9 642
Subscribers
No data24 hours
-67 days
-6230 days
Posts Archive
9 642
#ውሾች_ይጮሃሉ_ግመሎች_ይሄዳሉ..
🐪🐪🐪 🐕 🐕
ማንም ምንም ይበል Keep going forward ! What others think about you is none of your business!
እንግሊዘኛ ትምህርትን በእስፖርት⛹♂ መምህር ተምሬ ይሄን ያህል እንግሊዘኛ ከፃፍኩ መደነቅ የለብኝም ታዲያ🤷♂
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 36..🥀
.
.
.
.
ሊባኖስም "እሺ ልነግርክ ነው ያቺ ልጅ ዛሬ ሞታለች" አለችው። ያቤፅ ግራ ተጋባ "ቆይ አንቺ ሴት ምን እያወራሽ ነው በፈጠረሽ አምላክ? አምላኬ ሆይ አሽሙር አደለም በለኝ ቆይ ፅናት ትሞታለች እያልሽ ነው" አላት።
ሊባኖስም "አይ እንደዛ ሳይሆን" አለች። ያቤፅ የሊባኖስን እጅ ይዞ እንባ እየተናነቀው "ቆይ ምንድነው ንገሪኛ በፈጣሪ" አላት። ሊባኖስም "እየውልክ ልጅትዋ የሞተችው እኮ በሽታውን መቋቋም ስላቃታት ነው። ደሞ የኔ ሚጢጢን በሽታውን እንድትቋቋም ለማረግ አሁን ብዙ የሚያስደስቷትን ነገሮችን ማረግ አለብን ተስማማን?" አለችው። ያቤፅም "አዎ አዎ እሺ ተስማምተናል" አላት። ሊባኖስ ፈገግ ብላ "እሺ ጥሩ ዛሬ ሁለቱ ቆነጃጂት እህትማማቾች ሲመጡ ጥሩ ጊዜ እናሳልፍለን" አለች። ያቤፅን አቅፋው
ያቤፅም "እሺ ጥሩ ግን ፅኑ አትመጣም"አላት። ሊባኖስም "እንዴ ለምን ለምንድነው እማትመጣው የት ልትሄድ አለችው" ያቤፅም የተፈጠረውን ነገራት። ሊባኖስ "ባክህ ዝም በላት ትመጣለች ጨክና አትቀርም በእኛ ብጨክን በእህቷ ጨክና አትቀረም አሁን በቃ እምንሰራውን ነገር ገዛዝቼ ልምጣ" ብላ ብድግ አለች።
ያቤፅ "እህ አብሬሽ ልሂድና እሸከምልሻለው" ሲላት። ሊባኖስ "አይ አያስፈልግም ይልቅ ደመቁ ብስኩት ልትሰራ ትመጣለች ስለዚህ እሷን ውሀ በማጋዝ አግዛት" ብላ መኝታ ቤት ገብታ ተዘጃጅታ የሳሎኑ በር ላይ እንደደረሰች ደመቁ መጣች። ሊባኖስም "ውይ ደምዬ መጣሽ እንዴት ነሽ ጀርባሽን ተሻለሽ " አለቻት።ደመቁም "አይይይ ዛሬ አልሰራም ልልሽ ነው አመጣጤ በጣምምም አሞኛል" ስትላት።ሊባኖስ "እሺ በቃ ሂጂ ቤትሽ እረፍት አርጊ ልጅ ያቤፅ በል ና አብረከኝ በሩን ቆልፈክ" አለችው። ያቤፅም በሩን ቆልፎ ከ ሊባኖስ እና ከደመቁ ጋር ወጡ።
ሰአቱ 12:15 ሆኖዋል የእነ ፅናት ቤት ፉዋዋዋ ብሎ ቡና ተፈልቷል የተለያዩ የምግብ አይነቶች ጠረጴዛ ላይ ተደርድረዋል።ፅናትም ልክ እሷ እና ያቤፅ ተጣልተው ታክሲ ከያዘችበት ቦታ ደርሳ ከታክሲው ወረደች። የሁሉም ሰው አይን ፅናት ላይ ነው። ፅናት ልክ ትንሽ እንደተራመደች ከፊለፊቷ አንድ ሸበላ በጣም የሚያምር የጨርቅ ሱሪ በሸሚዝ እና ፍላት ጫማ አርጎ እየመጣ ነው።ፅናት በውስጧ "እሰይይ ሰው ሁሉ እኔ ላይ ሲያፈጥ እኔም እማፈጥበት ሰው አገኘው" አለች። ልጁ ወደ እስዋ እየቀረበ መጣና ከፊት ለፊትዋ ቆመ። ፅናትም አንገቷን ቀና አርጋ አይኖቹን አየቻቸው።
እሱም ትኩር ብሎ አያትና "ፅኑ" አላት። ፅናት ማመን ተሳናት ይሄ ከፊትለፊቷ የቆመው በጣም ማራኪ ቁመና እና መልክ ያለው ልጅ ያቤፅ እንደሆነ ስታውቅ "ያቤፆ" አለችው።
"ወዬ ፅኑዬ" አላት። ፅናት ፈገግ ብላ "የእውነት አንተ ነክ ፤ የእውነት አንተ ነክ ግን" አለችው። ያቤፅም "አዎ ፅኑዬ እኔ ነኝ እንዴት ነው አምሮብኛል?" አላት እጆቹን ከፍ አርጎ ፅናት ፈገግ ብላ "በጣም የኔ ሸበላ ቃል የለኝም ጨበሬ ፀጉርክ፤ችፍፍፍ ያለው ፂምህን ተስተካክለክ ያንን ኮተት ልብስ ቀይረክ እንዴት እንደምታምር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፊትህን በደብ ያየውት ስለተቀየርክ ደስስስ ብሎኛል"ብላ አቀፈችው። ያቤፅም ይበልጥ አጥብቆ እቅፍ አርጓት "ፅኑዬ" አላት። ፅናትም "ወዬ ያቤፆ" ስትለው "ጠዋት ላስከፋውሽ ነገር ይቅርታ እማትመጪ መስሎኝ ከፍቶኝ ነበር ነገር ግን ሊቦ ትመጣለች ብላ ተስፋ ሰጠችኝ አላት። ፅናትም ከያቤፅ እቅፍ ሳትወጣ "የምር ብቀር ታዝን ነበር?" አለችው። ያቤፅ ከእቅፉ አውጥቶ ጉንጭ እና ጉንጯን በሁለቱ መዳፉ ይዞ "በጣም በጣም ፅኑዬ እኔ ያላንቺ አልችልም" አለና ግንባሩዋን ሳማት። ይህኔ ነበር የፅናት ልብ በሀያሉ የመታው ያቤፅ ብሏት እማያውቀውን ቃላቶች ብሏት ከዛም አልፎ ደሞ ግንባርዋን ለመጀመሪያ ጊዜ በፍቅር አይን እያየ ሲስማት እንዴት ልብዋ አይመታም ይመታል እንጂ።
ፅናት ቀና ስትል ከያቤፅ አይኖች ጋር ተገጣጠሙ ያላወቀችው ሀይል መጥቶ ወደ ያቤፅ ከንፈር መራት። አይኑዋን ጨፈነች ያቤፅም አይኑን በስሱ ጨፍነው ያሉበት ቦታ ታክሲዎች በፍጥነት የሚጓዙበት እንጂ ሰው የሚያልፍበት አደለም። ልክ በከንፈሮቻቸው መካከል ትንሽ ክፍተት ሲቀር ልባቸው ለጉድ ይመታ ጀመር። በመጨረሻ ከንፈር እና ከንፈራቸው ተነካካ እና ሳመችው እሱም ሳማት።
ይህኔ ነበር ፅናት ያቤፅ እቅፍ ውስጥ ሆና ከሀሳብዋ የነቃችው ያቤፅ እቅፍ ውስጥ ሆና በሰማችው የመኪና ክላክስ ነበር። ፅናት "ወይ እውነት አልሆነ ወይ ሀሳቤ ላይ አልቆየው" አለች በውስጧ የመኪና ክላክስ ወደሰማችበት አቅጣጫ እየዞረች። ባለ ክላክሱ የበፀሎት አለቃ ነበር። ፅናት የያቤፅን እጅ እየጎተተች።ከኋላ ገቢና ላይ በፀሎት አለች። መኪና ውስጥ ከገቡ በኋላ ፅናት "እህቴ እንዴት ነሽ አንተስ እንዴት ዋልክ"አለች። የበፀሎትን አለቃ እያየችው። "ደና ነኝ አንቺስ" አላት በቀኝ እጁ እያሽከረከረ በግራ እጁ ደሞ የበፀሎትን ጣቶች ከጣቶቿ አጣምሮ ይዞ። ፅናት ይህንን ስታይ ማመን አቃታት "እህቴ" አለቻት። "ወዬ የኔ ልዩ" ስትላት። "እጅሽ" አለቻት። የበፀሎት አለቃ ደንግጦ የበፀሎትን እጅ ሊለቃት ሲል በፀሎት "ቆይ" አለችና እጁን ይበልጥ አጥብቃ ያዘችው እና "የኔ እህት ፅናትዬ አትንቀልቀይ እሺ ጥያቄሽ በኋላ ይደረሳል" አለቻት።
ፅናትም "እሺ እህቴ"አለች። ድምፅዋን ቀነስ አርጋ። ከዛም በልብዋ "ምን አለበት ያቤፅም እጄን ቢይዘኝ" ብላ ተመኘች። ያቤፅ በመስኮቱ በኩል አፍጥጧል። አሁን ቤት ደረሱ። ያቤፅ ከሁሉም ቀደም ብሎ በሩን ከፈተው ፅናት "እንዴዴዴዴዴ ኧረ ጉድድ ደስ ሲል " አለች። በፀሎት ግራ ገብቷት "እንዴ እህቴ ምነው" አለች። በእዚህ ሰአት ነበር የሊባኖስ አይን የበፀሎት እና የአለቃዋን የተጣመረ እጅ ላይ አይኑዋ ያረፈው። "ኧረ ጉድድድ ዛሬ ሰርፕራይዝ አረጋለው ብዬ እራሴው ተደረኩኝ"አለች።
ፅናት እና ያቤፅ ፈገግ አሉ። የበፀሎት አለቃ ተሸማቀቀ ምክንያቱም ሊባኖስ ከተጣመረው እጃቸው አይኑዋን መንቀል ስላልቻለች።ሊባኖስ በመጨረሻ ሀሳብዋን ሰብስባ "በሉ በሉ ቁጭ በሉ"አለች። ከዛ ቤቱ ድምቅ አለ። ሊባኖስ ቡና እያፈላች ነው ሁሉም ሊባኖስ የሰራችውን ጣፍጭ ምግብ እየተመገቡ ነው በቃ ቤቱ በጣምምም ደምቋል ልክ ምግባቸውን ተመግበው ሁለተኛ ቡና እየጠጡ በፀሎት ድምፅዋን ከፈ አረጋ "ስሙኝ ዛሬ ሁለት ደስስ የሚሉ ነገሮች እነግራችዋለው"አለች። ፅናትም "እሺ እህቴ በያ ንገሪን እባክሽ" አለቻት። በፀሎት እምትናገረው ጠፍቶባት መንተባተብ ጀመረች። የሁሉም አይናቸው፤ ልባቸው እና ጆሮአቸው በፀሎት ላይ ሆኖዋል።
በፀሎት ግን መናገር አቃታት። ሊባኖስ "በያ የኔ ቆንጆ ንገሪን አታጓጊን እንጂ" አለቻት። ፅናትም በጣም ጓጉታ "እህቴ እባክሽን ንገሪን" ስትላት። ያቤፅ "ኧረ በፂ ይደብራል ምንድነው እንዲ ማጉዋጋት"? አላት። በፀሎትም "ማጉዋጉዋት ፈልጌ እኮ አደለም እንዴት ብዬ መግለፅ እና መናገር እንዳለብኝ ከብዶኝ እንጂ ዛሬ 2 ነገሮች እነግራችዋለው " አለችና ብድግ ብላ እጅዋን ወደ አለቃዋ ሰደደችው እሱም ተነስቶ እጅዋን ያዛት።
.
.
.
ከ 150 like ቡሀላ ክፍል 37 ይቀጥላል...
👇👇👇
በየቀኑ እንድንለቅላቹ አንብባቹ ስጨርሱ ሼር ላይክ አርጉ ♥️
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 35..🥀
.
.
.
.
ከዛም ወደ በፀሎት ሄዶ ቁጭ አለ ና ፅናትንም ስቦ አስቀምጦ ሁለቱንም አቅፎአቸው "በጣም ውብ ከውቦችም ውብ ናቹህ እኔ በህይወቴ እንደ እናንተ አይነት ቀርቶ ከ እናንተ በጥቂት የሚያንሱ ቆንጆዎች እራሱ አይቼ አላውቅም ደሞ እኮ ከ ፀጉሯቹ እና ከ ማጠር እና መርዘም እንዲሁም ከፊት ከለራቹ በስተቀር ፍፁም አንድ አይነቶች ናቹህ የፈጣሪ ያለ የኔ አምላክ ልቤን ጠብቅልኝ" አለ።
ሊባኖስም ሳቀች። ፅናትም "በሉ ሰዎች ወደየ ጉዳያችን እንሂድ ዛሬ ለእኔ እና ለእህቴ አዲስ ጅማሮ ነው።በይ እህቴ ተነሺ የመኪና ክላክስ በእርግጠኝነት የእህቴ አለቃ ነው የሚሆነው በሉ እስቲ አሁን ደሞ አለቃ ተብዬው እህቴን ሲያያት ምን እንደሚሰማው እንይ" አለች። በፀሎትም "በይ ዝም በይ እህቴ ሆሆሆ እኔ እራሱ እራሴን በመስታወት ለማየት ጓጓው እኮ" አለች። ያቤፅም "እረ እንኳን አላየሽው በራስሽ ውበት ተማርከሽ ብቀሪስ ለማንኛውም ነይ እስከበር ልሸኝሽ" አለና ከ ወገብዋ አቀፍ አርጓት የውጪው በር ላይ ደረሱ።
ያቤፅ እነ እሱ ጋር መኖር ከጀመረ ጀምሮ በፀሎትን ሁሌም ይሸኛታል። ልክ በሩን ከፍተው ሲወጡ የበፀሎት አለቃ በፀሎትን ሲያያት ከመኪናው ፈዞ ወረደ።አይኑን ከበፀሎት ሳይነቅል ወደ እስዋ ተጠጋና "እእእእ በጣም ቆንጆ ነሽ የምር አንቺ በፀሎት ነሽ" አላት። ያቤፅም "አዎዎ በፂ እኮ ናት እይዋት እይዋት እንደእዚህ ውበት እንደጉድ የፈሰሰባት ልጅ አለች ሁላችሁም ዙራቹ እይዋት" እያለ መጮህ ጀመረ።
በፀሎት ተሸማቀቀች። "ያቤፅዬ እባክህን ዝም በል ልለምንህ" አለችው። ያቤፅ ግን የበፀሎት ልመና ችላ ብሎ አሁንም መጮሁን ቀጥሏል ፅናት ምን ተፈጠረ ብላ ወደ ውጪ ለመውጣት የውጪውን በር ከፈተችው ሊባኖስም ተከትላት ወጣች። ያቤፅ ወደ ውጪ በር ዞር አለ ፅናትን አያት ወደ ፅናት ሄዶ እጇን እየጎተተ ከእህትዋ አጠገብ አስቆማትና...
"ተመልከቱ እዩ ተመልከቱ የእነዚህን እህትማማች ውበት" የያቤፅ ድምፅ የት እና የት ይሰማል እየጮኸ መናገሩን ቀጥሏል። "እንዲህ አይነት ውበት ማነው አይቶ የሚያውቅ ንገሩኛ " ካለ በኋላ ወደ በፀሎት አለቃ ዞር ብሎ "አንተ አይተክ ታውቃለክ" አለው። የበፀሎት አለቃም በድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆኖ ኧረ በጭራሽ"አለ። ያቤፅ እብደቱ እና ጩኸቱ ባሰበት "አቤቱ አቤቱ የፈጣሪ ያለ አቤቱ ምንድነው ዛሬ ያየውት"አለና ፀጥ ብሎ ቆየ።
የሰፈሩ ሰው ከህፃናት እስከ አዋቂ ከበቧቸው። ያቤፅ አሁን መጮሁን ትቶ ወደ በፀሎት እና ፅናት በመሄድ አንድ አንድ እጃቸውን ይዞ የምር ዛሬ ባየውት ውበት ተደምሜያለው አላቸው። በፀሎትም "ቆይ አንተ ልጅ አብደሀል እንዴ" አለችው።
ያቤፅ ወዲያው ፈገግ ብሎ "በእዚህ ፀባዬ ነበር ልክ አንቺ አብደሀል እንዴ ብለሽ እንደጠየቅሽኝ ሳይጠይቁኝ አብደሀል ብለው እብዱ ያቤፅ ያሉኝ"አላት። ፅናትም እየሳቀች "እና እንዲ እየሆንክ እብዱ ያቤፅ ቢሉክ ምን ይገረማል"አለችው። ያቤፅም "እሱማ አይገርምም በቃ ነይ ፅኑዬ ልሸኝሽ" አላት። ሊባኖሰ"አዎ ሂዱ በሉ በፀሎቴ በይ አንቺም አታስጠብቂው አለቃሽን አንተ እብድ በል አድርሳትና አንተም ና ዛሬ እፈልግሀለው" አለችው። ያቤፅ "እሺ እንዳልሽ በይ ነይ ቦርሳሽን ይዘሽ ፅኑ " አላት። ፅናት ፈገግ ብላ "እሺ ጌታው ያቤፅ" አለችና ቤት ገብታ የበፀሎትንም ቦርሳ አምጥታ ሰጥታት "በይ መልካም ቀን የኔ ቆንጅዬ እህት አለቻት።የበፀሎት አለቃም "እንዴ አብራችሁን ኑ እንሸኛቹ" ሲል ያቤፅ "አይ አያስፈልግም እባክህ ዛሬ ይህቺን ቆንጆ በመንገዱ ላይ ይዣት ሽርርር ልበል ልጎርር ደረቴን ነፍቼ ልሄድ አዳሜውን ላስቀናው አይመስልክም" አለው።
አሁን ፅናት ከያቤፅ ጋር አውላላ አስፓልት ላይ እየተጓዘች ነው። ፅናት ከ ያቤፅ አይኗን አልነቀለችም የሆነ ልትለው የምትፈልገው ነገር ያለ ይመስላል። ያቤፅም እጁን በለበሰው ኮታታ ሹራብ ከቶ እየተጓዘ ነው በሀሳብ ስምጥ ብሏል።የሆነ ሀሳብ ውሰጥ ገብቷል ።ፅናት በልብዋ ምን እያሰበ ይሆን? ለምንድነው እኔን ከ ሰው ጋር ብቻ ስሆን እያወራኝ ለብቻችን ስንሆን ምንም እማይለኝ?" አለች። ያቤፅ ያቀረቀረ አንገቱን ቀና አርጎ ፅናትን እልም ያለ ፍቅር በሚያሲዝ አስተያየት አይቷት ከዛ መልሶ አንገቱን ሰበረ። ፅናት ይህ ነገሩ ጭራሽ አይገባትም ለምን? እንዲ ትሆናለክ ብላ መጠየቅ ፈልጋለች ግን አንደበትዋ አላወራ አላት። ከያቤፅ ጎን ስትሆን ውስጧ በሀሴት ይሞላል ያቤፅም ከፅናት ጋር ሲሆን እንደዛው ግን ሁለቱም ስለሚሰማቸው ነገር መነጋገር አልቻሉም።
ፅናት ወሬ ለመጀመር ያህል "ያቤፆ" አለችው። ያቤፅም "ወዬዬ ፅኑዬ" አላት። መንገደኛው ሁሉ እያየኝ እኮ ነው"አለችው። ያቤፅም "አዎ ፅኑ ልክ ነሽ ባያዩሽ ይገርመኝ ነበር በጣም ውብ እንደሆንሽ ነገሬሻለው"አላት። እረጋ ባለ ድምፅ። ፅናትም "ታቃለክ እረጋ ስትል እብደትህ ስታብድ ደሞ እርጋታክ ይናፍቀኛል"አለችው። ያቤፅም
"ማለት ፅኑ አልገባኝም "አላት። ፅናትም ፈገግ ብላ "እስቲ እባክህ አንዴ ቀና ብለክ እያየከኝ አውራኝ ቆይ እህቴንም አለቃዋ መጥቶ መውስደ ከመጀመሩ በፊት አንዳንዴም ሳይመጣ ሲቀር ሰትሸኛት በእዚህ መልኩ ነው" አለችው። ያቤፅ ዝም ብሎ ቆመና የፅናትን ፊት እያየ "አደለም ፅኑ ከ በፂ ጋር ስሆን ቃል አይጠፋብኝም ካንቺ ጋር ስሆን ግን አሁን አሁን እምናገረው ነገር እየጠፋብኝ ነው ፅኑዬ አልቻልኩም እባክሽ የሆነ ነገር ብለሽ ገላግይኝ" አለ በውስጡ።
ፅናት ዝምታው አስፈራት "እሺ እሺ በቃ ተወው እዚህ ጋር ታክሲ ይዤ እሄዳለሁ ተመለስ ካላዋራከኝ እርምህን ዛሬ ብትሸኘኝ ያውም ደሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ጊቢ በምገባበት ቀን እንደውም በቃ ዛሬ እዛው ጊቢ ነው እማድረው አልመጣም" ብላ ወደ ዩንቨርስቲ የሚወስዳትን ታክሲ አስቁማ ሄደች። ያቤፅ ከአስፓልት ወደ እግረኛ መንገድ ተጠግቶ ቁጭ አለ። ፅናትም የያዛት ታክሲ ያዟት ከነፈ።
ያቤፅ ከቆይታ በኋላ ከሊባኖስ ጋር ቁጭ ብሉዋል።ሊባኖስ ዛሬ ፅናት እና በፀሎት ሲመጡ አንድ ነገር እናረጋለን። አለችው።ያቤፅም "ወይ አንቺ ፅኑ እኮ አልመጣም ብላለች"ሲላት።እንዴ ለምን አለችው ምክንያቱን ነገራት። ሊባኖስም "ዝም በላት ቅርብ ነው ዩኒቨርሲቲው የ አንድ ታክሲ እና የትንሽ እግር መንገድ የቦታ እርቀት አታስብ እሱዋን እኔ አመጣታለው" ስትለው ያቤፅ "እሺ ምንድነው እነግርሀለው ያለሽኝ?" ሲላት ሊባኖስ "መጀመሪያ እንቢ እንዳትለኝ ቃል ግባልኝ"አለችው እሺ በይ ንገሪኛ አላት። ሊባኖስም ለመናገር ተመቻችታ ያቤፅን አይኑን አተኩራ እያየችው ነው።
"እየውልክ የኔ ሚጢጢ እንደምታውቀው በተደጋጋሚ እራስዋን ትስታለች" አለችው። ያቤፅም "እና ምን" አላት። ሊባኖስም "ለማለት የፈለኩት የሆነ ጊዜ ላይ ጋሽ በሬሳ ጋር አንድ ታካሚ መጥታ ነበር እና እራስዋን በተደጋጋሚ ልክ እንደ የኔ ሚጢጢ ስታ ትወድቅ ነበር" አለችው። ያቤፅ መንጎራደድ ጀመረ "ቆይ አንቺ ሴት አብደሻል እንዴ የፈጣሪ ያለ ቆይ እና ምን ይሁን ነው ምትይው ምልክታቸው አንድ አይነት ሆኖ ነገር ግን የተለያየ በሽታ እንዳለ አታውቂም እሺ በይ ቀጥይ" አላት እጁን እያወናጨፈ እና ይበልጥ በፍጥነት እየተንጎራደደ። ሊባኖስም ማውራቷን ቀጠለች። "እኔ ለማለት የፈለኩት" ስትል ትግስት ያጣው ያቤፅ ሊባኖስ አጠገብ ቁጭ ብሎ እያፈጠጠባት "ሆሆሆ ሊላ ለምን እምትናገሪውን ነገር አትናገሪም" አለ።
ይቀጥላል...
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 34..🥀
.
.
.
ለሊቱን ያቤፅም ፅናትን ፅናትም ያቤፅን በማሰብ እና ፈገግ በማለት ከዛ ደሞ በመተኛት አልፎ ጠዋት ብርሀን በፀሀይ ፈክታ ፀሀይም በብርሀን ፈክታ ለስለስ ያለች ፀሀይ ወጥታለች። የእነ ፅናት በር ተንኳኳ ፅናት ለሊቱን የተጓዘችው የፍቅር መንገድ እንቅልፏን ስለተሻማባት በጭራሽ አልሰማችም በፀሎትም ከእንቅልፏ ለመነሳት ሁነኛ ቀስቃሽ ያስፈልጋታል አልያም እንቅልፏን መጨረሰ ያስፈልጋታል። ሰአቱ 1:15 ሆኑዋል። ያቤፅ ተነስቶ በሩን ከፈተው። ሊባኖስ ነበረች። "እንዴ ጎረምሳው እንዴት መጣክ" አለችው። ያቤፅም "በምክንያት"
ብሏት ገባ። ሊባኖስም እንደመደናገር ብላ
"በምክንያት?"አለች ቃሉን እረገጥ አድርጋ። ያቤፅም ወደ ቤት ገብቶ ጥቅልል ብሎ ተኛ። ሊባኖስ ወደ ቤት ገብታ ወደ እነ ፅናት መኝታ ቤት ገባች። ፅናት እና በፀሎት ተቃቅፈው ተኝተዋል። ሊባኖስም ወደ እነሱ ተጠግታ በፍዘት ውስጥ ማየትዋን ተያያዘችው በድንገት ፅናት ከ እንቅልፍዋ ነቅታ "ደና አደረሽ ሊቦዬ ምንድነው ነገሩ በጣም ተመስጠሻል " አለቻት። ሊባኖስም "ውበታቹ እኮ ገርሞኝ ነው የኔ ልእልት በጣም ቁንጅናቹ ቱቱቱ ከአይን ያውጣቹ"
አለች። በፀሎትም እየተንጠራራች "ምንድነው ነገሩ ዛሬ ደሞ በጠዋቱ ነው የቀሰቀሳችሁኝ እንዴት አደራቹ? " አለቻቸው። ሊባኖስ እና ፅናትም "ደና አንቺ እንዴት አደረሽ አሉዋት። በፀሎትም "ደና አድሪያለው ኧረ ለነገሩ በጠዋት መነሳቴ ጥሩ ነው"ስትል ሊባኖስ ክትክት ብላ ሳቀች። በፀሎት ግራ ተጋብታ "ምነው ምንድን ነው የሚያስቅሽ ሊቦቲዬ" አለቻት። ሊባኖስም "እንዴት አልሳቅ 1:30 ተነስተሽ በለሊት እንደተነሳ ሰው ስትሆኚ" አለቻት። ፅናትም ተደረባ ሳቀች እና "እኔም ዛሬ ማመልከቻዬ እንደተሳካ እና እንዳልተሳካ አያለው እዚሁ በሆነች ብላቹ ፀልዩ እባካቹ አለች።
........... ከ ወራቶች በኋላ..........
ዛሬ ፅናት የ 12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድል አጠናቃ ልክ እንደምኞቱዋ ያለችበት ክልል ላይ ተመድባለች። እናም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀሎት እና ፅናት አዲስ ህይወትን ለመልመድ ያህል ፊታቸው ላይ የሚጠመጥሙትን ሻርፕ ከፊታቸው ላይ አውልቀውታል ፅናትም ወደ ዩንቨርስቲ በፀሎትም ወደ ጨርቃጨረቅ ማሰልጠኛው ሊሄዱ ነው። አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስ ጀምረውታል። ያቤፅ ሁለት ወር ሙሉ ሻርፓቸውን አስወልቆ መልካቸውን ማየት እስኪቀረው ድረስ ፊታቸውን እንዲያሳዩት ሲለማመጣቸው ቆይቷል። እሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የፅናትን እና የበፀሎትን የፊት ገፅ ማየት ጓጉቶ ሳሎን ላይ እየተንጎራደደ ነው። ሊባኖስም ትልቁ ሶፋ ላይ ተቀምጣ ያቤፅን እየታዘበችው ነው። ያቤፅ አቁነጥንጦታል። ለነገሩ በእሱ የማሳመን ብቃት ነው ዛሬ ላይ ፊታቸውን ለማየት የመጓጓቱ ቀን የመጣው።
ሊባኖስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ "እናንተ ልጆች በሉ ፈጠን በሉ"አለቻቸው። ያቤፅም ወደ ሊባኖስ ጠጋ ብሎ አጠገብዋ ተቀምጦ "ስሚኝ እማ ሊባኖስ እስቲ በደንብ ንገሪኝ እስኪወጡ ድረስ ትናትና ፀጉሯቸውን ስታስተኩሻቸው አምሮባቸው ነበር እሺ ፅኑ እንዴት ነበረች? ፅኑ አምሮባት ነበር? የፅኑ ፊት ምን አይነት ነው?ቀይ እንደሆነች አውቃለው ግን ምን አይነት ፊት ነው ያላት? እሺ በፂስ እሱዋስ አምሮባት ነበር?" አላት። ሊባኖስ ሳቅ እየተናነቃት የያቤፅን ወሬ ከሰማች ሳቀች። ያቤፅም "እባክሽ ንገሪኝ እሺ ምን አይነት ልብስ ነው የገዛሽላቸው?" አላት።
ሊባኖስ ሳቁዋን ማቆም አቅቷታል። የመኝታ ቤቱ በር ተከፈተ ያቤፅም በፍጥነት መኝታ ቤቱ በር ላይ ሄዶ ቆመ። ሊባኖስ የያቤፅን ሁኔታ እያየች መሳቁዋን ማቋረጥ አቃታት። ያቤፅ አይኑን ማመን ተሳነው ፊት ለፊቱ የሚያያት ፀይም ፀጉሯን በአጭሩ የተቆረጠችው እና የለበሰችው ነጭ ሼፒ ቀሚስ የሰውነት ቅርፅዋን በደንብ አሳምሮ ያወጣላትን ልቅም ያለች ቆንጆ ሴት አየ። በፀሎትን አይቷት ፈዘዘ "በፂ በፂዬ ወይኔ ጉዴ የፈጣሪ ያለ እንዴት ነው የምታምሪው" አለ አፉን ይዞ "አሁን እሺ እንዴት ነው ካንቺ አይኔን እምነቅለው የፈጣሪ ያለ እኔ ልጮህ ነው። ቆይ ምንድነው አይኔ የሚያየው ይህንን ውበት ማመን አልቻለኩም በጭራሽ አላምንም ወይኔ አምላኬ ቆንጆ ሴት በምናብህ ሳል ብባል እራሱ እንደ አንቺ ውብ አርጌ ልስላት አልችልም።" ብሎ ያለ ትንፋሽ ካወራ በኋላ መንጎራደድ ጀመረ። መንጎራደዱን ገታ አድርጎ በፀሎትን አየት ያረጋታል በፀሎትን አይቶ ፅናትን እርስት አርጓታል።
በፀሎት በዳበሳ ወደ ሶፍው ሄዳ ቁጭ ብላ "እንዴ ምንድነው ነገሩ ሊቦዬ ያቤፅ ምን ነክቶት ነው ያቤፅ በሰላም ነው?" ስትል ሊባኖስ ይበልጥ እየሳቀች "ውበትሽ ነዋ እንዲ የሚያስለፈልፈው" አለቻት። ያቤፅ ከአጠገብዋ ተቀመጠና "ወይኔ ወይኔ ወይኔ በጣም ውብ ነሽ ቆይ ለምንድን ነው ይህንን የመሰለ ውበትሽን እስከዛሬ አሳይኝ ስልሽ እንቢ ያልሽው ወይ አምላኬ ወይ ፈጣሪ" አለ። በፀሎትም "እኔን አይተክ እንዲ ከሆንክ ፅናቴን ብታያት እራስክን ልትስት ነው እንዴ በእረግጥ ፅናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ካየዋት አመታት ቢያልፉም በልጅነቷ እራሱ የነበራት ውበት በቃላት የሚገለፅ አደለም"አለችው በፀሎት ፈገግ ብላ።
ያቤፅም "ውይኔ አምላኬ ስትስቂ እራሱ እንዴት ነው ምታምሪው"አላት። በፀሎትም "አመሰግናለሁ ያቤፅዬ" አለች። ያቤፅ ዝም ብሎ ያያት ጀመረ። በድንገት ፅናት "እሺ ያቤፆ እኔስ ባክህ" አለች። ያቤፅ ፈጠን ብሎ ልቡን ያዘ አይኑ ለጉድ ፈጠጠ ቀይ ከበፀሎት ረዘም ብላ ቀጠን ያለች የሚስብ የሰውነት ቅርፅ ያላት ፀጉሯ እጅግ በጣም ረዥም ከወገብዋ ያለፈ።ፈገግ አለች ልክ እንደታላቅ እህቷ በፀሎት ጉንጭዋ ስርጉድ አለ። ድድዋ የተነቀሰ ይመስላል የጥርስዋ ንጣት ለጉድ ነው ብቻ ያቤፅ በበፀሎት ከፈዘዘው በላይ ፈዞ ድርቅ ብሎ ሀውልትን ተክቷል በበፀሎት ውበት የለፈለፈው ምላሱ አሁን በፅናት ውበት ልሳኑ ተዘግቷል ቃል ማውጣትም አቃተው ይህኔ ነበር በፀሎት፣ሊባኖስ እና ፅናት በያቤፅ ከት ብለው ሲስቁበት የባነነው እና "የፈጣሪ ያለ፤ የአምላክ ያለ፤ ይህቺኛዋን ደሞ እዩልኝ ወይ አምላኬ ኧረ የልቤን ነገር አደራክን ዛሬ የልብ ድካም ሊይዘኝ ነው" አለ። ፅናትም ወደ ያቤፅ ተጠግታ "ኣ እኔ ለእራሱ በድንጋጤክ ባሳየከው ፊት ልብ ድካም ሊይዘኝ ነው እኮ" አለችና "እስቲ" ብላ ወደ ደረቱ ተጠግታ የልብ ምቱን አዳመጠችው እና ከት ብላ እየሳቀች "ኣኣኣኣ የ ያቤፆ ልብ በጣም እየመታ ነው እእእ የምርም በጣም ደንግጧል" አለች። ያቤፅም የፅናትን እጅ ይዞ እያያት ድምፁን ለስለለስ አርጎ በጣም ውብ ነሽ" አላት።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል...
9 642
.
.
**ኧረ ወገን ላይክ ሼር አርጉ😳
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 33..🥀
.
.
ከ እለታት በአንዱ ቀን ሰው በመግደል የሚታወቅ እና የሚደሰት አንድ ሰው ነበረ። ታዲያ ይህ ሰው ያለበት ሁኔታ ሚስቱ ያሳስባትና የኔ ባል ደስታህ ደስታዬ ነው ህመምህም ህመሜ ስለዚህ እንደማይህ ሰው በጣም መግደል ያስደስትካል ስለዚህ እኔም ልክ እንዳንተ ገዳይ ልሁን። 10 ሰው ልትገል ካሰብክ እኔ 5ቱን ልግደልልክ ፅድቅ ከሆነ አብሪክ ልፅደቅ ኩነኔ ከሆነ አብሪክ ልኮነን አለችው። ሰውየውም በንግግሯ ተረብሿ እና ተናዶ ሚስቱን ጥልዋት ይሄዳል። ከዛም ሚስቱ ተከትላው ትሄዳች። ሰውየውም ሊገላቸው የተዘጋጀለትን ሰዎች ሊገል ሲል ሳያስበው ሚስቱ ሽጉጡን ቀምታ አንደኛው ሰው ላይ ደቀነችበት። ይህ ሰው የሚስቱን መኮነን እና ሀጢያት አይፈልጉውምና ተይ ተይ እባክሽ ሲላት። ሚስትየውም እንዲ አለች። ፅድቅ እና ኩነኒ ቢኖረም ባይኖረም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀረም አለችው። ሰውየው ሚስቱ በብልሀቷ ተጠቅማ የዛሬ ሀጢያቱን አትርፋለት የተገዳዮችንም ነብስ አተረፈችላቸው ይባላል።
ስለዚህ ከችግሩ ማውጣት የምትፈልጊውን ሰው ማንነት ይዘሽ ሳይሆን የያዝሽ መስለሽ ነው ከችግሩ ማውጣት የምትችይው" አለቻት። ፅናትም "ጥሩ ታሪክ ነው እህቴ... " ብላ ተናግራ ሳትጨረሽ። የውጩ በራቸው በሀይለኛው ተንኳኳ ፅናት ቶሎ ተነስታ ከፈተችው የያቤፅ እናት ሶስና ነበረች። ፅናት ደንግጣ " ምነው አለቻት" ሶስናም "ልጄ ያቤፅን አጣሁት ልጄ ሞተ እረዳዋለው ብላቹ አልነበረ " ብላ መጫህ ጀመረች። ፅናት ደንግጣ መናገረ አቃታት።
የእብዱ ያቤፅ እናት ባለሱቋ ሶስና እያለቀሰች ነው። ፅናትም እንደዛው። በፀሎትም የሶስናን ድምፅ ስትሰማ ተደናግጣ እየደባበሰች ወደ እነ ፅናት ተጠጋች እና "ምንድነው ለምድነው ቆይ እንዲ እየጮውሽ ያለሽው" አለቻት። ሶስናም ተንበርክካ ማልቀስዋን ቀጠለች። በፀሎትም "ቆይ ለምን የሆንሽውን አትነግሪኝም ፅናቴ እህቴ ምን እየተፈጠረ ነው" አለች። ፅናትም "እህቴ ያቤፅ ሞተ ነው ምትለው" አለች። በፀሎትም "ምን ምን እያልሽ ነው መጀመሪያ ተረጋጊ ያቤፅ እኮ ቅርብ ሰአት አብሮን ነበረ" አለቻት። ፅናትም በለቅሶዋ ላይ ፈገግ እያለች "አዎ አሁን ቅርብ ሰአት አብሮ ነበር" አለች። ሶስናም "ሁሉም ሰው አይቶታል ልጅሽ ሞቷል አስክሬኑን ወስደውታል ብለውኛል ደሞ እዚህ በር ላይ ነው ያሉኝ" አለች። ፅናትም "ተመቶ በራችን ላይ የሞተው እኮ ያቤፅ ሳይሆን የያቤፅ አባት ናቸው"አለቻት።
ሶስናም እንባዋን እየጠራረገች "እውነት ነው? ልጄ በህይወት አለ፤ያቤፅዬ ልጄ በህይወት አለ?" አለች ይህኔ ነበር ከየት መጣ ሳይባል እብዱ ያቤፅ እራቅ ብሎ ቆሞ "አዎ ልጅሽ ያቤፅ በህይወት አለ፤ አዎ ያንቺ ልጅ ያቤፅ፤ እብዱ ያቤፅ፤ ያበደው ልጅሽ ያቤፅ፤ እናቱን ያልተረዳው ያቤፅ ፤ አሁንም በህይወት አለ። እናቴ እኔ በህይወት አለው ፤ አሁንም እኔ በህይወት አለው አባባ ግን የለም ፤አባባ ግን ሞቷል
፤ የማይረዳኝ እና እብድ እንደሆንኩኝ እራሱን ያሳመነው አባባ ግን ሞቷል፤ በምኖርበት አከባቢ የተሰማኝን በመናገሬ እብዱ ያቤፅ ብለው ስም አውጥተው እብዱ ያቤፅ መጠሪያ ሰሜ ሲሆን ዝም ብሎ ለአመታት አብዷል ብሎ የእብድ መዳኒት ሲወጋኝ እና ይበልጥ ባለማወቅ የሰው ወሬ ሰምቷ መርፌ እየወጋ ይበልጥ ሲያሳብደኝ የነበረው አባባ ግን ሞቷል።"
አለ እብዱ ያቤፅ ድምፁን ከፍ አድረጎ እያለቀሰ።
ሶስናም ወደ ልጇ ተጠጋች እብዱ ያቤፅ ግን እናቱ አንድ እረምጃ በተጠጋችው ቁጥር እሱም እየራቃት እሷ በተጠጋችው ቁጥር አሁንም በድጋሜ እየራቃት መጣ። የእናት ልብዋ አልችል አላት ሶስና አሁንም ተጠጋችው ልጇ ግን አሁንም እራቃት "እማማ እንዳትጠጊኝ እማማ ወደእኔ መምጣትሽን አቁሚ፤ ተይ እናቴ ፤ ተይ ማሚዬ ፤ አትጠጊኝ ለ5አመታት ሱቅሽ ፊት ለፊት እየመጣው ስተኛ ወደ እኔ መጥተሽ አታውቂም ያ አብድዋል ብሎ ያሰበው አባቴ የማይገባኝን መዳህኒት በመርፌ ሲሰጠኝ አንድ ቀን መተሽ አቁም ብለሽ ታስቆሚዋለሽ ብዬ አስቤ ነበር። ግን እማማ ፤ ግን ማሚዬ ፤ ግን እናቴ ፤ አንቺ አላዳንሽኝም። የኔ እናት እኔ ያንን መርፌ አባባ ሲወጋኝ ማስቆም አቅቶኝ አልነበረም። እማማ አንቺ መተሽ እንድታስቆሚው ሰለምፈልግ እንጂ። እኔ አላበድኩም ይህንን ደሞ አንቺ በደንብ ታውቂያለሽ እናቴ። ታዲያ ለምን አባባን አላስቆምሽውም ለምን ዝም ብለሽ ሰዎች ይበልጥ አብድዋል ብለው እንዲያስቡ ፈቀድሽላቸው ታውቃያለሽ እማማ እየውልሽ ስሚኝ ሰዎች ሲሸሹ፤ ሰዎች ሰው ይገላል ብለው ባልገደልኩት እና ባልሰራውት ሀጢያት ሲፈርዱኝ እና ሲርቁኝ" አለና እናቱን አልፎ ፅናት ጋር ሄደና ወደ ፅናት እየጠቆመ "ይህቺ ሴት ናት የቀረበችኝ እና ልክ አንቺ እግር ስር ሆኜ ድሮ የማሳልፈውን ሲከፌኝ የምነግርሽን ቀናቶች እንዳሳልፍ እና እግሯ ስር ቁጭ እንድል የፈቀደችልኝ ልክ አንቺ ድሮ ሳለቅስ ምክንያቴን ሳታውቂ ስላለቀስኩኝ ብቻ እንዳለቀሽው እስዋም ያውም ያለ ምክንያት ያለቀሰችው። እና የሚያዳምጠኝ ሰው እንዳለ እንዲሰማኝ ያረገችው እሷ ናት እማማ ልክ ሳያት ነበረ እምትረዳኝ ሴት እንደሆነች የታወቀኝ እሷን ውስጤ ካስገባዋት አመት አልፎኛል በቃ እማማ አሁን ወደመጣሽበት ሂጂ" አለ። ሶስናም ምንም ሳትናገረ በሩጫ ነበር እያለቀሰች የሄደችው።
ፅናት አለቀሰች በፀሎትም እንደዛው እብዱ ያቤፅም ወደ ፅናት ይበልጥ በመጠጋት "የፅናትን እጆች ይዞ በጣም ይቅርታ ያለ ፍቃድሽ ፊት ለፊትሽ ስላማውሽ" አላት። ፅናትም ሳቀችና "ምንም አደል" አለችው። አሁን በፀሎት እና ፅናት ስለ እብዱ ያቤፅ ይበልጥ ማወቅ ፈልገዋል። ፅናትም "በልና ግባ አለችው። እና ሲገባ የውጪን በር ቆልፈው እህቷን አቅፏት ያቤፅን ደሞ በእጅዋ ይዛው ወደ ቤት ገቡ።
ቤት ከገቡ በኋላ ፅናት በቅጡ ያልዳነውን እና የደማውን ጭንቅላቱን አየችው። "እንዴ ጭንቅላትክ እኮ ደምቷል ያቤፆ" አለችው።ፅናት እህቷን ሶፋው ላይ እያስቀመጠቻት። እብዱ ያቤፅም "ማን ብለሽ ነው የጠራሽኝ" አላት። ፅናትም "ያቤፆ" አለችው። እብዱ ያቤፅም "አሁንም ደግመሽ ጥሪኝ እባክሽን ሲላት።ፅናት ፈገግ ብላ "ያቤፆ" አለች።
በፀሎትም "በሉ አሁን ተኙ እሺ መሽቷል በቃ ነይ ፅናቴ" ብላ መኝታ ቤት ገባች። ፅናትም "እሺ እህቴ ቆይ ፋሻውን ልቀይርለት እና እመጣለው" አለች። ከዛም ከ ጠረጴዛ ስር ፋሻ እና የቁስል መጥረጊያ እንዲሁም አልኮል አመጣችና "በል በጀርባህ ተኛ እሱ ላይ" አለችው። ተኝታበት የነረውን ትልቁን ሶፋ እየጠቆመች። ያቤፅም "እሺ" ብሎ ተኛ።
ፅናት በጥንቃቄ ከፋሻው ጋር ባመጣችው ጥጥ እና አልኮን ተጠቅማ ካፀዳችለት በኋላ እንዲቀመጥ አርጋው ጭንቅላቱን ጠመጠመችለት። "አመሰግናለሁ"አላት። ፅናትም "ይቅርታ እኔ ነኝ እንዲ ያረኩክ ግን ምንም አላልከኝም"አለችው። ያቤፅም "አውቀሽ እኮ አደለም" አላት ድምፁን ለስለሰ አድረጎ። ፅናትም "እሺ ስለተረዳከኝ ደስ ብሎኛን ደና እደር" አለችው። እሱም እሺ
"ደና እደሪልኝ" አላት። ፅናት ወደ መኝታ ቤት ሄዳ እህቷ ያሞቀችው አልጋ ውስጥ በእህትዋ እቅፍ ገባች።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል...
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 32..🥀
.
.
ፅናትም "አውቃለሁ እርሶ ባልነበሩበት ወቅት ሀኪም ቤት ሄጄ ታይቼ ነበር እና" ብላ ሁሉንም ነገር ነገረቻቸው። ጋሽ በሬሳም "ሁሌም ቢሆን ጠንካራ ሰዎች አሽናፊ ናቸው ልጄ አንቺ ጠንካራ ነሽ በይ አሁን ልሄድ ደና ሆነሽ እንደሚሻልሽ እረግጠኛ ነኝ" ብለው የፈጩትን ነገር ሰተዋት "በይ ይህንን ማታ ማታ ሁሌም አፍንጫሽ አከባቢ ተቀቢው አልያም ልክ እኔ አሁን እንዳረኩልሽ አርጊ ጥቅሙ የሚያስደነግጥጡሽ ነገሮችን እንድትቋቋሚ ያረጋል ነገር ግን ተሳስተሽ ስለ እዚህ መዳህኒት ጥቅም ለማንም እንዳትናገሪ "ብለዋት ሊወጡ ካሉ በኋላ መለስ ብለው "ይህንን የሚያውቅ ሰው አለ ልጄ " አሉዋት። ፅናትም "አይ ማንም አያውቅም" ስትላቸው "ጥሩ ጥሩ አደረግሽ በይ ሰላም አምሺ" ብለዋት ወጡ።
ጋሽ በሬሳ ከመኝታ ቤት ሲወጡ ሊባኖስ "በሉ ቁጭ በሉ ሻይ ላፍላሎት" ስትላቸው። "አይ ብዙ ያልተቋጨ ጉዳይዎች አሉብኝ ይልቅ ሸኚኝ" አሉዋት። ሊባኖስም ጋሽ በሬሳን ልትሸኝ ወጣች። በፀሎት ደሞ በዳበሳ ወደ መኝታ ቤት ሄደች። ፅናት እህቷን ስታያት "እህቴ ነይ ነይ ቁጭ በይ" አለቻት። በፀሎትም "እሺ እህቴ " ብላ በዳበሳ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች። ፅናትም "እህቴ ሊቦ የለችም እንዴ " ስትላት ። "ጋሽ በሬሳን ቆይ ልሸኛቹ ብላ ነው የወጣችው" አለቻት። ፅናትም "እሺ እህቴ ያቤፅስ?" አለቻት። በፀሎትም "እሱ የለም ውይ እህቴ እሱም ነበር ለካስ ጭራሽ እርስት አርጊዋለው" አለች። ፅናት ከተኛችበት አልጋ ላይ ተስፈንጥራ ተነሳችና "የምረሽን ነው እህቴ እየቀለድኩኝ ነው በይኝ እንዴት እንዴት ትረሱታላቹ ቆይ ምን መሆናቹ ነው እህቴ" ብላ ጮከች። በፀሎት ደነገጠች። "እንዴ ቆይ እህቴ ለምንድነው እንዲ እየጮሽ የምታወሪው" አለቻት።
ፅናትም "አሁን ዝም በይኝ እህቴ ዝም በይኝ እንዴት እንዴት ትረሱታላቹ መልሽልኝ እህቴ" አለቻት። እንዲ ሲጯጯሁ ነበር ሊባኖስ የደረሰችው "የኔ ሚጢጢ ምንድነው እሱ ለምንድነው ቆይ እህትሽ ላይ ያለ ልማድሽ የምትጮሂባት?" ስትላት። ፅናት እያለቀሰች "ቆይ እንዴት ለቀቃችሁት" አለቻቸው። በፀሎት "እኔ ምንም እማውቀው ነገር የለም እህቴ"አለቻት። ሊባኖስም "ቆይ መጀመሪያ ተረጋግተሽ ቁጭ በይ እና የተፈጠረውን ላስረዳሽ የእኔ ሚጢጢ" አለችና ከ በፀሎት አጠገብ አስቀመጠቻት። ፅናት ግራ ገባት። "እሺ በይ ንገሪኛ" አለቻት።
ሊባኖስም የመኝታ ቤቱን በር ዘጋችውና "እስቲ ጠጋ በሉ እባካቹ" አለቻቸው ከዛም ተጠጉላትና ከ ፅናት አጠብ ተቀመጠች። ከዛም ፅናት ከ በፀሎት እና ከ ሊባኖስ መሀል ሆነች። ሊባኖስም እጅዋን ወደ ትራሰ ጌ ሰዳ ፅናት ለብሳው የነበረውን ጋቢ አመጣችና ለፅናት ደረበችላት። ፅናት የሊባኖስ በቶሎ አለመናገር በጣም አናዶታል እናም ደሞ በጣም ውስጧ ፈርቷል። ፅናት "ሊቦዬ እባክሽ ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ" አለች። ሊባኖስም "እኔ እና ያቤፅ ከ ቤት ተደናግጠን ስንመጣ ያው እንደሰማችሁት ውጪ የመሳሪያ ድምፅ ነበር። በራችን ላይ የ ያቤፅ አባት ተተኩሶባቸው ወድቀው ነበር።ልክ እኛ ከቤት ስንወጣ ነው የ ያቤፅን አባት የመቷቸው ማክስ ያረጉ ሰዎች ቀይ መኪና ውስጥ ገብተው በመስኮት ወጥተው እየተኮሱ የሂዱት። የ ያቤፅ አባት እያቃሰቱ "ልጄን ልጄን ነው የሚፈልጉት እባካቹ ልጄን አድኑት" እያሉ ነበር። እና ብዙ ሳይቆዩ ነው የሞቱት" ስትል። ፅናት "ምን ምን ማለትሽ ነው ሞተ ማለት የያቤፅ አባት ሞቱ እያልሽ ነው?እሺ ያቤፅስ" አለች። ሊባኖስ ላይ እያፈጠጠች። ሊባኖስም "ያቤፅ የት እንደሄደ አናውቅም ድንገት ነው የተሰለበውን አለቻት። ፅናት እሪ ማለት ጀመረች። ሊባኖስም "ቆይ የኔ ሚጢጢ ለያቤፅ ያለሽ ስሜት የተለየ ነው አደል" ስትላት። ፅናትም "እሱን ማዳን አለኝ" አለች።በፀሎትም "እንዴ እህቴ ቆይ ምንድነው ምትይው እኛም እኮ እሱን ማዳን እንፈልጋለን ግን ቆይ ያንቺ እንዲ መሆን ምን ይሉታል?" ስትላት። ፅናት "ኡፍፍ በቃ አሁን ልተኛ ተውኝ በቃ አለችና ከመሀላቸው ወጥታ ወደ አልጋው ተመልሳ ጋደም አለች። ሊባኖስም "እሺ በቃ አሁን ተኚ አለቻት። ፅናትም "ቆይ እሺ የያቤፅ አባት አስክሬን የት ተወሰደ?" አለች። ሊባኖስም "ሰዎች ነው የወሰዱት በአምቡላንስ ጭነው በቃ የኔ ሚጢጢ ጥያቄ መጠየቅሽን እና እኛ ላይ ማልቀስ እና መጮህሽን ትተሽ ተኚ" አለቻት። በፀሎትም "ሊቦቲዬ እባክሽ በቃ ዛሬ ሁላችንም ጥሩ ውሎ አልዋልንም ስለዚህ በሩን ዝጊውና እንተኛ አንቺም እኛ ጋር እደሪ አለቻት። ሊባኖስም " አይ የኔ ቆጆ እኔ መሄድ አለብኝ እሺ በቃ በውጪ ቆልፌው እሄዳለው ተኙ እናንተም፤ ጠዋት ብርቱካን ለፓስቲ መስሪያ የሚሆን ዘይት ይዛ ትመጣለች የኔ ሚጢጢ ከ ቀደምኳት ክፈችላት እሺ" ብላ ሁለቱንም ግንባራቸውን ስማቸው ልትሄድ ስትል። ፅናት "በቃ ሊቦዬ በመንገድሽ እያየሽው ሂጂ ገና አልተሻለውም የሆነ ነገር እንዳይሆን" አለችና ፊቷን ወደ ግድግዳ አዞረች። ሊባኖስም "ሆሆ" አለችና ወደ በፀሎት ጆሮ ጠጋ ብላ "ስሚ እህትሽ በፍቅር ባህር እየዋኘች ነው ኧረ እንደውም ሰምጣለች" አለቻት። ከዛ በፀሎት ፈገግ ብላ "ኧረ እንዳሰማሽ ዛሬ እህቴ ተነስቶባታል በይ አንቺም ወደ ቤትሽ ሂጂ እንዳይመሽብሽ እኔ ዛሬ እህቴን ማፅናናት እና ደስተኛ ማረግ አለብኝ" አለቻት። ሊባኖስም ከመንሾካሾክ ወጥታ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ "እሺ በቃ የኔ ውቦች በሉ ደና አምሹ" አለችና መኝታ ቤቱን ዘግታው ወጣች።
ሊባኖስ ከሂደች በኋላ በፀሎት ፅናትን ለማዝናናት እና ካለችበት ጭንቀት ለማውጣት ምን ማድረግ እንዳለባት ስታስብ ቆይታ አንድ ዘዴ መጣላት እና ፈገግ አለች። በፀሎት ዝም ብላ ስለ ፍቅር ብታወራ ፅናት እንደምትደሰት አሰበች። ከዛም ማውራት ጀመረች። " ፍቅር ግን በጣም ይገረማል" ብላ ጀመረች። በፀሎት የፅናትን ሀሳብ መስረቅ አልቻለችም። ከዛም ትንሽ ቆይታ "አይይ ያቤፅ በጣም ጥሩ ልጅ ይመስላል በጣምምም እውቀቱ እና ከአንደበቱ የሚወጡት ቃላቷች በጭራሽ ከ እብድ የሚወጣ አይመስልም" አለች። አሁን ፊቷን ወደ ግድግዳው ያዞረችው ፅናት ወደ እህትዋ ዞረች። በፀሎትም በአልጋው እንቅስቃሴ ፅናት የተኛችበትን አቅጣጫ እንደቀየረች ተረዳች።
ፅናትም "ልክ ነሽ በጣም ጥሩ ልብ ያለው ነው። እህቴ እሱን መረዳት አለብኝ" አለች። በፀሎትም ፈገግ ብላ "አዎ እኛም እናግዝሻለን ታውቂያለሽ ለቅሶ ላይ ያለውን ሰው አልቃሽ ሆነሽ ፤ፍቅር ላይ ያለን ሰው አፍቃሪ ሆነሽ፤ በቀል ላይ ያለውን ሰው ተበቃይ ሆነሽ ነው ሰውን ወደ እራሱ እንዲመለስ ምታረጊው አንድ ታሪክ ልንገረሽ እህቴ....
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል...
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 31..🥀
.
.
ልክ ሹፌሩ ማርቆስ መኪናውን ሲያቆም ፅናት በፍጥነት ከመኪናው ወረዳ እህቷ ላይ ተጠምጥማ ቆየች።በፀሎትም ፅናትን አጥብቃ አቅፋት "እህቴ ፈርቼ በፍርሃት ልሞት ነበር እማጣሽ መስሎኝ ነበር" አለቻት። ፅናትም " አትጨነቂ የኔ ውድ እህት እህትሽ ደና ናት" አለቻት።
ማርቆስ እብዱ ያቤፅን ደግፎ በፀሎት እና ፅናትም ተቃቅፈው ሊባኖስም ከኋላቸው እየተከተለቻቸው ቤት ገቡ። ቤት ከገቡ በኋላ ፅናትን ሊባኖስ ከበፀሎት እቅፍ አውጥታ ደግፋ አመቻችታ አንደኛው ትልቁ ሶፋ ላይ ጋደም እንድትል አረገቻት። ከዛም እብዱ ያቤፅን ደግፎ ያቆመውን ሹፌሩ ማርቆስን ሊባኖስ "ማርቆስ በል አሁን ፈጠን ብለክ እንግዳችንን እዛኛው ሶፋ ላይ አረፍ እንዲል አርገው" አለችው። ማርቆስም ሊላኛው ሶፋ ላይ ያለው ተመቻችቶ የተቀመጠ ትራስ ላይ አሳርፈው። ከዛም ማረቆሰ ምንም ቃል ሳያወጣ ቤቱን ለቆ ወጣ ሊባኖስም የቆመችውን በፀሎት ተቀመጭ እንጂ ብላ ባለ አንድ ( ለአንድ ሰው ብቻ የተሰራ) ሶፋ ላይ አስቀምጣት።
ማርቆስን ተከትላው ወጣችና ልክ መኪናውን አስነስቶ ሊሄድ ሲል ደረሳበት አስቆመችው። ሊባኖስም "ስማኝ ማርቆስዬ ሊላ የተጨመረ አለ? አለችው። ማርቆስም በአንገቱ እንደሊለ ገለፀላት። ሊባኖስ ፈገግ አለች። ማርቆስም መኪናውን አስነስቶ ሊባኖስን
በእጁ ተሰናብቷት ሄደ።ሊባኖስም ማርቆስ ወደ ቅያሱ ታጥፎ ሲቀየስ እስዋም ወደ ቤት ገባች።
ሊባኖስ ቤት ስትገባ ቤቱ በዝምታ ተውጦል። "ምነው ዝም አላቹ ተጫወቱ እንጂ " አለች። ፅናትም " እኔ እምልሽ ሊቦዬ ቆይ ለምንድን ነው ሹፌርሽ እማያወራው ማውራቱን ተይውና ፈገግ እማይለው" አለቻት። ሊባኖስም "አይይይ የኔ ሚጢጢ ማርቆስ እኮ ማውራት አይችልም ግን መስማት ይችላል" አለቻት። ፅናትም "እና ቢያስ ፈገግ አይልም እንዴ?" አለቻት። ሊባኖስም ፈገግ የሚያስብለው ነገር ከተገኘ ይላል።" አለች። በፀሎትም "ይህ የእኔም ጥያቄ ነበር " አለቻት። ሊባኖስም "ማርቆስ እኮ የሚያስቁት ነገሮች በጣም ጥቂት ናቸው እሱን ለማሳቅ የአለም ቀልደኛ ቢመጣ እንኳን አይስቅም ነገር ግን ሰውን በጭራሽ ፈገግ እንኳን በማያረገው ነገር ነብሱ እስኪወጣ ያስቀዋል " አለቻቸው።
በፀሎት እና ፅናት በጣም ገረማቸው። እብዱ ያቤፅም " እዚህ አለም ላይ ምንም ፈገግ ሚያስብል ነገር የለም ይህቺ አለም በጣም ታስጠላለች በህይወት መኖር ማለት በቃ ያስጠላል በተለይማ ሰዎች ሞተው እሬሳ ከሆኑ በኋላ "አለ። ሊባኖስም " አይ አስተሳሰብክ ልክ አደለም" አለች። የተረፈው ሶፋ ላይ ማለትም ከበፀሎት ፊት ለፊት ያለው ሶፋ ላይ ተመምጣ።
በፀሎትም በልቧ " እንዴ ቆይ እብዱ ምን እያለ ነው ከ አንደበቱ የሚወጡት ቃላቶች በጭራሽ ከእብድ የሚጠበቅ አደለም " አለች። ሊባኖስም በፀሎትን አተኩራ እያየቻት "ቆንጂት ወዴት ሄድሽ" አለቻት።
በፀሎትም "አለው አለው እየሰማዋቹ ነው" አለች። እብዱ ያቤፅም "ቆይ ለምንድነው አንቺ እና አንቺ ፊታችሁን በሻርፕ የጠመጠማችውት" አለ። በአንድ እጁ በፀሎት ጋር በሊላኛው እጁ ደሞ ፅናት ጋር እየጠቆመ። ማንም መልስ አልሰጠውም እብዱ ያቤፅም ንግግሩን ቀጠለ።
በፀሎት እና ፅናት ጋር የቀሰረውን እጅ አውርዶ ፅናት ላይ በቀሰረበት እጁ ሊባኖስ ጋር ቀስሮ "እሺ አንቺስ ለምን ልክ እንደ እነሱ ሻርፕ አልጠመጠምሽም?" አላት። አሁንም ማንም ሰው ምንም አልመለሰለትም እብዱ ያቤፅም "በቃ ተውታ ሁሌም ቢሆን ሰዎች እራሳቸውን ድብቅ አረገው ነው የሚኖሩት" አለ። በድንገት የውጩ በራቸው በመሳሪያ ተኩስ እና በኳኳታ ተቀወጠ ሁሉም መውጣት አሰፈራቸው።
እብዱ ያቤፅ ግን ካለበት ተነስቶ የሳሎኑን በር በርግዶ ወጣ። ከዛም ሊባኖስ እናንተ እዚሁ ቆዩ ብላ እብዱ ያቤፅን ተከትላው ወጣች።
የእነ ፅናት ቤት በሀይለኛ ተኩስ ታጅቧል። ፅናት ደነገጠች ወደ እህትዋ ሄዳ እህቷ እቅፍ ውስጥ ገባች።የጨነቀ እለት ነውና ነገሩ ባለ አንዱ ሶፋ ላይ ሁለቱም ተቃቅፈው ተቀመጡ። ፅናት ከ ደቂቃዎች በኋላ እየጨነቃት እና ጭንቅላትዋ ከአቅምዋ በላይ ሆነ።እኛም በደከመ አንደበትዋ "እህቴ አልቻልኩም በቃ አልቻልኩም" አለች። በፀሎትም ፍርሀት ያንቀጠቀጠውን ድምፅዋን እንደምንም አውጥታ። "ምነው እህቴ አመመሽ አንዴ?" አለቻት። በፀሎት ከፅናት መልስ አላገኘችም። በድጋሜ "እህቴ አለችና የፅናትን ፊት ፊቷ ላይ በጠመጠመችው ሻርፕ ስር ገብታ ነካችው። ፅናት በላብ ተጠምቃለች። በፀሎት ደነገጠች አሁንም "እህቴ" አለች። ፅናት ግን ዝምም ብላለች።
በፀሎት ጮክ ብላ "እህቴቴቴ" አለች። ማንም አልሰማትም። ውጪ ያለው ብጥብጥ እና ተኩስ እንደቀጠለ ነው። ከእዛም አልፎ አንፖላንስም መጥቶ ቀውጢ ሆኖዋል። በፀሎት ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ጉሮሮዋ እስኪዘጋ " እህቴቴ፤
ፅናቴቴቴ፣ የኔ ብሌን ፣ እባክሽ ንቂ" እያለች ሳለ የሳሎኑ በር ተበረገደ።
"ማነው ማነው" አለች። ሊባኖስ ነበረች። "እኔ ነኝ ተረጋጊ ምንድነው የተፈጠረው?" አለች። በፀሎትም "እህቴ እህቴ በድጋሜ እራስዋን ሳተች የዛሬው ግን ይለያል እንዲ ሆና አታውቅም "አለች።
ሊባኖስም "በቃ ተረጋጊ ምንም አትሆንም የኔ ሚጢጢ ጠንካራ ናት አሁን ጋሽ በሬሳ ጋር ይዣት እሄዳለው በቃ" ስትል። "እሺ " አለች። ሊባኖስም ስልኳን ከ ጠረጴዛው አንስታ ሹፌሩ ማርቆስን ጋሽ በሬንሳን ይዟቸው እንዲመጣ ነገረችው እና ፅናትን አቅፋ ወደ መኝታ ቤት ወሰደቻት። ከ ግማሽ ሰአት በኋላ ሹፌሩ ማርቆስ ጋሽ በሬን ይዟቸው መጣ። ጋሽ በሬሳም በሉ ማንም እንዳይገባ ብለው መኝታ ቤቱን ከቀረቀሩ በኋላ ለፅናት አንድ እምነ በረድ የሚመስመል ነገር በያዙት ትንሽዬ ሙቀጫ እና ዘነዘና አድቅቀው በትንሽዬ የአብጀዴ ክር አስረው አፈንጫዋ ላይ አረጉላት።
ፅናትም ብዙ ሳትቆይ ነቃች። አይኑዋን ስትገልጥ ጋሽ በሬሳ ወዲያ እና ወዲህ እየተንጎራደዱ ነበር። ፅናትም "ተመስገን አምላኬ እዛ ቤት አደለሁም" አለች። ጋሽ በሬሳም የፅናትን መንቃት አይተው አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጠው "እየውልሽ የኔ ልጅ የያዘሽን በሽታ በደንብ አርጌ አውቀዋለው ነገር ግን እኔ እራስሽን በሳትሽ ቁጥር እየመጣው ባነቃሽም በጣም ትልቅ ህመም ይይዝሻል ህመምሽ ሲነሳብሽ ደሞ የግድ ጨለማ ክፍል መቀመጥ ነው ያለብሽ ለእዚህ ህመም መዳህኒት ባይኖረውም የስቃይሽን ጊዜ ማለትም የህመምሽን የመጨረሻ ጊዜ ለማራዘም መድሀኒት አለ። እሱ መድሀኒት ደሞ የዘመናዊ ሀኪሞች ጋር ታገኚዋለሽ ህመምሽ ከባድ ነው ግን ቻይው ያልፋል እየውልሽ ዶክተሮች ጋር ሄደሽ ታይው ሁለት ምርጫ ይሰጡሻል አንደኛው በቀዶ ጥገና ሊላኛው ደሞ በራሱ ጊዜ ነው ሚለቀው የቀዶ ጥገናው ከባድ ነው ልጄ እንዳመረጭው" አሉዋት።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 30..🥀
.
.
እብዱ ያቤፅን ሁሉም ሰው በግርምት እና በድንጋጤ ማየት ጀምሯል ማንም ሳይጠጋዉ ማንም ሳያስቆመው እራሱን በእራሱ ዝም አስብሎ ከፅናት እግር ስር ሳይነሳ ድምፁን ለስለስ አድርጎ። "ብዙ ሳቅን የሚቀሙ ሰዎች አሉ። መንገድ አትክፈችላቸው ሳቅ የተፈጥሮ ህግ ነው ፣ሳቅ የፈጣሪ ህግ ነው ፣የሰው ህግ አደለም። የሰይጣን ህግ ቢሆን ኖሮ ሰዎች አይቃወሙም ነበር።" አለ። ፅናት ምንም ማለት አልቻለም በውስጧ ምታስባቸው ነገሮች ግራ አጋብተዋታል። እብዱ ያቤፅም " ምነው ምነው ዝም አልሽ ፊትሽ ተሸፍኗል ስሜትሽን ማወቅ አልቻልኩም አንቺ እኔን ታይኛለሽ እኔ ግን በትንሹ አይንሽን ብቻ ነው ማየት የቻልኩት በአይኖችሽ ውስጥ ድንጋጤ ይታያል። ለምን ደነገጥሽ?" አላት። መልሱን ከአይኗቿ እየፈለገ።
ፅናትም በሚንቀጠቀጥ ድምፅ "እእእእ አአአንተ"ብላ ፀጥ አለች። ከዛም እብዱ ያቤፅ" ምነው ምንድን ነው ለማለት የፈለግሽውን ለምን ተውሽው" አላት። ድምፁን በጣምም ለስለስ አርጎ። ማስተዛዘን እና ምፀና ባጀበው ድምፅ ፅናትም "በቃ አሁን ቤቴ መሄድ አለብኝ " አለች። እብዱ ያቤፅም ከ ፅናት ስር ተነስቶ ቆመ።
ከዛ ፅናት በፍጥነት ተነስታ መራመድ ጀመረች። ልክ ቤተ እምነቱ በር ላይ ስትደርስ ተሳልማ ወጣች። እብዱ ያቤፅም ፅናትን ከኋላዋ መከተል ጀመር።
ፅናት የሆነ ሰአት ላይ ኮቴው ሲጠፋ ዞር ስትል እብዱ ያቤፅ በአከባቢው የለም። በውስጧ " የት ሄዶ ነው " አለች። ግራ እየተጋባች ባለፈው እብዱ ያቤፅን ያገኘችበት መታጠፌያ ላይ ስትደርስ እብዱ ያቤፅ ትልቅ ድንጋይ ተሸክሞ ተንበርክኳል። ፅናት ግራ ገባት። ሳታስበው ድምፃዋን ከፍ አድርጋ " ምን እየሆነ ነው ደሞ በየት ቀደመኝ" አለች። ከዛም ወደ እሱ እየተጠጋች ስትመጣ እብዱ ያቤፅም በእንብርክኩ ወደ ፅናት እየተጠጋ መጣ። ፅናት እርምጃዋን ፡ገታች። እብዱ ያቤፅም ተጠጋት ልክ እርስዋ የቆመችበት ጋር ሲደርስ " ይቅርታ ይቅርታ አድርጊልኝ እባክሽ" አላት። ፅናትም ድንጋዩን እየተንቀጠቀች ልታነሳለት ስትል የድንጋዩ ክብደት ከመንቀጥቀጧ ጋር ተደማሮ ያንን ከባድ ድንጋይ እብዱ ያቤፅ ላይ ጣለችበት። ፅናት በድንጋጤ ደርቃ ቀረች። እብዱ ያቤፅም እራሱን ስቶ ወደቀ።
ፅናትም ስትደነግጥ እና ድንጋጤዎችን ከአቅምዋ በላይ ሲሆን ማስተናገድ ስለማችል እርስዋም እራስዋን ስታ ወደቀች። እብዱ ያቤፅ እና ፅናት እራሳቸውን አያውቁም። በወደቁበት አከባቢ እንኳንስ በምድር የሚጉዋዝ
በሰማይ የሚበር በራሪ አእዋፍም የለም።
ከእብዱ ያቤፅ እና ከፅናት በስተቀር።
ፅናት ወደ እራስዋ ስትመለስ ግን እራስዋን ያገኘችው ባለፈው እሷ እና እህቷ በፀሎት ለመታከም ገብተውበት የነበረበት ያ በግዙፉ ግቢ ውስጥ ያለው ትንሽዬ ቤት ፅናት እና እህቷ ተሳቀው ምሽቱን ያሳለፉበት ፤ትንሽዬ ቤት ውስጥ ናቸው። እዛ የሚገረም ነገሮችን ያየችበት ቤት ውስጥ ናት። ፅናት ደንግጣለች። አንገቷን እንደምንም ብላ አዙራ ወደ አንደኛው አልጋ አይኑዋን ወረወረችው የጠበቀችውን ነገር ነው ያየችው በአሁኑ ሰአት በእህቷ ቦታ እብዱ ያቤፅ በሆዱ ተኝቶ ነበር። ፅናት ብድግ ብላ ወደ እብዱ ያቤፅ ሄደች። የፊቷን ሻርፕ እብዱ ያቤፅ ጭንቅላት ላይ አስረውለታል። ፅናት እጅዋን ወደ እብዱ ያቤፅ ጭንቅላት ላከችውና በቀስታ ጭንቅላቱን መዳበስ ጀመረች።
እብዱ ያቤፅም የፅናት ውብ ጣቶች ሲነኩት ሰውነቱን ሲነዝረው፤ ልቡም ሲመታ ፤ አይኖቹም በሀይለኛው ሲጨፈኑ ይሰማዋል የፅናትን ጠረን ያውቀዋል ምን አልባትም በአለም ላይ ከሚወዳቸው ጠረኖች አንዱ የፅናት ጠረን ይሆናል። እብዱ ያቤፅ በፅናት እጆች በፅናት የጣት እንቅስቃሴዎች ተማርኳል። "በህይወታችን ተሰምቶን የማያውቀው ስሜት ሲሰማን አንድን ሰው ስንነካው ብቻ ስላም ሲሰማን፤ ሊላ የሰላም አለም ውስጥ የሆንን ያክል ሲሰማን እና ከሚሰማን ስሜት መራቅ ሳንፈልግ ስንቀር ይህ ስሜት ምን ሊባል ይችላል? ለእዚህ ስሜት ቤካን የሚለው ቃል ትክክለኛ መገለጫው ነው።" አለች ፅናት በስሱ የእብዱ ያቤፅን ጭንቅላት እየዳበሰች። እብዱ ያቤፅም ልክ እንዳልሰማ ሆኖ የፅናትን የጣቶቿን ጨዋታ አይኑን እንደጨፈነ ማጣጣም ቀጠለ። በመሀል ግን ፅናት ጣቶቿን ከጭንቅላቱ ላይ አንስታ "ይቅርታ" ብላ ወደ አልጋዋ ተመልሳ ወጣች። አልጋዋ ላይ ሆና "ማነው እዚህ ያመጣን እሺ ሊቦ ልትሆን ትችላለች ምን አልባት" አለች።
በሩ ተከፈተ ጋሽ በሬሳ ነበሩ ፅናት ጋሽ በሬሳን ለመጨረሻ ጊዜ ካየቻቸው ቆየች። ጋሽ በሬሳ ማለት ለፅናት እና ለበፀሎት ብቸኛ መላካቸው ናቸው።
ተነስታ ብታቅፋቻው ደስ ይላት ነበር። ግን አትችልም ምክንያቱን ባታውቀውም በጣም አርጋ እየወደደቻቸው የምትፈራቸው ሰው መካከል እሳቸውን እና ሊባኖስ ናቸው።
ጋሽ በሬሳ ፅናትን " እንዴት ነሽ ልጄ" አሉዋት። ፅናትም እየተርበተበተች "ደና ደና ነኝ" አለች። እሳቸውም "ጥሩ " አሉና ወደ እብዱ ያቤፅ ተጠግተው እብዱ ያቤፅን በጀረባው ገለበጡት። ጋሽ በሬሳን ላዩዋቸው እንኳንስ ሰው እንዲ በቀላሉ የሚገለብጡ ብርጭቆ እንኳን አንስተው ለመጠጣት የሚቸግራቸው ያክል የጃጁ ነበር የሚመስሉት።
ጋሽ በሬሳም የእብዱ ያቤፅን ሁለት እጆች ተጠቅመው ቀና አርገው እንዲቀመጥ አረጉት። "እንዴት ነህ ጎረምሳው " አሉት። እብዱ ያቤፅም "በደና በመሆን እና ባለመሆን ውስጥ እየዋኘው ነው" አላቸው። ጋሽ በሬሳም ተጠንቅቀህ ዋኝ ዋና ሲበዛ ያዳክማል ከምንም በላይ ደሞ ልብን ያደክማል ከዛም እራስህን ስትስት ትሰምጣለክ ወይ ደና መሆንን ወይ ደና አለመሆንን መርጠክ ዋኝ። እንደእኔ ግን ደና ባለመሆን ውስጥ ብትዋኝ ባይ ነኝ ምክንያቱም ደና አለመሆን ጤነኝነት ነው" ብለውት ሄዱ።ፅናት ጋሽ በሬሳ ከወጡ በኋላ "ቆይ ምን ማለታቸው ነው? ወይ ፈጣሪ ምን አይነት ውስብስብ ሰው ናቸው እሳቸውስ የሚሰሩት ሰውን ደና ለማድረግ አደል እንዴ" አለች።ፊትዋን ወደ ግድግዳው እንዳዞረች። እብዱ ያቤፅም
"ልክ ናቸው፤ያሉት ልክ ነው፤ደና አለመሆን ደና ወደመሆን እንድንጓዝ ያረገናል ደና መሆን እና ደና አለመሆንን ብዙ ሰዎች ልክ ከመሆን እና ልክ ካለመሆን ጋር ያገናኑታል በጭራሽ አይገናኑም" አለ። እብዱ ያቤፅ እጁን እያወናጨፈ። ፅናት ግራ ተጋብታ ዝም ከማለት ውጪ ምንም ማለት አልቻለችም። ያሉበት ቤት በር ተከፈተ ሊባኖስ ነበረች። ፅናት ልክ የሊባኖስን "እንዴት ቆያቹ" የሚል የሰላምታ ድምፅ ሰትሰማ "ሊቦዬ" ብላ ከተኛችበት ተስፈንጥራ ተነስታ አቀፈቻት እና ሊባኖስ በእጅዋ የያዘችውን ሻርፕ ተቀብላ ፊቷ ላይ ጠመጠመችው።
ሊባኖስም "በሉ ተነሱ ወደ ቤት እንሄድ " አለች። ፅናትም ወደ ሊባኖስ ጆሮ ጠጋ ብላ እሱም እኛ ቤት ይመጣል?" አለቻት።ሊባኖስም " አዎ አብሮን ይሄዳል እንከባከበዋለን" አለች። ፅናት ደስ አላት።ከዛም ወደ ቤታቸው ከ እብዱ ጋር ሄዱ። ልክ ቤት ሲደርሱ በፀሎት በር ላይ ቆማ አገኝዋት። ፅናት መኪና ውስጥ ሆና ነበር እህቷን ያየቻት። ፅናት ልክ እህቷን ስታያት ከተቀመጠችበት ጋቢና ወንበር ልትወረድ ምንም አልቀራትም።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 29..🥀
.
.
.
ከሳምንት በኋላ ፅናት ጠዋት ተነስታ ቤተክርስቲያን ልትሳለም የቤታቸውን በር ከፍታ ወጣችና የውጩንም በር ስትከፍት እብዱ በራቸው ጥግ ላይ ጥቅልል ብሎ ተኝቶ አገኘችው። ፅናት በጣም ደነገጠች ጠጋ ብላ በፍርሀት ውስጥ እጇ እየተንቀጠቀጠ ትከሻውን ነካ ነካ አደረገችው። እብዱ ያቤፅ ግን አልተነሳም። ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበር። ፅናት በድጋሚ ሀይሉዋን ጨምራ ነካ ነካ አደረገችው አሁን ተነሳ ፤ አሁን ነቃ፤ አሁን የፅናት መቀስቀስ ሰራ ቀና ብሎ አያት። ፊቷ ላይ ሻረፕ ጠምጥማለች ልክ ከእዚህ በፊትም እብዱ ያቤፅ ፅናትን በሻርፕ ውስጥ እንጂ ያለ ሻርፕ አያውቃትም። ግን ባለፈው ሲጠጋት ያላት ጠረን ገና አይኑን ሳይገልፅ እሷነቷን አሳውቆታል። ብድግ ብሎ እንደመደንገጥ እያደረገው "ሰሰሰላም" አላት። ፅናትም " ሰላም" አለችው። እብዱ ያቤፅም በድንጋጤ ባኖ ከዛም ደሞ ከተቀመጠበት መሬት ተነስቶ ቆመ።ፅናት ውስጧ ብዙ አሰበ "እብድ እንዴት ሰላም አጥቶ ሰላምታ ይጠይቃል?" የሚለው ግን ከ ጥያቄዎቿ አንዱ እና ዋነኛው ነው።
እብዱ ያቤፅም " ቆሞ በዝምታ ፅናትን ካያት በኋላ በፍጥነት ተራምዶዋት ሊሄድ ሲል ፅናት ሳታስበው "ቆይ አትሂድ"
የሚል ድምፅ አወጣች። እብዱ ያቤፅም
እርምጃውን ገታ አድርጎ ቆመ ፅናትም
መዳፎቿን እያፋተገች እና እየተርበተበተች " ፍቃደኛ ከሆንክ እና ካላስቸገረኩክ እባክክ ቤተ ክርስቲያን አብረን እንሂድ " አለችው። እብዱ ያቤፅም " እሺ " ነይ አላት። ከዛም ጎን ለጎን ሆነው አንድም ትንፋሽ ሳያወጡ እና ሁለቱም በተራ በተራ እየተነፈሱ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ደረሱ።
ፅናት ቤተ እምነት ለመግባት ያሉትን መስፈርቶች አሙዋልታ ገባች። እብዱ ያቤፅ ግን " ልክ እንደ ጎደኛው ወይም የራሱ ቤት ሰተትትት ብሎ ገባ።
ፅናትም " ሆ አሁን እብድነቱን ማወቂያ ምክንያት ያገኘው መሰለኝ" ብላ። ተከተለችው።
እብዱ ያቤፅም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከተደረደሩት ሳፋ መሰል በምነ በረድ ከተሰሩት የምእመናን መቀመጫ ላይ ተቀመጠ ፅናትም ከጎኑ ተቀመጠች
እብዱ ያቤፅ ወደ ሰማይ አንጋጦ ብዙ ደቂቃዎችን አስቆጥሮ ከዛም ደሞ አንገቱን አቀረቀረ። ዛሬ ዲያቆን ዘረሀ ያቆብ ናቸው ትምህርት የሚሰጡት እኚህን ሰውዬ ፅናት አጥብቃ እንደ ነብሷ ትወዳቸዋለች። በመንፈሳዊው አለም እሳቸውን በአለማዊው ደሞ ደራሲ መሀመድ ሳላዲንን ትወዳቸዋለች። የሚናገሩትን ቃላቶች ስሰማቸው በደረቅ ጉሮሮ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ሲገባ ፍጥረትን የሚያረካውን ያክል ያረካታል።
ዲያቆን ዘርሀ ያቆብ ዛሬ የህይወትን ብልሀት እያስተማሩ ነው። ታዲያ ለምእመናን ( የታዳሚው) አንድ ምሳሌ እንዳላቸው በመናገር ምሳሌያቸውን እንዲ ብለው መናገር ጀመሩ። ድምፃቸው እጅግ በጣም ይማርካል እና ከማይኩ እና ከወኔያቸው ጋር ተደምሮ ድባቡ ይስባል። " ከቀናት በአንዱ ቀን አንዱ የቀዬ ባለሀብት ትልቁ እና ለማየት ከሚደክመው እርሻው ላይ ወቅቱን ያገናዘቡ የተለያዩ ምርቶችን ዘራ።እናም እናትህ በጠና ታማለች በነብስ ድረስላት ተብሎ መልክተኛ ተላከበት። እሱም እርሻውን ለቀጠረው እረኛ አደራውን ከእምነት ጋር ጥሎ ወደ እናቱ ሄደ። እናቱን ሲያስታምም ከቆየ ሰንበት አለ። እናቱም አገገሙ ባለ ቀየውም እርሻዬን ልየው ብሎ ወደ ግዛቱ ተመለሰ። ታዲያ ወደ ግዛቱ ሲመለስ እረኛው የለም። እናም ደሞ የዘራበት መሬት በእሾ ተከቧል። የዘራቸው ዘሮችም የሉም። ይህ ሰው ግራ ተጋባ። ወደ መሬቱ ጠጋ አለ። መሬቱ ሙሉ በእሾህ ተሞልቷል። ሰውየው አነባ "ምን ልበላ ነው ምንስ ሽጬ ለእናቴ ላረግላት ነው?" አለ። ግራም ተጋባ ይህ ሰው ለማሰብ ከፍ ያለ ቦታ ላይ መሆን ምርጫው ነውና ከእርሻው አጠገብ ካለው ግዙፍ ዛፍ ላይ ወጣ።
ከዛፉ ላይ ሆኖ እርሻውን ሲያየው ከእሾኮቹ መሀል የተከላቸውን እህሎች ተመለከታቸው። ከቆይታ በኋላ እረኛው መጣ። ለምንድነው እኚ እሾኮች በእህሉ መሀከል የበቀሉት አለው። እረኛውም እሾኮቹን ከእህሉ ጋር የተከላቸው እሱ እንደሆነ ነገረው ሰውየው በንዴት እየተንቦገቦገ ለምን እንዲ እንዳረገው ጠየቀው እረኛውም እንዲ አለው። "እኚህ እሾኮች ዘሮቹ ለመታጨድ ከመድረሳቸው በፊት ረግፈው ያልቃሉ ከዛም አፈር ከነካቸው በኋላ በቶሎ ይበሰብሳሉ ይህንን ያረኩት አንድም ሌቦች እንዳይሰረቁ እና ሰርቀውም ሀጢያት እንዳይገቡ ሲሆን ሊላው ደሞ አንተ የለፋክበትን ሊላው ሰው ሳይሆን እራስክ እንድትጠቀም ነው" አለው። ሰውየው በእረኛው ጥበብ ተደመመ እና አመስግኖት ለእረኛው ከዘራቸው ዘሮች እሩብ እንደሚሰጠው ነገረው። ገበሬውም "እኔ ካንተ ደስታክን እንጂ ላብክን ወይም ጉልበትክን አልሻም ከእዚ ቀደም ሰዎች የዘራውትን ፍሬ ሰረቁኝ ስትል ስለሰማው ነው።ብሎ መለሰለት። " አሉ ዲያቆን ዘርሀ ያቆብ።
ፅናትም በልቧ "ልክ እንደ እረኛው የሰውን ፈገግታ ብቻ አስቦ የሚለፉ ሰዎችን አምላክ ይባረካቸው" አለች። እና ጮክ ብላ "አሜን" አለች። እብዱ ያቤፅም ተከትሎዋት "አቤትትትት" አለ። ፅናትም ግራ ተጋብታ "እእ" አለችው። እብዱ ያቤፅም "ምነው "አቤትትት ስትይ አቤትትት አልኩኝ" ሲላት። ፅናት "ኧረ እኔ አሜንን ነው ያለኩት" ብላ ሳቀች። ምእመናኑ ፅናትን እየዞረ ማየት ጀመረ። ደንግጣ ሳቋን አቋረጠች። እብዱ ያቤፅም " ምነው ለምን መሳቅሽን አቋረጥሽ ሳቂ እንጂ እነዚህን ፈርተሽ ነው ወይስ ፈጣሪን ፈጣሪ ቤቴ መታቹ አልቅሱ ብቻ አላለም" እብዱ ያቤፅ ድምፁ ለጉድ ይጮካል ይባስ ብሎ ከመቀመጫውም ተነስቶ ፅናትን እያየ ሰዎችን በአይኑ እየገላመጠ
" ሳቂ እነሱን ተያቸው አምላክ ለምን ሳቅሽ ብሎ አይቆጣም እባክሽ ሳቂ በደንብ ሳቂ አምላክ ለምን ሳቃቹ አይልም ከጠየቀሽም እኔ አስቂያት ነው እለዋለው" እያለ መጮኩን ቀጠለ ፅናት በተቀመጠችበት ደርቃ ቀረች። እብዱ ያቤፅም ንግግሩን ቀጠለ። ሰዎች እሱን መጠጋት ፈሩ። ይህንን ያየው ያቤፅ " እ ኑ ኑዋ አብዶል ብላቹ ፀበል ውሰዱኝ ፈራቹ " አለና ፅናት እግር ስር ተቀምጦ ሳቂና ሳቅ የሚያስከፍል ከሆነ እኔ እከፈልልሻለው ሳቂና ሳቅ የሚያስቀጣ ከሆነ እኔ እቀጣልሻለው " እያለ መጮ ቀጠለ። እብዱ ያቤፅን ማንም አልተጠጋውም።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 28..🥀
.
.
.
የውጩ በር ሲከፈት ተስማቸው። በፀሎት "ውይ ሊቦቲዬ መጣች" አለች።ፅናትም "ውይ እድሜዋ እረጅም" ነው። አለች በቀጣይ የሳሎኑ በር ተከፈተ ሊባኖስ ብቻዋን አልነበረም የመጣችው። የመጣችው ከብዙ ሚስጥሮች ባለቤት እና የእብዱ እናት ከሆነችው የባለ ሀብቱ የልጁ እናት ከሆነችው ባለ ሱቋ ጋር ነበር።
ፅናት ባየችው በፀሎት ባላየችው ነገር ግራ ተገብተዋል። ሊባኖስም " ነይ ነይ ቁጭ በይ" አለቻት። ባለ ሱቋም ልክ እንደ ቤቷ ፈጠን ቀልጠፈ ብላ እግሮቿን ሶፋው ላይ አጣምራ ሰቅላ ቁጭ አለች። ፅናት በባለሱቋ ሁኔታ ተገርማ የበላችበትን ሰሀን አንስታ ወደ ኩሽና ሄደች። በፀሎት እየሆነ ያለውን ነገር ባለ መረዳትዋ ግራ እየገባት። "ሊቦቲዬ እንግዳ አለን እንዴ" አለቻት።
ሊባኖስም " አዎ ዛሬ ከባድ እንግዳ ነው ያለን በህይወታችን ካሉ ጭንቀቶች መሀል አንደኛውን የሚፈታልን ሰው ነው ይዤ የመጣውት" አለች። ፅናት ሰሀኑን አስቀምጣ መጣችና ከ እህቷ ጎን ተቀመጠች። ሊባኖስ ብቸኛው ሶፋ ላይ ተቀምጣ። "እየውላቹ እሷ ማለት ባለፈው የነገርኳቹ ባለ ሱቋ ናት። በእብዱ ልጅ በኩል የሚያስጨነቀንን ጥያቄ ትመልስልናለች። ሶስና ትባላለች የልጇ ስም ያቤፅ ነው። አሁን በቃ እድሉን ለእሷ እሰጣታለሁ" ብላ ዝም አለች።
ሶስናም ስለ ልጇ መናገር ጀመረች። ፈገግ ብላ "ልጄ ያቤፅ በትምህርቱ እጅግ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው እሱ እብድ አደለም፤ ግን እብድ ነው ፤እሱ ሰው ይገላል፤ ግን አይገልም አለች። ሶስቱም ይህ አባባልዋ ግራ ገባቸውና ይበልጥ እንድታብራራላቸው በጉጉት ጆሮአቸውን አዘጋጁ።
ሶስና "ማለት የፈለኩት ግልጽ አደለም?" አለች። ፅናትም "ገና ምን አልሽንና ይልቅ ስለ ልጅሽ ሁሉንም ነገር ንገሪን" አለቻት። ሶስናም "እኔ ማለት የፈለኩት ሁሉ ግልፅ ነው። ያው ልጄ ሰው ነው ብሎ የሚያስበው አይነት ሰው ሳይሆን በተቃራኒው ነው።" አለቻት። ሊባኖስም "እና ሰዎች ለልጅሽ የሰጡት ስም አሉባልታ ከሆነ ሰዎችስ ከየት አመጡት" አለቻት። በእዚህ ሰአት በፀሎት "እባክሽ በደንብ ንገሪን ስለ ልጅሽ ያቤፅ እኛ የቻልነውን አረገን እንረዳዋለን " አለቻት። ፅናት በውስጧ " ግራ ያጋባል ቆይ ምን ጉድ ነው ሴትየዋ ምታወራው" አለች። ሶስና ይበልጥ ተመቻችታ እየተቀመች " አሁን ልላቹ የሚገባኝ ነገር ልጄን በጭራሽ መፍራት እንደሊለባቹ እና አቅርባቹ የውስጡን ሀሳብ እንድትረዱት ነው ነገር ግን ይህንን ጭራሽ አባትየው እንዳያውቅ ተጠንቀቁ" አለቻቸው አይኖቿን ጭፍን አድርጋ። ሊባኖስም "አታስቢ ይህ ጥያቄ የመጣው ከእሱ ነው ስለዚህ ሀሳብ አይግባሽ" ስትላት። ሶስና ተመቻችታ የተቀመጥችበት ሶፋ በድንገት አንዳች እሾህ አብቅሎ የወጋት ይመስል ብድግ አለችና የሳሎኑን በር በፍጥነት ከፍታ ወጥታ ሄደች። ማንም ሰው አልተከተላትም።
ዝም ብለው ቁጭ ባሉበት ፅናት " እኔ ይህንን ልጅ መርዳት እፈልጋለሁ " አለች። በፀሎት " አይ እህቴ አይሆንም እሱ በጣም ብዙ ዋጋ ነው የሚያስከፍልሽ ስለ እዚህ ቢቀርብሽ ባይ ነኝ" አለቻት። ፅናትም ወደ ሊባኖስ አይኖቿን ወርውራ " እሺ ልቦዬ አንቺስ ምን ትያለሽ" አለቻት።ሊባኖስም እረጅም ትንፍሽ ካወጣች በኋላ " እንረዳዋለን " አለች። ፅናትም በደስታ ከተቀመጠችበት ወደ ሊባኖስ ሄዳ ሊባኖስን አቅፋ ሳመቻት በፀሎትም " እንዴ ግን እህቴን አንድ ነገር ቢያረጋትስ" አለች። ሊባኖስም "አታስቢ ምንም የሚፈጠር ነገር የለም" አለች።
ፅናትም " አዎ ሊቦዬ ልክ ናት አምላክ ይረዳናል በቃ መጣው እሺ የኔ ውዶች " ብላ ከሊባኖስ እቅፍ ወጣች። በፀሎትም " እንዴ የት ልትሄጂ ነው ቆይ ሁለታችሁም የሆነ ነገር ካወራን በኋላ መጣው ብሎ መውጣት ጀምራችኋል" አለች። ብስጭትጭት እያለች። " ፅናትም አታስቢ እህቴ እኔ ከጓደኛዬ ጋር ተቀጣጥሬ ነበር አንድ የምንሰራው ነገር አለ ቶሎ እመለሳለሁ።" ብላ ወጣች።
ከ ግማሽ ሰአት በኋላ ፅናት ስትታከምበት የነበረበት ሆስፒታል ውስጥ ከዶክተር ዳመነ ጋር ለማውራት የቢሮውን በር አንኳኩታ ገባች። ዶክተር ዳመነም በተለመደ ፈጣን አነጋገሩ "እንኳን ደና መጣሽ ፅናት እንደውም ጥሩ ዜና ስላንቺ ሰምቼ የቀጠሮቻንን ሰአት በጉጉት ስጠብቅ ነበር ቀድመሽ ስለመጣሽ ደስ ብሎኛል ቁጭ በይ ቁጭ በይ" አላት። ፅናትም " ደናነኝ ምን ነበር ማለቴ ለምን ነበር የፈለከኝ" አለች። ዶክተሩም ፈገግ እያለ። " በሽታሽ ትንሽ ምልክት በሚያሳይበት ወቅት አንድ የሚወሰድ መዳኒት እሰጥሻለሁ ከዛም እሱ አንዱ ብልቃጥ ለ 6 ወር ያገለግልሻል። ከስድስት ወር በኋላ ደሞ ለ4 ወራት የሚያገለግል መርፌ ትወጊያለሽ ይህ ማለት ደሞ ያለ መዳኒት 1 አመት በመዳኒት ደሞ 10 ወር ትቆያለች ማለት ነው። ከዛ በላይ ግን ምንም ላረግልሽ አልችልም" አላት። ፅናት በደስታ ፊትለፊቷ ቆሞ የሚያወራውን ዶክተር ዳመነን አቀፈችው።ከዛም "እኔ ምፈልገው ይህንን ነው በቃ ላስብኩት ነገር አመት ከ 10 ወር በቂዬ ነው። " አለች።ዶክተሩም " እሺ ጥሩ ደስ ስላለሽ ደስ ብሎኛል ያስብሽውን ፈጣሪ በጥበቡ ያሳካልሽ ብሎ እቅፉ ውስጥ ያለችውን ፅናት አቅፎት ቆየ። ተቃቅፈው ብዙ ከቆዩ በኋላ በሩ ተከፈተ ዶክተር ይስሀቅ ነበር። ፅናት ዞር ብላ አየችውና ከዶክተር ዳመነ እቅፈ ወጥታ ዶክተር ይስሀቅ እቅፉ ውስጥ ገብታ እያለቀሰች "ለእኔ አመት ከ አስር ወር ያሰብኩትን ለማሳካት በቂዬ ነው" አለች።
ዶክተር ይስሀቅ የፅናት በድንገት እቅፉ ውስጥ መግባትዋ ቢያስደነገጠውም እሱም ልክ እንደ ዶክተር ዳመነ አቅፎአት " መልካሙን ዜና ሰምተሻል ማለት ነው" ብሎ ፈገግ አለ።ፅናትም ከ እቅፉ ሳትወጣ "አዎ በትክክል " አለችና ከእቅፉ ወጥታ የሁለቱን ዶክተሮች እጅ ጥብቅ አድርጋ ይዛ አመሰግናለሁ። አለችና እጃቸው ደሞ ለቃ ወንበሩ ላይ ተቀምጣ እራስዋን ካረጋጋች በኋላ "በድጋሜ አመሰግናለሁ" ብላ ወጥታ ወደ ቤቷ ሄደች።
ቤቷ ስትደርስ ሊባኖስ ቡና እያፈላች በፀሎት ደሞ የቡና ቁርስ ቆሎ እየበላች ለስለስ ያለ መዝሙር ተከፍቶ ቤቱ በእጣን ታውዶ ጠበቃት። ልክ በሩን ከፍታ "ሰላም የኔ ውዶች። ብላ ገባች።
በፀሎትም "ተመስገን አምላኬ አንቺ ብቻ ነው የመጣሽው" አለች። ፅናትም
" አይይ እህቴ ቆይ ሊቦ አንዴ መጣው ብላ በድንገት ተነስታ ሶስናን ይዛ መጣችና እኔም አንዴ መጣው ብዬ ሊላ ሰው ይዤ እመጣለው ማለት ነው?" አለችና ጫማዋን አውልቃ ገብታ ሁለቱንም ሳመቻቸው ። ሊባኖስም "ምንድነው የኔ ሚጢጢ ድምፅሽ በእንባ የተዘጋ ነው የሚመስለው " አለች። በፀሎትም " አዎ ችግር አለ የኔ ውድ " አለቻት። ፅናትም "አይ አይ ደና ነኝ እኮ ጉንፋን ሊይዘኝ ነው መሰለኝ" አለችና ሻርፕዋን ስታወልቀው በእንባ ያበጡ አይኖቾን ሊባኖስ አየቻቸው። ከዛም በምልክት እጆቿን እያወራጨች "ምንድነው?" አለቻት። ፅናትም አንገቷን ወዲያ እና ወዲህ በማረግ "ምንም" አለች። ከዛ ቡናቸውን ጠጥተው እራታቸውን በልተው ከጨረሱ በኋላ። ሊባኖስ ወደ ቤቷ ሄደች። ፅናት እና በፀሎትም እስከበር ሊባኖስን ከሸኗት በኋላ ወደ ቤታቸው ገብተው ተኙ።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 27..🥀
.
.
ፅናት ከድንጋጤዋ የተነሳ ምንም ማለት አልቻለችም ደርቃ ፈዛ ብቻ ነው የቀረችው። የእብዱ የጭንቅላት ፀጉር እንዲሁም ደሞ ፊቱ ላይ ቹፍ ያለው ፂሙ ፊቱ እንዳይታይ አረርጎታል። እብዱ ማውራት ጀመረ። ድምፁ ፍፁም እርጋታን የተላበሰ እና ማራኪ ነበር ልክ እንደ ድሮ ጋዜጠኛ "ተረጋጊ ምንም አላረግሽም አብረሽኝ ልትቀመጪ ትችያለሽ እባክሽ " ብሎ እጇን እየጎተተ አልፈው ወደሄዱት መታጠፊያ ቦታ ይዟት ተመለሰ የመጀመሪያ መታጠፊያ ቦታ እንደደረሱ የሚታየው የድድ ማስጫ ድንጋይ ወዳለበት እጇን እየጎተተ ወሰዳት።
ፅናት አንድም ትንፋሽ አላወጣችም ከድንጋዩ ፊት ለፊት ከቆመ በኋላ ከላይ የለበሰውን ቁሽሽ ያለ ሹራብ አውልቆ ለ4 አጣጠፈና ድንጋዩ ላይ አርጎ ካመቻቸ በኋላ "ነይ ተቀመጭ አላት" ፅናት ነገሩ ሁሉ አልገባ ቢላት ህልም ነው ወይስ ቅዠት አለች በውስጧ እብዱ አንገቱን አቀርቅሮ ወደ አመቻቸላት መቀመጫ እየጠቆማት "ቁጭ በይ ቁጭ በይ እንጂ" አላት። ፅናት በፍርሀት መንፈስ ውስጥ ሆና በዝግታ ሄዳ ተቀመጠች።
እብዱም እግሯ ስር ተቀምጦ እጁን ታፋዋ ላይ አስደግፎ በሀሳብ ጭልጥ አለ። ፅናት ግራ ገባት እብዱ እያለቀሰ ነው። ፅናት ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ተመላለሱ "ለምን ጠራኝ? ለምንድነው የሚያለቅስው? ለምንድነው ወደዚህ ይዞኝ የመጣው? ለምንስ ነው በጣምምም የተረጋጋ እብድ የሆነው እንዴትስ አንድ እብድ ሹራብን አውልቆ ለእኔ የተመቻቸ መቀመጫ ሰራልኝ" የሚሉ ጥያቄዎች ውስጧ አሉ። እብዱ የፅናትን አይን ፍዝዝ ብሎ ያያት ጀመረ። የፅናት አይን ከእብዱ ጋር ተገጣጠሙ ፅናት ልቧ ሲመታ ታወቃት የእብዱ እንባ ለጉድ ይዘንባል።
ፅናት ሳታስበው ነበር እጆቿ የእብዱ እንባ ከሚረግፍበት ጉንጭ ላይ ያገኘችው ደንግጣ እጇን በፍጥነት ልታነሳው ስትል እብዱ በእጁ ያዝ አደረጋት ፅናት ልቧ በጣም ይመታል እብዱም ከ አይኖቹ እንባ ለጉድ ይጎርፋል። ፅናትም ሳታስበው አይኖቿ በእንባ ተሞሉ ለምን ብትባል መልስ የላትም ግን እያነባች ነው። ፅናት ብድግ አለችና ወደ ኋላ መራመድ ጀመረች። ልክ የመንገዱ ቅያስ ጋር ስትደረስ ፊቷን አዙራ በፍጥነት መራመድ ጀመረች። ፅናት የእሩጫ ታናሽ ወንድምን እርምጃ እየተራመደች ቤቷ በር ላይ ደረሰች እጇ እየተንቀጠቀጠ ከቦርሳዋ የውጭ በር ቁልፍ አውጥታ ከፍታ ገባች። ሊባኖስ እና በፀሎት የሙዚቃ ግብዣዎች የሚለውን ፕሮግራም በሬዲዮ እየሰሙ ነበር።
የሳሎኑን በር በርግዳ ስትገባ ሊባኖስ እና በፀሎት ደነገጡ "ምንድነው ነገሩ ማነው?" አለች ደንግጣ ሊባኖስም በፍጥነት ወደ ፅናት ሄደች ፅናት ሊባኖስን አቅፋ ማልቀስ ጀመረች። ሊባኖስ እና በፀሎት ግራ ተጋቡ። እና በእኩል ድምፅ "ምን ተፈጥሮ ነው?" አሉ። ፅናትም ከሊባኖስ እቅፍ ወጥታ እህቷ አጠገብ ተቀመጠች ሊባኖስም ፊት ለፊት ካለው ሶፋ ላይ ተቀመጠች። ሁለቱም ፅናት ለምን እንዲ እንደሆነች ማወቅ ፈልገዋል የውስጣቸው ጥያቄም ነው። ፅናት ለቅሶ እና ፍርሀት ባጀበው ድምጿ የተፈጠረውን ሁሉ ነገረቻቸው። ሊባኖስ እና በፀሎት የሰሙትን ማመን አቃታቸው። ፅናት እየቀለደችም አልያም ደሞ በህልም አለማቸው እያዩት(እየሰሟት) መሰላቸው።
ሊባኖስ ፅናት ንግግሯን ከጨረሰች በኋላ "የእኔ ሚጢጢ እየቀለድሽ መሆን አለበት ቆይ እንዴት እንዲ ሊሆንስ ቻለ የፈጣሪ ያለ" አለች።በፀሎትም ከ ሊባኖስ ንግግር በኋላ "ማለቴ ልጁ ቆይ እብድ ነው ሰው ይገላል ስትሉት አልነበረ እንዴ" አለች። ፅናትም "አዎ ሊቦዬ እንደዛ ነው ያለችው እኔም በአይኔ ከእዚህ በፊት ያየውት እብደቱን ነው ደሞ በንግግሩ መሀል ከባድ የ ኢንግሊሽ ቋንቋዎችን ይጠቀማል እኔም ጥያቄ የሆነብኝ ይህ ነው ሰው እንዴት የተረጋጋ እብድ ሊሆን ይችላል የሚለው" አለች። ፅናት ንግግሯን እንደጨረሰች ሊባኖስ በድንገት ብድግ ብላ የሳሎኑ በር ላይ ቆማ ጫማ ማረግ ጀመረች። ፅናትም በግርምት ሊባኖስን እያየቻት "እንዴ ሊቦዬ የት ልትሄጂ ነው?"አለቻት። ሊባኖስም " እመጣለው እሺ ጠብቁኝ ብላ ወጣች። በፀሎት ግራ ቢገባትም ምንም ቃል ግን አላወጣችም።
ሊባኖስ ከሄደችበት ሰአት ጀምሮ በፀሎት እና ፅናት በዝምታ ቁጭ ብለው ነበር።ፅናት ዝምታውን "እህቴ" ብላ በፀሎትን በመጥራት ሰበረችው። በፀሎትም "ወዬ ፅናቴ " ብላ የቤቱን ዝምታ እንክትክቱን አወጣችው። ፅናት ለቅሶ በዘጋው ድምፅ " በህይወታችን ዙሪያ እያጋጠሙን ያሉት ነገሮች ሁሉ ግን አይገርምም ማለቴ የሚገጥሙን ሰዎች አለቻት" በፀሎትም "በጣም በጣምም ነዋ እህቴ " አለች። ፅናትም ( አባታችንን ተይው ለምሳሌ ከእማማ ብንጀምር ለእኛ በጣም ጥሩ ሴት ነበሩ በጣም እንወዳቸው እና ይወዱን ነበር የሞተችዋን እናታችንን ሀዘኗ ባይወጣልንም እንድንፅናና አርገውናል። ተመልከች ደሞ ሊባኖስን ሊቦዬ ወደ ህይወታችን ከገባች በኋላ የ እማማን ሀዘን እና ደሞ የእናታችን መፅናኛ ሆና ሁሌም ከጎናችን ናት ያው ያልነገረችን ታሪኳ ማለቴ ያልጨረሰችልን ታሪኳን ባናውቅም ተመልከች ሲከፋን አትወድም አብራን ነው ምትከፋው አብራን ነው የምታለቅሰው ፈጣሪ ሁሌም መፅናኛ ይልክልናል። አሁን ደሞ ይህ እብድ ከጭንቅላቴ ማውጣት አቅቶኝ ያለ ማቆረጥ እያሰብኩት ነው። ማለቴ እሱስ ህይወታችን ውስጥ ገብቶ ምን ሊፈጠረ ነው እያልኩ እራሴን ጠየኩት ደሞ እኮ በጣም ልጅ ነው በጣም አለች" በፀሎት ፅናትን ሰምታ ከጨረሰች በኋላ " እንዴት እንዴት ማለት መጨረሻ ላይ የተናገረሽውን ልታብራሪልኝ ትችያለሽ የኔ ውድ እህቴ" ብላ ሳቀች።
በፀሎት የፅናትን ፊት አላየችም እንጂ ብታይ ኖሮ በጣምም ትስቅ ነበር። ምክንያቱም የፅናት ፊት ፍፁም ፈገግታን ተላብሶ ነበር። ለነገሩ ከአነጋገሯም በፈገግታ ታጅባ እያወራች እንደነበር ያሳብቃል። ፅናትም " እንዴ እህቴ ቆይ አንቺ እራስሽ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?" አለች።ደንገጥ ብላ በፀሎት አሁንም ሳቋን አላቋረጠችም። ፅናት "ኧረ እህቴ በፈጣሪ ቆይ ለምንድን ነው እየሳቅሽ ያለሽው " አለቻት። በፀሎትም "አይ እህቴ ዝም ብዬ ነው እሺ እርሽው በቃ እና ክላስ እንዴት ነበር" አለቻት። ፅናትም "እሺ ካልሽ ክላስ ጥሩ ነበር ዛሬ ፕረዘንቴሽን ነበረኝ በጣም ከባድ ነበር ግን ተማሪዎቹን ማየቱ በጣም አስፈሪ ነው። ማለቴ በቃ ያስፈራሉ" አለች። በፀሎትም "ጎበዝ የእኔ ልዩ ቀስ በቀስ ትለምጃቸዋለሽ እሺ " አለቻት።ከዛም በፀሎት መሳቅ ጀመረች።
ፅናት የእህቷ ሳቅ ተጋብቶባት መሳቅ ጀመረች። ከዛ በመሀል ሳቋን አቁማ "እህቴ ግን ዛሬ በጣም ሳቅ ሳቅ ብሎሻል " አለቻት። በፀሎትም በድጋሜ ክትክት ብላ እየሳቀች "የአብዬን ወደ እምዬ " አለች። ፅናት "ሆሆ ቆይ ምን ማለት ነው ይሄ እሺ አሁን ሊቦ የት ነው የሄደችው እኔ ከመምጣቴ በፊት የነገረችሽ ነገር አለ?" አለቻት። በፀሎትም
"አይይ አይይይ ምንም ነገር አልነገረችኝም አህቴ ግን ምነው" አለች።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 26..🥀
.
.
.
ሊባኖስ የፅናትን ሁኔታ አይታለች። ስለዚህም ነው አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ የፅናትን ጉልበት እያሻሸች "የኔ ሚጢጢ፤ የኔ ውብ ምን ሆነሽብኝ ነው?" ያለቻት። ፅናት አሁን ከሀሳብዋ ነቅታ "እ ሊቦዬ ምን አልሽኝ? አአአ ምንድነው የሰራሽው ሽታው በስማም የሚገርም ፍርፍር እና የሚገርም የቅመም ሻይ" አለች ተነስታ ትራሱን ለመደገፍ አመቻችታ እየተቀመጠች። በፀሎትም "አዎ ጥሩ ሽታ ያላቸው ነገሮች ናቸው በሉ እንብላ በቃ" አለች። መብላታቸውን ቀጠሉ። ሊባኖስ ተነስታ ሻይውን አምጥታ ቀድታ ለሁለቱም ሰጠቻቸው ሻዩን ጎንጨት ፍርፍሩን ጎረስ እያረጉ በዝምታ ሻዩን እና ፍርፍሩን ጨረሱ። ሲጨርሱ ሊባኖስ የበሉበትን እና የጠጡበትን እቃ ይዛ ወጣችና በረንዳ ላይ ማጠብ ጀመረች። እቃውን አጥባ እያለቀለቀች እህትማማቾች የቴዲ አፍሮን የሚወደውን ሰው አምላክ ይፈትናል.... የሚለውን እየዘፈኑ ሰምታቸው ፈገግ አለች። ስትጨርስ እነሱን ተቀላቅላ ብዙ ዘፋኞችን በጋራ ሲዘፈኑ ቆዩ። ሊባኖስም እስቲ እኔ ተረት ልንገራቹ አለች።ከአልጋው ጠርዝ ተነስታ መሀላቸው ገብታ ልክ መጀመሪያ እንደተኛችው ሆና። ሁለቱም እሺታቸውን ገለፁ። ከዛም "ተረተረት አለች ሊባኖስ" እህትማማቾችም በጋራ "የላም በረት" አሉ እና ተሳሳቁ ሊባኖስም የሁለቱንም ጭንቅላት እያሻሸች መናገሯን ቀጠለች።
"በድሮ ጊዜ አንድ ወርቁ የሚባል ልጅ ነበር ይህ ልጅ በምታኖረው ሴት ይበደል ነበር ሴቲቱ የእንጀራ እህቱ ናት ምግብ እና ውሀም ብዙ አሰጠውም ነበር ከእለታት በአንዱ ቀን ወርቁ ትልቅ የሾላ ዛፋ ስር የወዳደቁ ሾላዎች አግኝቶ ሲበላ ቆየ ግን ያገኛቸው የሾላ ፍሬዎች ወርቁን ማጥገብ አልቻሉም። ወርቁ ተዳከመና ከዛፍ ስር ጋደም አለ። ከተጋደመበት ዛፍ ላይ አንዲት ወፍ ሾላውን ለወርቁ ማርገፍ ጀመረች።
ወርቁ የሾላዎቹ ፍሬዎች ሲወዳድቁበት ተሰምቶት ቀና አለ እናም ወፏን አያት። ወርቁ የሾላ ፍሬውን እየለቀመ እየበላ ወፊቱን በግርምት ማየቱን ቀጠለ።
የሾላ ፍሬዎችን በልቶ ከጠገበ በኋላ ወደ ቤቱ ሄደ። በቀጣይ ቀንም መጣ በድጋሜ የሾላ ፍሬዎችን ለማውረድ ሞከረ ግን አልተሳካለትም ከዛም ወፏ በድጋሜ መጣችና የሾላ ፍሬዎቹን ልክ እንደ ትናትናው ማርገፈ ጀመረች ወርቁ አሁንም ጠግቦ ወደ ቤቱ ሄደ። ወርቁ አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ዛፍ ሄደ የሄደው ግን ወፊቷን ተስፈ አርጎ ነበር። ተሰፈ አርጎ አልቀረም ወፊቷ የሾላ ፍሬዎችን አረገፈችለት እየበላ ከወፏ የሚማርክ ድምፅ ሰማ በዘፈን መልክ..
"ወርቁ ልጄ የ እግዚአብሔር አደራ እንካ ሾላ ብላላላላላ" የሚል። ከዘፈኑ ጋር መአት የሾላ ፍሬዎች መውረድ ጀመሩ። ወረቁ በልቶ ጠገበና ለማታውም በኪሱ ይዞ ሄደ። እርግቧን ምንም አይነት ጥያቄ አልጠየቃትም ምክንያቱም ልጅ ስለነበረ። ወርቁ በነጋታውም እዛው ዛፈ ስር ሄዶ ቁጭ አለ። ወዲያው እረግቧ
"ወርቁ ልጄ የእግዚአብሔር አደራ እንካ ሾላ ብላ " አለችና በዜማ ሾላውን ታረግፈለት ጀመረ። ወርቁም በልቶ ጨረሳ ሊሄድ ሲል።
"ወርቁ ልጄ እህትክ እንዴት ትልሀለች" ስትለው በዘፈን መልክ
እሱም "በወንፊት ውሀ አምጣ ትለኛለች ውሀው ሲፈስብኝ ትመታኛለች" አለና እየሮጠ ሄደ። ወርቁ በነጋታው ዛፉ ጋር ሲደርስ አንድ ላም ቁጭ ብላለች። ወርቁም ከላሚቷ እራቅ ብሎ ተቀመጠ
እርግቧም መጥታ ላሙዋ የእሱ እንደሆነችና ያላትን ምግብ እንደምትሰጠው ነገረችው። ወርቁም ዳቦ ቆሎ አለ።
ላሚቷም አቀረበችለት። ዳቦ ቆሎውን እየበላ እርግቧ በዜማዊ (በዘፈን) ድምፅ "ወርቁ ልጄ እህትክ እንዴት ትልሀለች " ስትለው በወንፊት ውሀ አምጣ ትለኛለች ውሀው ሲፈስብኝ ትመታኘኛለች"። ብሎ ሮጦ ሄደ። የወርቁ እህትም ወርቁን ወንፊት እና ጭድ ሰጥታ እንደተለመደው አዘዘችው ወርቁም እሳቱን ጭዱ ሳይቃጠል ውሀውም ሳያፈስ ይዞላት መምጣት ጀመረ። ይህ እንዲሆን ያረገችው ወፏ ነበረች።ወርቁ ትልቅ ልጅ እስኪሆን በእዚህ መልኩ ቆየ።ወርቁ ሊያገባ አንድ ቀን ሲቀረው ለእርግቧ ነገራት። ደስስስ አላት። ወርቁም ደስታውን አጋርቷት ጥያቄ ጠየቃት "አንቺ ማነሽ" ብሎ እርግቧም የእናቱ የጡት ቁራጭ እንደሆነች ነገረችው አለቀሰ ፣አለቀስ አለቀስ፣ እያለቀስ ቤት ሲደረስ እህቱ የለችም። እህቱ ወርቁ የአባትዋ የሚያሳድገው ልጅ ሳይሆን ትክክኛ ወንድሟ እንደሆነ በወሬ ሰማች።አባትዋን የገደለች ሴት ስለሆነች ለወርቁም ያሰጋል። በአከባቢያቸው ወደምትገኝ ብልህ ሴት ሄዳ ነገሩን ሁሉ አጫወተቻት ብልሀተኛዋ ሴትም "ወንድምሽ ምልክት አለው ማወቄያ?" አለቻት እሷም "አዎ ጥረርሱ ሸራፋ ነው" ስትላት "እና የወርቁስ" አለቻት። "እሱ መች ይስቃል" ስትላት "እንደዛ ከሆነ ዛሬ ውኑ እሱን አጠገብሽ አርገሽ ስስ ልብስ ልበሽና ተልባ ቁይ ተልባውን አትክደኚው ተልባው ልብስሽ ላይ ሲያረፍ እና ሲያቃጥልሽ በምታሳይው ነገር ወርቁ መሳቁ አይቀረም ያኔ ጥርሱን ማየት ትችያለሽ።" አለቻት። በእዛ መልኩ ነበር የወርቁ እህት ወርቁ ትክክለኛ ወንድሟ እንደሆነ ያወቀችው ከዛም ወርቁን ይቅርታ ጠይቃ ለወረቁ ሰርግም ዝግጅቶን ጨረሳ ወረቁን ዳረችው እና ለሰረጉ እለት ወፏ በደስታ ወረቁን ስትዞረው አንድ ሰው በወንጭፍ መቶ ገደላት ግን በጣር ውስጥ ሆና ወርቁ የመታት ስለመሰላት ወርቁ "ወርቁ አጥንቴ ዩጋክ ደሜ ይከርፋክ" ብላ እረግማው የሞችው። ወርቁም በእረግማኑ መሰረት ካገባ በ2ተኛ ቀኑ ሞተ። ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ" አለች ሊባኖስ ተረቱን ተርካ ስትጨርስ። ፅናት "ውይይይይ ሲያሳዝን" አለች። በፀሎትም "በጣምምም የኔ ምስኪን" ስትል ሊባኖስ "በሉ አሁን በቃ እንተኛ ተኙ ተኙ" አለች ሶስቱም ተቃቅፈው ተኙ።
ሰአት ሄዶ ለሊት በቀን ቀን በለሊት ተተክቶ ፅናት ከህመሟ አገግማ ከትምህርቷ ወደ ቤት እየሄደች ነው። ሊባኖስ እና በፀሎትም ፅናት እስክትመጣ እየጠበቋት ነው። ፅናት ሁሌም የዶክተሩ ንግግር ያቃጭልባታል። ወደ ቤቷ እየሄደች የምታውቀው ኮቴ ከጀርባዋ ሲከተላት ተሰማት ኮቴው ወደ እሷ ቀርቧል ወደ ኋላ ሳትዞር በፍጥነት እየሄደች አንድ ጠንከር ያለ እጅ ያዛት። ፅናት ዞር ብላ አይታው ደነገጠች መልኩን ባታውቀውም የለስውን ልብስ ግን ከሩቁ ታየው ነበር ያ እብድ ነው ፅናት ደርቃ ቀረች።
.
.
በየቀኑ እንዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ቤተሰብ ♥️
ይቀጥላል
9 642
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 25..🥀
.
.
.
በፀሎት እና ሊባኖስ ከዶክተሩ ሌላ ተጨማሪ ቃል ፈልገዋል። ዶክተሩ ንግግሩን ቀጠለ ሲናገር ሁለቱንም በተራ እያየ ነበር። "እእእእእ እየውላቹ ፅናት እስከዛሬ ከባድ ነገሮችን ማለቴ ጭንቅላቷ መሸከምም ሆነ መቋቋም ከምትችለው በላይ እንዳሳለፈች ያሳያል። ቀሪ ውጤቱን ደሞ ሙሉ ምርመራው ካለቀ በኋላ የምንነግራቹ ይሆናል ለጊዜው መናገር የምንችለው ይህንን ነው አለ። በፀሎት ከተቀመጠችበት ብድግ አለች እና "ሊቦቲዬ ነይ ተነሽ እንሄድ" አለች። ሊባኖስም "እሺ" ጥሩ በቃ እንሂድ" አለች። ሊባኖስ በፀሎትን ደግፋ ከቢሮ ወጡ።
ዛሬ ፅናት ሀኪም ቤት ከገባች 2 ቀን ሆኗታል። ፅናት መታከሚያ ክፋሏን ለቃ ወደ ቤት ለመሄድ ደሞ 6 ሰአታት ቀርቷታል። በፀሎት እና ሊባኖስ ፅናት የተኛችበት ክፍል ከፅናት ጋር ናቸው። በሩ ተንኳኳ ሊባኖስ "ይግቡ" አለች። በሩ ተከፈተና ዶክተሩ መጣ።ሲያወራ በጣምምም ይፈጥናል "እንዴት አደራቹ ሰዎች ፅናት ዛሬ ያው ከሀኪም ቤቱ የምትወጪበት ቀን ነው ለመውጣት 6 ሰአታት ይቀረሻል ጉልኮስሽ እስኪያልቅ ማለቴ ነው። ልትወጪ ስትይ ግን ወደ እኔ ነይ አንዳንድ መነጋገር ያሉብን ነገሮች አሉ" አለ የፅናትን የልብ ምት ለማዳመጥ ማዳመጫውን ደረቷ ላይ አርጎ። ፅናትም "እሺ እመጣለሁ አመሰግናለሁ በጣም" አለች። ዶክተሩ "የሙያ ግዴታዬን ነው የተወጣውት ለማንኛውም እንደነገርኩሽ ወደ ቢሮዬ መምጣት እንዳረሺ" አለና
ወጣ።
በፀሎት ዶክተሩ ከወጣ በኋላ "ሆሆ ወይ አምላኬ ምንድነው ቆይ እንዲ በፍጥነት ማውራት ቃላቶቹ አይጠፉበትም እንዴ" ስትል ሊባኖስ "ወይ አንቺ ልጅ እንደው ምን ይሻልሻል ያው ተፈጥሮ እኮ ነው አለች። ፅናትም በወሬያቸው ጣልቃ ገብታችሁ "ሊቦዬ እህቴ እኮ ልክ ናት ደና አደራችሁ ብሎ መልስ ሳይጠብቅ እኮ ነው ወደ ጉዳዩ የገባው በእዛ ላይ ያለ እረፍት የ 1 ሰአቱን ወሬ በ1ሰከንድ ጨረሰው" አለች።ተሳሳቁ
የፅናት ወደ ቤት የመሄጃ ጊዜዋ እስከሚደርስ ቁጭ ብለው ሲያወሩ ቆዩ ያው የፅናት መዳከም እና በየመሀሉ መተኛት እንዳለ ሆኖ። የዶክተሩ ቀጠሮ ስአት እና የፅናት ወደ ቤት መሄጃ ሰአት ደረሰ። ነርሶቹ መተው የመውጫ ሰአቷ እንደደረሰ ተናግረው ግሉኮሷን ነቀለውላት ወጡ። ሊባኖስም ፅናትን ፡ደግፋ ወደ ዶክተሩ ወሰደቻት በፀሎትንም በሊላኛ እጇ ይዛታለች።የዶክተሩን ቢሮ አንኳኩተው ገቡ። ዶክተሩም ሊባኖስ እና በፀሎት እንዲወጡለት እና ፅናትን ለብቻዋ ማውራት እንደሚፈልግ ነግሯቸው ሁለቱም ያለ ምንም ጥያቄ እና ጭቅጭቅ ተያይዘው ወጡ። ፅናት ዶክተሩ የሚላትን ለመስማት ጓጓችም ፈራችም ዶክተሩ ያለምንም ዛዛታ በተቀላጠፈ እና በፈጠነ አንደበት ፅናት የጭንቅላት ህመም እንደያዛት እና ይህ ህመም ደሞ ቀስ እያለ እየባሰበት መጥቶ ለከፍተኛ ህመም ሊዳርጋት እንደሚችል በተጨማሪም ደሞ በሽታው ገፈቶ ትልቅ ደረጃ ላይ ደረሶ እሷን ማሰቃየት ሲጀምር ጨለማ ክፍል ውስጥ ሆና እራስዋ ላይ በር ዘግታ እራስዋን እንድታስታምም አልያም ደሞ በህይወቷ ትልቁን ውሳኔ ወስና ከመቶ 10%የመዳን እድል ያለውን የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እንድታደርግ ነገር ግን ህመሙን ችዬ እስኪለቀኝ ጨለማ ክፍል እቆያለሁ የሚል ሀሳብ ካላት የመትረፈ እድሏ 50% እንደሆነ ነገራት።
ፅናት ደነገጠች ግን ደሞ እራስዋን አልሳተችም ዶክተሩ ከወንበሩ ተነስቶ ፅናት ጉልበት ላይ በርከክ አለ ለፅናት ከ ግሉኮሱ ጋር ምንም አይነት ክፉ ዜና ብትሰማ እራስዋን እንዳትስት የሚያረግ መዳኒት ሰቷት ስለነበር ፅናት ትንሽ ብቻ ደነገጠች። የዶክተሩን እጅ ያዘችውና "እባክክ ልለምንክ ይህንን ነገር በጭራሽ ለእህቴ እና ሊቦ አትንገራቸው" አለችው።ዶክተሩም "የታካሚ መረጃ ያለ ፈቃድ ለማንም አይሰጥም ስለዚህ አታስቢ ግን እራስሽን ከአስጨናቂ ነገር ማራቅ አለብሽ ደስተኛ ለመሆን መሞከሩም ጥሩ ነው በማንኛውም ሰአት በሽታሽ ሊነሳብሽ ይችላል ከፈጣሪ ጋር ትወጪዋለሽ የሚል እምነት አለኝ"።አላት በር ተንኳኳ "ይግብ" አለ ዶክተሩ ዶክተር ይስሀቅ ነበር የፅናት ሊላኛው ዶክተር ነበር ገባ። ዶክተር ዳመነም "ኦኦ ዶክተር ይስሀቅ ግባ ግባ" አለው ዶክተር ይስሀቅም "ሰላም ፅናት እንዴት ነሽ" አላት።ይሄኛው ረጋ ያለ ነው። ፅናትም "ደና ነኝ ደናም እሆናለው " አለች።
ዶክተር ይስሀቅም "ያው ዶክተር ዳመነ እንደነገረሽ ነው ህመምሽ ምን ወሰንሽ?" አላት። 50% ሊያድናት የሚችለውን ውሳኔ እንደወሰነች እና ማንም ሰው እንዲያውቅ እንደማትፈልግ ለዶክተር ይስሀቅ ነገረችው ። ዶክተር ይሳቅ ወደ ዶክተር ዳመነ እያፈጠጠ "እንዴ ቆይ እንዴት ቤተሰብ እማ ማወቅ አለበት" አለ።ዶክተር ዳመነም "ፅናት በቃ መሄድ ትችያለሽ " አላት። ፅናትም ምንም ሳትናገር በቀስታ ወጣች። ፅናት ከወጣች በኋላ ዶክተር ዳመነ እንደ እሳት በፈጠነ አንደበቱ "እየውልክ ዶክተር ለቤተሰቦቿ ብንነግራቸው እሷን ትሬት ለማረግ በሚሞክሩበት ሰአት ታካሚያችን መንፈስ ጭንቀቷ ይበረታባታል ሁለተኛው ደሞ የታካሚን መረጃ ያውም እንዲ አይነት ኬዝ ያለ ፍቃዳቸው አይሰጥም ይህንን ደሞ ላንተ አልነግርክም" አለው።ዶክተሩ በዶክተር ዳመነ ንግግር በሽቆ በሩን ጓ አርጎት ወጣ። ሲወጣ ኮሊደሩ አከባቢ ፅናት እህቷ በፀሎትና ሊባኖስን አቅፋቸው እያለቀሰች ነው።
ፅናት አሳዘነችው ለእሷ አለማዘን ፈፅሞ አልቻለም።ቆሞ ማየቱን ትቶ ወዲያው ሄደ። ሊባኖስም ፅናትን እና በፀሎትን ቅርባቸው ባለው ወንበር ላይ አስቀምጣቸው ስልኳን አውጥታ ለሹፌሩ ደውላ እንዲመጣ ነገረችው። ሹፌሩም ወዲያው መጣና ቤታቸው አደረሳቸው።
ቤት ከደረሱ በኋላ ሹፌሩ ወደ መጣበት ተመለሰ።ሶስቱም ቤት እንደደረሱ እነ ፅናት አልጋ ላይ ከመሀል ሊባኖስን በግድግዳው ጥግ ፅናት በሊላኛው ጎን በፀሎት ሆና ሊባኖስ ሁለቱን ቆነጃጂት እህትማማቾች በቀኝ እና በግራ ክንዶቿ ላይ አንተረሳቸው አይናቸውን ጨፍነው ሁለቱ እህትማማቾች ወደ እንቅልፍ አለም ተሰደዱ። ሊባኖስም እያፈራረቀች ካየቻቸው በኋላ እሷም ተከተለቻቸው ሶስቱም እንቅልፍ ላይ ናቸው። ጭንቅላታቸው በእንቅልፍ ምክንያት ማሰቡን ትቶ እረፍት ላይ ነው።
ሳያስቡት ፀሀይ ጠልቃ ጨረቃ ወታለች።ንጋትም ጠፍቶ ጨለማን አንግሷል።ሊባኖስ ተነስታ ጣራ ጣራውን እያየች ነው ሊባኖስ ሳታስበው ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ
አለች። ይህ ድምፅ እህትማማቾችን ካሉበት እና ከተጓዙበት እንቅፍ አባነናቸው
ሊባኖስም "በሉ ከአልጋ እንዳትወረዱ ብርድ በጣም አለ።እኔም ዛሬ እናንተ ጋር ነው የማድረው የኔ ሚጢጢዬ እስኪሻላት የትም አልሄድም" አለችና ከመኝታ ቤት ወጥታ ወደ ኩሽና ገባች።እንጀራ አድርቀው የሚያስቀምጡበትን ባሊ ከፈተችና ድርቆሽ በጎድጎዳ ሰሀን ቀንሳ ካወጣች በኋላ ባሊውን መልሳ ዘጋችው።
በፀሎት እና ፅናት እስካሁን ምንም ትንፋሽ አላወጡም ሁለቱም በዝምታ ውስጥ ናቸው። በመሃላቸው ሊባኖስ ተኝታ የተነሳችበት ክፍተትም ባለበት ነው። በቃ ሁለቱም ካሉበት ቦታ አልተነቃነቁም። ሊባኖስ ፍርፍር ሰርታ ሻይ አፍልታ እስክትጨርሽ ድረስ። ሊባኖስም ሀሳብ ውስጥ ናት። ምግቡን እና ሻዩን ይዛ መኝታ ቤት መጣች።በፀሎትም "ውይይይ ሊቦቲዬዬዬዬዬዬዬዬዬዬ ሽታው በጣም ደስስ ይላል የቅመም ሻይ በጣፋጭ ድርቆሽ ፍርፍር" አለች። ሊባኖስም እንዴታ"ባለሙያ አደለው እንዴ አትርሺ እንጂ?" አለች።ፅናት ከሀሳብዋ አሁንም አልነቃችም ሀሳብ ፣ ጭንቀት እና ጉዳት ላይ ናት።
👍👍👍 ላይክ ሼር ❤️❤️❤️
9 642
አንዱ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅር ስትሰራ የተቀረፀውን ቪዲዮ ልከውለት አይቶ ከጨረሰ ቡኃላ ለሚስቱ ደውሎ...
:
#አንቺ_አሰዳቢ ««« ምናለ አዲሱ ፓንትሽን👙 ብታደርጊ እንዳልገዛሁልሽ የምታሳጪኝ😳🙊
