en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Dr. Tesfaye Robele

Dr. Tesfaye Robele

Open in Telegram

ተስፋዬ ሮበሌ (ዶ/ር) ሥነ መለኮት እና ፍልስፍና ያጠና ባለ ጥልቅ እውቀት አቅብተ እምነት ነው። ሥነ መለኮትን እና ፍልስፍናን ለመማር ከፈለጉ ይቀላቀሉን። ይህ ቻናል የራሱ (የዶክተር ተስፋዬ) አይደለም፤ ነገር ግን እኛ መውደዳችንን ለመግለፅና ሰው ሁሉ የእርሱን ጽሑፍ ወይም ቪድዮ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ካለን ፍላጎት የተከፈተ ነው። Ethiopia No: +251921319299 @chereGC

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Dr. Tesfaye Robele

Channel Dr. Tesfaye Robele (@tesfayerobele) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 10 357 subscribers, ranking 8 908 in the Religion & Spirituality category and 3 312 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 10 357 subscribers.

According to the latest data from 28 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 32 over the last 30 days and by 3 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 33.48%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects N/A% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 468 views. Within the first day, a publication typically gains 0 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 164.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“ተስፋዬ ሮበሌ (ዶ/ር) ሥነ መለኮት እና ፍልስፍና ያጠና ባለ ጥልቅ እውቀት አቅብተ እምነት ነው። ሥነ መለኮትን እና ፍልስፍናን ለመማር ከፈለጉ ይቀላቀሉን። ይህ ቻናል የራሱ (የዶክተር ተስፋዬ) አይደለም፤ ነገር ግን እኛ መውደዳችንን ለመግለፅና ሰው ሁሉ የእርሱን ጽሑፍ ወይም ቪድዮ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ካለን ፍላጎት የተከፈተ ነው። Ethiopia No: +251921319299 @chere...”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 29 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

10 357
Subscribers
+324 hours
+217 days
+3230 days
Posts Archive
Norman L. Geisler (1932 – 2019)
Norman L. Geisler (1932 – 2019)

ከዐሥራ ሁለት ዓመት በፊት፣ በሰሜን አሜሪካ እየታተመ የሚሠራጭ፣ “ተስፋ” የሚባል የምርምር መጽሔት (Journal) አዘጋጅቼ ማሳተምና ማሠራጨት ጀምሬ ነበር! አይ የእኔ ነገር!
ከዐሥራ ሁለት ዓመት በፊት፣ በሰሜን አሜሪካ እየታተመ የሚሠራጭ፣ “ተስፋ” የሚባል የምርምር መጽሔት (Journal) አዘጋጅቼ ማሳተምና ማሠራጨት ጀምሬ ነበር! አይ የእኔ ነገር!

ውድ ወንድሞና እኅቶቼ ‍እንኳን ለዐዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! ዐዲሱ ዓመት ብዙዎች ወደ ጌታ የሚመጡበት፣ ጌታን ያወቅነው በቃሉና በምግባር የምናድግበት እንዲሆን እመኛለሁ! እጸልያለሁም! እወዳችኋ
ውድ ወንድሞና እኅቶቼ ‍እንኳን ለዐዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! ዐዲሱ ዓመት ብዙዎች ወደ ጌታ የሚመጡበት፣ ጌታን ያወቅነው በቃሉና በምግባር የምናድግበት እንዲሆን እመኛለሁ! እጸልያለሁም! እወዳችኋለሁ! ተባረኩልኝ! “ጌታ ሆይ፤ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።” (መዝሙር 90:1-2 አመት)

የዛሬ ሪፓርት ከተስፋዬ ሮበሌ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባቀረቡት የርዳታ ጥሪ መሠረት ዛሬ በውስጥ መስመር አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ዶላር ተሰብስቧል። ስጦታችሁን +16166174746 እንዲሁም በGo
የዛሬ ሪፓርት ከተስፋዬ ሮበሌ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባቀረቡት የርዳታ ጥሪ መሠረት ዛሬ በውስጥ መስመር አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ዶላር ተሰብስቧል። ስጦታችሁን +16166174746 እንዲሁም በGoFundMe (https://gofund.me/39a7427d6) መስጠት ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ፈቃዱ ከሆነና በዚህ መጠን በልግስና የሚሰጡ ሰዎች ከተገኙ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ ይህን መጽሐፍ እንደምናዳርስ እሙን ነው! ይህ ($1,300) ዛሬ በውስጥ መስመር የተሰበሰበው ብቻ እንደ ሆነ ልብ ይሏል! እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

በውስጥ የደረሰኝ መልእክት!
በውስጥ የደረሰኝ መልእክት!

በውስጥ የደረሰኝ መልእክት! ዶ.ር እንዴት ቆየክ ? ሁሉ ሰላም ነው ? ቤተሰቦችህ ፣ ልጆች ፣ አገልግሎት ፣ ስራ ሁሉ እንዴት ነው ? ሁሉም በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት መልካም እንደሆነ እርግጠኞች ነን። Dr. እኔ ይሁን ኢያሱ እባላለሁ። በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሳር ካምፓስ የ 4ኛ ዓመት የህክምና(Medicine ) ተማሪ እና አሁን ላይ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሳር ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በሰብሳቢነት የማገለግል መሪ ነኝ። Dr. ይህንን መልእክት ልጽፍልዎት የደፈርኩት አንድ ትንሽ ጥያቄና ልመና ስላለን ነው። እርስዎ የጻፏቸውን መጽሐፍት ተማሪዎች በማንበብ እንዲማሩና በእምነታቸውም እንዲያድጉ በጣም ፍላጎት አለን። በተለይም በፌሎሺፓችን ውስጥ ብዙ ተማሪዎች መጽሐፍትን ለማንበብ ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ በኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸው ምክንያት መጽሐፍትን መግዛት አይችሉም። ስለዚህ Dr. በትህትና ልንጠይቅዎት የፈለግነው፣ ከመጽሐፍትዎ የተወሰኑ ቅጂዎችን ለፌሎሺፓችን ልትለግሱልን ብትችሉ በጣም ትልቅ ስጦታ ይሆንልናል። እኛ የምንፈልገው ለግል ጥቅም ወይም ለሽያጭ ሳይሆን በፌሎሺፓችን ውስጥ በ Financial አቅም ማጣት ምክንያት መፅሐፍ ገዝተው ማንበብ ለማይችሉ ልጆች አንድ ትንሽዬ ቤተ-መጽሐፍት መጀመር እንፈልጋለን። መጽሐፍቱን መግዛት የማይችሉ ተማሪዎች በነፃ እንዲያነቡ፣ እንዲማሩባቸውና የተማሩትንም በሕይወታቸውን እንዲገነቡ ነው ዓላማችን። Dr. አንድ ተማሪ የእርሶን መጽሐፍ አንብቦ ቢማርና ቢባረክ ነገ ለብዙ ሰዎች ሊተርፍ ይችላል ብለን እናምናለን። ስለዚህ ከእጅዎ የሚመጣ ማንኛውም መጽሐፍ፣ ብዛቱ ምንም ይሁን ምን፣ ለእኛ ትልቅ ዋጋ አለው። እርስዎ ያደረጉትን ይህንን አገልግሎት እናከብራለን። ስለዚህ ይህንን ጥያቄ ስናቀርብ በጣም በትህትና ነው። የሚችሉ ከሆነ ከመጽሐፍትዎ የተወሰኑትን ለፌሎሺፓችን በልግስና ቢሰጡን እኛም በዩኒቨርስቲ ግቢያችን ለተማሪዎች በረከት እንዲደርስ ብናስችል። ይህ ለእኛ ብቻ የሚደረግ እርዳታ ሳይሆን፣ እነዚህን መጽሐፍት ለሚያነቡ ብዙ የዩኒቨርስቲ ወጣቶች እና በኋላ ለሚያገለግሉት ሰዎች የሚደርስ የእውቀትና የመንፈሳዊ ውርስ እንደሚሆን እናምናለን። ጊዜዎን ወስደው ይህንን መልእክት ስላነበቡልን በጣም እናመሰግናለን Dr. እግዚአብሔር በጽሑፍ አገልግሎትዎ ብዙ ሕይወቶችን እንዲነካ እና እንዲጠቀምዎት ጸሎታችን ነው። ይሁን ኢያሱ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሳር ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት ሰብሳቢ አረንጓዴው መጽሐፍ ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት የምትፈልጉ በgofundme ተሳተፉ!

"... ዕለት በዕለት “አምላክ እንዲህ ይልሃል…” መባል የለመደ ሰው፣ ለምን ብሎ መጽሐፍ ቅዱሱን ያነባል? ክርስቲያን ቅዱሳት መጸሕፍትን የሚያነበው መለኮታዊ ዕውቀት ለመቅስም ብቻ ሳይሆን፣ መለኮታዊ
"... ዕለት በዕለት “አምላክ እንዲህ ይልሃል…” መባል የለመደ ሰው፣ ለምን ብሎ መጽሐፍ ቅዱሱን ያነባል? ክርስቲያን ቅዱሳት መጸሕፍትን የሚያነበው መለኮታዊ ዕውቀት ለመቅስም ብቻ ሳይሆን፣ መለኮታዊ ምሪት ለማግኘት ጭምር ነው፡፡ አምላክ አፍ ለአፍ፣ ዕለት በዕለት ይናገረኛል የሚሉ፣ ዐይነ ደረቅ ቈርጦ ቀጥሎች እንደ ጭስ አፍነውት፣ በምን ቀዳዳ ቃለ እግዚአብሔርን የማጥናት ትንፋሽና ብርታት ሊያገኝ ይችላል? ብዙዎች በውል ያላስተዋሉት ትልቁ እንቈቅልሽ ይህ ነው፡፡ ... ክርስቲያኖች ሁሉ ካህናት ናቸው።ከዚህም የተነሣ ያለ አንድ መካከለኛ ክርስቶስ ኢየሱስ ዘንድ በቀጥታ መቅረብ ይችላሉ ፤ አምላክን ማናገር ይችላሉ'' የሚለውን ትምህርት በማመናችን ከካቶሊክና ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተለይተን ነበር። ዛሬ ግን የታሪክ ምጸት ወድቆብን አባይ ነባዮችን የየቀን ካህን አድርገን ሹመናል። አባይ ነባይ ``የየቀን ውሎህን ወለል አድርጌ እነግርሃለሁ'' የሚለው ትውልድ ከቅዱሳት መጻሕፍት የመሟገት ዐቅም ከየት ሊያመጣ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት በመሄድ በኩረ ጽሑፋትን ለመመርመር ብርታቱን ከየት ሊያገኝ ይችላል? የሕይወት ፍልስፍናውን ለማጥለል ሊቃውንትን መጻሕፍት በምን ጉልበት ይመረምራል? መጠይቃዊ ህይወትንስ የጉዞ መስመሩ እንዴት ማድረግ ይቻለዋል? ይህን እንቆቅልሽ በትክክል ሳንፈታና ሳናስፈታ ትውልዱን በትክክል ማገልገል እንችላለን ማለት ሲበዛ ዘበት ነው።ይህ ሁነኛ ጥያቄ በትክክል የማይመለስ አገልግሎት ለትውልዱ ነቀርሳ ፍቱን መድኀኒት ሊያመጣ አይችልም። አባይ ነባይ [ዶ/ር Tesfaye Robele ፤ ገጽ 12]

በእነዚህ ቍጥሮች ልታገኙን ትችላላችሁ:- 0921319299 0911463670

“ሰማያዊ ሥጋ” ተስፋዬ ሮበሌ “ሰማያዊ” ሥጋ የሚባለው ኑፉቄ የተክሌ ዘሀገረ ጮማ እምኒ ግኝት ነው! ዛሬ በዓለም ላይ ይህን ትምህርት የሚያስተምር ብቸኛ የዓለማችን ድርጅት የኢትዮጵያው “Only Je
+2
“ሰማያዊ ሥጋ” ተስፋዬ ሮበሌ “ሰማያዊ” ሥጋ የሚባለው ኑፉቄ የተክሌ ዘሀገረ ጮማ እምኒ ግኝት ነው! ዛሬ በዓለም ላይ ይህን ትምህርት የሚያስተምር ብቸኛ የዓለማችን ድርጅት የኢትዮጵያው “Only Jesus” ኑፋቄ ነው! አረንጓዴው መጽሐፍ ስለ ሰማያዊ ሥጋ ሰፊ ትምህርት አለው (ገጽ 377-446)! አንብቡ፤ አስነብቡ! የወንጌልን እውነት ጠብቁ ፤ አስጠብቁ! ለበለጠ መረጃ እነዚህን ስልኮች ተጠቀሙ:- 0921319299 0911463670

ጠቃሚ መረጃ! ብዙዎች እውነትን እያወቁ ውሸትን እያፈረሱ ነው! እርስዎም በአካባቢዎ ብርሃንና ጨው ይሁኑ! አረንጓዴው መጽሐፍ በብዙ የአገሪቱ አካባቢዎች በትጋት እየተጠና ነው! በእናንተም አካባቢ ማጥናት የምትፈልጉ ሰዎች ተሞክሮቸውን የሚያጋሩ ወገኖችን ልናገናኛችሁ እንችላለን!

photo content
+5

photo content
+9

photo content
+9

ዐርብ ዕለት ጥናታዊ ጽሑፍ አቀርባለሁ! የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ለዐሥራ ሦሰተኛ ጊዜ በአትላንታ ባዘጋጀችው ዐውደ ጥናት ላይ፣ “የቤተ ክርስቲያን አባቶች (አብዛኞቹ) የውሃ ጥምቀት ለድ
+2
ዐርብ ዕለት ጥናታዊ ጽሑፍ አቀርባለሁ! የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ለዐሥራ ሦሰተኛ ጊዜ በአትላንታ ባዘጋጀችው ዐውደ ጥናት ላይ፣ “የቤተ ክርስቲያን አባቶች (አብዛኞቹ) የውሃ ጥምቀት ለድነት ወሳኝ ነው ማለታቸው፣ የውሃ ጥምቀት የድነት ቅደመ ሁኔታ አይደለም ከሚለው ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አስተምህሮ አንጻር እንዴት ይብራራል!” ለሚለው ጭብጥ ታሪካዊና ነገረ መለኮታዊ ትንታኔ አቀርባለሁ! ይህ ጥያቄ የእኔም ጥያቄ ነው የምትሉ የአትላንታ ነዋሪዎች በዚህ ዐውደ ጥናት ተሳተፉ!

የዕቅበተ እምነት መጻሕፍት ለተማሪዎች እንዲደርስ እንፈልጋለን የምትሉ፣ በዚህ GoFundMe እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን! https://gofund.me/303724e1d 👆 👆 👆 See
የዕቅበተ እምነት መጻሕፍት ለተማሪዎች እንዲደርስ እንፈልጋለን የምትሉ፣ በዚህ GoFundMe እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን! https://gofund.me/303724e1d 👆 👆 👆 See less

ጽሑፎቼን ከሚከተለው ደረ ገጽ ላይ በቀጥታ በነጻ ማንበብ ትችላላችሁ! https://substack.com/@tesfayerobele951743?r=1rik0m&utm_medium=ios&utm_source=stories&shareImageVariant=light

የዕቅበተ እምነት አገልግሎት ዕውቅና ፕሮግራም (ባለፈው ዓመት) Jul 27, 2025 https://youtu.be/cQCCZNHWkiM

ይህ GoFundMe የተከፈተው ለመጻሕፍት ሥርጭት ነው! በተለይ የኮሌጅ ተማሪዎች እነዚህን የዕቅበተ እምነት መጻሕፍት እንዲያገኙ ነው! ስለዚህ በዚህ ትልቅና ክቡር ተግባር ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል! ጌታ ይባርካችሁ! https://gofund.me/8da28cf61

ተጋባዛችኋል!
ተጋባዛችኋል!

እግዚአብሔር ፍቅር ነው! ከተስፋዬ ሮበሌ ፍቅር የሌለበት አገልግሎት ሁሉ ሿሿታ ነው (1ቆሮ. 13፥1)። ዕውቀት ቢሆን ይሻራል፤ ትንቢትና ልሳንም ቢሆኑ ይቀራሉ (ቁ. 8 )። በጀግንነት የተሞላ ነገር ግን ፍቅር የሌለበት አገልግሎት ሁሉ ከንቱ፣ ከንቱ፣ ከንቱ፣ የከንቱም ከንቱ ነው (እባክዎን 1ቆሮንቶስ ምዕራፍ 13ን በጥሙና ያንብቡ፤ “በጀግንነት የተሞሉ” ያልኋቸው አገልግሎቶች ምን እንደ ሆኑ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በስፋት ዘርዝሯቸዋል። እነርሱም ቢሆኑ ፍቅር ከሌለባቸው ከንቱ ናቸው)። ዕቅበተ እምነት ከሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች የተለየ አይደለም! እንዲያውም ዕቅበተ እምነት ፍቅርን በብርቱ የሚሻ አገልግሎት ነው! የሳተን ከስሕተቱ የሚመልስ አገልግሎት ነውና። ጌታ ሳምራዊቷን ሴት ከሳምራዊ እምነቷ እንዴት እንደ ታደጋት ልብ ይሏል (ዮሐ 4)! እንዲያውም በጎልጎታው ፍቅር የሚመራ ቀዳማይ አገልግሎት ቢኖር፣ ያ አገልግሎት ክርስቲያናዊ ዕቅበተ እምነት ነው! የዕቅበተ እምነት ግብ ሰዎችን ለክርስቶስ መማረክ ነው! ማንም ግን እንደ ተነቀፈና እንደ ተጠላ ካሰበ፣ ይጠላኛል ብሎ የሚያስበውን ግለሰብ እምነት ሊከተል አይፈልግም! ለዚህም ነው ሰዎች ክርስትናን ከክርስቲያኖች ነጥለው አይመለከቱም የሚባለው። ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ የጌታን ፍቅር ከማያሳይ ርኅራኄና ምሕረት ከሌለበት ማንኛውም አገልግሎት ራሳችሁን አርቁ! ፍቅር የርቱዕ ሃይማኖት መስፈሪያ (መለኪያ) ነው! በቅርቡ የአንድ ሃይማኖት መምህር “ግ.ደ.ሉ” እያለ ቁ.ራ.ና.ዊ ጥቅስ ሲናገር ሰምተናል! ክርስትና ግን ለወንድሞቻችሁ ሙቱ እንጂ ወንድሞቻችሁን ግደሉ አይልም! በክርስትና ወንድምን መጥላት እንኳ፣ እንደ ግደያ የሚታይ ትልቅ ወንጀል ነው! በማኅበራዊ ሚዲያ በርዕቱ ትምህርት ሽፋን እየተነገረን ያለው ግን (ሲዘረዘር) ግደሉ ነው! እውነተኛ ትምህርት ያክማል፣ ሕይወት ይሰጣል እንጂ አይገድልም! ሰይጣን ሊገድልና ሊያጠፋ ነው የመጣው! ጌታ ግን ሕይወት እንዲሆንልን እንዲያውም እንዲበዛልን ነው የመጣው (ዮሐንስ 10፥10)! ወገን፣ “አስወግደው” የሚልን አግልግሎት እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ ያስወግድልን! እውነትንና ሐሰትን ከምንለይበት መስፈርት መኻል አንዱ ፍቅር ነው! ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም! እግዚአብሔር ፍቅር ነውና! የሚያየውን ወንድሙን የማይወድ እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም (መልእክተ ዮሐንስ ቀዳማዊን አንብቡ—ስለ ፍቅር ሰፊ ትምህርት አለው)። የሁላችንም አገልግሎት ከዚህ አንጻር መመዘን አለበት! ፍቅር! ፍቅር! ፍቅር! ልጇን አኝካ ከምትውጥ ድመታዊቷ ዕቅበተ እምነት ራሳችሁን ጠብቁ! (እኔ “ድመታዊ ዕቅበተ እምነት” የምለው መበላላት የሰፈነበትን አገልግሎት እንጂ ግለሰቦችን እንዳልሆነ በፍቅር መግለጽ እሻለሁ)! ዕቅበተ እምነትና ፍቅር ጣራና ግድግዳ ናቸው! ሠናይ ወእቱ!