cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TheDeepThingsOfGod

Glorious Church the bride of Christ. Rapture ready!

Show more
Advertising posts
1 810Subscribers
No data24 hours
-47 days
-2530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቅዱሳት መጽሐፍትን የማንበብ፣ የማሰላሰል እና የማድረግ(የመለማመድ) አንዱ ውጤት ኢየሱስ ክርስቶስን ተገልጦ ማየት ነው። @TheDeepThingsOfGod
Show all...
ቅዱሳት መጽሐፍት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንዳልኩት ሁለቱም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "የእግዚአብሔር ቃል" በመባል ተጠርተዋል። ቅዱሳት መጽሐፍትም ኢየሱስ ክርስቶስም የእግዚአብሔርን ሃሳብ፣ ምክር፣ በሕሪይ...ወዘተ የምናይባቸው ናቸው። በሁለቱም መካከል ፍጹም የሆነ አንድነት አለ (the scriptures and Jesus are identical) ቅዱሳት መጽሐፍት የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል የያዙ ስሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ አካላዊ (personal) የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅዱሳት መጽሐፍት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ናቸው ስንል ያልተጻፋ የእግዚአብሔር ቃል አለ ማለት ነው፥ ይሄ ማለት ቅዱሳት መጽሐፍት ጠቅላላውን የእግዚአብሔር ሃሳብ፣ ስራ፣ ንግግር እና በሕሪይ በዉስጣቸው አልያዙም ማለት ነው፥ ነገር ግን የሰውን ልጆች ወደ አካላዊዉ(personal) ቃል ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጠቆም እና ለመምራት ከበቂ በላይ የሆነ እውነት በውስጣቸው ይዘዋል። 29 ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው። ዘዳግም 29፥29 እግዚአብሔር በቅዱሳት መጽሐፍት በኩል ያልገለጠው ምሥጥር አለ፥ ነገር ግን በቅዱሳት መጽሐፍት የተገለጠው ሁሉ ለጥቅማችን ነው፥ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ የገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ። አሁን የቅዱሳት መጽሐፍትን ዋና ዓላማ መመልከት እንችላለን፥ ይህም የሰውን ልጅ ወደ ኢየሱስ መጠቆም እና መምራት እንጂ በፍጹም ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ መግለጥ አይደለም። ቅዱሳት መጽሐፊት መስካሪዎች ናቸው---39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ዮሐንስ 5፥39 --- በዚህ ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳት መጽሐፍት ስለእርሱ የሚመሰክሩ እንደሆኑ ይናገራል፥ ምስክር ማለት ስለሌላ አካል ያለን እውነታ የሚናገር ማለት፥ የምስክር ስራው ያየውን እና የሰማውን መናገር ወደ እውነታው መጠቆም እና መምራት ነው፥ ቅዱሳት መጽሐፊትን የሚያነብ ወይም የሚሰማ ሰው የሚመራው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ የትኛውም ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን በግል ከማወቁ በፊት የግዴታ የቅዱሳት መጽሐፊትን ምስክርነት፣ መሪነት እና ጥቆማ ይሻል፥ ከልሆነ ግን በራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ማድረስ አይችልም። ቅዱሳት መጽሐፍት በሰውና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ያሉ መንገዶች ናቸው፣ በቅዱሳት መጽሐፊት ብርሃን የሚመላለስ ሰው በመጨረሻ የሚደርሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፤ ያኔ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር እውቀት ይገኛል፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ያለው ሁሉ ነው፥ በሁሉ ነው። @TheDeepThingsOfGod @TheDeepThingsOfGod
Show all...
የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ነዉ፥ ምጡቅ አእምሮ ያላቸዉ ሰዎች ከራሳቸዉ ሃሳብ እና ፈቃድ አመንጭተው ያቀረቡልን የሰዎች ስራ ሰይሆን ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የተናገሩት እና የጻፉት የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ነዉ። @TheDeepThingsOfGod @TheDeepThingsOfGod
Show all...
እግዚአብሔር ራሱን የገለጠ እና የሚገልጥ አምላክ ነዉ! እግዚአብሔርን ማየት ትፈልጋለህ? አዎ ከሆነ መልስህ የት ሄደህ እግዚአብሔርን ማየት እንደምትችል እነግርሃለዉ፥ እግዚአብሔርን የማየት ጥልቅ ፍላጎት ከሌለህ ግን ይሄንን ጽሑፍ ማንበብ አቁም። እግዚአብሔር ራሱን የገለጠ አምላክ ነዉ፥ አዎ እግዚአብሔር ራሱን ሰዎች ማየት ወደሚቻላቸዊ ስፍራ አቅርቦል። እግዚአብሔርን ለማየት ልቡን ያዘጋጀ የትኛዉም ሰዉ ወደዚህ አይኖቹን ማቅናት ነዉ የሚጠበቅበት ከዚያም እግዚአብሔርን ማየት እና ማወቅ ይጀምራል። ታዲያ ምንድነው? ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ መልሴ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ!። እግዚአብሔር እራሱን የገለጠበት መንገድ እና ስፍራ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ ---"እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፤ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር።" -1ኛ ሳሙኤል 3፥21 "እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር" ---እነዚህ ቃላት በግልጽ የሚነግሩን እግዚአብሔር ራሱን በቃሉ እንደገለጠ ነዉ። ‘የእግዚአብሔር ቃል’ የሚለው ሐረግ በመጀመሪያ የተጻፉትን ቅዱሳት መጽሓፍት (the written word of God, scriptures) ወይም መጽሐፍ ቅዱስን እናም በመቀጠል ኢየሱስ ክርስቶስን (the personal word of God) የሚገልጽ ነዉ። እግዚአብሔር በመጀመሪያ በቅዱሳት መጽሐፍት ከዛ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎች እርሱን ማየት እንዲችሉ ራሱን ገልጦል። ከቅዱሳት መጽሐፍት ጋር ሰፊ ጊዜ ስናሳልፍ የእግዚአብሔርን ስም፣ ስራ፣ ሃሳብ፣ ፈቃድ፣ እቅድ፣ ፍላጎት፣ የሚወደውን እና የሚጠላዉን ሁሉ ማወቅ ድምዑንም መስማት ይሆንልናል፤ በመቀጠልም ስንታዘዘው ከማወቅ እና ከመስማት አልፈን ማየት እንጀምራለን፥ የልብ አይኖቻችን ዘላለማዊ ፊቱን ማየት ይጀምራሉ። በማንበብ እና በመስማት ማወቅ የጀመርነውን እግዚአብሔርን በማየት እና በልምምድ (experience) በማወቅ እንቀጥላለን። ቅዱሳት መጽሐፍት የዚህ ታላቅ እና ዘላለማዊ ጉዞ መጀመሪያዎች ናቸዉ፥ በቀጣይነትም ከእግዚአብሔር ጋር እንድንሄድ የሚያስችሉን እነርሱ ናቸዉ። @TheDeepThingsOfGod @TheDeepThingsOfGod
Show all...
Show all...
TikTok · Victor_M

Check out Victor_M's video.

መገለጥ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ በአንድ ጊዜ የመገኘት በሕሪይ (omnipresent) አምላክ ነዉ። “ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።” — ኤርምያስ 23፥24 እግዚአብሔር አሁን በለንበት አለ! ይሄንን ታዉቃላችሁ? መዝሙር 139 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ⁸ ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። ⁹ እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ ¹⁰ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች። ብዙዎች እንደሚመስላቸዉ እግዚአብሔር በሰማይ የተቀመጠ አምላክ ብቻ አይደለም ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ቃል እርሱ አጽነፈ-ሰማዩን ሁሉ የሞላ እንደሆነ ይናገራል፥ በሁሉም ቦታ መገኘቱ ለአምላክነቱ ማረጋገጫ ሆኖም በዋናነት የሚጠቀስ በሕሪይ ነዉ። ታዲያ እንዴት ነዉ ይሄንን በልምምድ( experience ) ማወቅ የሚቻለዉ? መገለጥ የሚለዉ ቃል የሚመጣው እዚህ ጋር ነዉ። እግዚአብሔርም ሆነ የእግዚአብሔር ነገሮች በአእምሮ (reasoning) ወይም/እና በስምቶቻችን (feelings) ጨርሰን ማወቅም ሆነ መረዳት የምንችላቸዉ አይደሉም። የእኛ የማሰብ አቅም (reasoning) እጅግ የተወሰነ መሆኑን ለመረዳት በሕይወት ስንት ጊዜ ትክክል እንደሆንን አስበን የመረጥናቸው መልሶች ስህተት ሆነዉ እንዳገኘናቸዉ ማስተዋል በቂ ነዉ፥ ስሜቶቻችንም ተለዋዋጭነት ያላቸዉ እንደሆኑ ሁላችንም የምንረዳዉ ነዉ። በተወሰነ አእምሮ እና በተለዋዋጭ ስሜት ወሰን የሌለዉን እና የማይለወጠዉን አምላክ ለማወቅ የሚቻል አይደለም፥ ብዙዎች የሚሰሩት ስህተትም ይሄዉ ነዉ። እግዚአብሔር የሚታወቀዉ በመገለጥ ነዉ፥ ከጥንት ዘመን ጀምሮ በብሉይ ኪዳንም ሰዎች እግዚአብሔርን ማወቅ የቻሉት እግዚአብሔር እራሱ በዘጋጀዉ መገለጥ በሚባል መንገድ ነዉ። በአዲስ ኪዳንም ሐዋሪያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።”— ኤፌሶን 1፥17 --በማለት እግዚአብሔር የሚታወቀዉ በመገለጥ እንደሆነ ያስረዳል። የእኔም ጸሎት ይሄዉ ነዉ። እግዚአብሔር እርሱን እንድናዉቀው የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጠን እጸልያለሁ። @TheDeepThingsOfGod @TheDeepThingsOfGod
Show all...
Show all...
TikTok · Victor_M

Check out Victor_M's video.

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው፤ ዮሐንስ 21፥1
Show all...
Repost from TheDeepThingsOfGod
አባት ሆይ😭 ከአገልግሎት በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ከብዙ ተከታዮች በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ተጽዕኖ ፈጣሪ ከመሆን በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ከመውደድ በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! በዓለም ሁሉ እየዞሩ ከማገልገል በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ከማስተማር እና ተዓምራት ከማድረግ በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ታላቅ ሰው ከመሆን በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! የእግዚአብሔር ሰው ከመባል በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ዘመኔን በብልጽግና መጨረስ ከምፈልገው በላይ ኢየሱስን እፈልገዋለሁ! ከሁሉም በላይ ኢየሱስ ያስፈልገኛል እኔም እፈልገዋለሁ!😭 ልሰማው፣ ላየው፣ ልመለከተው እና ልዳስሰው እፈልጋለሁ! መንፈስ ቅዱስ እባክህ ኢየሱስን አሳየኝ😭 @TheDeepThingsOfGod @TheDeepThingsOfGod
Show all...
ዓላማ ከሌላቸዉ ሰዎች ይልቅ ለራሳቸዉ ዓላማ ፈጥረዉ የሚኖሩ ሰዎች የተሻሉ ናቸዉ፥ ከሁለቱም የሚልቁት እግዚአብሔር እነሱን በማህጸን ከመስራቱ በፊት ያዘጋጀላቸዉን ዓላማ አግኝተዉ የሚያደርጉት ናቸዉ። @TheDeepThingsOfGod
Show all...