cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tana haik secondary school

Show more
Advertising posts
1 479
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ውድ የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ‼️ ✅የ 2015 የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት እስከ መስከረም 15 ድረስ ይፋ ይሆናል መባሉ ይታወሳል። 🧡ስለዚህ ተማሪዎች ይሄንን ውጤት ለማየት በጉጉት ይጠብቃሉ። ውጤቱ በሚለቀቅበት እለት #ኔትወርክ መጨናነቅ በጣም ይፈጠራል ። 🧡አብዛኛውን ጊዜ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስሉ #Internet ቤቶች ላይ ተሰልፈው የመጨናነቅ ስሜት ውስጥ ይገባሉ። 🧡ለተማሪዎች ውጤታቸውን በፈጣን 5G Internet ያለምንም ክፍያ ለማሳየት አንድ #መስፈርት አስቀምጠናል። መስፈርቱም ይሄን ቻናል Join ማድረግ ነው ሲለቀቅ በ comment section ላይ በመጠየቅ ወዲያው ማየት ትችላላቹ፡፡ 🎯 👇፨ለጥቆማ እና ለፈጣን መረጃ 👇 #For more join our telegram channel                                                             @ministryofeducationinfo @ministryofeducationinfo                                                                                                                                                                                                                               CLICK JOIN BUTTON ✅👇💯
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በ2015 ዓ.ም ከ91 ተቋማት የመጡ 4,413 የትምህርት ማስረጃዎችን ማጣራቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ። የማጣራት ሥራ ከተደረገባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ውስጥ 3 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት ሐሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል። ውጤት መቀየር፣ ያልተማሩበትን የትምህርት ማስረጃ መያዝ እና ሌሎች ሐሰተኛ መረጃዎች መገኘታቸውን በአገልግሎቱ የዲጂታል ትምህርት መረጃ አስተዳደርና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደሳለው ታፈሰ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ሐሰተኛ ሰነዶችን ማምከንና ግለሰቦቹን ከሥራ በማገድ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ተቋማት ሠራተኞችን ሲቀጥሩና የደረጃ እድገት ሰሲጡ የትምህርት ማስረጃዎችን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ኃላፊው አሳስበዋል፡፡ #FBC መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! https://t.me/+A2s5HvD0sO9lOGY0 https://t.me/+A2s5HvD0sO9lOGY0
Show all...
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መቼ ይገለፃል ? የቀጣይ አመቱ ፈተናስ በየትኛው ካሪኩለም ይሰጣል ? የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስከ  መስከረም 2016 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ይፋ ለማድረግ እቅድ መያዙ ታውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ በማድረግ በጥቅምት ወር የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲጀመር የማድረግ ዕቅድ መያዙን ከሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ በ2015 ዓ.ም. በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች ባለመፈተናቸው ዘንድሮ መጨረሻ ድረስ ተፈትነው እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በጎንደር በነበረው ግጭት ወቅት ፈታናዎቹን ያልወሰዱት በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደነበሩ የሚዘነጋ አይደለም። በሌላ መረጃ ደግሞ ፤ በቀጣይ ዓመት 2016 ዓ/ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አዲሱ እና የቀድሞው ካሪኩለም ድብልቅ ፈተና እንደሆነ ታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ቀጣይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆኑ እስከ 11ኛ ክፍል የተማሩት በድሮው ካሪኩለም መሆኑን ገልጸው በቀጣይ አመት የሚማሩት ግን በአዲሱ ካሪኩለም መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ የሽሽግር ስራ በሚሰራበት ወቅት ብሔራዊ ፈተናው ተደባልቆ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። ከታች ያሉትን በድሮው ካሪኩለም አሁን ገብተው የሚማሩትን በአዲሱ ካሪኩለም ተደርጎ ነው ፈተናው የሚዘጋጀው በዚህ ላይ ችግር አይፈጠርም ብለዋል። በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! https://t.me/+A2s5HvD0sO9lOGY0 https://t.me/+A2s5HvD0sO9lOGY0
Show all...
ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ላልወሰዱ ከ18 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በጎንደር፣ በጋምቤላ፣ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች 17,753 ተማሪዎች እንዲሁም 300 በውጭ ሀገራት ለሚገኙ ተማሪዎች ፈተናው እንደሚሰጥ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለኢዜአ ተናግረዋል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሦስት መፈተኛ ጣቢያዎች ሲፈተኑ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል ከ16 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሁለት እስከ ሦስት የትምህርት ዓይነቶች ሳይፈተኑ መቅረታቸውን አስታውሰዋል። በጋምቤላ ደግሞ ከ100 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ አልወሰዱም ብለዋል። በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 982 ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናው ይሰጣል ብለዋል። በውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ 300 ተማሪዎች ከዛሬ ነሐሴ 28/2015 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 02/2015 ዓ.ም ፈተናው ይሰጣል። ለዚህም የፈተና ጣቢያ አስተባባሪዎች ከኢትዮጵያ ፈተናው ወደሚሰጥባቸው ሀገራት መጓዛቸውን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። #ENA መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! https://t.me/+A2s5HvD0sO9lOGY0 https://t.me/+A2s5HvD0sO9lOGY0
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የጣና አጥር ትውስታ
Show all...
24/11/2015ዓ.ም ለጣና ሀይቅ አጠ /2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ የት/ቤቱ ቤተ መጽሐፍ ክፍል ሁል ጊዜ ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት ቀናት ክፍት ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ስለሆነ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በድጋሚ እናሳስባለን። ት/ቤቱ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.