የሆሄያት ህብር📝📝
Open in Telegram
ውድ የሆሄያት ህብር ቻናል ቤተሰቦች ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።👍👍 ቻናላችን፦ 👉በግጥም 📔📰📼📼 👉በድርሰት📚📚 👉በትረካ📀🎼 👉በስዕል🃏🃏 👉ወጎች📜📜 👉በአጫጭር ልብ ወለዶች ወደ እናንተ እንደርሳለን። ለሀሳብ እና አስተያየት ፦ሊዮ ማክ፦ @Leoyri ፦ዮሲ ማን፦ @yosikeman ፦የሪ፦ @yerijo ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል 👉 @gGetem
Show more855
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-130 days
Posts Archive
855
855
855
መስቃ
(በእውቀቱ ስዩም)
ተፈጥረን በጎግ ማጎግ ምድር
በሰላም ተኝተን አናድር፤
ሀውልታችችን የቃየን ድንጋይ
ስማችን ሽብሩ፤ ኢጄታ ፣ ገላጋይ
ነፍስ ሳናውቅ፤ ከነፍሰ ገዳይ ተዋውቀን
ከመርባታችን ተላልቀን
በጥይት ተገበያይተን
በፈንጅ ወረዳ፤ ሰኞ ማክሰኞ ተጫውተን፤
ጎልማሳው ከሚስቱ ፅዋ ፣ ተጎንጭቶ ሳይረካ
ከጫጉላ ወደ ጫካ
የወጣቱ፤ ለጋ ጣቱ፤ ከቃታ ጋር ተጣብቆ
የብር ቀለበት የት አውቆ፤
የጅራፋችን ድምጽ፤ በጥይት ድምጽ ተለውጦ
ሞፈራችን ተፈልጦ
ካረስነው ትልም በላይ፤ የቆፈርነው ምሽግ በልጦ
በሙሉ ልብ ለመሞት ፤ በግማሽ ልብ አኖራለን ፤
ደረት መትተን ጥለን፣ ገድለን፤ ደረት ደቅተን እንቀብራለን፤
ጎረቤቶቻችን ሁሉ፤ ያምባ ጉዋሮ ቤት ሆነው
መኖራችንን ተቀናቅነው፤
ቤት ለእምቦሳ ብንላቸው፤ ወይፈን ሆነው እያደሩ
ወደ ስስ ብልታችን ፣ ቀንዳቸውን እየወደሩ፤
እሳት አንጫጫር ብለው ገልና ፍም ተውሰው
በየለቱ ሲጋብዙን፤ እሳተ ጎመራ ጠንስሰው፤
የመላእክት ጭምብል ለብሰው
እንኩዋን ከሰው
ካውሬ ብሰው፤
@gGetem
@gGetem
@gGetem
855
#ይከብደኛል
:
:
እውነት ለመናገር ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል፤
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶም ይመስለኛል።
:
:
ለምን ይመስልሻል ውሸታም እንዳይለኝ፤
ፈራ ተባ ምለው ልቤ እንዳይኮንነኝ?
:
:
ይሄኔ እኮ አንቺ አሉታ አስበሻል፤
ምንም ትዝ ያላልሺኝ እንደዚያ መስሎሻል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ...
እረስቼሽ ብቻ የመሰለሽ እንደው፤
እንዲያ በማሰብሽ በጣም ነው ምነደው።
:
:
ምክንያቱ ደግሞ...
እንኳን ተራርቀን እንኳን ሳንተያይ፤
ቀኑን አብረን ውለን ማታ ስንለያይ፤
አንድ ሁለት እርምጃ እንደመሰንዘሬ፤
ባሳብ እነጉዳለው እያሰላሰልኩኝ ውሎዋችንን ዞሬ።
ያላየውሽ ቀንም ያነጫንጨኛል፤
ሰዎች ሰላም ሲሉኝ አሽሙር ይመስለኛል።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ንፋስ ለምናለው ማደርገው ሲጠፋኝ ልክ አማራጭ ሳጣ፤
የጥሪኝን ዝባድ ሚያስንቅ ጠረንሽን ካለሁበት ድረስ ይዞት እንዲመጣ።
:
:
ይህ እንዳለ ሆኖም ...
እውነት ለመናገር ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል፤
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶም
ይመስለኛል።
:
:
ለምን ይመስልሻል ውሸታም እንዳይለኝ፤
ፈራ ተባ ምለው ልቤ እንዳይኮንነኝ?
:
:
ይሄኔ እኮ አንቺ አሉታ አስበሻል፤
ምንም ትዝ ያላልሺኝ እንደዚያ መስሎሻል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ...
እረስቼሽ ብቻ የመሰለሽ እንደው፤
እንዲያ በማሰብሽ በጣም ነው ምነደው።
:
:
ምከንያቱ ደግሞ...
ገና ከጅምሩ ስላንቺ ማንነት ውጥኑን ሳሊዘው ምኑንም ሳልቃኘሁ፤
አይተሽ የለም እንዴ ካንጀት ስትስቂ ግራ ጎን አጥንቴን እንዳልኩኝ አገኘሁ።
መቼስ ታውቂዋለሽ ለማብሰል ስታገል ወጥን በስልቻ፤
ያለምንም ስስት አንቺ እንደሰጠሺኝ ድስትና ጉልቻ።
ይሄም አይጠፋሽም ልክ ዐይንሽን ሳየው የልቤ ትርታ፤
በፊት ከነበረው ፈጥኖ እንደሚመታ።
:
:
እርግጥ ነው ታውቂያለሽ እኔም ብሆን አውቃለው፤
ይህ በንዲ እንዳለ አንቺን ናፍቀሺኛል ማለት እፈራለው።
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶ ይመስለኛል፤
ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል።
:
:
ቢልም እውነቱን ነው ...
እርግጥም ውሸት ነው ...
:
:
እንደው እንደዘበት ናፍቀሺኛል ፍቅሬ ብሎ ለመናገር አንቺን የከበደኝ፤
ስጋት ያደረብኝ የራሴው ልብ ዞሮ እራሴን መልሶ እንዳያዋርደኝ፤
ለዚህ ነው ንግስቴ ለዚህ ነው እንቁዬ፤
በልቤ ተክዬሽ እንዲያው ስለማድር ከመናፈቅ በላይ ስናፍቅሽ ውዬ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
855
እናት
እማ
ከመውደዶች ህንፃ ከፍቅሮች ከተማ
የተገነባሽው የማትፈርሽ ሀገር
የማትበታተኝ እፁብ ድንቅ ነገር
የቴውድሮስ ውጥን አስቀድሞ የገባሽ
አንቺ አንድ ሆነሽ ብዙውን ያግባባሽ
.
በአለም ኑሪ ከፍ ብለሽ እንደ ማማ…
የሰላም የተስፋ የርህራሄ አርማ
በውስጥሽ ለሚኖር የአናብስት ግርማ
ምድርን አንቀጥቅጦ ሰማትን ፈልጦ
ለሚገዛ ንጉስ ድንበርን አቋርጦ
ዙፋን እና መንበር ቀድመሽ የምትሆኚ
ለልጅሽ ፍስሀን ደስታን ምትመኚ
.
እናት
በአለም ኑሪ ከፍ ብለሽ እንደ ማማ
ዘእንበለ ድካም ወፃማ
ካንቺ ልግባባ እንጂ ካለም አልስማማ
አንቺን ከሚወስዱ ህይወቴን ልቀማ
እንዳሻቸው ሁሉ ከቤቴ ያስወጡኝ
ያለኝን ሀብት ንብረት ሁሉንም ይንጠቁኝ ሁሉንም ያሳጡኝ
ካንቺ አይነጥሉኝ በዚህ ሁሉ ግና
እንዳቺ የሚሆን ከቶ የለምና፡፡
05/09/2007 ዓ.ም
😉 @gGetem
👕👉 @gGetem
👖
855
Repost from የሆሄያት ህብር📝📝
ልጠይቅህ መልስልኝ
ልጠይቅህ መልስልኝ
ልብን ከፍተህ መልስልኝ
ለይቅርታ ተንበርክኬ ስለምንህ
እያነባው ስማፀንህ
በቸልታ የገፋከኝ
አሁን ስሞት ይቅርታህን የምትሰጠኝ
ላልመለስ መሄዴን ረስተሀው ነው?
ፍቅርን በተራብኩኝ
መወደድን በፈለኩኝ
አንዲትን ቃል የነፈግከኝ
አሁን ስሞት የምትነግረኝ
ፈገግ እንድል ደስ አንዲለኝ?
በቁም ሳለሁ ረስተኀኛል
መች አንደሰው ቆጥረኀኛል
አሁን አሁን እኔ ልቅደም የምትለኝ
ባስቀድምህ ከፊት ትሆን ነበር?
የእውነት የእወነት ትወደኝስ ነበር
አሁን ያልከኝ እቺ አጭር ቃል
ሳትዋሸኝ በቁም ሳለሁ ከአንደበት ይወጣል?
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@gGetem
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
4 any comment
@leoyri
በገጣሚ ጆሲ: @Joyefull
❥❥__⚘_❥❥
855
ናፍቀሽኛል በብዙ
ናፍቀሽኛል ሳላይሽ
ጠረንሽን ሳልስበው
ከንፈርሽን ሳልስመው
ገላሽን ሳልሞቀው
እቅፍሽን ስላለው
አካልሽን ሳልነካው
ናፍቀሽኛል በብዙ
እንዲ ከቀጠለ
ብዙ ነው መዘዙ
ናፍቀሽኛል በባዶ
አቅሜን እስከማጣ
ሆነብኝ በረዶ
አትናፍቂኝ በጭራሽ
ወይ እኔ ካልመጣሁ
ወይ አንቺ ካልመጣሽ
ሀገር ላገር ሆነን በሩቅ ተነፋፍቀን
ምኑንም ላናተርፍ ምንም ሳኒ'ዘው
ደርሶ ባዶ ሜዳ ዝም ብሎ መንከርፈፍ
በመፋቀር ሰበብ በዜሮ መንሳፈፍ
ፍሬ ካላፈራ ጥንስሱ ካልጣመ
የምን ሸጋ ለሊት ? ከንቱ ህልም አለመ!
ተይ እንቀጣጠር
ተይዞ ግን እንገናኝ
መርሳት በርሽ ሳይቆም መረሳት ሳይወርሰኝ
ተይ ግን ቶሎ ልምጣ
ተይ ግን በቶሎ ነይ
በመጠበቅ መሀል ምን ይታወቅና
ቀድሞ የሚሄደው ተነጥቆ ከሰማይ
@gGetem
855
#ይከብደኛል
:
:
እውነት ለመናገር ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል፤
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶም ይመስለኛል።
:
:
ለምን ይመስልሻል ውሸታም እንዳይለኝ፤
ፈራ ተባ ምለው ልቤ እንዳይኮንነኝ?
:
:
ይሄኔ እኮ አንቺ አሉታ አስበሻል፤
ምንም ትዝ ያላልሺኝ እንደዚያ መስሎሻል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ...
እረስቼሽ ብቻ የመሰለሽ እንደው፤
እንዲያ በማሰብሽ በጣም ነው ምነደው።
:
:
ምክንያቱ ደግሞ...
እንኳን ተራርቀን እንኳን ሳንተያይ፤
ቀኑን አብረን ውለን ማታ ስንለያይ፤
አንድ ሁለት እርምጃ እንደመሰንዘሬ፤
ባሳብ እነጉዳለው እያሰላሰልኩኝ ውሎዋችንን ዞሬ።
ያላየውሽ ቀንም ያነጫንጨኛል፤
ሰዎች ሰላም ሲሉኝ አሽሙር ይመስለኛል።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ንፋስ ለምናለው ማደርገው ሲጠፋኝ ልክ አማራጭ ሳጣ፤
የጥሪኝን ዝባድ ሚያስንቅ ጠረንሽን ካለሁበት ድረስ ይዞት እንዲመጣ።
:
:
ይህ እንዳለ ሆኖም ...
እውነት ለመናገር ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል፤
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶም
ይመስለኛል።
:
:
ለምን ይመስልሻል ውሸታም እንዳይለኝ፤
ፈራ ተባ ምለው ልቤ እንዳይኮንነኝ?
:
:
ይሄኔ እኮ አንቺ አሉታ አስበሻል፤
ምንም ትዝ ያላልሺኝ እንደዚያ መስሎሻል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ...
እረስቼሽ ብቻ የመሰለሽ እንደው፤
እንዲያ በማሰብሽ በጣም ነው ምነደው።
:
:
ምከንያቱ ደግሞ...
ገና ከጅምሩ ስላንቺ ማንነት ውጥኑን ሳሊዘው ምኑንም ሳልቃኘሁ፤
አይተሽ የለም እንዴ ካንጀት ስትስቂ ግራ ጎን አጥንቴን እንዳልኩኝ አገኘሁ።
መቼስ ታውቂዋለሽ ለማብሰል ስታገል ወጥን በስልቻ፤
ያለምንም ስስት አንቺ እንደሰጠሺኝ ድስትና ጉልቻ።
ይሄም አይጠፋሽም ልክ ዐይንሽን ሳየው የልቤ ትርታ፤
በፊት ከነበረው ፈጥኖ እንደሚመታ።
:
:
እርግጥ ነው ታውቂያለሽ እኔም ብሆን አውቃለው፤
ይህ በንዲ እንዳለ አንቺን ናፍቀሺኛል ማለት እፈራለው።
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶ ይመስለኛል፤
ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል።
:
:
ቢልም እውነቱን ነው ...
እርግጥም ውሸት ነው ...
:
:
እንደው እንደዘበት ናፍቀሺኛል ፍቅሬ ብሎ ለመናገር አንቺን የከበደኝ፤
ስጋት ያደረብኝ የራሴው ልብ ዞሮ እራሴን መልሶ እንዳያዋርደኝ፤
ለዚህ ነው ንግስቴ ለዚህ ነው እንቁዬ፤
በልቤ ተክዬሽ እንዲያው ስለማድር ከመናፈቅ በላይ ስናፍቅሽ ውዬ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
855
የግራ ጎን አጥንት
"""""""""""""""""""""
ከቀደምት ፍጥረቱ፥
ከአደም ከጥንቱ፥
ከአዳም ከብርቱ!
ከአንድ እርምጃ ኃላ ፥ተከተለች ሃዋ፤
የአደምን ብርታት ፥እርጋ መመኪያዋ!
ከአንድ እርምጃ ኃላ ፥ሄዋን ተከተለች፤
ከአዳም ከግራ አጥንት
ፍልቀቷን አድርጋ፥ ከጀርባው ዋለለች!
እና በዚህ አለም፥ በፍጥረታት ሚስጥር፤
ሃዋ ከአደም ፊት
ሄዋን ከአዳም ፊት ፥ቀድማው ብትፈጠር!
ከእልፍ አመት በኃላ ፥ነገር ይጣረሳል፤
የፈጣሪ ስራ
የእሽክርክሮሽ ሂደት፥ ከህይወት ይፋረሳል፥
የአንዱ የጎን አጥንት
የሌላውን ሃዋ
የሌላውን ሄዋን፥ የሱ አድርጎ ያፍሳል!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
855
855
መልካም አዲስ መርዶ¡¡
(አሌክስ አብርሃም)
ደግሞ ጠፋ ሌላ ኩራዝ፣አንድ ኮከብ ረገፈ
ሰማያችን ከትከሻው፣ አንዳች ፀዳል ተገፈፈ!
እንዴት ሞተ ምን አገኘው
በየት አልፎ ጣር ጎበኘው?
ቢባልም ወግ ለማሳመር
ሞት እንደሁ አይመረመር!
በዕድሜ ሲነጥፍ ላምባው
ወይ ከለላ ግርዶሽ አጥቶ
ውሽንፍር ነፋስ ሲገባው
ምናልባትም ትንፋሻችን
ካውሎ ነፋስ ክንድ የከፋው
እሱ ይሆናል ያጠፋው!
ብቻ አንድ ሰው ሞቶልናል፣ ስምና ፊቱን ትቶልን
እናወራ እንፀፈው፣ለቸገረን ቀን ወጣልን!
በቁማችን ለጠነዛን ፣የሐሳብ ጠኔ ለመታን
እንኳን ደስ አለን ሙታን!
ተሰርዟል ከሰልፋችን ፣ተቀንሷል አንዱ ጉምቱ
«ረዢም ነበር አንገቱ
ልብስ ከልሎት ክንፉን
ከኛጋር ሲራመድ ኑሮ
ይሄው አረፈ ዘንድሮ»
እንበል ሕምህምታው ይናኝ
ስም አደባባይ እንገናኝ!
ፎቶውን አውጡ እንለጥፍ
እናጋን፤ ስሙን እናግዝፍ
ዝግባው ፣ወይራው ፣ አድባር ዛፉ
ተራራው እንበል አጥናፉ!
አብረን በላን አብረን ጠጣን
በምናብ ጨረቃ ወጣን...
ምንም እንበል ምንም ከቶ
"ውሸት ነው" አይል ተነስቶ
ምስጋና ይግባው ለፎቶ!
ከጎኑ አቁሞ ላስቀረን
ለ "አውቀው ነበር" መስተካከል
ማስረጃ ሰንደቅ ቅርሳችን
ብልጭታው ዘላለማችን¡
አዘናግቶን ከነክብሩ፣ ሳይታሰብ ተከተተ
"በደንብ ሳናዋርደው" በቁሙ ሳንገድለው ሞተ¡
ዝም እንዳለ በመንበሩ
ተዘግቷል የቀብር በሩ
ተፈፅሟል ምዕራፉ
ተሰብሯል የመኖር ክንፉ!
አንጠፍጥፎ ጨልጧታል የሞላንለትን ፅዋ
ወይን ፍሬ ነበርን እንበል፣ምድረ ጎምዛዛ ግራዋ!
ልብ ካለን ለፀፀት ፣ልባችን አፉን እንዳይከፍት
ደረታችንን እንደልቅ ፣ከከርሰ ህሊናችን ውስጥ
አስመሳይ ኩሸት አናፍልቅ!
"የት ነበሩ እስከዛሬ?"
እንዳይል ጓደኛ ዘመድ
የነበር ገመድ እንግመድ
በሙት ላይ ችሎት አቁመን
በጅናዛው ላይ እንፍረድ!
ቀኝ እጁ ነበርን እንበል
ዝና ነው የሕይዎት አበል¡
እንደወርቅ ጥርስ ነቅለን
ስሙን ካስከሬኑ ላይ
ለአፍታ ደምቀን እንታይ!
ቤተኞች ነበርን ያላችሁ
ቤቱን ስትጠይቁ
ግዴለም አትሳቀቁ¡
ሳይከስም ወሬው ሳይጠፋ፣ ሳይወጣባችሁ ሰልስቱ
ወፍ ሳትቀድማችሁ ለመርዶው ፣ በጨረባ ተራኮቱ!
ዳዋ ሳይወርሰው መቃብሩን
የመዋጮ ሀውልት ሳይፈርስ
ለወሬ አሁን ነው መድረስ፤
አሁን ነው ያዞ እንባ ማፍሰስ!
አውጁ ሞቱን አውጁ!
ዝግባው ቢወድቅም ቅሉ
ከጠራራው መንፈሳችሁ
በስም ታዛው ተጠለሉ።
Alex Abreham
@gGetem
@sirak6
@gGetem
855
ፀደይን በመስኮት
.
( በእውቀቱ ስዩም)
.
.
ክረምቱ ሲወጣ
ርጥብ ዳሱን ነቅሎ
አዳሜ
ከተሜ
ጃንጣላውን ሰቅሎ
ካቦርታውን ጥሎ
አዳም ከሄዋኑ
(ድስት ከነክዳኑ)
ላጤውም ለብቻው
ወንዱ ደረት ሊያሳይ
በባህር ዳርቻው
ሴቱም እንደልቡ፤ ቂጡን እየጣለ
በሙቅ አሸዋ ላይ
እየተንጋለለ
ቅብጠት ድርያ፤ ሲያምረው፤
ማጭድ ታጥቆ ገባ
ሁሉን የማይምረው፤
ፊት ያለውን ሁሉ
በብረት መዳፉ፤ የሚያጠናግረው ፤
እምቢልታ ተነፋ
ደወል ተደወለ
ያልታደለው ጠፋ
ቀሪው እቤት ዋለ
ሰው ቤቱ መሸገ
መስኮት እንደጋሻ፤ አየወለወለ፤
በየአደባባዩ
እዩኝ እዩኝ ባዩ
እንዳልተጀነነ
ሰው ለመኖር ብሎ፤ ከኑሮ መነነ!
እኔም እንዳገሬው፤ ለነፍሴ ብሳሳ
ለብሻት ሰነበትኩ፤ ቤቴን እንደገሳ፤
አምና እንዳልነበርኩኝ
የተፈጥሮ ሚዜ፤ የፀጋው ተካፋይ
የእልፍኝ እስረኛ ነኝ ፤ አጮልቄ የማይ
ያውና እዚያ ማዶ፤ጥርት ያለ ሰማይ
ያቻት እዚያ ማዶ፤ ያልተሞቀች ፀሀይ!
በየልምላሜው
በየዛፍ ቅጠሉ
ንቡ ወፉ ትሉ
ሲቦርቅ ሲራኮት!
እኔ ግን ሸኘሁት! ፀደይን በመስኮት
855
(በላይ በቀለ ወያ)
በሰው አእምሮ ልክ
በሰው እውቀት መጠን፤ ያለሁ ተወስኜ
የአሁንን ብቻ ነው...
ልነግርሽ ምችለው ፤ እርግጠኛ ሆኜ
በኋላ ምን ቢሆን ፤ ነገ ምን ቢፈጠር
መገመት ነው እንጂ ፣
ተስፋ መድረግ እንጂ ፣
እርግጠኛ ሆኜ አልችልም በናገር፡፡
እናም አሁን ላይ ነው !
ከራስ አስበልጦ ፣
የኔ አንቺን መውደድ ፣ የኔ አንቺን ማፍቀር፡፡
።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በኋላ ብርቅሽ ፣
ነገ ላይ ብጠላሽ ፣
‹‹አይወደኝም ነበር›› ዋሽቷል እንዳትይኝ
የአሁን እውነቴን ፤ ዘላለም እመኚኝ፡፡
ምክንያቱም የኔ ውድ
በኋላን ያለፈ ፤ ነገን የሚሻገር
አሁን ነው ሰው መጥላት፤ አሁን ነው ሰው ማፍቀር
ቅፅበት ነው መለየት ፤ ቅፅበት ነው መጣመር፡፡
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
እናም አሁኔ ላይ…..
ከራሴ አስበልጬ ፣ አንቺን ያፈቀርኩሽ
እናም አሁኔ ላይ…..
የዘልዓለሜ ነሽ ፣ ብዬ እንደነገርኩሽ
ቀናቶች ወራቶች ፥ አመታቶች ሁሉ
እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ
የእድሜ ዘመናቶች ፣ አሁኔ ላይ አሉ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በኋላ ብርቅሽ
ነገ ላይ ብጠላሽ
"አይወደኝም ነበር " ፣ዋሽቷል እንዳትይኝ
የአሁን እውነቴን ፤ ዘላለም እመኚኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
@gGetem
@gGetem
@gGetem
855
Jose & Leo mak
የሆሄያት ህብር🦋🦋
Leo @Leoyri 🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂
JOSI @yosikeman 🕺🕺🕺🕺🕺
@gGetem
@gGetem
🎬🎤🎹🎼🎧🎤🎤🎧🎧🎲
Memory 😳
855
ልጠይቅህ መልስልኝ
ልጠይቅህ መልስልኝ
ልብን ከፍተህ መልስልኝ
ለይቅርታ ተንበርክኬ ስለምንህ
እያነባው ስማፀንህ
በቸልታ የገፋከኝ
አሁን ስሞት ይቅርታህን የምትሰጠኝ
ላልመለስ መሄዴን ረስተሀው ነው?
ፍቅርን በተራብኩኝ
መወደድን በፈለኩኝ
አንዲትን ቃል የነፈግከኝ
አሁን ስሞት የምትነግረኝ
ፈገግ እንድል ደስ አንዲለኝ?
በቁም ሳለሁ ረስተኀኛል
መች አንደሰው ቆጥረኀኛል
አሁን አሁን እኔ ልቅደም የምትለኝ
ባስቀድምህ ከፊት ትሆን ነበር?
የእውነት የእወነት ትወደኝስ ነበር
አሁን ያልከኝ እቺ አጭር ቃል
ሳትዋሸኝ በቁም ሳለሁ ከአንደበት ይወጣል?
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@gGetem
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
4 any comment
@leoyri
በገጣሚ ጆሲ: @Joyefull
❥❥__⚘_❥❥
855
855
በቀን እንደሞትኩ...
ከአፈሩ አፈሩን ጥለነው
ከሰማዩ ሰማያቱን አልፈነው
ሄድን ሄድንና...
ከፈጣሪ የፍርድ መንበሩ ጋር ደረስን፤
ተረኛ ነበርና...
ደጃፉ ላይ ወንበር ስበን ተቀመጥን።
ተረኛ እስኪጠራ ፥ እስኪገባ ፈጣሪው ጋ
ትዝ ይለኛል ፥ ባንዲት ርዕስ ስናወጋ።
ሞትኩኝ...
የሚላስ የሚቀመስ አጥቼ
ሞትኩኝ...
"ትን" ብሎኝ ብፌ አሰናድቼ
ሞትኩኝ...
አልጋ ላይ ላመታት እንዳልነበርኩ ማቅቄ
ሞትኩኝ...
ስዝናና ውዬ ስመለስ ደክሞኝ መሪ ለቅቄ
ሞትኩኝ...
በተኛኹበት ወዳጄ ባልኩት በሰው ታንቄ
ሞትኩኝ...
ሞትኩኝ ሲሉ ፥ ኹሉ ኹሉም በየተራው
በቀኑ እንደሞተ ፥ ኹሉ ሰው ሚያወራው።
እኔ ግን...
እኔ ግን...
በቅጡ መኖሬን
በቅጡ መሞቴን ስላላወኩ
በቀኔ ሳይሆን በቀን እንደ ሞትኩ
አስታውሼ ነበር ፥ የተናገርኩ!
@gGetem
@gGetem
855
