cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሆሄያት ህብር📝📝

ውድ የሆሄያት ህብር ቻናል ቤተሰቦች ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።👍👍 ቻናላችን፦ 👉በግጥም 📔📰📼📼 👉በድርሰት📚📚 👉በትረካ📀🎼 👉በስዕል🃏🃏 👉ወጎች📜📜 👉በአጫጭር ልብ ወለዶች ወደ እናንተ እንደርሳለን። ለሀሳብ እና አስተያየት ፦ሊዮ ማክ፦ @Leoyri ፦ዮሲ ማን፦ @yosikeman ፦የሪ፦ @yerijo ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል 👉 @gGetem

Show more
Advertising posts
507
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

❤️❤️😷የታፈነ ፍቅር😷❤️❤️ ክፍል 2 ደራሲ :ዮሲ ማን&ሊዮ ማክ ግን አንድ ቀን ጎደኞቹ በቁም ነገር ይዘው እቺ ብዙ ያለላትን ምዕናባዊ ሴት ከሀሳቡ ጋር እንዲያስተዋዉቃቸው ቀጠሮ ይዘው አገኙት ።ጆርጅም ለተወሰነ ደቂቃዎች በእሩቅ አድማስ ከሚታየው የሀሳብ ባህር ሰጠመ። እነርሱም ከእነሱ በብዙ የሀሳብ እርቀት ጥሎአቸው እንደ ነጎደ ባስተዋሉ ጊዜ የማወቅ ጉጉታቸው በእጥፍ ጨመረ። ከአበራ የተደጋጋሚ ጥሪ በኃላ ጆርጅም ጥሎአቸው ከሰጠመበት የሀሳብ ባህር በሰመመን ባኖ አለው አለ። እናም መናገሩን ቀጠለ፡ ፀጉሯ እረጅም ፣መልኳም የቀይ ዳማ(ጠየም ያለች)፣ቁመቷም መካከለኛ፣እና ፍፁም ኢትዮጵያዊ ማንነትን የተላበሰች በአለባበሷም ቢሆን ሰውነትን አጋልጦ ለሰዉ እይታ ሊሰጥ የማይችል ልብስ የምታዘወትር ብትሆን ብሎ ገና ሳይጨርስ ሀብትሽ በሳቅ ተከተለው። ጆርጅም የእኔ ብሎ ደብቆ ያስቀመጣትን ሴት ከምዕናብ የስዕል ብሩሹ ቀለሙ ሳይለቅ በሀብትሽ ሳቅ ተናዶ ፡ ምን ያስቅሀል አለው? እርሷ ናታ አሁን ያልካት ሴት እኮ ከዳይኖሰር ጋር መጥፋቷን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማውጣቱን ዘነጋኸው እንዴ? ጆርጅም በሀብታሙ የፌዝ የመልስ ምት ተበሳጭቶ ከተቀመጠበት ወንበር በንዴት ተበሳጭቶ ወጣ። ግን ከእነርሱ ቢለይም እንኳን ለዘመናት ከሰው ሁሉ ደብቆ ያስቀመጣትን ሴት በመናገሩ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማው እና እራሱን በመውቀስ ላይ ሳለ አንድ ቀልቡን የሳበውን ንግግር በድንገት ወደ ጆሮው ዘለቀ። እንደ ዋዛ ግን ማለፍ አልቻለም። ከወዴት እንደሆነ ድመፁን ለማረጋገጥ ዞር አለ.... ክፍል 3 በቅርብ ቀን ይጠብቁን። share&join አርጉልን ለሀሳብ እና ለ አስተያየት #link በዚህ ላኩልን 👇👇👇👇👇👇👇👇 ዮሲ ማን 👉@ yosikeman ሊዮ ማክ 👉 @Leoyri የግጥም ለዛ @gGetem @gGetem
Show all...
❤️❤😷የታፈነ ፍቅር😷❤️❤️ ደራሲ፡ዮሲ ማን&ሊዮ ማክ ጊዜዉ 2000 ዓ/ም ነበር።ወራቱ ደግሞ ጥር ሲሆን ሰረግ የሚበዛበት ወቅት ነው ጆርጅም የብቸኝነት ሀያል አቅም የተገነዘበበት ወቅት ነበረ። ሶስት ጓደኞች ነበሩት። ከነዛም መሃል በነሱ ኣጠራር ሀብትሽ የሚሉት ግን የስም ሀብታም የሆነ የሚኖረው ኑሮ ከእጅ ወደ ኣፍ የሆነ ለስሙ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ጓደኛቸዉ ነው እና ሀብትሽ ከሌለ ሰዓታቸዉ እና ጊዜያቸው ያለ እርሱ የማይደምቅ ነው። ሌላው ጓደኛቸው ደግሞ አበራ እጅግ የተለየ ቁም ነገረኛ እና በእድሜው በሰል ያለ ሲሆን ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በጭንቅላቱ ላይ እና ሁሌ ከአገጩ ስር የማይጠፋው እጁን ከእርሷ ላይ ለደቂቃ እንኳን የማያነሳባት ፂሙ ላይ አለፍ አለፍ ብሎ ወደ እርጅና የእድሜ እርከን። መግባቱን ማሳያ የሆኑ ነጫጭ ሽበቶች በኑግ መሀል ተደባልቆ እንደበቀሉ ሱፎች ከእርቀት ይታያሉ። ሌላኛው እና የመጨረሻው በእነርሱ ዘንድም እንኳ እንብዛም ቦታ የማይሰጡት ሰለሞን እጅግ ሩህሩህ ከእራሱ በላይ ለሰው የሚኖር ሰዉ ሲሆን በጣም ምስኪን ደሀ እናቱን ያለ እረዳት የሚጦር መልካም ሰው ነው።እናም ከጆርጅ በስተቀር ውሀ አቅጣጫቸውን በማግኘት የትዳር ረጅም እና ጣፋጭ መንገድ ጀምረዋል። ለዚህም ይመስላል የጆርጅ ከወትሮ በተለየ ለትዳር ያለው ጉጉት እና ተነሳሽነት የጨመረው። ጊዜው ይብዛም ይነስ እንጂ ዕለት ከዕለት የጓደኞቹ ጉትጎታ ና ንዝነዛ ከእነርሱ እርቆ አያዉቅም ነበር።ከዚህም የተነሳ እርሱ የሚያገባት አይነት ሴት ፈልጎ እንደ አጣ ከማስረዳት ቦዝኖ አያውቅም። ግን አንድ ቀን........ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል ✍✍✍✍ዮሲ ማን👉 @yosika Leo Mak👉@Leoyri @gGetem @gGetem ተፃፈ 6/5/2012 ዓ/ም
Show all...
🍭የበአል ሳምንትና እሱ🤦‍♂🙎‍♂ Makhi ክፍል 2😉
Show all...
🍭የበአል ሳምንትና እሱ🤦‍♂🙍‍♂ ✍Makhi😉 ክፍል - 1
Show all...
ጥቁር ደም ክፍል 1 ደራሲ አንዳርጌ መስፍን ተራኪ እኔ ማን ነኝ @Ggetem
Show all...
🤔🤔🤔 አንድ ቀን......🤔🤔🤔 #ፀሐፊያን_ዮሲ_ማን_እና_ሊዮ_ማክ #አንባቢ_ማሂ 🎤🎤🎤🎤🎧 የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋🦋 @gGetem @gGetem
Show all...