cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ᴇʟ ᴏʟᴀᴍ...

The Everlasting God: El Olam (אֵ֥ל עוֹלָֽם) El Olam is the Hebrew name for God who has no beginning and no end. He is the Everlasting God or the Eternal God. #ማራናታ🙌

Show more
Advertising posts
5 988
Subscribers
+324 hours
-67 days
-6330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

12
ኢየሱስን ማን ገደለው?
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? (ሮሜ 8፥32)
ከበርካታ ዓመታት በፊት፣ በአሜርካ ግዛት ውስጥ ባለች ኢሊኖይስ በምትባል ከተማ መጋቢ ሆኖ ያገለግል የነበረ አንድ ጓደኛዬ፣ በሆሳእና በዓል ሳምንት፣ በመንግስት እስር ቤት ውስጥ ለታሰሩ እስረኞች ይሰብክ ነበር። በመልዕክቱም መሀል ቆም በማለት እስረኞቹን፣ ኢየሱስን የገደለው ማን እንደሆነ ያውቁ እንደሆነ ይጠይቃቸዋል። ታዲያ አንዳንዶቹ ወታደሮቹ ናቸው ሲሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አይሁዶች ናቸው አሉ። ሌሎቹም ጲላጦስ በማለት መለሱ። ከዚያም ጓደኛዬ ዝም እስኪሉ ጠበቀና “አባቱ ነው የገደለው” ብሎ መለሰላቸው።  የሮሜ 8፥32 የመጀመሪያ አጋማሽ የሚለው ይህንን ነው፦ እግዚአብሔር ለገዛ ልጁ አልራራለትም፤ ነገር ግን ለሞት አሳልፎ ሰጠው። “እግዚአብሔር በጥንት ውሳኔውና በቀደመው ዕውቀቱ ይህን ሰው [ኢየሱስን] አሳልፎ በእጃችሁ ሰጣችሁ” (ሐዋርያት ሥራ 2፥23)። ኢሳይያስ 53ም የበለጠ ግልጽ በሆነ መንገድ ያስቀምጠዋል፦ “እኛ ግን በእግዚአብሔርም እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። . . . መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር (የአባቱ) ፈቃድ ነበር” (ኢሳይያስ 53፥​4, 10)። ወይም ደግሞ ሮሜ 3፥25 እንደሚናገረው፣ “እግዚአብሔር የማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ [እርሱን] አቅርቦታል።” ልክ አብርሃም በልጁ በይስሐቅ አንገት ላይ ቢላውን እንዳነሣ፣ ነገር ግን በዱር ውስጥ በግ ስለ ነበረ ልጁን እንዳተረፈው ሁሉ፣ እግዚአብሔር አብም በልጁ በኢየሱስ አንገት ላይ ቢላዋውን አነሣ — ነገር ግን አልራራለትም፤ ምክንያቱም ያ በግ እርሱ ነበር፤ እርሱ ምትካችን ነበር። እግዚአብሔር ለገዛ ልጁ አልራራለትም፤ ምክንያቱም ጻድቅ እና ቅዱስ አምላክ መሆኑ ሳይነካ፣ ለእኛ ርህራሄን ሊያሳየን የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ይህ ነበር። የመተላለፋችን ጥፋት፣ ለበደላችን የሚገባን ቅጣት እና የኃጢአታችን እርግማን ወደማናመልጥበት የገሃነም ጥፋት ይከተን ነበር። እግዚአብሔር ግን ለገዛ ልጁ አልራራለትም፤ ስለ መተላለፋችን እንዲወጋ፣ ስለ በደላችንም እንዲደቅቅ፣ ስለ ኃጢአታችንም እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።  ይህ ክፍል — ሮሜ 8፥32 — እጅግ አብልጬ የምወደው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ሁሉን አቀፍ ለሆነው የእግዚአብሔር የወደፊት የጸጋ ተስፋ መሠረት የሚሆን ክፍል ነው። ታላቅና ቅዱስ በሆነ አምላክ ፊት ይቅር ተብዬ፣ ከእርሱም ጋር ታርቄ፣ ጸድቄ፣ ተቀባይነት አግኝቼ፣ በቀኙም ከዘላለም እስከ ዘላለም የማይነገሩት የተድላ ተስፋዎች ተካፋይ ሆኜ እቆም ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ቅጣቴን፣ በደሌን፣ ኩነኔዬን፣ መተላለፌን ሁሉ በስጋው ተሸከመ። ክብር ለዘለዓለም ለስሙ ይሁን! @Elolam_the_Everlasting_God
Show all...
9🙏 2👍 1
3
#Identification /#መታወቂያችን የሕማማት ሰሞን ማስታወሻ ደጉ ጌታ ሰው ሆኖ ሲመላለስ የእግዚአብሔር ልጅ መኾኑ፣ ለዘመናት ይጠበቅ የነበረው መሢሕ መኾኑ፣ አማኑኤል (የእግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል መገኛ ምክንያት) መኾኑ ... እንደምን ታወቀ? ኢሳይያስ ይህን ስቅዩ ሎሌ 'እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም' ማለቱንስ (አሁንም) ያስተዋለ አለን? የእግዚአብሔር መሆኑ ወይም ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን መለያው ታዲያ ምንድነው? እግዚአብሔር የታወቀው በመስዋትነት ፍቅሩ ነው። ይህ ዓለም ያውቀው ዘንድ የወደደው በፍቅሩ ነው። 'እግዚአብሔር ፍቅር ነው።' ያለው ሐዋርያ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ/እንድንታወቅ አባት እግዚአብሔር 'አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር' ምንኛ ታላቅ ነው! ይለናል [1 ዮሐ. 3፥ 1]። በዚህ በወደቀው ዓለም፣ በዚህ እርሱን በማታውቀው ዓለም፣ በዚህ ጠላትነትና እርስ በእርስ መፈራራት በሰፈነበት ዓለም፣ በዚህ ኃያላን ነን ባዮች በጡቻቸው ለመታወቅ በሚንደፋደፉበት ዓለም፣ በዚህ ጦርና የጦር ወሬ ዜና ሆኖ በገነነበት ዓለም፣ በዚህ ለድሆችና ለምስኪኖች ሥፍራ በሚነፍግ ዓለም፣ ... ወዘተ የታራቂውና የሰላሙ ንጉስ፣ የድሃ አደጉ አባትና የመበለቲቱ ዳኛ የሆነው አምላክ - ልጆቹ ተብለን እንድንጠራ መታወቂያችን የእርሱ ፍቅር ይሆነን ዘንድ አፈሰሰልን። ሽንቁር የመላው ሕይወታችን፣ ለመብታችን ስንሯሯጥ የተሰበረው መያዣችን አስቸገረን እንጂ እርሱማ 'ፍቅሩን' አትረፍርፎ አፈሰሰልን። የምንታወቅበት የእግዚአብሔር ፍቅር አብዮተኛ ነው። ለምስኪኖች ይወግናል፣ የድምፅ አልባዎች ምትክ ያረጋል። የታመሙትንና ያልጋ ቁራኞችን ምንጣፍ አራግፎ ያነጥፋል፣ የተራቡትን ከአፉ ነጥቆ ያጎርሳል፣ ከራሱ ቁስል ይልቅ የሌላውን ያክም ዘንድ የቀረችውን ትንሽዬ ዘይት በባልንጀራው ቁስል ላይ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ፍቅር ሙሉ መልክ ኢየሱስ ነው። የመስቀል አርበኛ። የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ፈሰሰ ሲለን - 'ውይ እግዜር እንዴት ይወደኛል' እያልን የኮንፍረንስ መዓት፣ የፍቅር ዜማ መዓት ... ወዘተ እንዲኖረን አይመስለኝም። እርሱ ኢየሱስ እንደተመላለሰ እንድንመላለስ ነው እንጂ። የእግዚአብሔር ፍቅር የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ። ዕለተ - ሐሙስ የፍቅር አብዮት ተገለጠ። ጌታ የባርያውን እግር አጠበ! ተገኝ ሙሉጌታ
Show all...
9👍 2
15
ልብ ብቻውን ሲቀር በሃሳብ ሲወረር በሁነኛ ነፋስ በማዕበል ሲሰወር ደጋፊ ከሌለው ማን ከማን ያስጥላል ልብ የወደቀ ቀን ለሞት እጅ ያሰጣል ልቤን የሚታደግ ብርቱ ግንብ አለቴ አጥር ሃይሌ ስምህ ነው የተስፋ ጽናቴ አንተ ነህ እግዚአብሔር ጽኑ መታመኛ አደራ የምለው አንተን ነው የልቤን መገኛ ሀና ተክሌ
Show all...
18😭 8
😭 14 11
13🥰 3