en
Feedback
TheDeepThingsOfGod

TheDeepThingsOfGod

Open in Telegram

Glorious Church the bride of Christ. Rapture ready!

Show more
1 810
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ጥያቄ: እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን በዚህ ምድር ላይ ለመስራት ያሰበው ትልቅ እቅድ ምንድነው? የሚቀጥለው ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ አደራረግ(አሰራር) ምን ላይ ያተኮረ ይሆናል? ብዙዎች እንደሚሉት በቀላል ቃል የሚመጣው የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ(ሪቫይቫል) ምን አይነት ነዉ? ይህንን ጥያቄ መመለስ በጣም አስፈላጊ ነዉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና እቅድ ማወቅ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ-ሰራተኛ ለመሆን ያስችለናልና። መልሳችሁን በራሳችሁ አገላለጽ ኮሜንት አድርጉ ወይም @GFI777

የእግዚአብሔር ቃል + የእግዚአብሔር መንፈስ = እውነተኛ እና ቀጣይ ሪቫይቫል

ክርስቲያን ክርስቶስን የሚኖር ሰው ነዉ። -Victor

እኔ አይቻለሁ እትዮጵያ ምድር ላይ ክርስቶስን ራሱን የሚመስሉ ወጣቶች!🔥

የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች የእግዚአብሔር ሕይወት አላችሁ፤ ተራ ኑሮ ለመኖር እምቢ በሉ፥ ለእግዚአብሔር መንግስት ትልልቅ ስራዎች ለመስራት ወስኑ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ተጠቅማችሁ ሕይወታችሁን ፈጽሞ ለውጡ። Sons and daughters Of God, you have the life of God. Refuse to live an ordinary life and make a decision to do greater things for Gods kingdom, Use the word of God and transform your life. ነገ አደርጋለሁ የሚል እሳቤ ከአእምሮአችሁ አስወግዱ ጊዜው አሁን ነዉ ፥ ምክንያቱም ነገም የራሱ ነገ አለው፥ መደረግ ያለባቸውን ነገሮች አሁን አድርጉ። @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit

mehali:-via-inbox. ደስ ይላል !!! Open talk.. Representing Christ well..😭❤️ Victor ምን ማለት እንዳለብኝ አላቅም😭ብቻ ግን God ሲያወራኝ ነበር አንተ ካወራኸው አኩዋያ😭እና አሁን በቃ voicun ስሰማ ሙሉ ሆነልኝ።ሙሉ ሆነልኝ ስልህ በቃ Christ ሀሳቡን ደመደመልኝ።በቃ ምን ብዬ ልግለፀው አገኘውት በቃ።ባንተ በኩል ሆኖ በደንብ አድርጎ ነገረኝ በቃ። የህይወቴን ከዚህ በኋላ ያለውን መንገዴን ነው የቃኘው😭 አመሰግናለው😭😭😭😭 ከልቤ ወድሀለው❤️ No የኔ ጎደኝነት አይደለም😭😭የኔ እሱን መጋበዝ እይደለም😭it's all about Jesus😭

በ-inbox የተላከልኝ ስለ Open talk. ደስ ይላል!!! Victor Egziabher yebarkh About the open talk. I am going to listen to it #again and #again. Accurate and precise yehone ngr new yetenagerkew. Becha betam new desyalegne Be Blessed more and more. Yeah ye lay lay hiwet bibekan ena Ye ewnet menor benjemr tru new. Thankyou so much.

አሁን ስሙኝ...

ክርሲቲያን ለማያምኑ ሰዎች ያለውን ፍቅር የሚገልጥበት ትልቁ እና የመጀመሪያው መንገድ ወንጌልን ማጋራት ነዉ። -Victor

ኢየሱስን ያላየ ሰው አይኑን መጠቀም አልጀመረም። -Victor

ይሄንን open talk በንጹሕ ልብ ስሙት ሕይወታችሁን ይለውጠዋል፥ እኔ እራሴ ደጋግሜ እየሰማሁ ነዉ።🙌 +SHARE አድርጉ...

የማታውን መልእክት በተመለከተ በ-inbox ከተላኩልኝ አንዱ ነዉ፤ ደስ ይላል!!! 👇 Today's message 🙏😭❤️I have heard it three times. This voice has changed my life Yes i am Christs ambassador. GBU Victor.

ይሄ ትንሽ ጠንከር ያለ ንግግር እንደሆነ አውቃለሁ😂...ይሄንን ስሰሙ አንዳንዶች ይሄንን ቻናል ለቀው እንደሚወጡ አውቃለሁ እውነት ግን አይለወጥም። ኢየሱስ እንጀራው እኔ ነኝ እኔን ብሉኝ ዛሬ ስል ከ ተወሰኑ ሰዎች በስተቀር ሺዎች ተበተኑ😂 እውነት ነዋ። እግዚአብሔር የሳበው ግን ኢየሱስን ያየዋል። ሰዎችን ለማስደሰት የምናደርገው 1 ነገር የለም🙌

ሐዋሳ ያላችሁ በቅርቡ ተዘጋጁ! ጥልቅ የትምህርት፣ የትንቢት፣ የነጻ መውጣት እና ፀጋን የማካፈል ጊዜ ይኖረናል። "ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውን እናገራለሁ"

በጌታ ያልሆነ ሰው:- ከአንተ ወዳጅነት በላይ የኢየሱስ አዳኝነት ያስፈልገዋል። ከጓደኝነትህ በላይ ሰባኪነትህ ያስፈልገዋል። ከካፌ ግብዣህ በላይ አንተ ጋር ያለው ወንጌል ያስፈልገዋል። ከቀልድህ በላይ በልብህ ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያስፈልገዋል። የኢየሱስ አዳኝነት እንጂ የአንተ ወዳጅነት ከዘላለም ሞት አያድነውም፥ በልብህ ያለው ወንጌል እንጂ የካፌ ግብዣህ አይለውጠውም፥ የተቀበልከው የእግዚአብሔር እውነት እንጂ ጓደኝነትህ ከኃጢአት ባሪነት ነጻ አያወጣውም። ወንጌልን በግልጥ ስበክ!

Open talk😁🥰 ክርስቶስን በሚገባው መልኩ መወከል! Representing Christ well..... 〽️ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 〽️ @TheDeepThingsOfGod @TheDeepThingsOfGod

የእኛን ቻናል መቀላቀል እና እዚህ መቆየት በእውነት በረከት ነዉ! ኩሩ የ @TheDeepThingsOfTheSpirit ቻናል አባል እና አካል ከሆናችሁ መልእክቶቹን እና ሊንኩን ለወዳጆቻችሁ አጋሩ!

Joining and being in our channel is truly a blessing! If you are a proud member of @TheDeepThingsOfTheSpirit share our messages and the link to your friends, now!

ሰማይ ሰማይ እጅግ በጣም የሚያስገርም ድንቅ መንፈሳዊ ስፍራ ነዉ፥ ከተወሰነ ጊዜ በፊት በእግዚአብሔር ፀጋ የመጀመሪያው ሰማይ ውስጥ መመልከትና መስማት ያለብኝን ነገር እንዳይ እና እንድሰማ በእግዚአብሔር መልአክ ተወስጄ ነበር፥ የፀሃይ ክብር ከጨረቃ የተለየ እንደሆነ ሁሉ እያንዳንዱ ሰማይ የራሱ የሆነ ክብር አለው። እኔ የተወሰድኩት ወደ መጀመሪያው ሰማይ ነበር በዚያም "የእግዚአብሔር ልጆች" የሚባሉ የመልእክት ነገድ ነበሩ አሁን በጽሑፍ የማልገልጻቸውን ነገርች ተመልክቻለሁ፥ መንፈሳዊ ዓለም ላይ የጊዜ ጽንሰ-ሃሳብ ተግባራዊ ስላልሆነ ምድር ላይ ብትሆኑ ለመመልከት እና ለማወቅ ዓመታት የሚፈጅባችሁን ነገር 'ምንም ወይም ዜሮ' በሚባል ጊዜ ማወቅ ትችላላችሁ። እኔ በዚያ የነበርኩት በሰዓት ከሰላነው የተወሰነ ደቂቃ ነዉ፥ ያገኘሁት እና የተማርኩት ግን በዓመታት ላገኘው የማልችለውን ነዉ፥ ስለነዚህ ነገሮች ለማውራት ጊዜ ያጥረኛል። በጣም የደነቀኝ ሰማያት የተሰሩበት ክብር ነው፥ በዚያ ስመለከት በፊት ስለ ሰማይ የነበረኝ አመለካከት ተለውጧል፤ መጽሐፍ ቅዱስ “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ።”— መዝሙር 19፥1 በማለት የተናገረው ምን ማለት እንደሆነ የተረዳሁት የዚያን ቀን ነዉ፥ እኔ በአንደኛው ሰማይ እንደተመለከትኩት ሁሉም ነገር ይናገራል፥ የተመለከትኳቸው የመላእክት ነገድ የተሰበሰቡበት ስገባ ቀድሞ አይኖቼ የተመለከቱት የአዳራሹን ግድግዳ ነበር እጅግ በጣም ግሩም ነው በእኔ አገላለጽ "ግድግዳው ሕይወት አለው" ነበር ያልኩት፥ ሕይወት ያለው ግድግዳ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ሕይወት ያለው እቃ አይታችሁ ታውቃላችሁ? በቃላት የማይገለጽ ነዉ። 100 ዓመት በዚያ ብቆይም እንኳ አይኖቼን ከግድግዳው ላይ የማነሳ አልመሰለኝም፥ ከዚህ መረዳት የቻልኩት ሰማይ ከምንገምተው በላይ እግዚአብሔር በፈቃዱ መገኘት የሞላው ቦታ መሆኑን ነዉ። ሰማይ ስትሄዱ ብዙ ነገር ለማየት አትፈጥኑም፥ መጀመሪያ የተመለከታችሁት ነገር ላይ ዘመናት ቢፈጅም አይሰላቻችሁም። የዚህ ምስጢር ግን ምንድነው? ሰማይ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ነገር ሙሉ ለሙሉ ልብ የሚገዛው እና የማይሰለቸው ለምንድነው? ምክንያቱ ይሄ ነዉ 'ሰማይ እግዚአብሔር ሕልውናውን በፈቃዱ የገለጠበት እና ያኖሩበት ስፍራ" መሆኑ ነዉ። አንድ ታላቅ የእግዚአብሔር ድምፅ እንደዚህ ያለው ትዝ ይለኛል "ሰማይን ሰማይ ያደረገው የእግዚአብሔር ሕልውና ነዉ፥ እግዚአብሔር ሕልውናውን ሙሉ በሙሉ ከሰማይ ከልክሎ ገሃነም ውስጥ ቢያደርገው ገሃነም ሰማይ ይሆን ነበር እናም የሁላችንም ጸሎት ገሃነም ለመድረስ ይሆን ነበር" በማለት ሰማይን ሰማይ ያደረገው የእግዚአብሔር ሕልውና እንደሆነ በጠለቀ መረዳት ገልጿል። እግዚአብሔር በፈቃዱ የሚገለጥበት የትኛውም ስፍራ እንደሰማይ ነዉ። ሰማይን ሰማይ ያደረገው ሕልውናው ነዉ፥ ይሄ ማለት የእግዚአብሔር ሕልውና በሰማያት በፈቃዱ እንደሆነ ሁሉ በእናንተም ሕይወት ከሆነ እናንተ ራሳችሁ እንደሰማይ ናችሁ። የእግዚአብሔር ሕልውና መንፈሳችሁን፣ ነፍሳችሁን እና ስጋችሁን እንዲሞላ እጸልያለሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን። 〽️ 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺 〽️ @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit