህንኑ እያደረግሁ እቀጥላለሁ! Today is my birthday! I want to express my heartfelt thanks to everyone who sent their best wishes. I remain steadfast in my commitment to defend and commend the truth claims of Christianity. “knowing that I am put here for the defense of the gospel.” (Phil. 1:16)
Show all...
205🎉 65🥰 30👍 26🔥 4👏 2❤‍🔥 1
አራት ጥራዝ መጻሕፍት! ከተስፋዬ ሮበሌ ፍልስፍናዊ ነገረ መለኮት ላይ አራት ቅጽ ተከታታይ መጻሕፍትን ማዘጋጀት ከጀመርሁ ቆየሁ! የመጀመሪያው ቅጽ፣ "የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የሰብአውያን ነጻ ፈቃድ!" በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው! ምናልባት እስካሁን ካዘጋጀኋቸው መጻሕፍት ይልቅ፣ እነዚህ ሥራዎች በብዙ እርጋታና በትልቅ ትጋት የሚነበቡ መጻሕፍት ናቸው! "ከዚህ በፊት የጻፍኻቸው ከብደውኛል፣ ለመረዳት ተቸግሬአለሁ" የሚሉ ሰዎች፣ እነዚህን መጻሕፍት እንዳይገዙ እንዳያነቡም እመክራለሁ! "ጦሳችሁን ይውሰድ!" ቢከብድም በትዕግሥትና በትጋት የተላለፈውን ትምህርት እመረምራለሁ፣ እውነትን ገንዘቤ አደርጋለሁ የሚሉ፣ "ልባም የቤርያ ሰዎች" ብዙ እንደሚጠቀሙ ቃሌን ልሰጣቸው እችላለሁ! ለምሳሌ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቅድመ ምዳቤ ከሰብአውያን ነጻ ፈቃድ ጋር የሚታረቅ አይመስላቸውም! ወይም የሰብአውያን ነጻ ፈቃድ ከዘላለም ዋስትና ጋር የሚጣጣም አይመስላቸውም! ከዚህ የተነሣ አንዱን በመካድ ሌላውን ማመን ዕጣ ክፍላችን ሆኗል! በዚህ አግባብ አገሪቱ በሁለት ተከፍላለች-- ከዚህም የተነሣ ወይ በወንድም ካልቪን ወይ በወንድም አርሜኔዎስ አንጻር መሰለፍ የግድ ሆኖል! [የአምላክን የመጻኢ ዘመን ዕውቀት የማይቀበሉ፣ “ክፍት አማኒያን" (Open Theism) እንዳሉ በጭምጭምታ ሰምቻለሁ! አንድ ወይም ሁለት!] ለሃያ ሰባት ዓመት የወንድም ካልቪን ዐስተሳሰብ ትክክል ይመስለኝ ነበር! ብዙዎች ይህን ነባቤ ቃል እንዲቀበሉ በብዙ ሞግቻለሁ! (ይህን በመሞገት ቁጥር አንድ ሳልሆን አልቀርም!) ለድኅረ ምረቃ ካልቪን የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ሲሄድ አርሜናውያን የሆኑ ብዙ ወዳጆቼ፣ "እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ!" ብለው ነበር! ካልቪን በነበርሁበት ወቅት የትምህርት ቤቱ የበላይ ኀላፊ የስመ ጥሩ የሃይማኖት ፈላስፋ የአልቪን ፕላንቲንጋ (Alvin Plantinga) ታናሽ ወንድም ቆርኔሌዎስ (ኒል) ፕላንቲንጋ (Cornelius Plantinga Jr) ነበር! እርሱን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ቤቱ ዕውቅ መምህራን "ካልቬኒዝም በግማሽ ተሳስቶአል" የሚል አቋም ያላቸው እንዲሁም "የመኻል ዕውቀት" (Middle Knowledge) ይህን ክፍተት ይሞላል የሚል ዐስተሳሰብ የሚያራምዱ ሆነው ተገኙ! ኋላም ታይም መጽሔት (Time magazine) “America’s leading orthodox Protestant philosopher of God.” (1980 ዓ.ም) ሲል ያደነቀው አልቪን ፕላንቲንጋ፣ ከኖተርዳም ዩኒቨርስቲ ወደ ካልቪን "Harry Jellema " በሚባለው ወንበር ተሰይሞ መጣ! በዚህ ጊዜ ነው "Warranted Christian Belief" የተባለውን ኮርስ በራሱ በአልቪን ፕላንቲንጋ ሥር የመማር ዕድል ያገኘሁት! በዚህ ጊዜ ነበር "የካልቬኒዝም" ዐስተሳሰቤ ትልቅ አደጋ የገጠመው! ከዚያ ኋላ ነገሩን በጥሙና መመርመር ጀመርሁ! አቋም ለመያዝ ግን ስድስት ዓመት ያህል ፈጀቶብኛል (በዚህ ረገድ ያሉ መጻሕፍት ውስብስብ እንዲሁም ብዙ ናቸው)! ከዚያም "የመኻል ዕውቀት" (Middle Knowledge) ዐስተሳሰብን ተቀበልሁ! ይሁን እንጂ ዛሬም ካልቪናዊነት ያሳዝነኛል! አንጀቴን ይበላዋል! (ዐፈር ልብላ!) የዚህ ዐስተሳሰብ ባለቤት Alvin Planning ብቻ አይደለም! የካቶሊኩ ኢየሱሳዊ (Jesuit) ቄስ ልዊስ ሞሊና (Luis de Molina) ከ500 ዓመት በፊት ይህ ዐይነት ዐስተሳሰብ ያራምድ እንደ ነበር ይነገራል! calculusን Isaac Newton እና Gottfried Leibniz በተለያየ ወቅትና መንገድ እንዳገኙት ሁሉ! "የመኻል ዕውቀትን" (Middle Knowledge) ያገኙት ፕላንቲንጋና ሞሊና ናቸው! ዐሳቡን በጥልቀት በመተንተን ብዙ ፈላስፎች እንዲቀበሉት ያደረገው ግን ፕላንቲንጋ ነው! የኦክስፎርዱ የሃይማኖት ፈላስፋ Richard G. Swinburne "በአልቪን ፕላንቲንጋ መጠን ትልቅ ተጽእኖ የፈጠረ ኀላዪ (thinker) እኔ አላውቅም" ያለለት ትልቅ ሰው ነው! በሕይወት እያለ ከ30 ሰዎች በላይ የዶክትሬት መመረቂያ ጽሑፋቸውን የጻፉበት አስደናቂ ሰው ነው! ዛሬ የዚህ ሰው ዐስተሳሰብ ብዙ ተከታይ እያገኘ ተቃዋሚዎቹን እየናጠ ነው! ብዙ የካልቬኒዝም አፈ ቀላጤዎች ለዚህ ዐስተሳሰብ እጃቸውን ሰጥተዋል! በቅርቡ እንኳ ታዋቂው የካልቬኒዝም ተሟጋችና የ"Southern Baptist Theological Seminary" የደርዛዌ መለኮት ፕሮፌሰር Bruce A. Ware ይህን አስተምህሮ ተቀብሏል! YouTube ላይ በብዛት የምታገኙት ግን ካልቬኒዝምን ወክሎ ሲሟገት ነው! እርሜኒዮስ ከካልቪን ጋር ይታረቃል እያልህ ነው? ለምትሉኝ መልሴ እንዴታ ("ስነግርህ!") እንደ ኒቆዲሞስ በስውር (በሌሊት) ልታወያዩኝ የምትፈልጉ የነገረ መለኮት ሰዎች በስውር ምክር ልሰጥ እችላለሁና አግኙኝ! ደግነቴ መቼ ነጥፎ ያውቃል! ትሕትና የዕውቀት ቁልፍ ናት!
Show all...
89👍 38🏆 11🥰 4😱 3🥱 3💩 1
አራት ጥራዝ መጻሕፍት! ከተስፋዬ ሮበሌ
Show all...
🤩 3🏆 1
አፊዎተ እግዚአብሔርና ቀኖናውያት መጻሕፍት ክፍል ሁለት ከተስፋዬ ሮበሌ ዕቅበተ እምነትና ቅዱሳት መጻሕፍት ባለፈው ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን በተመለከተ፣ አራት መሠረታውያን የሆኑ ጒዳዮችን ተመልክተን ነበር፡፡ አንድ መልእክት ከአምላክ ወደ ሰው ሲተላለፍ፣ “ግልጠት እግዚአብሔር” [“አፖካሊፕሲስ” (ἀποκάλυψις) ወይም “ፋኔሮ” (φανερόω)]፣ ከተገለጠለት ሰው ወደ ጽሑፍ ሲሻገር፣ “አፊዎተ እግዚአብሔር” [“ቴዎፊኒስቶስ” (θεόπνευστος)]፣ ከጽሑፍ (ከወረቀት) ወደ አንባቢ ልብ ሲዘልቅ፣ “አብርሆተ እግዚአብሔር” [ፎቲስሞስ “φωτισμός”]፣ ከልብ ወደ ኑሮ ሲሸጋገር ተግባራዊ የሆነ ክርስቲያናዊ ሕይወት እውን ይሆናል፡፡ ክርስቲያናዊ ዕቅበተ እምነት ነባራዊ መሠረት ይፈልጋል፡፡ አመክንዮ ብቻ ሳይሆን ነገረ መለኮትም ነባራዊ ነው የሚል ጽኑ እምነት በአማንያኑ ዘንድ ሁሉ አለ፡፡ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያን ትውፊት ተከትለን፣ ክርስትናን ከወደረኞቹ (ከባላንጣዎቹ) ልንጠብቀውም ሆነ ልናስጠብቀው አንችልም፡፡ ከላይ ለማየት እንደ ሞከርነው ክርስትና የሚገለጸው አንጡራ እምነቶቼ ናቸው በሚላቸው በመሠረታውያን ትምህርቶቹ ነው፡፡ የዕቅበተ እምነት ቀዳማይ ዐላማና ግብ፣ እነዚህን መሠረታውያን ትምህርቶች ከጥቃት መጠበቅ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ይህን ትምህርት በመቀበል፣ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸውና ጌታቸው እንዲቀበሉ ማስቻል፤ የተቀበሉን ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ዕገዛ ማድረግ ነው፡፡ ይህ እውን መሆን የሚችለው ታዲያ፣ ክርስትና የማይነቃነቅ ነባራዊ መሠረት ሲኖረው ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ:— ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከትውፊት አንጻር የሚታያቸው እጅግ በርካታ ድርሳናት፣ ገድላት፣ ተኣምራት፣ ፍካርያት ወዘተ አሉ፡፡ እንኳን በካቶሊክና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያለ አማኒ ይቅርና፣ በሌላ ዓለም የሚገኙ ኦሬንታል ኦርቶዶክሳውያን የሆኑ ሰዎች እንኳ፣ እነዚህ መጻሕፍት መኖራቸውን በጭራሽ አያቅም፡፡ መሠረታዊ የሆነው ሌላ ነጥብ እነዚህ ድርሳናት፣ ገድላት፣ ተኣምራት፣ ፍካርያት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ እርስ በርሳቸውም በብዙ ጒዳዮች ላይ የመቃረንና የመምታታት ጠባይ አላቸው፡፡ ምንም እንኳ አንዳንድ ሰዎች የተለያዩ ሥነ ትርጓሜዎን በመጠቀም ቅራኔዎቹ ለማብረድ ቢሞሩም፣ የቅራኔዎቹን ብዛትና ጩኸት ማፈን ግን በጭራሽ አልተቻለም1፡፡ ከዚህ ጋር ተዛመጅ የሆነው፣ የኢትዮጵያ ኦቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጽላትንና ታቦትን በተመለከተ ያላት እጅግ ሰፊ ሐተታና፣ በሌላ ዓለም ለሚገኘው ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ድርሳኑም ሆነ ሥርዐቱ እጅግ ሲበዛ ባዕድ ናቸው፡፡ ይህ ጒዳይ እንኳን በሌላ አብያተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ክርስቲያን ይቅርና፣ በየዘመናቱ ኦርቶዶክሳውያንን ሊቃውንትን በብዙ እያሳሰበ የሚገኝ፣ እልባት ሊበጅለት በጭራሽ ያልቻለ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቅ ችግር ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ይህን ጉዳይ አበክረው እንዲመለከቱት በትሕትና እጠይቃለሁ:: ቅራኔን፣ “ትውፊት” በሚል መጐናጸፊያ ልንሸፍነው፣ ችላ ብለን ልናልፈው፣ አናንቀን ልንተወው፣ አይተን እንዳላየ ገሸሸ ልናደርገው አንችልም፡፡ እርስ በርስ የሚምታታን ትምህርት ልናጸድቅም ሆነ፣ በዕቅበተ እምነት ከአደጋ ልንጠብቀው በጭራሽ አንችልም2፡፡ በአብያተ ክርስቲየናት ዘንድ ይህንና ይህን መሰል እጅግ በርካታ አንጻራዊ አካሄዶች ባሉበት ሁኔታ፣ ነባራዊ መሠረት ሳይኖር፣ ክርስትናን ከወደረኞቹ መጠበቅ አይቻልም፡፡ ይቀጥላል… ኅዳግ መዘክር ———————— ለአብነት ያህል፣ “ገድል ወይስ ገደል” የሚለውን መጽሐፍ ይመለከቷል፡፡ እጅግ መሠረታውያን የሚባሉ የሥነ አመክንዮ ሕግጋት ሦስት ናቸው፡፡ የእነዚህም ሕግጋት ማዕከል ቅራኔን ውግድ ማለታቸው ነው፡፡ የያውነት ሕግ (law of identity)፣ ማዕከለ ውጋጅነት ሕግ (law of excluded middle)፣ ቅራኔ አልቦ ሕግ (law of non-contradiction) ናቸው፡፡
Show all...
👍 24🥰 4
አፊዎተ እግዚአብሔርና ቀኖናውያት መጻሕፍት ክፍል ሁለት ከተስፋዬ ሮበሌ
Show all...
👍 2
እነዚህን መጻሕፍት አግኝታችኃል?
Show all...
🤷‍♂ 48👍 26 22😢 11👎 3
ትንሣኤ ሙታን የአካል ወይስ የመንፈስ? ክፍል ሁለት ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ https://youtu.be/RlcrEF2HDX4
Show all...

27
አፊዎተ እግዚአብሔርና ቀኖናውያት መጻሕፍት ክፍል አንድ ከተስፋዬ ሮበሌ ሀ. ትልም የዚህ ተከታይ ጽሑፍ ቀዳማይ ዐላማ:— (1) በዕቅበተ እምነት ውስጥ የቅዱሳት መጻሕፍት ያላቸውን ጒልህና ትክክለኛ ቦታ ማሳየት፣ (2) በሃይማኖት ገበያ ውስጥ የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣናዊ ቃልነት ለሚቃወሙ ሁለት አግድም ዐደግ ዐሳቦች፣ አጸፋ መዘንዘር ነው፡፡ ለ. መግቢያ የክርስትና ሃይማኖት፣ “አምላክ ፍጥረቱ ለሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ፣ ራሱን በተለያየ መንገድ ገልጾአል” ብሎ ያምናል፤ ያሳምናል፤ ያጠምቃል[1]፡፡ በነገረ መለኮት ትምህርት፣ አምላክ በሥነ ፍጥረት ወይም በታሪክ ሂደት ውስጥ ራሱን የገለጠበት መንገድ፣ “አጠቃላይ መገለጥ”[2] (ጥቅልል አስተርዮት[3]) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ አምላክ ራሱን በስፋት የተነተነበት መንገድ ደግሞ፣ “ልዩ መገለጥ”[4] (ልዩ አስተርዮት) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ጥቅልል አስተርዮት ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር[5] የተወሰነ ጥቈማ ቢኖረውም፣ የአምላክን ባሕርይና ዕቅድ በዝርዝር አይናገርም፡፡ ልዩ አስተርዮት ግን የአምላክን ማንነት፣ ለፍጥረቱ ያለውን ዘላለማዊ ዕቅድና ምግባራዊ አኗኗር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጒዳዮችን በዝርዝር ይተነትናል፡፡ ከብዙ አንጻር ሲታይ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የተለየ መጽሐፍ ነው፡፡ በብዙ መጻሕፍት ውስጥ በእማኝነት የተጠቀሰ፣ እጅግ ብዙ በሆኑ የዓለማችን ቋንቋዎች የተተረጐመ፣ እጅግ ጥንታዊ የሆነ፣ በብዙ ሚሊዮን ሳይሆን በብዙ ቢሊዮን ቅጆች ታትሞ የተሠራጨ፣ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ እጅግ ትልቅ አዎታዊ ተጋቦት (ተጽእኖ) የፈጠረ…እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ አንዳችም መጽሐፍ የለም ቢባል፣ እንኳን እብለት ነቊጥ ታህል ግነት የለበትም፤ በጭራሽ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለዓለም ሥልጣኔ፣ ፍልስፍናና ሳይንስ ፈር ቀዳጅ ፋና ወጊ መሆኑን ማን ይክዳል? ይህና ይህን መሰል ጒዳዮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ በሰው ልጆች ሕይወትና ታሪክ ውስጥ ትንግርታዊ ክሥተት፣ ተኣምራዊ ሁነት አድርገውታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልዩ አስተርዮት ነው በሚለው አስተምህሮ ውስጥ አራት መሠረታውያን ጒዳዮች አሉ፡፡ ይኸውም:— (1) ግልጠተ እግዚአብሔር (አስተርዮተ እግዚአብሔር)[6]፣ (2) አፊዎተ እግዚአብሔር (እስትንፋሰ እግዚአብሔር)፣ (3) አብርሆተ እግዚአብሔርና (4) ተግባራዊ ክርስቲያናዊ ሕይወት ናቸው፡፡ ሐ. አስተርዮተ እግዚአብሔር እነዚህን አራት መሠረታውያን የነገረ መለኮት ጭብጦች፣ በቅኝት መልክ እንመልከት፡፡ በመጀመሪያ ግልጠተ (አስተርዮተ) እግዚአብሔርን እንመልከት፡፡ የዐማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጒሞች፣ “መገለጥ”[7] ብለው የተረጐሙትን ቃል፣ የዐዲስ ኪዳን ግሪክ መጻሕፍት፣ “አፖካሊፕሲስ” (ἀποκάλυψις)[8] እና “ፋኔሮ” (φανερόω)[9] የሚሉትን ሁለት ቃላት፣ ቀያይረው ተጠቅመዋል፡፡ የግሪክ መዛግብተ ቃላት[10]፣ ሁለቱም ቃላት መሠረታዊ ትርጒም አንድ መሆኑ፣ በዐማርኛው አንድ ቃል ወክሏቸው መገኘቱ፣ አንዳችም የትርጒም ተፈልሶ እንዳይኖር አድርጓል፡፡ የሁለቱም ቃላት መሠረታዊ ትርጒም አንድ ነውና፡፡ ይኸውም:— ተሸፍኖ የነበረን ነገር ሽፋኑን በማንሣት ምንነቱን ወይም ማንነትን ማሳየት፡፡ በድቅድቅ ጨላማ ውስጥ ያለን ነገር፣ በበርሃን ወጋገን ግልጥልጥ አድርግጎ መመልከት፣ ስውሩንና ድብቁን ነገር ገሓድ ማውጣት፣ ለቀትር ፀሓይ ማጋለጥ፣ ርቃኑን ማስቀረት ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ በክርስትና ሕይወት እንዲሁም በዕቅበተ እምነት አገልግሎት ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዳለው አመልካች ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች፣ ራሱንና ዐላማውን በዝርዝር ተንትኖአልና[11]፡፡ አምላክ ራሱን ለቅዱሳት መጻሕፍት ጸሓፊዎች የገለጠው እጅግ ብዙ በሆነ መንገድ ነው፡፡ በራእይ፣ በህልም፣ በድምፅ፣ ተኣምራዊ በሆነ መንገድ ወዘተ፡፡ (የሚከተሉትን ክፍሎች ይመለከቷል ዘፍ. 12፤ 32፤ ዘፀ. 3÷10፤ 33÷20፤ 13÷20-22፤ 24÷9-11፤ ዘዳ. 31÷14-15፤ ኢያ. 5÷13-15፤ ዳን. 3፤ ዕብ. 1÷1-2፤ ማቴ. 3፤ 5÷17፤ 3÷13-17፤ ዮሐ. 16÷8-11፤ ዮሐ. 1÷1-14፤ ሐሥ. 2÷3-4)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጻሕፍት ፍጹም ልዩ የሚያደርገው፣ አምላክ ልዩ በሆነ መንገድ ለፀሓፍያኑ ራሱን መግለጡ ብቻ ሳይሆን፣ ከአምላክ የተገለጠው ሐቅ፣ በአምላክ ሉዓላዊ ጥበቃ በትክክል ተጽፎ መቅረቡ ነው፡፡ ግልጠተ (አስተርዮተ) እግዚአብሔር አምላክ ለፀሓያኑ ራሱን የገለጠበት መንገድ ሲሆን፣ አፊዎተ እግዚአብሔር ደግሞ፣ ፀሓያኑ ጒዳዩን በጽሑፍ ያስቀመጡበት ሂደት ነው፡፡ መ. አፊዎተ እግዚአብሔር አሁን ደግሞ፣ “አፊዎተ[12] እግዚአብሔር” የሚባለው ፅንሰ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ፣ ዐጭር ቅኝት እናድርግ፡፡ በግሪክ፣ “ቴዎፊኒስቶስ” (θεόπνευστος) የሚለው ቃል፣ በዐዲስ ኪዳን በኲረ ጽሑፋት ላይ አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሲሆን (2ጢሞ. 3÷16)[13]፣ ነባሩ እንዲሁም ዐዲሱ መደበኛ ትርጒም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው” መጻሕፍት ብለውታል፡፡ የእንግሊዝኛ መጻሕፍት፣ “inspiration” የሚል አቻ ቃል ቀምረውለታል፡፡ የቃሉን ጭብጥ በትክክል ለማረዳት የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት እንዲሁም ዘላለማዊነት ታሳቢ አድርጎ መነሣት የግድ ይላል፡፡ ምክንያቱም በዚህ መጠን ጥልል ጥንፍፍ ያለ ሥራ ማከናወን የሚለው፣ አምላክ ብቻ ነው፡፡ አምላክ “እንዴት?” አይባልምና፡፡ □ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ፣ ልብንም ለማቅናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል”፡፡ እነዚህ መጻሕፍት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን (2ጢሞ. 2÷15) እንዲሁም በወቅቱ እየተነበቡ የነበሩትን፣ የዐዲስ ኪዳን መጻሕፍት (2ጴጥ. 3÷16) ሊያመለክት ይችላል፡፡ አብ ኢየሱስን በላከበት ሥልጣን (ዮሐ. 20÷21)፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን መላኩ፣ ደቀ መዛሙርት የቤተ ክርስቲያን መሠረት እንዲሆኑ አድርጓል (ኤፌ. 2÷19-22)፡፡ ይህ ባሕርይ በዐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ላይ መታየቱ፣ ቃሉ ለብሉያት ብቻ ሳይሆን፣ ለዐዲስ ኪዳን መጻሕፍትም እንዲገለግል ምክንያት ሆኗል፡፡ በዐማርኛ የተዘጋጁ የነገረ መለኮት መጻሕፍት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ይዘት፣ “አፊዎተ እግዚአብሔር”፣ “አምላካውያት መጻሕፍት”፣ “እስትንፋሰ አምላካውያት” ወይም “ቀኖናውያት መጻሕፍት” ብለውታል፡፡ አንዳንድ ጸሓፍያን ደግሞ፣ “አሥራው መጻሕፍት” ይሉታል፡፡ “አሥራው” የሚለው ቃል፣ “ሥረ መሠረት”፣ “መሠረቶች” የሚለውን ቃል የሚያመለክት ቅመራው፣ “የመጻሕፍት ሁሉ ሥረ መሠረት” ለማለት ተፈልጎ ነው[14]፡፡ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውን፣ “መጻሕፍት አምላካውያት” ያሏቸው ሲሆን፣ “አምላክ ያጻፈቸው፣ በአምላክ ፈቃድ የተጻፉ፣ የአምላክን ነገር የሚናገሩ” ለማለት ነው[15]፡፡
Show all...
👍 17 2
“ቴዎፊኒስቶስ” (θεόπνευστος) የመጽሐፉን ይዘት (ጭብጥ) ብቻ አመልካች ሳይሆን፣ ሂደቱ (የተገለጠው ነገር ወደ ጽሑፍ የተላለፈበት መንገድ) ሕጸጽ አልባ መሆኑን አመልካች ነው፡፡ ይኸውም የአምላክን እስትንፋስ የተሸከመ መጽሐፍ መሆኑ (ማቴ. 4÷4፤ 2ሳሙ. 23÷2፤ ዕብ. 1÷1)፣ አፊዎተ (እስትንፋሰ) እግዚአብሔር እንዴት ሊሆን ቻለ፣ የሚለውን ዐሳብ የሚመልስልን 2ጴጥሮስ 1÷21 ነው፣ “በእግዚአብሔር ተልከው፣ ቅዱሳን ሰዎች፣ በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” የሚለው ዐሳብ ነው፡፡ የዐማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጒሞች፣ “በመንፈስ ተነድተው” ሲሉት፣ እናት ቋንቋው (ግሪክ)፣ “ፌሮማይ” φέρομαι) ወይም፣ “ፌሮ” (φέρω) ይለዋል[16]፡፡ ቃሉ በግሥ መልክ ግልጋሎ ላይ መዋሉ፣ ጒዳዩ ሂደት (ግብር) አመልካች ነው፡፡ ጥንታውያን መርከቦች ሞተር ስላልነበራቸው፣ የሚንቀሳቀሱት በንፋስ ኀይል ነበር፡፡ የካፒቴኑ ተግባር፣ የንፋሱን መቀበያ ከንፋሱ ተቃራኒ አቅጣጫ በማድረግ መርከቧ በንፋሱ፣ “እንድትነዳ” (“ፌሮማይ” φέρομαι) ማድረግ ነው፡፡ መርከቧን የሚሾረው ካፒቴኑ ቢሆንም የታሰበው ቦታ፣ “እየነዳ” (“ፌሮማይ” φέρομαι) የሚያደርሳት፣ ግን ንፋሱ ነው (ይህን ዐሳብ ሐዋርያት ሥራ 27÷9-20 ጋር ያነጻጽሯል)፡፡ ይህ ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት እውን በመሆናቸው ሂደት ውስጥ፣ አምላክ ሰዎችን መጠቀሙ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ዐሳብ በሰብአውያን ቋንቋ መተላለፉን አመልካች ነው[17]፡፡ ስለዚህ፣ “ግልጠተ አምላክ” መልእክቱ ከአምላክ ወደ ጸሓፊው የተላለፈበት መንገድ ሲሆን፣ ከጸሓፊ ውደ ጽሑፍ የተላለፈበት ሂደት ደግሞ፣ “አፊዎተ እግዚአብሔር” ነው[18]፡፡ ሠ. አብርሆተ እግዚአብሔር አንባብያን በመንፈስ ቅዱስ ዕገዛ፣ አንድ ምንባብ ምን ትምህርት አለው የሚለውን ጒዳይ በትክክል ሲገነዘቡ፣ አምለክ መልእክቱን ሲያበራላቸው፣ “አብርሆተ እግዚአብሔር” አገኙ እንላለን፡፡ አብርሆተ እግዚአብሔር፣ ቅን አንባቢዎች ትክክለኛን የትርጓሜ ስልት ተከትለው በማበብ፣ የአንድን ክፍል ምንባብ በትክክል የሚረዱበት ሂደት ብቻ ሳይሆን፣ ቃሉ በትክክል ወደ ልቦናቸው መዝለቁን አመልካች ነው፡፡ አማኞች የተማሩትን ትምህርት ወደ ገቢር ሲቀይሩ (በዕለት ሕይወታቸው ውስጥ እንዲታይ ሲያደርጉ) ምግባራዊ የሆነው ክርስቲያናዊ ሕይወት በሰዎች አኗኗር ውስጥ በገሓድ መታየት ይጀምራ፡፡ በዐጭሩ አንድ መልእክት ከአምላክ ወደ ሰው ሲተላለፍ፣ “ግልጠት እግዚአብሔር”፣ ከሰው ወደ ጽሑፍ ሲሻገር፣ “አፊዎተ እግዚአብሔር”፣ ከጽሑፍ (ከወረቀት) ወደ አንባቢ ልብ ሲዘልቅ፣ “አብርሆተ እግዚአብሔር”፣ ከልብ ወደ ኑሮ ሲሸጋገር ተግባራዊ የሆነ ክርስቲያናዊ ሕይወት እውን ይሆናል፡፡ የኅዳግ መዘክር ------------------ [1] ይህ የአብያተ ክርስቲያናት (ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስ፣ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት) መሠረተ እምነት ነው፡፡ [2] Natural or General Revelation [3] “አስተርእዮት” መገለጥ ማለት ነው፡፡ በግእዝ፣ “ርእይ” ወይም “ርእዮት” ማለት፣ “ማየት መመልከት፣ ማስተዋል፣ መመርመር” ማለት ነው፡፡ በዚህ አግባብ፣ “አስተርአየ” ተደራጊ (passive) ስለሚሆን አሳየ፣ ገለጠ፣ አበራ፣ አስተማረ ማለት ይሆናል (ኪ.ወ.ክ፤ “ታየ ማለት ስሕተት አሳየ ማለት እውነት” ገጽ 816-817)፡፡ ቃሉ ተደራጊ መሆኑ፣ ከነገረ መለኮቱ ጋር በጥሩ መንገድ ይገጥማል፡፡ እኛ አምላክን አልገለጥነውም፣ እርሱ ነው ራሱን የገለጠልን፡፡ ጸሎተ ሃይማኖት ላይ፣ “የሚታዩትንና የማይታዩትን” (ዘያስተርኢ፣ ወዘኢያስተርኢ) የሚለውን ሐረግ ያስታውሷል፡፡ [4] Special Revelation [5] Existance of God [6] በግሪክ፣ “ቴዎፋኒ” በመባል ይጠራል፡፡ “ቴዎስ” እና “ፋኔሮ” ከሚሉት ቃላት የተገኘ ነው፡፡ “ቴዎስ” (θεός) እግዚአብሔር፣ “ፋኔሮ” (φανερόω) መገለጥ ማለት ነው፡፡ [7] በእንግሊዝኛ ከቀረቡት ገለጻዎች በኋላ ያሉትን ምንባባት ይመለከቷል፡፡ [8] ἀποκάλυψις, εως (eōs), ἡ (hē): n.fem.; ≡ Str 602; TDNT 3.563—LN 28.38 revelation, what is revealed, a disclosure (Lk 2:32; Ro 16:25; 1Co 1:7; 14:6; 2Co 12:1; Gal 1:12; Eph 1:17; 2Th 1:7; 1Pe 1:7; Rev 1:1). [9] φανερόω: vb.; ≡ Str 5319; TDNT 9.3—1. LN 24.19 cause to be seen; (pass.) be disclosed, be displayed (Jn 21:1; Mk 16:12, 14 v.r.); 2. LN 28.36 make known, reveal, show (2Co 5:11). [10] James Swanson, Dictionary of Biblical Languages With Semantic Domains: Greek (New Testament), electronic ed. (Oak Harbor: Logos Research Systems, Inc., 1997). Johannes P. Louw and Eugene Albert Nida, vol. 1, Greek-English Lexicon of the New Testament: Based on Semantic Domains, electronic ed. of the 2nd edition., 278 (New York: United Bible Societies, 1996). [11] በፍልስፍናዊ ነገረ መለኮት ሦስት የዕውቀት ዐይነት አለ:— (1) ሥነ ዕውቀታዊ ዕውቀት (propositional knowledge or knowledge-that)፣ (2) ትውውቃዊ ዕውቀት (acquaintance knowledge)፣ እንዲሁም (3) ሙያዊ (ክሂሎታዊ) ዕውቀት (knowing-how) ናቸው፡፡ በክርስቲያናዊው ነገረ መለኮት፣ “እግዚአብሔርን ማወቅ” ስንል፣ የክርስትናን አስተምህሮ ማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን በግል ማወቅ ይጨምራል (በቊጥር 1 እና ቊጥር 2)፡፡ ስለዚህ በክርስትና አስተርዮተ አምላክ፣ ቊጥር አንድንና ቊጥር ሁለትን ጥያቄ በትክክል መላሽ ነው፡፡ [12] አፊው ወይም አፊዎት በልሳነ ግእዝ፣ “መተንፈስ፣ እፍ ማለት፣ መናገር” ማለት ነው (ኪ.ወ.ክ፤ ገጽ 235)፡፡ “አፊዎተ እግዚአብሔር” ማለት አምላክ እፍ ያለበት፣ አምላክ የተናገረው፣ አምላክ የተነፈሰበት ማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛ፣ “inspiration” የሚለውን የነገረ መለኮት ቃል በትክክል ይወክላል፡፡ [13] θεόπνευστος, ον (on): adj.; ≡ Str 2315; TDNT 6.453—LN 33.261 inspired of God, inspired (neb, reb), God-breathed (niv), (2Ti 3:16+). James Swanson, Dictionary of Biblical Languages With Semantic Domains: Greek (New Testament), electronic ed. (Oak Harbor: Logos Research Systems, Inc., 1997).
Show all...
7👍 3🥰 2
[14] አፊዎተ እግዚአብሔርን ከሚያስተምሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ተዘውትርው ከሚጠቀሱት መኻል ጥቂቶቹን እነሆ:— 2ጢሞ. 3÷16-17፤ ማቴ. 4÷4፤ ዮሐ. 17÷17፤ ሐሥ. 1÷16፤ 1ቆሮ. 2÷12-13፤ 1ተሰ. 2÷13፤ 2ጴጥ. 1÷20-21፤ 3÷15-16፤ 2ሳሙ. 23÷2፤ ኢዮ. 32÷8፤ ኤር. 1÷9፤ ማቴ. 10÷20፤ ሉቃ. 12÷12፤ ዮሐ. 14÷26፤ 16÷13፤ 1ዮሐ. 4÷1፤ ዘፀ. 20÷3-4፤ 24÷3-4፤ ኤር. 36÷2፤ ሕዝ. 1÷1-3፡፡ [15] አባ መልከ ጼዴቅ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት፤ (በርክሊ፤ ካሊፎርኒያ፤ 1992 ዓ.ም)፤ ገጽ 53-68፡፡ [16] φέρομαι, φέρω: vb.; ≡ Str 5342; TDNT 9.56—1. LN 15.11 (dep.) move (Ac 2:2); 2. LN 13.58 (dep.) progress (Heb 6:1); 3. LN 15.187 carry (Lk 23:26; Ac 4:34); 4. LN 15.166 bring, cause to move to a place (Mk 15:22); 5. LN 15.160 drive along, carry along (Ac 27:17); 6. LN 36.1 guide (Ac 15:29 v.r.); 7. LN 82.12 lead into (Ac 12:10); 8. LN 13.133 bring about, bring against (Jn 18:29); 9. LN 85.42 put, place an object (Jn 20:27); 10. LN 90.64 experience, undergo something burdensome (Heb 13:13); 11. LN 13.35 sustain, maintain (Heb 1:3); 12. LN 70.5 demonstrate reality of (Heb 9:16); 13. LN 31.55 accept, receive (Heb 12:20); 14. LN 25.176 endure, put up with (Ro 9:22); 15. LN 23.199 καρπὸν φέρω (karpon pherō), bear fruit (Jn 15:2, 4, 5, 8, 16; Mt 7:18 v.r. NA26). James Swanson, Dictionary of Biblical Languages With Semantic Domains: Greek (New Testament), electronic ed. (Oak Harbor: Logos Research Systems, Inc., 1997). [17] በየትኛው መጽሐፋቸው እንደ ሆነ ትዝ አይልኝም እንጂ፣ እንግሊዛዊው የነገረ መለኮት መምህር ጆን ስቶት (John Stott) እንዲህ የሚል ንግግር አላቸው፣ “መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ቃል ብቻ ነው ማለት ለዘብተኝነት (liberalism) ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ብቻ ነው ማለት አክራሪነት (ጽንፈኝነት) (radicalism) ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል በሰብአውያን ቋንቋ ተከትቦ የቀረበበት ክትበተ ቃል ነው ማለት ግን፣ ሚዛናዊ ክርስትና (balanced Christianity) ነው”፡፡ [18] የነገረ መለኮት ምሁራን፣ “በርግጥ አፊዎተ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው?” በሚለው ጒዳይ ላይ የተለያየ ዐሳብ አላቸው፡፡ ዋና ዋና ከሚባሉት ነባቤ ቃላት መኻል ጥቂቱን እነሆ:— (The Intuition Theory, The Illumination Theory, The Dynamic Theory, The Verbal Theory, The Dictation Theory)፡፡ ይህን ጒዳይ ማስተንተን የዚህ መጽሐፍ ዐላማ ስላልሆነ ዐልፈነዋል፡፡ በጒዳይ ላይ ጥናት ማድረግ የሚፈልጉ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ፣ የደርዛዌ ነገረ መለኮት መጻሕፍትን መመልከት ይችላሉ፡፡
Show all...
👍 27 14