cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ

ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።

Show more
Advertising posts
16 462Subscribers
+424 hours
-127 days
+2930 days
Posts Archive
አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡ || ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን... * እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:- «አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል። ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል። : ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ። : እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል... ሃሃሃ! ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው... : ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ... (ያዝ እንግዲህ¡) በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው። ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት። ሃሃ! : ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት። ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ። ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል። ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው። እህእ! : ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ። ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ። : ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም። ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም። : አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ። እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ። ሃሃሃ! : ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ። በዚህ መልኩ ሁሉም ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...» ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ።
Show all...
😁 75🤣 32👍 25 17💔 2
እንኳን ለ 1,445ኛው የተከበረው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም በጤና አደረሳችሁ። አላህ ወሩን ተቀባይነት ያለው የዒባዳ፣ የዚክር፣ የዱዓና የቂርኣት ያድርግላችሁ።
Show all...
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተከበራችሁ ወንድሞችና እሕቶቼ! የአቦኪቾውን መስጂድ በተመለከተ የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉ በቪዲዮው ላይ የተለቀቀው አካውንት በደንብ ላልታያችሁ ይኸው ከታች በተፃፈው አካውት አስገቡ ማክሠኞ በተለመደው ሠአት እረሞዳን እንዴት እንቀበለው አጠር ያለ ደርስ በኡስታዝ አቡሀይደር እንዲሁም በኡስታዝ አብ ፈርሀን እርዝቅና ጋብቻ ( ትዳር ) እለቱ ለየት የሚያደርገው ሁለቱ አጋፋ ኡስታዞቻችን ይገኛሉ በዚሁም የኡስታዛችን መስጅድ ለማስጨረስ ፍንሺንግ ገቢ ማሠባሠብያ ይኖረናል ሁላቹ እንድትገኙ በአላህ ስም እንጠይቃቹሀለን እለቱ ማክሠኞ ማታ ቀን ከነ ቤተሠቦ ተጋብዞአል 27/02/2024 ሠአት ከምሽቱ በኤሮፕ 20.pm በኢትዮጵያ ከምሽቱ 4.00 ሠአት በዳሩ ቁራአን ዙም ምቲግ ሁላቹ እንድ ትገኙ Join Zoom Meeting https://us02web.zoom.us/j/6138373158?pwd=bFo5ZVFrcUpWbFV5YVNZMDlwZ2piQT09 Meeting ID: 613 837 3158 Passcode: 12345 እንዲሁም ቴሌግረም ቻናል መቀጥታ ይተላለፋል ሊኩ https://t.me/D_Q_2024 SADIK MOHAMMED AHMED 1000425034638 COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA ኡስታዝ ማናገር ከፈለጋቹ ስልክ ቁጥር 00251911 10 32 31 1011300008645 ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ 0014688820101 ZAMZAM BANK ABYSSINIA BANK 83047178 DASHEN BANK 2900714650011 01425212425200 Awash Bank Betel Branch 1001162290001 Hijra bank
Show all...
እጅግ በጣም …በጣም አስቸኳይ (በፈጣሪ ይሁንባችሁ ሼር በማድረግ እንተባበር) #አስቸኳይ_ነው_ሼር_አድርጉት ይህ የምታዩት የእጅ ፖርሳ በውስጡ ገንዘብ ( ዶላር ) እና ፓስፖርት እንዲሁም ቪዛን ጨምሮ ሌሎችንም ለባለ ንብረቷ ህይወት እጅግ አስፈላጊ እና ወሳኝ ከባድና ልዩ ልዩ ዶክመንቶችን እንዲሁም ስልክና ሌሎችንም በርከት ያሉ የቤተሰቧን ወሳኝ የግል ዶክሜንቶች ይዟል በፖርሳው ውስጥ ከተገኘው …ከፓስፖርቷና ከመረጃዎቿ ለመረዳት እንደሚቻለው ባለ ንብረቷ ስሟ… ሊዛ ኻሊድ አህመድ… ይባላል…ትውልደ ኢትዮጲያዊ ስትሆን የስዊዲን ዜግነት አላት በሙያዋ ነርስ ነች ይህንን ንብረቷን ያለፈው አርብ እለት ከሰአት 4:15 አካባቢ New York ኤርፖርት ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ወድቆ ያገኘው ሰው ንብረቷን በአማና ይዞ እያፈላለጋት እየጠበቃት ይገኛል እስካሁን ሊያገኛት አልቻለም …ንብረትና ዶክመንት የጠፋባት እህታችን ሙሐጅሩ መሃመድ አቡ ከውሰር ን በፌስ ቡክ ሜሴንጀሩ በኩል ወይም በቴሌግራም ቁጥር +966540941584 በማናገር ንብረቷን መረከብ ትችላለች ውድ ወገኖች እባካችሁ እህታችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ዶክመንቷን እና ንብረቷን ታገኝ ዘንድ ይሄንን መልዕክት ሼር በማድረግ እንተባበር 🙏
Show all...
ዐሹራእ ደረሰ በአቡ ሀይደር አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡ #ዐሹራእ ምንድነው? ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አስረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡ #ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡ ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አስረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡ #ለምን ይጾማል? ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡ ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡ #ጥቅሙስ ምንድነው? አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡ በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡ ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡ #መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና? የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡- እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡ #መቼ እንጀምር? የሙሐረም አስረኛው ቀን(ዐሹራእ) የፊታችን ጁምዓ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡- ሀ. ጁምዓ ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡ ለ. ሀሙስና ጁምዓ ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡ ሐ. ከ ሀሙስ-ቅዳሜ ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡ መ. ጁምዓና ቅዳሜ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው አላህ ይወፍቀን፡፡ #ስምንቱ የፆም ቀናት አላህ ፆምን ያገራለትና የወፈቀው ሰው ደግሞ ከፈለገ በተከታታይ ለስምንት ቀናት መፆም ይችላል፡፡ እንዴት ካሉም፡- ከሀሙስ-ቅዳሜ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐመረም 9ኛ 10ኛና 11ኛ ቀናት ስለሆኑ፡ ከዐሹራእ ፆም ጋር በተያያዘ መልኩ ይፆማሉ ማለት ነው፡፡ ሰኞ፡- ይህ 13ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡ ሰኞ -እሮብ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐረም 13ኛ 14ኛና 15ኛ ቀናት ናቸው፡፡ አያሙል-ቢድ በመባልም ይጠራሉ፡፡ የወሩን ሶስት ቀናት በነዚህ ቀናት መፆም በላጭ ነው፡፡ ሀሙስ፡- ይህ 16ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡ Click and Like ➤➤ http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
Show all...
እንኳን ለ 1,444ኛው የዒዱል አድሓ በዓል አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!! ጌታ አላህ ዒዱን የተባረከ፣ የመደሰቻ፣ ምስኪኖችንም የማስደሰቻ ቀን ያድርግላችሁ። ዒዱኩም ሙባረክ፣ ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም
Show all...
ይህ የቁርኣን አፕ ቁርኣንን በምትቀሩበት ጊዜ ስህተቶችን እንድታርሙ ይረዳችኋል
Show all...
ለዶ/ር ሁንዴ አህመድ ልጅ የድጋፍ ጥሪ እንደሚታወቀው ወንድማችን ዶ/ር ሁንዴ አህመድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት  እና የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የጅማ ቅርንጫፍ  ፕሬዝዳንት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። ልክ እለተ ዓርብ ጥዋት ነበር ውድ ባለቤቱ ዘጠኝ ወራትን በሆዷ ታቅፋ የከረመችውን ወንድ ልጃቸውን በሰላም በመገላገሏ ደስታቸው ወደር የለሽ ነበር።  ታድያ ይህ ደስታቸው በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ትካዜ ተቀየረ። የተወለደው ህፃን ትንፋሽ ያጥረውና መታገል ሲጀምር በተደረገለት ምርመራ በሚያሳዝን ሁኔታ በተፈጥሮ የሚከሰት የልብ ችግር “ Transposition of Great Arteries”  (የታላቅ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ቦታ መቀያየር) እንዳለበት ታወቀ።  ህክምናው ከፍተኛ ወጪ የሚፈልግ በየደረጃው የሚደረግ የልብ ቀዶ ጥገና በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈር ተደርግዋል። የመጀመሪያው ደረጃ  ቀዶ ጥገና ህክምና በኢትዮጵያ ውስጥ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብ ህክምና ማዕከል በመኖሩ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ሁለተኛው ቀዶ ጥገና ደግሞ በውጭ አገር የሚደረግ ይሆናል። ለቀዶ ጥገናው በአጠቃላይ አስራ አንድ ሺህ ዶላር($11000) ወይም አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር(1,100,000 ብር) ያስፈልጋል። ይህንን ገንዘብ ለማሰባሰብ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።  ታድያ  ውድ ልጃቸው ታክሞላቸው ድኖ ዳግም ደስታቸውን እንድናይ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከጎናቸው እንድንቆም በትህትና እንጠይቃለን። አካዎንት ቁጥር CBE 1000097223991 ሁንዴ አህመድ ዩያ ለበለጠ መረጃ፡ ይደውሉልን ☎️ 0919118817 (ዶ/ር ሁሴን ታሲ) እና 0916183436 (ዶ/ር አብደላ አሊ) በየቀኑ ያለውን መረጃ ማሳወቁን እንቀጥላለን! https://t.me/+0dIMrouBGpc3NDE0
Show all...
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተከበራችሁ ሙስሊም ወንድሞችና እሕቶች! እንኳን 1,444ኛው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም አደረሳችሁ!! አላህ ወሩን የዚክር፣ የዱዓእ፣ የቂያም፣ የድል ወር ያድርግልን
Show all...
📌 የትብብር ጥያቄ 📌 270,000 ብር ብቻ ''እኛ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ዙርያ የምንሰራ ኢማን የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ልማት ድርጅት እንባላለን። ከማህበራት ማደራጃ ፍቃድ ያለን ህጋዊ ተቋም ነን። ህዳር 19 ላይ አለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ኮንፈረንስ ጋምቢያ ላይ እንድንሳተፍ የጥሪ ደብዳቤ ተልኮልናለን። ስብሰባው ለመላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም መስማት የተሳናው ይጠቅማል ብለንም እናምናለን። ግን አሁን እኛ የደርሶ መልስ የአየር ጉዞ ቲኬት ለመክፈል አቅሙ የለንም። የምንሄደው 3 ሰዎች ነን። ለያንዳንዳችን ከ80 እስከ 90ሺህ ብር ወይም ለ3ታችን 270ሺህ ብር ገደማ ይጠበቅብናል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የትብብር ደብዳቤ ፅፎልናል። እባካችሁ በኮንፈረንሱ ላይ እንድንሳተፍ ለአላህ ብላቹ ተባበሩን ይላሉ'' መልዕክታቸው። ሁላችንም ብንተባበራቸው ቀላል ገንዘብ ናት። መስማት የተሳናቸውን፣ አይነ ስውራንን የመሳሰሉ ወገኖቻችንን በእምነታቸው እንዲጠነክሩ ማገዝ የሁላችንም ግዴታ ነው። ከታች ባሉ አካውንቶች ድጋፍ በማድረግ እናግዛቸው። 📌 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 📌 1000461347936 📌 IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGA (IEDDO) 🔴 ሒጅራ ባንክ 🔴 1002450020001 🔴 IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGA (IEDDO) 📌 ዘምዘም ባንክ 📌 0009389910301 📌 IMAN ETHIO DEAF DEVT ORGAN
Show all...
የምስራች ... ማዕከላችን ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በአሏህ ﷻ እገዛ ከዚያም በታች በብርቱ ወንድሞችና እህቶች ጥረት ህጋዊ ሒደቱን አጠናቆ በይፋ ስራዎችን ጀምሯል። በሀገራችን እየተንሰራፋ የሚገኘውን የአክፍሮተ ሀይላት እንቅስቃሴ በዳዕዋ ለመመከትና እስልምና ያልደረሰባቸው አካባቢዎች ሪሳላውን ለማስፋት ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ማዕከላችን ስራውን በተጠናከረ መልኩ ለመስራት ጉዞውን በአሏህ ﷻ ፍቃድ ጀምሯል። ... በተጨማሪም የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚያስፈልግባቸው አካባቢዎች ላይ ስራዎችን ለመስራት ራሱን የቻለ ህጋዊ የበጎ አድራጎት ፍቃድ ያለው ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሱ እምነት ፈታኝ መከራዎች በተቻለው መጠን ለመስራት እንቅስቃሴውን ጀምሯል። የማዕከላችን አባል በመሆን በጉልበት እንዲሁም በገንዘብ የአቅማችሁን መደገፍ ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው የጎግል ፎርም አባል እንድትሆኑ እየጠየቅን በቀጥታ ለመደገፍ ከዚህ በታች ያለውን የማዕከሉ ኦፊሺያል አካውንት መጠቀም ትችላላችሁ። አካውንት - 1000499318212 የአካውንት ስም - Hidaya Islamic Center በአጭር ቁጥር - 8212 መጠቀም ይችላሉ። ____ በተሰማሩበት መስክ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመኾን ዳዕዋውን ማገዝ ከፈለጉ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ የአባልነት ቅፅ በመሙላት ሊቀላቀሉን ይችላሉ፦ https://bit.ly/3r7DhoY
Show all...
◉ ይህ▸ https://youtu.be/5YYX3k9Orho የኡስታዝ ኢልያህ ማሕሙድ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ነው። የተለያዩ ኢስላማዊ እና ንፅፅራዊ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ብቸኛው ገጹ ስለሆነ Subscribe/Like/Share በማድረግ ዳዕዋውን ለወገኖቻችን በፍጥነት ያድርሱ። ® Ustaz Eliyah Mahmoud Telegram Channel.
Show all...
እህታችን በብድር ተይዛ ተጨንቃለች፣ከእዳ ብድር ጭንቀት አላህ ይጠብቃችሁ ፣የቻልነውን ያህል እንተባበራት እህታችን እንዲህ ትላለች አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ የአላህ እዝነትና ቸርነት በናንተ በወገኖቼ ላይ ይሁን እኔ እህታቹ ወ/ሮ ሀናን ጀማል በጓደኞቼ እና ባመንኩዋቸው የስራ ባልደረቦቼ የደረሰብኝን መከዳትና መጭበርበር ስገልፅላችሁ አላህ ከእንደዚህ አይነት ነገር እንዲጠብቃችሁ በመመኘት ጭምር ነዉ ወገኖቼ ያዋጣኛል ነገ ህይወቴን ይቀይርልኛል ብዬ አስቤ ከብዙ ሰዎች ላይ ተበድሬ የሰጠዃቸዉን 3,200,000 (ሶስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሺህ) ብር ይዘዉብኝ ተሰዉረዋል አበዳሪዎቼ ደግሞ ወደ ክስ ሄደዉ ከ አንዴም ሁለቴ ታስሬ አሁን ላይ በዋስ ወጥቼ በፍጥነት አምጥቼ እንድከፍል አ ስጠንቅቀዉኛል አሁን ላይ ደሞ የ 7 ወር ነብሰ ጡር ነኝ በዛ ላይ ደግሞ ታምሚያለሁ በዚህ ሰአት ደሞ ይሄንን ገንዘብ የመክፈል አቅም የለኝም ይሄን ገንዘብ ካልከፈልኩ ደሞ በድጋሚ ለእስር እንደምዳረግ አስጠንቅቀውኛል:: ውድ ወገኖቼ እንደኔ ካልታሰበ ኪሳራ እና ችግር አላህ ይጠብቃችሁ እያልኩ እዳዬን እንድከፍል የበኩላችሁን ታደርጉልኝ ዘንድበ አላህ ስም እጠይቃችሁአለዉ የባንክ አካዉንት Nigd bank 1000491549916 ሀናን ጀማል ሽፋ abysinya 88569048 ሀናን ጀማል ሽፋ Awash 01425589998100 ሀናን ጀማል ሽፋ
Show all...
የዱራሜው መስጂድ ቢላል ጉዳይ ከምን ደረሰ? በአቡ ሀይደር በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው ከሁሉ በፊት አማኝ ባሪያዎቹን በማነሳሳትና በማገዝ: ከፊሉ በገንዘቡ፣ ከፊሉ በዕውቀቱ፣ ከፊሉ በማስተዋወቅና የተቀረው ደግሞ በቦታው ላይ በመሳተፍ ለመስጂዱ ህልውና አስተዋጽኦ እንዲያደርግ: ተውፊቁ (እገዛው) ላልተለየን ጌታ አላህ ምስጋና ይድረሰው። ያለሱ እገዛና ፈቃድ ምንም ነገር ሊከሰት አይችልምና። በመቀጠልም: የዱራሜው ቢላል መስጂድ ሁኔታ፤ ሙአዚንና ኢማም በሆኑት ሰውዬ ብቻ ሶላት መከናወኑ: እረፍት የነሳው ወንድማችን የ Islam Selam አካውንት እና የዚህ ዩቱብ https://youtube.com/channel/UC1phBbwcq_sXeSKKV_JtUMg ባለቤት ጉዳዩን በፌቡ በመልቀቅ ለሙስሊሞች መነሳሳት ሰበብ ስለሆንከን ጀዛከላሁ ኸይራ። በመሰለስም: ይህ ጉዳይ ለሁሉም ወንድምና እሕቶች በሰፊው እንዲዳረስና ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በተደጋጋሚ በመፖሰት ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖረው ለለፋኸው ወንድም አቡ ዳዉድ ዑሥማን ጀዛከላሁ ኸይራ። በመረበዕም:– በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዊች (በፌቡ፣ በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ፣ በቲክቶክና በዩቱብ) ስርጭቱ እንዲስፋፋ ላደረጋችሁ ወንድምና እሕቶች በመላ ጀዛኩሙላሁ ኸይራ። በመጨረሻም:– በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም በመሆን ይህ የዱራሜው ቢላል መስጂድ ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው በማለት በገንዘባቹ የተሳተፋችሁ ወንድምና እሕቶች: ገንዘብና ልጆች በማይጠቅሙበት ቀን አላህ ባወጣችሁት ገንዘብ ተጠቃሚ ያድርጋችሁ። እንዲሁም ቦታው ድረስ በመገኘት ለተሰበሰበው ሕዝብ ኢስላማዊ ትምሕርት የሰጣችሁ (ኡስታዝ ዐብዲ፣ ኡስታዝ ጁንዱላህ፣ ኡስታዝ መሐመድ ሸምሱ)፣ በቦታው በመገኘት የፕሮግራሙ ድምቀት የሆናችሁ ተሳታፊዎች በሙሉ (በተለይ የሐላባ ጀመዓዎች)፣ ቦታውን በማበጃጀት ላስተካከላችሁ በመላ (በተለይ ወንድም ሱልጣን ናሲር፣ ወንድም መሐመድ ኢብራሂም እና ወንድም ፉአድ) ጀዛኩሙላሁ ኸይራ። አዲስ ነገር ምን ተሰራ ምንስ ቀረ? 1/ በመስጂዱ ላይ ሙአዚን እና ኢማም ከነበሩት አባት በተጨማሪ: ለመስጂዱ ቋሚ ኢማም (በመግሪብ፣ ዒሻእና ፈጅር ላይ አሰጋጅ) ተመድቧል። ይህ ኢማም ከኢማምነት በተጨማሪ:– የአካባቢውን ህፃናት ቁርኣን ማስቀራት፣ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ለመጣው ሰው ቋሚ የሙሐደራ ፕሮግራም መስጠት፣ በግላቸው የተለያየ ኪታብ መቅራት የሚፈልጉ ወንድሞችን ማቅራት ሥራው ይሆናል። 2/ ቅዳሜና እሕዱ (ከ 14/12/14—15/12/14) ለሁለት ቀናት በመስጂዱ ላይ ለተሰበሰበው ህዝብ ኢስላማዊ ት/ት መስጠት። በዳዕዋው ሰበብም ወደ 9 ሰዎች ሸሀዳ በመስጠት ሰልመዋል። ለተሰበሰበው ሰውም በሁለቱ ቀናት የምሳ ግብዣ ፕሮግራም ተካሂዷል። 3/ የመስጂዱ ውስጣዊ ችግር (ኮርኒስ) እደሳ ተካሂዷል። በአሁን ሰአት ከአዲሱ ኢማም በደረሰኝ መረጃ መሰረት ከ10 እስከ 15 የሚደርሱ ሰዎች ወደ መስጂዱ በመመላለስ የጀመዓ ሶላት እንደሚሰግዱ ማወቅ ተችሏል። ቁርኣን መማር የጀመሩ ህፃናትም (ወንድና ሴትን ጨምሮ) ወደ 15 ደርሰዋል። የቀረው ሥራ ደግሞ:– መስጂዱን ዙሪያውን ማጠር: በሶስት ወይም በየ አራት ወራት በመስጂዱ ላይ የዳዕዋ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት። ምን ያህል ገንዘብ ተሰበሰበ? ምን ያህልስ ወጪ ተደረገ? የተሰበሰበው ገንዘብ ከገመትነውና ከጠበቅነው በላይ ነው። በአጠቃላይ እስካሁኑ ሰአት ድረስ የተሰበሰበው ገንዘብ 2,585,113·32 ሳ (ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ፣ አንድ መቶ አሥራ ሶስት ብር ከሰላሳ ሁለት ሳንቲም) ነው። ወጪ የተደረገው ደግሞ:– 242,997 ብር ነው። ከወጪ ቀሪ የሚሆነው:– 2,342,116·32 ሳ ይሆናል። በቀጣይ ምን ታሰበ? ይህ የተሰበሰበው ገንዘብ ለቢላል መስጂድ ሙአዚን እና ኢማም እንዲሁም ኡስታዝ ለሆኑት በተጨማሪም ለአጥር ግንባታው ከሚያስፈልገው በላይ የተረፈ በመሆኑ: ይህ የተረፈ ገንዘብ ለሌላ ኸይር ሥራ እንዲውል:– 1/ በዋንኝት በአካባቢው የሚገኘውን የካምፓሱ ሙስሊም ተማሪዎችን ማገዝ። የዱራሜ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች ከካምፓሱ ፊትለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሰሩትን መስጂድ ጎብኝቼዋለሁ። መስጂዱ ቀሪ ሥራዎች (በተለይ በሴቶች በኩል ምንጣፍ፣ በርና መስኮት እንዲሁም ችፑድና መፀዳጃ ቤት)፣ መድረሳው ሙሉ እድሳት ያስፈልጉታል። እንደተነገረኝ ከሆነ ወደዚህ መስጂድ በመመላለስ የሚሰግዱ ወንድምና እሕቶች ወደ 300 ይጠጋሉ። ስለዚህ እነዚህ ሰጋጆች: ከሶላት በተጨማሪ መንፈሳዊ ማንነታቸውን የሚያጠናክርላቸው ሁለት ኡስታዞችን መቅጠር ያስፈልጋል። 2/ በዛው ዱራሜ ከተማ: ከቢላል መስጂድ ራቅ ብሎ በገጠራማው ክፍል ለሚገኙ ሙስሊም ነዋሪዎች የኡስታዝ እጥረት ያለባቸውን ቦታዎች ጥናት በማድረግ ኡስታዞችን መቅጠር ዋነኛ ስራችን ይሆናል። 3/ ገንዘቡ የሚተርፍ ከሆነ ከሀላባ ከተማ ወደ ከንባታ በሚወስደው መንገድ 12 ኪ ሜ ርቃ የምትገኘውን የአቦኪቾ ከተማ በኡስታዞችና በዳዕዋ መድረስ ሌላው ስራችን ይሆናል። ይህ ከተማ ከ1000–1,500 የሚደርሱ አባወራዎች አሉት። 85 በመቶ የሚሆነው ሙስሊም ነው። ያሉት መስጂዶች ብዛት በጭቃ የተሰሩ 3 ብቻ ናቸው። መደረሳ ማፊ፣ ኡስታዝ ማፊ!! ስለዚህ ቦታው የኡስታዝና የመድረሳ ትኩረት ይሻል። ወንድምና እሕቶቼ ሆይ! ይህ የኸይር ሥራ ቀጣይነት እንዲኖረው የናንተን እገዛ ይሻልና: በቻላችሁት መጠን አሁንም ከመተባበር ወደ ኋላ አትበሉ። አላህ ያግዛችሁ ወሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
Show all...