en
Feedback
TheDeepThingsOfGod

TheDeepThingsOfGod

Open in Telegram

Glorious Church the bride of Christ. Rapture ready!

Show more
1 810
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
እግዚአብሔር ያድሳል! መሰዊያ ይታደሳል። ጸሎት ይታደሳል። ትጋት ይታደሳል። ጾም ጸሎት ይታደሳል። ቅድስና ይታደሳል። ኪዳን ይታደሳል። አገልግሎት ይታደሳል። ፍቅር ይታደሳል። ሃይል ይታደሳል። የቆሸሸ አእምሮ ይታደሳል። ቅንነት ይታደሳል። እግዚአብሔር ዛሬ እናንተን እና የእናንተ የሆነውን ነገር ሁሉን እንዲያድስ እጸልያለሁ! የፈረሰባችሁ ነገር ካለ ተስፋ በመቁረጥ እና በጸጸት እትቀመጡ እግዚአብሔር የሚያድስ አምላክ ነው፥ እንደገና ጀምሩ፥ ተነሱ። @TheDeepThingsOfTheSpirit

RESTORE US AGAIN LORD PLEASE?😭

RESTORE US LORD PLEASE?😭

ክርስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆችን በመጠቀም አሸናፊ ሕይወት የመኖር ጉዳይ ብቻ አይደለም፥ እዚሁ ምድር ላይ እግዚአብሔርን በግል የማወቅ፣ የመለማመድ እና እግዚአብሔርን ራሱን ለመምሰል የመለወጥ ሕይወት ነዉ። Christianity is not just living a victorious life by engaging Bible principles, but it's a life where you personally know God, experience Him and transfigure to be like him in this life. -Victor 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

የእግዚአብሔር ቃል ያለው ሰው የተጽዕኖ ሰው ነው። መቼም በየትኛውም ቦታ ዓለም( ዓለማዊያን እና ለእግዚአብሔር መንግስት የማይገዛ የዓለም ስርዓት) ተጽዕኖ እንዲያሳድሩብኝ አልፈቅድም፥ በእነርሱ ላይ ተጽእኖ የማደርገው እኔ ነኝ! ከእኔ ይኮርጃሉ እንጂ ከእነርሱ አልኮርጅም። የእግዚአብሔር ልጆች ከምታውቁት በላይ ትልቅ የተጽእኖ አቅም ውስጣችን አለ፥ ይህም የተጽእኖ ሃይል "የእግዚአብሔር ቃል" ይባላል፥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የተጽዕኖ ሃይል ስናገር “እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።” ሐዋርያት 19፥20 ይላል። በየትኛውም ሁኔታ የሚያድግ እና የሚያሸን የተጽዕኖ ሃይል ነዉ። ሁልጊዜ እንደ እግዚአብሔር ቃል ማሰብ፣ መናገር እና ማድረግ ጀምሩ እና የምትፈጥሩትን እውነተኛ ተጽዕኖ ለራሳችሁ ተመልከቱ፥ ነገሮችን ሁሉ በቃሉ መነጽር መመልከት ጀምሩ፥ ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሁሉ በቃሉ የተቃኘ ይሁን። እንደ እግዚአብሔር ቃል ለማሰብ፣ ለመናገር እና ለማድረግ አትፍሩ፥ በጣም ደፋሮች ሁኑ፥ ራሳችሁን እንደ እግዚአብሔር ልጆች አስቡ፥ ከአምላክ እንደተወለደ የአምላክ ልጅ አስቡ፥ በፍጹም በየትኛውም ዓይነት መንገድ ዓለማዊያን እና ስርዓታቸው ተጽእኖ እንዲያደርጉባችሁ አትፍቀዱ፥ እነርሱ እናንተ ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ብቁ አይደሉም ማንም እና ምንም ቢሆኑም ጨለማ የጨለማ ልጆች ናቸው እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ብርሃን ናችሁ። ይህ ትዕቢት አይደለም እውነት ነዉ፥ አንዳንዴ እውነትን ስንናገር ትዕቢት መምሰሉ የሚያስገርም ነዉ። የእግዚአብሔር ልጆች የተሰጣችሁን የተጽእኖ ሃይል ተጠቀሙ። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የእግዚአብሔር ቃል በሙላት እንዲኖርባችሁ እጸልያለሁ፥ አሜን። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

መጽሐፍ ቅዱስ ዓለም በማለት የሚገልጸው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላመኑ ሰዎችን ሁሉ እና ለእግዚአብሔር መንግስት የማይገዛ ስርዓትን ሁሉ ነዉ። What the Bible calls the world is all the unbelievers and every system that is against Gods kingdom. @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

እውር የሚመራው ብሩህ እና ዓለም የምትመራው ክርስትያን አንድ ናቸው፥ ሁለቱም ማስተዋል የላቸውም። -Victor @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

ይሄንን አስገራሚ እና አስተማሪ ታሪክ ስሙት... ሸክላው ሲረግፍ ላኩ ሙሉ በሙሉ ወርቅ ነበር😁 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

TheDeepThingsOfGod ጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ነገር የምንማርበት እና የምንለማመድበት መንፈሳዊ ቻናል። 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን

በ Inbox የተላከልኝ ነዉ፥ ፈገግ ብዬ ነው እየሰማሁ የጨረስኩት፥ እናንተም ስሙት እና ትማሩበታላችሁ! የእግዚአብሔር መንግስት ጉዳይ ትኩረታችን ይሁን።🥰

በ Inbox የተላከልኝ ነዉ፥ ፈገግ ብዬ ነው እየሰማሁ የጨረስኩት፥ እናንተም ስሙት እና ትማሩበታላችሁ! የእግዚአብሔር መንግስት ጉዳይ ትኩረታችን ይሁን።👇🥰

1.71 MB

ዓለም እና የእግዚአብሔርን ቃል ያላገኙ ነገር ግን መድረክ ላይ ያሉ ሐሰተኞች ስለ ስኬት የነገሩን ሁሉ ውሸት ነዉ። ስኬት ለእኔ እና ለወንጌል አማኞች ሁለ የሚገለጸው ከላይ ባለው ምስል ነዉ፥ አትሳቱ
ዓለም እና የእግዚአብሔርን ቃል ያላገኙ ነገር ግን መድረክ ላይ ያሉ ሐሰተኞች ስለ ስኬት የነገሩን ሁሉ ውሸት ነዉ። ስኬት ለእኔ እና ለወንጌል አማኞች ሁለ የሚገለጸው ከላይ ባለው ምስል ነዉ፥ አትሳቱ ፍለጋችሁ የእግዚአብሔር መንግስት እና ጽድቅ ይሁን ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል። “ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” — ማርቆስ 8፥36 #JesusChristIsComingSoon! @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

ጌታ ሆይ በቀኑ መጨረሻ የትውልድ መፈወሻ አድርገኝ አንተን በመፍራት አሳድገኝ።

የኢትዮጵያን ሪቫይቫል እውን የማድረግ ፀሎት🔥🔥 ነሀሴ 1 ልንጀምር የነበርው ወደ ነሀሴ 3 ተዘዋውሯል ከሰኞ በኋላ ክብር ብቻ ነው😭 የአባቴ ልጆች ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ❗️ ከ3 ቀን በፊት እንዳልኩችሁ ሀምሌ/27/2013 መንፈሳዊ አለም ላይ ከምለው በላይ ከባድ የክብር ደመና እንደቀረበ.. ሪቫይቫል በምድሬ ኢትዮጵያ ልጀምር ጥቂት የምባል ጊዜ ብቻ እንደቀረ መንፈስ ቅዱስ እንደ ተነገረኝ አሳውቄአችሁ ነበር። ስለዚህ ጌታ ክብሩን ልየፈስ ስል በቦታ እንደንተጠ😭 ከበፊቱ በላይ አጥብቀን መፀለይ አለብን... ስለዚህ ከእኔ ጋ ከነሀሴ 3 ጀምሮ በቀን ውስጥ ሁለት(2) ሰዓት ብቻ😳 ስለሚመጣው ሪቫይቫል እንፀልይ፣እንሞላ እና ለሪቫይቫሉ በቅ ዝግጅት እናድርግ ብዬ ጥሪዬን አቀርባለሁ🙏 በዚህ ሃሳብ የምስማማ ሁሉ አሁኑኑ አነግሩኝ👉👉👉 @messengerkibreab #አስተውሉ 1- ፀሎቱን የምናደርገው በተመሳሳይ ሰዓት #ግን ባለንበት ቦታ ሆነን ነው😳 ደስ ይላል አይደል❗️ 2-ነሀሴ ሦስት(3) ፀሎት ስለምንጀምር እስከዛ ብቻ ነው መመዝገብ የሚቻለው 🙏 ለበለጠ👉 @messengerkibreab ለምፈልጉ ሁሉ አሳውቁ 🙏 ሼር አድርጉ ሪቫይቫል የምለው ቃል እንደይቃልብን😭

እግዚአብሔርን ለመምሰል ራስን ማሰልጠን በየቀኑ የሚሰራ የሙሉ ጊዜ ተግባር እንጂ በቤተክርስቲያን ውስጥ ባለን ቆይታ በሕይወታችን ላይ የሚፈጠር ተዓምራት አይደለም። @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

The important differences between the rapture and second coming are as follows: 1) At the rapture, believers meet the Lord in the air (1 Thessalonians 4:17). At the second coming, believers return with the Lord to the earth (Revelation 19:14). 2) The second coming occurs after the great and terrible tribulation (Revelation chapters 6–19). The rapture occurs before the tribulation (1 Thessalonians 5:9; Revelation 3:10). 3) The rapture is the removal of believers from the earth as an act of deliverance (1 Thessalonians 4:13-17, 5:9). The second coming includes the removal of unbelievers as an act of judgment (Matthew 24:40-41). 4) The rapture will be secret and instant (1 Corinthians 15:50-54). The second coming will be visible to all (Revelation 1:7; Matthew 24:29-30). 5) The second coming of Christ will not occur until after certain other end-times events take place (2 Thessalonians 2:4; Matthew 24:15-30; Revelation chapters 6–18). The rapture is imminent; it could take place at any moment (Titus 2:13; 1 Thessalonians 4:13-18; 1 Corinthians 15:50-54). @Godsgospel @Godsgospel

ጌታ ተመልሶ እንደሚመጣ በምን አውቃለሁ? የመጀመሪያው የእግዚአብሔርን ቃል በማመን ነዉ። የእግዚአብሔር ቃል የታመነ ነዉ፥ እጅግ በጣም ብዙ በቃሉ የተነገሩ ትንቢቶች እየተፈጸሙ አይተናል ደግሞም እያየን ነዉ። ሌላው ደግሞ በነቢያት መሲሕ ይወለዳል ተብሎ እንደተነገረው ኢየሱስ ተወልዷል፥ እርሱ በምድር ላይ ስመላለስ እጅግ ብዙ ድንቆችን እና ምልክቶችን አድርጓል፥ ከሁሉም የሚያስደንቀው ግን የሚሞትበትን ሰዓት አውቆ ለተከተሉት እንደሚሞት ተናግሮ ሰዓቱ ስደርስ በፈቃዱ መንፈሱን አሳልፎ ሰጥቷል፥ ከመሞቱ ቀድሞ ደግሞ በሦስተኛው ቀን ከሙታን መካከል እንደሚነሳ ተናግሯል፥ በተናገረውም መሰረት በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነስቷል። " ስለ ኃጢአት እሞታለሁ" ብሎ በተናገረው መሰረት የሞተ፥ በሦስተኛው ቀን ከሙታን እነሳለሁ ብሎ እንደተናገረው ከሙታን የተነሳ፥ ደቀመዛሙርቱ እየተመለከቱት ወደ ሰማይ ያረገው እርሱ "ተመልሼ እመጣለሁ" እንዳለ ተመልሶ ይመጣል። ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል፥ እኔ እየጠበኩት ነዉ፥ የእርሱ የሆኑት ሁሌም ይጠብቁታል። @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ በቶሎ ይመጣል፥ ዛሬ ለእናንተ ያለኝ መልእክት ይህ ነው፡ ንስሃ አድርጉ ክፉ መንገዳችሁን ተው፥ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ባለ እምነት ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን አድርጉ፥ እግዚአብሔር ይወዳችኋል በኃጢአት ስትሞቱ ማየት አይወድም፥ ይህንን ድምጽ እንደሰማችሁት እምቢ በማለት ልባችሁን አታደንድ፥ ይልቅ ለኃጢአት እምቢ በማለት ለእግዚአብሔር እና በሕይወታችሁ ላለው ግሩም ሃሰብ ታዘዙ። #JesusChristIsComingBack! @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

Those Who live in Hossana don't miss this prophetic meeting, Prophet kabod will be there to minister to you all! ሆሳዕና ያላችሁ ይህ
Those Who live in Hossana don't miss this prophetic meeting, Prophet kabod will be there to minister to you all! ሆሳዕና ያላችሁ ይህ ፕሮግራም አያምልጣችሁ።