cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Orthodoxs Daily

በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ የሚታሰብ ቅዱሳን፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፤ ብሂለ አበው እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ፅሁፎች ያገኙበታል::Share https://t.me/ethiopianorthodoxs //like page on facebook fb.me/ethiopianorthodxs ለሀሳብ አስተያየትዎ @Yakob520

Show more
Advertising posts
6 382
Subscribers
+824 hours
+207 days
+1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በሰሙነ ህማማት ወቅት የምንሰማቸው እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው በግብረ ሕማማት ውስጥ በግዕዝም ሆነ በኋላ በአማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የእብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፦ #ኪራላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ < ኪርዬ ኤሌይሶን> ነው። #ኪሪያ ማለት እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡ #ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፤ማረን" ማለት ነው። #እብኖዲ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይናን" ሲልም " አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው። #ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣አምላክ" ማለት ነው። #ማስያስ ፦ የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲህ" ማለት ነው። #ትስቡጣ ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው። #አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ- አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነው። #አምነስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግስትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነው። #አምነስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግስትከ -የሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን " ማለት ነው።
Show all...
ሚያዝያን ለመቄዶንያ! ወራችንን በመልካም ስራ እንጀምር
Show all...
Repost from Ethio telecom
ሚያዝያን ለመቄዶንያ! በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ አረጋዊያን እና ህሙማን መርጃ ማዕከል እንለግሳለን! እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ! ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን | ዩትዩብ | ቲክቶክ | ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ! #MatchingFundForSustainableFuture #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
Show all...
++++++#መዳን_በሌላ_በማንም_የለም#+++++++ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰው የተሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለምና።" በሚለው ንባብ ውስጥ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ መድኃኒት መኾኑ ተገልጿል። "ሌላ ስም የለም" ሲል የአብንና የመንፈስ ቅዱስን ስም አያድንም ለማለት አይደለም፤ ነገር ግን አብ ወልድን የላከው በእርሱ ስም በኩል ለዓለም ድኅነት እንዲኾን ነው። የወልድን ስም መጥራት ከእርሱ የማይለዩትን አብንም መንፈስ ቅዱስንም መጥራት ነውና። ሦስቱ የማይለያይ አንድነት ሥራ አላቸውና። (Tadros, Yacob Malaty, Commentary on Act, p 214)። ስለዚህ የዚህ ጥቅስ ጭብጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ መድኃኒት መኾኑን መግለጥ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም አምኖ የሚጠራ ይድናል የሚል ኹሉ አለ። ይህም የስሙን ታላቅነት መግለጥ ላይ መሠረት ያደረገ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ነው። ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ "የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" ይላል። ሮሜ 10፥13። ይህንኑ ሐሳብ ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ ጽፎታል። ሐዋ 2፥21። እነዚህ የሐዲስ ኪዳን ጥቅሶች የሚያስረዱት የክርስቶስን እግዚአብሔርነት እንደ ኾነ ለማስረዳት ነቢዩ ኢዩኤል አስቀድሞ "የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል " ብሏል። ኢዩ 2፥32። እንግዲህ ይህ በግልጽ የኢየሱስ ክርስቶስን የስሙን መድኃኒትነትና ኀይል የሚገልጥ ነው። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የክርስቶስን ስም ባልተገባ ምግባር ውስጥ ኾነው ቢጠሩት መዳን የማይቻል መኾኑን የሚያስረዳ ንባብ አለ። "ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚወርስ አይደለም" እንዲል። ማቴ 7፥21። ይህ ማለት እምነት ኖሮን በፍጹም ምግባር ጉድለት ውስጥ ኾነን፡ በተግባራዊ ሕይወት የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ሳናከብር ብንጠራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አንችልም ማለት ነው። ከላይ "የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" የሚለውን ይተረጉመዋል ማለት ነው። ዝም ብሎ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚል በሕይወቱ የጌታን ትእዛዛት የማይጠብቅ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባ ዘንድ እንዴት ይኾናል? ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ ይላል "ከመንግሥተ ሰማያት ውጭ የሚኾነው እምነት እያለው ምግባር ግን የሌለው ሰው ብቻ አይደለም። እምነት ከመያዙም ባሻገር ብዙ ገቢረ ተአምራትን መፈጸም ስንኳ ቢችል፥ መልካም ምግባር ግን ከሌለው ይህ ሰው ሳይቀር ከዚያ ከተቀደሰው ደጅ ውጹእ ይኾናል።" (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ (ተርጓሚ)፣ የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደ ተረጎመው ድርሳን 1-24፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 470)። ከላይ ከያዝነው ሐሳብ ጋር ተመሳሳይ በኾነ ኹኔታ ኢየሱስ ክርስቶስን በአግባቡ ለመጥራት የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መኾንን ይጠይቃል። ሰውነታችን በኃጢአት ምክንያት የርኩስ መንፈስ ማደሪያ ከኾነብን እንግዲያውስ እንዴት በአግባቡ ኢየሱስን የባሕርይ አምላክነቱን በሚገልጥ ኹኔታ ልንጠራው እንችላለን? ቅዱስ ጳውሎስ "ስለዚህም ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር "ኢየሱስ ውጉዝ ነው" የሚል እንደ ሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልኾነ በቀር "ኢየሱስ ጌታ ነው" ሊል አንድስ እንኳን እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።" ይላል። 1ቆሮ 12፥3። ትርጓሜያችን ይህን ሐሳብ "በብዔል ዜቡል ከሚል ከአይሁዳዊ በቀር አንድም ብዔል ዜቡል አድሮበት ፍጡር ከሚል ሰው በቀር፤ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ኢየሱስ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ ነው የሚል እንደሌለ አስተምራችኋለሁ። አንድም ብዔል ዜቡል አድሮበት በኅድረት ነው ከሚል በቀር በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት መለኮት ከትስብእቱ ፡ ትስብእቱ ከመለኮቱ ልዩ ነው የሚል እንደሌለ እነግራችኋለሁ። "ወአልቦ ዘይክል ብሂለ እግዚእ ኢየሱስ ዘእንበለ ዘመንፈስ ቅዱስ ላዕሌሁ።" ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ካደረበት ሰው በቀር ኢየሱስ የባሕርይ አምላክ ነው ብሎ ማመን የሚቻለው እንደሌለ እነግራችኋለሁ። " ይላል። (ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው፣ 2007 ዓ.ም፣ ገጽ 257)። እንግዲህ ይህም የሚገልጠው በእውነተኛ እምነት ውስጥ በመልካም ምግባር መኖር የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሚያደርግ መኾኑንና በሚያድርብንም መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ኢየሱስ ክርስቶስን በአግባቡ የምንጠራ መኾናችንን ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ አምነው ሲጠሩት ያድናል ማለት ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ "ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው" በማለት ኢየሱስን ጌታ ነው ብሎ በአግባቡ ለመጥራት መንፈሳዊ ልደትን ገንዘብ ማድረግ የሚገባ መኾኑን ይጠቅሳል። (St Gregory, Bishops of Nyssa, On the Faith)። ስለዚህ በአንዲት ጥምቀት በኩል መንፈሳዊ ልጅነትን ገንዘብ ያላደረገ ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ ነው ብሎ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ጋር ያለውን ዕሪና መናገር አይችልም። እንግዲህ የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ለእኛ የተሰጠን አምነንበትና ተረድተን በመድኃኒትነቱ እንድንጠቀም ነው። https://t.me/phronema
Show all...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

አኃውየ ተፋቀሩ፣ ወንድሞቼ ተዋደዱ፣ እስመ ኩሉ ዘይትፋቀር ዘልፈ እምእግዚአብሔር ውእቱ፣ ሁል ጊዜ የሚዋደድ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነውና፣ አፍቅሩ ቢጸክሙ በምልአ ልብክሙ፣ በሙሉ ልባችሁ ባልንጀራችሁን ውደዱ፣ እስመ ተፋቅሮ ይደመስሶን ለኩሎን ኀጣውእ፣ መዋደድ ሁሉንም ኀጢአቶች ያጠፋልና፣ አክብሩ ሰንበተ በጽድቅ፣ ሰንበትን በእውነት አክብሩ፣ ቅረቡ ኀቤሁ ለልዑል በልብ ንጹሕ፣ በንጹሕ ልብ ታላቅ ወደ ሆነው (ወደ እግዚአብሔር) ቅረቡ፣ ዘምሉእ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ በፍጹም እግዚአብሔርን በመፍራት፣ ሠርዐ ለነ ጾመ ለንስሓ፡ እስመ ጾም በቁዔት ባቲ፣ ጾምን ለንስሓ ሠራልን፣ ጾም ታላቅ ጥቅም አላትና፣ ክርስቶስኒ ጾመ በእንቲአነ አርአያሁ ከመ የሀበነ። ክርስቶስ ስለ እኛ ጾመ፣ አርአያነቱን ይሰጠን ዘንድ። ምንጭ፦ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ለመፃጉዕ ካዘጋጀው ዝማሬ (ዝማሬ ዘመፃጉዕ) ላይ በከፊል የተወሰደ ነው። እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን ታላቅ በረከት የምናገኝበት፣ በንጹሕ ልብ ወደ እርሱ ቀርበን ዋጋ የምንቀበልበት የጾም ወቅት ያድርግልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን! ይቆየን። ምሕረቱ ተገኝ (ዶ/ር) መጋቢት 21, 2016 ዓ.ም
Show all...
💠💠ንስሐ💠💠 ንሰሐ ሰው ሕይወቱን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ የሚያስችለው መንፈሳዊ ጥንካሬ ወይም ኃይል ነው:: ንስሐ በልቡናችን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ፍቅረ እግዚአብሔር እንዲወለድ ያደርጋል:: ምክንያቱም በንስሐ ሕይወት የምንኖረው ከሆነ እግዚአብሔር ስለ እኛ ብሎ የተሸከመልንን ሸክምና ይቅር ያለንን እጅግ የከፋ ኃጢአት እንድናስብ ስለሚያደርግና ለእግዚአብሔርም ያለን ፍቅር እያደገ ስለሚሄድ ነው:: 💠እናስተውል✔ በቅዱስ ወንጌል ላይ በሐዋርያት ሥራ 24-:-24-27 የፊልክስና የንጉሥ አግሪጳ ታሪክ የሚያስተምረን ታሪክ አለ:: ፊሊክስን የእግዚአብሔር መንፈስ የንስሐ ዕድል ሰጥቶት አነሣሣው እርሱ ግን ያገኘውን ዕድል በቀጠሮ አራዘመ:: መጽሐፍን ስናነብ ግን ንስሐ ስለመግባቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድም ቦታ አልተጠቀሰም አበውም አልነገሩንም:: ንጉሥ አግሪጳም ለማመን የተሰጠችውን የንስሐ ዕድል ሳይጠቀምበት ቀረ ዳግመኛም አላገኛታም::የሐዋ.ሥራ 26-:-19-29:: ኢትዮጵያዊው ጀንደረባ ግን ያገኘውን የንሰሐ ዕድል ሳያመነታ ወዲያው ተጠቀመበት አመነ በፊሊጶስ እጅ ተጠመቀ:: የሐወ. ሥራ 8-:-36:: 💠በቸርነቱ እንጠቀም✔ ንስሐ መግባት ሲገባን በተደጋጋሚ የተለያዩ ምክንያቶችን በማብዛት መዘግየት ንስሐን እንደመቃወም የሚቆጠር ነው:: ይህም በፈርዖን ሕይወት ውስጥ የታየ ነው:: ፈርዖን እስከ ዐሥር መቅሰፍቶች ደረሰ በአሥሩም መቅሰፍቶች መማር ንስሐ መግባት አልወደደም:: በእያንዳንዱ መቅሰፍት ተመክሮ ንስሐ እንዲገባ ዕድል ተሰጠው ነገር ግን በመዘግየቱ በዕድሉ ሳይጠቀምበት ቀረ ዕድሉ በባሕረ ኤርትራ መስጠም ሆነ::           💠ኦ ንለቡ ፍቁራንየ✔ በወንጌል የተነገረላት ሴት እርሷ በዕንባዋ የጌታን እግር አርሳው በጠጉሯም አብሳው ነበርና የበደለችውን ሁሉ አስባ:: ሉቃ.7-:-47:: እግዚአብሔር የበዛ ኃጢአቱን ይቅር ያለው ሰው የተደረገለትን ይቅርታና የተጨመረለትን ዘመን እያሰበ በልቡ የእግዚአብሔር ፍቅር እየጨመረ ይሄዳል:: የኃጢአታችንን ብዛት የእግዚአብሔርን ምሕረት እያሰቡ የሚኖሩ ሰዎች ፍቅረ እግዚአብሔር የገባቸው የመስቀሉን ዋጋና የተፈጸመላቸውን የማዳን ምሥጢር የተረዱ ናቸው:: ለመሆኑ እግዚአብሔር በቸርነቱ በፍጹም ፍቅሩ ዕለታትን ወራትን ዓመታትን እየጨመረ እየጨመረልን በሄደ ቁጥር የኛ ጽድቅ መንፈሳዊነት ትጋታችን እየጨመረ እየጨመረ ሄዷል? ወይስ የተጨመረችልንን የንስሐ ዘመን የበለጠ በኃጢአት ተንኮታኩተን በሥነ ምግባር ላሽቀን አንገተ ደንዳና ልበ ጠማማ ሆነናል? በምግባራችን ብሉሹ ሆነን እናት ሃይማኖታችን በማሰደብ ሌሎችን በማሰነካከል በየመጠጡ በየጭፈራው ቤት በመስከርና በመዳራት እየጨምርን እየጨመርን ነው ያለነው? በንስሐ የታደሰ ሕይወት ሃይማኖቱን በትምህር በእምነት ይጨምራል በንስሐ የታደሰ ሕይወት ጾም ጸሎት ሕይወቱ ነው ኃጢአት ደግሞ ጠላቱ ናት:: በእግዚአብሔር ኃይል ኃጢአትን ይረግማታል ኃጢአትን ይርቃታል ኃጢአትን ይጠላታል ኃጢአትን ይጠየፋታል በንሰሐ እያደሰ ሕይወትን ይጨምራል:: በስሙ ለተጠራን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተባልን ለኛ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው:: ንስሐ ገብተን አምላካችንን አባቴ እርሱም ልጆቼ ይበለን:: አሜን! 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Show all...