en
Feedback
ሰም እና ወርቅ

ሰም እና ወርቅ

Open in Telegram

ሀሳብን በብዕር!! . .. ... ለሙገሳ ለወቀሳ ቢፈልጉ ለከሰሳ ካስፈለግም ለሽልማት አልሆን ካለ ለውግራት ካሻወትም በርቱ ማለት (ደና ነገር እንደሰራ ሰው ምን የሚያስሞግስ ነገር አለ?) ማለቴ በቃ ከፈለጋቹ ይኸው @Eliyashabesha123 @Mypoint010

Show more
626
Subscribers
-124 hours
-27 days
-430 days
Posts Archive
ካልቻልክ ተው አትታገል ለማይሆን ነገ ዛሬን አትግደል አትልፋ፥አትሁን ባተሌ ንጉስ የሌለው አይሆንም ሎሌ። . #ኢልያስ #ሀበሻ

Repost from Dejaf TV
ዳዊት ተስፋዬ ከዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት የደጃፍ ጨዋታ ሁለተኛ ክፍል አሁን ተለቋል:: የመጀመሪያዎቹ ተመልካቾች ሁኑ! https://youtu.be/9E1A7moInqA
ዳዊት ተስፋዬ ከዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት የደጃፍ ጨዋታ ሁለተኛ ክፍል አሁን ተለቋል:: የመጀመሪያዎቹ ተመልካቾች ሁኑ! https://youtu.be/9E1A7moInqA

እስቲ መቀላቀላችሁን በላይክ ግለፁልኝ👍👍👍

ደጃፍ ቲዮብ የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ቃለመጠይቆች (interview) የሚቀርብበት የ YouTube Chanel ነው subscribe በማድረግ ተጠቀሙበት!

እሷ ትኑር ደግነቷ ዳር የሌለው እሷ ትኑር ልቦናዋ ፀአዳ ነው እሷ ትኑር ስጋ፤ ነብሷ የተስማማ ምትፀልየው ከአርያም የተሰማ እሷ ትኑር የመኖርን ልክ ያሳየች ሰው አድርጓት ሰው መሆንን ያስተማረች እሷ ትኑር ለመኗሯ ምክንያት ያላት ወሰን አልባ እድሜ፣ ጤና የተገባት እሷ ትኑር............. ...............እሷ እናት ናት። ከ፦ካሌብ

መኖር ለውጥ ካላመጣ መኖር "መኖር" ካልመሰለ ሰው በመኖር ተለውጦ በአስተሳሰብ ካልበሰለ ኑሮ፣ መኖር በቃል እንጂ በተግባር ላይ መች ቀጠለ ከ፦ካሌብ

የአንዳንድ ሰው....... . ሀሳብ ጥርስ መሀል ሲሰገሰግ፣ በዝምታ ውስጥ ሲሰነግ። በአእምሮ ማሕደር ሲጠቀጠቅ፣ በሙላቱ እስኪሰነጠቅ። ከአንደበት ጋር ተለያይቶ፣ ቃል ከድምፀት ተራቁቶ፣ ከአርምሞ ጋር ተስማምቶ፣ በመመሰጥ ላይ አንግቶ፣ በብእሩ ብቻ ያወራል፤ ይሰንዳል ተሞሙቶ። ከ፦ካሌብ

የዝምታ ጩኸት ዝም ብዬ ጮህኩኝ፣ ቁጭ ብዬ ሄድኩኝ፣ በሀሳብ ሀዲድ ላይ ባቡር ተሳፍሬ፤ የአፌን ዝምታ በውስጤ ሰበርኩኝ። ተወራጨው ተበሳጨሁ፣ በአካል ግን ቁጭ ብያለሁ። ከ፦ካሌብ

ሌላ ፀሀይ! . ምስራቅ ምዕራብ አታውቅ አትጠልቅም አትከስምም፥አትጠብቅም ሰዐት    ብቅ ስትል ይነጋል፥ፍክት ይላል የገረጣ መች ፅልመት ይፀናል እሷ ስትመጣ፥ስትወጣ። አለች እሷ              ተስፋ አብቃይ፥ህልምን ፈቺ አለች እሷ              በውበት ሞገሷ ጉልበትን አበርቺ አለች እሷ               ከምጥ ገላጋይ ከራስ ትንቅንቅ አለች እሷ               የታበየን ሀሳብ ከነብስ የምታርቅ .        ስለታየች ብቻ፥ይህ ሁሉ ተዓምር         ቃል ሳትሰድ፥ሳታለፋው ያን ውብ ከንፈር              በአይን ብቻ!                  በውበት ብቻ!         ነብስን ትገራለች የሺ ቃልን አቻ። . #ኢልያስ #ሀበሻ . https://t.me/Eliyaskedir https://t.me/Eliyaskedir

በዝግታ ተራመድ ኮቴህ ለምድሩ ይቅለለው፥ ትንፋሽህን ዋጥ አድርገህ ለጆሮህ ዝምታን አድለው፥ በጫጫታ፥በሁካታ             በግርግር፥ የታለ? እስኪባል ከገዛ ራስህ ጋር ስለራስህ ዘምር፥ በምላስህ አትረታ ነብስህን አውራት በዝምታ       በዳንኪራ ሲወድቅ ዳሱ       አዋራው ሲነሳ ሲነግስ ትርምሱ       ከበሮ ሲደለቅ ነጋሪት ሲጎሰም       እስክስታ ሲመታ ዝም ባይ ሲከስም አንተ! በዝምታ አብብ፥በዝምታ ክነፍ በአርምሞ ኖረህ ሳትሳሳት እለፍ። . #ኢልያስ #ሀበሻ . https://t.me/Eliyaskedir https://t.me/Eliyaskedir

እንሞክረው ያልን ለት ስንምክረው ብንሳሳት አንደነቅ አንደበቅ መቆም የለም ያለመውደቅ ከ፦ካሌብ

ለእውነት የቆመ እሩቁን ያለመ የነገ ተስፋውን አድምቆ ያቀለመ በተግባር ለመግለፅ ከፊት የቀደመ ዛሬን......................ተሸለመ ከ፦ካሌብ

እንኑር እንዝለቅ ከሞት እንላቀቅ እንሂድ እንሙት እውነት ወዳለበት እንረፍ እንተኛ

ኑ ባልዲ ደቅኑ ተበዳይ አንብቷል በዝቶ ክፉአኑ ኑ ባልዲ ደቅኑ እንባቸው ጎርፍ ነው ይበቃል ለሁሉ          ግን ከሁሉ በፊት አለኝ ማሳሰቢያ እንባቸው መራር ነው የህይወት አምሳያ። . ኢልያስ ሀበሻ . https://t.me/Eliyaskedir

❝ስሞት ልረፍ አንደኛዬን አሁን ላይ ግን ልንገላታ፣ ወጣትነት ሐይሌ ሳይሸሽ በዚህ ኑሮ ላይ ልበርታ። ዳገት ልውጣ ልውረድ ገደል፣ ዛሬን ደክሞኝ የነገዬን መቀመጫ ላደላድል። ቁርስ ይዝለለኝ ምሳም ይለፍ፣ ነገዬ ላይ እንኳን ለኔ ለተራበ ሰው እንድተርፍ። ሰዎች ይግፉኝ፤ በአለባበስ ይጠየፉኝ፣ ነገ ስለብስ በቀን ባትሪ በአየር ባቡር ሊፈልጉኝ።❞ ብዬ አላምንም፣ ዛሬን ልጥገብ አመስግኜ ስለነገ እኔ አላውቅም። ከ፦ካሌብ