الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Open in Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
2 192
Subscribers
+2824 hours
+447 days
+45130 days
Posts Archive
قال الشيخ ابن عثيمين
ሼኽ ኢብኑ ዑሠይሚን እንዲህ ብለዋል
مَنْ عَامَلَ النَّاسَ بِالسُّهُولَةِ عَامَلَهُ اللهُ تَعَالَى بِمِثْلِهَا
ሰዎችን በቅልልነት (በገርነትና በማመቻቸት) የያዘ ሰው/ አላህ ተዓላም በተመሳሳይ መልኩ በገርነት) ይይዘዋል
وَقَدْ جَاءَ فِي الحَدِيثِ وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالأخِرَةِ
በሐዲስም እንዲህ ተብሎ መጥቷል/ በተቸገረ ሰው ላይ ያገራን (ያቀለለን) ሰው አላህ በዱንያም በአኺራም ያገራለታል
አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት በንግድ / በዕዳ አከፋፈልም ሆነ በማንኛውም ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ነገሮችን የማያጠብቅ ሰዎችን የማይበድልና ገር የሚሆን ከሆነ አላህም በዕለተ ቂያማም ሆነ በዚህች ዓለም ጉዳዩን ያቀልለታል
✍
ከነብዩላህ አደም ዓ.ም ልጆች መገዳደል የወንጀል በር መጀመር ትልቅ ማስገንዘቢያ እና ማንቂያ ?!
_የአዳም ልጆች (ቃቢልና ሀቢል) መገዳደልን_ _ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ! እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በምድር ላይ ያለ አግባብ ለሚፈሰው እያንዳንዱ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል መጀመሪያ ለገደለው ሰው (ለቃቢል) የኃጢአቱ ተካፋይነት (የወንጀል እጣ) አለበት
ለዚህም ዋናውና ትልቁ ምክንያት በኢስላም መመሪያ መሠረት መጥፎን መንገድ ወይም መጥፎን ሥርዓት መጀመሪያ የጀመረና ለሰዎች አርአያ (ሰበብ) የሆነ ሰው የራሱንም ወንጀል እንዲሁም እሱን ተከትለው የሚሰሩትን ሰዎች ወንጀል እኩል _ስለሚሸከም ነው_
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ _አለይሂ ወሰለም) ይህንን አስመልክተው በግልጽ እንዲህ ብለዋል_
لَا تُقْتَلُ نَفْسٌ ظُلْمًا، إِلَّا كَانَ عَلَى ابْنِ آدَمَ الأَوَّلِ كِفْلٌ مِنْ دَمِهَا፣ لِأَنَّهُ كَانَ أَوَّلَ مَنْ سَنَّ القَتْلَ
ማንኛዋም ነፍስ ያለ አግባብ (በበደል) አትገደልም በመጀመሪያው የአዳም ልጅ (በቃቢል) ላይ ከደሟ ስምሪት (የኃጢአት እጣ) ያለበት ቢሆን እንጂ ምክንያቱም እርሱ መግደልን መጀመሪያ የጀመረ (ለሰዎች መጥፎ መንገድ ያሳየ) በመሆኑ ነው
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባስተማሩት ሌላ ጠቅላላ ሐዲስ ላይ እንዳብራሩት በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገርን ፈጥሮ ለሰዎች በር የከፈተ ሰው በውጤቱ ተጠያቂ ይሆናል
መጥፎ መንገድ የጀመረ ?አንድ ሰው ሰዎች የማያውቁትን ወይም የማይደፍሩትን መጥፎ ነገር (ለምሳሌ መግደልን ስርቆትን /ወይም ማንኛውንም በዲን ውስጥ የሌለ መጥፎ ፈጠራን) መጀመሪያ ከጀመረ/ እሱን አይተው ያንን ወንጀል የሚሰሩ ሰዎች ኃጢአት ሳይቀነስባቸው! ልክ እንደነሱ እኩል ኃጢአት መጀመሪያ ለጀመረው ሰው ይጻፍለታል
*መልካም መንገድ የጀመረ በተቃራኒው ደግሞ ሰዎች የተውትን ወይም የማያውቁትን መልካም የዲን ተግባር (ለምሳሌ ሰደቃን! ማስተማርን) መጀመሪያ የጀመረና ለሰዎች ሰበብ የሆነ ሰው? እሱን ተከትለው የሚሰሩት ሰዎች የሚያገኙት አጅር (ምንዳ) ሳይቀነስባቸው ለእሱም እኩል አጅር ይጻፍለታል*
_ቃቢል በምድር ላይ የመጀመሪያውን የደም መፋሰስ በወንድሙ ላይ በፈጸመ ጊዜ! ለሰው ልጆች ሁሉ /ነፍስን ማጥፋት ይቻላል! የሚል የጭካኔና የወንጀል በር ከፋች በመሆኑ !? እስከ እለተ ቂያማ ድረስ ለሚፈሰው ደም ሁሉ የወንጀሉ ተካፋይ ይሆናል ይህ ሐዲስ እኛም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ለሰዎች መጥፎ አርአያ ከመሆን እንድንጠነቀቅ ትልቅ ማስተማሪያ ነው_
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
بسم الله الرحمان الرحيم ✍
ትዳር የፈለግሺው እህቴ
ይህ አላህ መልካም ትዳርና ሳሊህ ልጆችን ለመለመን ያስተማረን ምርጥ ዱዓ ነው
رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا
ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) መጠለያ ስራና ትዳር በፈለገ ጊዜ ያደረገውና ወዲያውኑ መልካም ትዳር የተሰጠበት ታላቅ ዱዓ👇
رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ
👆
اللَّهُمَّ ارْزُقْهَا زَوْجًا صَالِحًا، تَقِيًّا، نَقِيًّا، مَخْمُومَ الْقَلْبِ، يُعِينُهَا عَلَى طَاعَتِكَ، وَيَكُونُ قُرَّةَ عَيْنٍ لَهَا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ
አላህ ሆይ ያንተን ታዛዥነት የሚያግዛት በዱንያም በኣኺራም ለዓይኖቿ ማረፊያ የሚሆን መልካም አላህን ፈሪ ልበ-ንፁህ የሆነ ሳሊህ ባል ይውፈቃት
اللَّهُمَّ اكْفِهَا بِحَلَالِكَ عَنْ حَرَامِكَ، وَأَغْنِهَا بِفَضْلِكَ عَمَّنْ سِوَاكَ، وَيَسِّرْ لَهَا أَمْرَ الزَّوَاجِ
አላህ ሆይ በሀላልህ ከሀራም አብቃት (ጠብቃት) በችሮታህም ከሌላው ሁሉ አብቃት የትዳርንም ነገር አግራልላት
አሏህ ላጤን ሁሉ ከነዚህ ከተዘረዘሩት ዱአወች ይስጣቸው ያረብ ያረብ
+1
﴿أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَنْ تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ الْحَقِّ.
ለነዚያ ላመኑት ልቦቻቸው አላህን ለማውሳትና ከእውነት ለወረደው (ለቁርአን) ሊፈሩ (ሊለዝቡ) ጊዜው አልቀረበላቸውም?https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
ከዘንጊዎቹም አትሁን
وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ
ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡
{ሱረት አል አዕራፍ 205}
👇👇ሸር ሸር
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
💔ከዚህ ክፉ በሽታ አላህ ይጠብቀን በቻናላቹህ ሸር አድርጉላት እንተጋገዝ እርዷት ያገሬ ልጆች💧💧💧👆
Repost from قناة ابي حنيفة حسين بن ادريس الوالربابي
+1
የእርዳታ ጥሪ ፦
ወጣት ፈጡማ ሰይድ ሁሴን በወረባቦ ወረዳ 18 ቀበሌ ላይ ምሽንጋ አካባቢ ተወላጅና የ23 አመት ወጣት ስትሆን እንደ አካባቢዎቿ ልጆች ስራ ለመስራት ወደ አረብ ሀገር ሂዳ የነበረ ቢሆንም ህመም ምክንያት ወደ ሀገር ቤት ተመልሳለች።
ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰች በኋላ በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምናዋን ስትከታተል የቆየች ቢሆንም ህመሙ እየጨመረ እያደገ በመሄዱ ወደ ካንሰርነት በመቀየሩ ወደ አድስ አበባ ታዝማ ሆስፒታል ሂዳ በጨረር ህክምና ማድረግ እንዳለባት ተገልፆላት ሪፈር ተብላች።
ወጣት ፋጡማ ከአንድ አመት በላይ ህክምና ስትከታተል ያላትን ገንዘብ በሙሉ በመጨረሷ እና ቤተሰቡም ወደ አድስ አበባ ይሄ የመሄድ አቅም የሌላቸው በመሆኑ እባካችሁ ያላችሁን እገዙኝ ስትል ትጠይቃለች !!!
ወኪል እህቷ ጦይባ ሰይድ
ንግድ ባንክ
1000156683063
አቢሲኒያ ባንክ
125923337
ጣይባ ሰይድ ሁሴን
ዳሽን ባንክ
293581556011
ጣይባ ሰይድ ሁሴን
ፋጡማ ሰይድን ማገኘት የፈለገ ጦይባ ሰይድ በኩል ማግኘት ይችላል ስልክ 0954169701
Follow this link to join my WhatsApp group: https://chat.whatsapp.com/KFiXoXk8qp2JqMCx6iaNFX?s=sw&p=a&mlu=2
+1
يَا مَنْ لَزِمْتُمْ نَهْجَ خَيْرِ الْوَرَى
وَسِرْتُمْ عَلَى دَرْبِ الْهُدَى وَالأَثَرْ
أَهْلَ الْحَدِيثِ وَالسُّنَّةِ الْغَرَّاءِ كَمْ
صُنْتُمْ عَقِيدَتَنَا مِنْ كُلِّ خَطَرْ
تَمَسَّكْتُمْ بِفَهْمِ السَّلَفِ الصَّالِحِ
فَكُنْتُمْ كَنُجُومٍ فِي اللَّيْلِ الْعَكِرْ
أَنْتُمُ الْأَقْمَارُ فِي دُنْيَا الْعِلْمِ،
حَفِظَكُمُ اللهُ يَا لآلِئَ الْأَثَر
የፍጥረታት ሁሉ በላጭ የሆኑትን (የነቢዩን) መንገድ አጥብቃችሁ የያዛችሁ
በቅኑ ጎዳና እና በሰለፎች ፈለግ ላይ የተጓዛችሁ
የሐዲስ እና የደመቀችው ሱና ሰዎች ሆይ
እምነታችንን ከአደጋና ከቢድዓ ሁሉ እንዴት ጠበቃችሁ
በደጎቹ ሰለፎች (ቀደምቶች) ግንዛቤ ተመርታችሁ
በውዥንብር ጨለማ ምሽት ውስጥ እንደሚያበሩ ከዋክብት ሆናችሁ
እናንተ በዕውቀት ዓለም ውስጥ ሙሉ ጨረቃዎች ናችሁ
አላህ ይጠብቃችሁ እናንተ የፈለግ የአሰር) እንቁዎች ሆይ
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته،
🎤አስደሳች ዜና!🔖በመድረሰቱ ''ኑሪ'ል የቂን ማዕከል ቃዒደቱ አን'ኑራኒያ በOnline ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን ለማስመረቅ የፊታችን ኡሑድ ፕሮግራም አዘጋጅቷል! 🎉ሌላ ብስራት¡ ከዚሁ ጋር አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ለወንድም/ለሴትም'ምዝገባን' አዘጋጅቷል! በመድረሳው:-የሚሰጡ የት/ት አይነቶች ቁርኣን :- ነዞር _ሒፍዝ_ቃዒደቱ ኑራኒያ ኩቱቦች:- ዓቂዳ_ ነሕዉ_ሶርፍ 🎉የዝግጅቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በክብር ተጋብዛችኋል። 🪑የመድረሳው ሐላፊና አስተማሪ ወንድም አቡ ነሚር ሙኽታር 📜አድራሻችን-ኢሞ እና ቴሌግራም ነው።
🪑ተጋባዣ ኡስታዞች"🍃ኡስታዝ አቡ ነሚር 🍃ኡስታዝ አቡ ጃቢር 🍃ኡስታዝ አቡ ዩስራ 📌https://t.me/AbuNemirMuktar
+1
تُفْتَحُ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ يَوْمَ الِاثْنَيْنِ وَيَوْمَ الْخَمِيسِ، فَيُغْفَرُ لِكُلِّ عَبْدٍ لَا يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا، إِلَّا رَجُلًا كَانَتْ بَيْنَهُ وَبَيْنَ أَخِيهِ شَحْنَاءُ، فَيُقَالُ: أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا
የጀነት በሮች በየሳምንቱ ሰኞና ሐሙስ ይከፈታሉ በአላህ ላይ ምንም ነገር ያላጋራ (ሽርክ ያላደረገ) ባሪያ ሁሉ ወንጀሉ ይማርለታል ነገር ግን በእሱና በወንድሙ (በእህቱ) መካከል ጥላቻ ቂም ወይም ኩርፊያ ያለበት ሰው ሲቀር (መላእክቶቹን) እነዚህ ሁለቱ እስኪታረቁና እስኪስማሙ ድረስ (የምህረት መዝገባቸውን) አቆዩት ይባላል
(ሰሒሕ ሙስሊም)
✍ ይችን አጠር ያለች ማስተካከያ ለኡሙ ረያን ቻናል አድርሱልኝ ስለማላዉቃት
እህቴ ትክክል ነሽ እኛ ጋብዘናቸዉ አብዛሀኛወቹ አይመጡም እሺም አይሉም ።
ላኪን በንደት ከነሱስር እየሰራን በሙሰሩት ነገር እጃችን አለበት ብለሽ ስራችንን መናገር አግባብ አይደለም ። ለአሏህ ብለን ከሆነ የምንሰራዉ እንደዚህ ማለታችን ከኢኽላሳችን ጋር እንዳይጋጭ ያስፈራል ።
✍ ዉድ እህቶቸ አብሽሩ ። ያዉ. እነሱም በተለይ አንዳንዶቹ ተሸግረዉ ይሆናል እንፈተናለንም በሚልም ይሆናል ። ችግር የለዉም እምቢ ታሉ እርስ በርሳቸዉ ሲገባበዙ እናዳምጣለን ስራችንን እንቀጥላለን አለቀ ።
ጥሪን አክብሩ ብለዋል ረሱል ብለዉ እያስተማሩን ነዉ ። እነሱ የኛን ጥሪ ባለማክበራቸዉ እራሳቸዉን ይፈትሹ አለቀ ።
⬇⬇አንድ ከታዘብኩት ነገር:-
▫️ እህቶች የዳዕዋው አንዱ አካል ናቸው ይባላል ፤ ግን ኡስታዞች ፤ወንዲሞች ፤ሴቶች እህቶች የዳዕዋ፣የሙሀደራ ፕሮግራም ሲጠሯቸው በሸም እሺ ይላሉ :ጥሪ ግን ለምን አያከብሩም?!! "እውነተኛ ሰለፍይነትን ለምን በተግባር ለምን አንኖረውም??!? " በየተኛውም የዳዕዋ ክፍል እኮ የኛም እጅ አለበት። አትዘንጉ ከማዘጋጀት እስከ ማስተባበር ። ለአላህ ብለን ነው እምንሰራው ። ቢሆንም ግን፤ ጥሪያችንን እንደወንዶች ሊከበር ለምን አይገባም፤ በጣም ቅር እያሰኘን ነው ። ስንት ጀግና የዳዕዋው የጎን አጥንት የሆኑ እህቶች እኮ ሞልተዋል። ሞራል ጠብቁ።
🌟ግደታ ፣ጓደኞቻችሁ፣የሚግባባችሁ ሰው መሆን አለበት ማለት ነው⁉️
መልክቴ ነው ለንግግሬ ይቅርታ🖊
وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا መልዕክተኛውም አለ ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርአን የተተው (የተጣለ) ነገር አድርገው ያዙት (ሱረቱ አል-ፉርቃን: 30?👆👆💧?
ያረብ ለእኔም ለእህቶቼም ቀልባችን የምትረካበትን አይናችን የምትደሰትበትን ከሲሳይም ከእውቀትም ከሁሉም ነገር የእረፍት እንጀራን ስጠን
ጌታችን ሆይ በዱንያም በዓኺራም ስኬትን አጎናጽፈን ህይወታችንን በበረከትና በውብ ትዕግስት አስውባት እርስ በርስ በቅንነትና በፍቅር የምንተዋወስ በእውነትና በጥሩ ንግግር የምንመራረቅ እህትማማቾች አድርገን አሚን ያረብ 🤲✨
اللَّهُمَّ ارْزُقْنِي وَأَخَوَاتِي رَاحَةً تَرْتَاحُ بِهَا قُلُوبُنَا، وَقُرَّةَ عَيْنٍ تَسْعَدُ بِهَا أَعْيُنُنَا، وَاكْفِنَا بِرِزْقٍ وَعِلْمٍ وَمِنْ كُلِّ خَيْرٍ يَكُونُ لَنَا أَمَانًا وَرَاحَةً دَائِمَةً.
اللَّهُمَّ اجْعَلْ أُخُوَّتَنَا خَالِصَةً لِوَجْهِكَ الْكَرِيمِ، وَاجْمَعْنَا عَلَى الْخَيْرِ وَالْقَوْلِ السَّدِيدِ في الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَأَسْعِدْ قُلُوبَنَا بِمَا نَتَمَنَّاهُ. اللَّهُمَّ آمِينْ. 🤍
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
ለወንድሞቼ ጠቃሚ ምክር
1. አላህን መፍራት (ተቅዋ) እና በትዳር ውስጥ ያለውን ኃላፊነት መገንዘብ
• ሸይኽ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ: "ትዳር የአላህ ውዴታ የሚገኝበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። ባል ሚስቱን በአግባቡ በመያዝ፣ በመንከባከብ እና በመደገፍ አላህን ሊፈራ ይገባል።" (ፈታዋ ኑር ዐለ ደርብ)
• በቁርኣን ላይ አላህ እንዲህ ይላል: "ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች ናቸው አላህ አንዳቸውን ከአንዳቸው ስላበለጠና ከገንዘባቸውም ስላወጡ፡፡ ስለዚህ መልካሞቹ ሴቶች ታዛዦች ናቸው፡፡ አላህ ባስጠበቃቸው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡"
• ተቅዋን መሠረት ያደረገ ትዳር ለመገንባት ቁርኣንን በደንብ መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። ባል ሚስቱን በአክብሮትና በርህራሄ በመያዝ የአላህን ውዴታ ለማግኘት መጣር አለበት።
2. ለሚስት መልካም መዋል እና ፍቅርን መግለጽ
• ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ መካከል በላጩ ለቤተሰቡ በላጭ የሆነ ነው፤ እኔም ለቤተሰቤ በላጫችሁ ነኝ።" (ቲርሚዚ)
• ኢማሙ አሕመድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ: "ለሚስትህ ያለህን ፍቅር መግለጽ ከሱና ነው፤ ይህ በትዳር ሕይወት ውስጥ ደስታን ይጨምራል።"
• ለሚስትሽ ያለህን ፍቅር በቃልም በተግባርም ግለጽ። ስጦታዎችን ስጣት፣ አመስግናት፣ አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ፣ እሷን እንደምታደንቃት በተግባር አሳያት።
3. በትዕግስትና በዲፕሎማሲ አለመግባባቶችን መፍታት
• ሸይኽ ሳሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ: "በትዳር ውስጥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በቁጣ ሳይሆን በውይይትና በመግባባት መፍታት ያስፈልጋል። በትዕግስትና በዲፕሎማሲ መስራት የትዳርን ሰላም ይጠብቃል።"
• አላህ በቁረአን ላይ እንዲህ ይላል: "ሴት ከባሏ በዓመፅ ወይም በመዞር ብትፈራ፣ በሁለቱ መካከል እርቅን ቢፈጥሩ በነሱ ላይ ኃጢአት የለባቸውም፡፡ እርቅ በላጭ ነው፡፡"
• አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ ቁጣን አስወግድ። በረጋ መንፈስ ሚስትህን አዳምጣት፣ ስሜቷን ለመረዳት ሞክር፣ ምክንያታዊ መፍትሄዎችን ፈልጉ። የቤተሰብን ሰላም ለማስጠበቅ ትዕግስት ቁልፍ ነው።
4. በጋራ ኢስላማዊ እውቀትን መፈለግ
• ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ: "ባልና ሚስት ቁርኣንን በመማር፣ ሐዲሶችን በማጥናትና ኢስላማዊ እውቀትን በመጨመር ትዳራቸውን ሊያጠናክሩ ይችላሉ።"
• ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል: "እውቀትን መፈለግ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።" (ኢብኑ ማጃህ)
• አብራችሁ ቁርኣንን ተማሩ፣ ሐዲሶችን አንብቡ፣ ኢስላማዊ ትምህርቶችን ተከታተሉ። ይህ በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ላይ በጎ ተጽዕኖ ከመፍጠሩም በላይ በትዳራችሁ ውስጥ መግባባትን ይጨምራል።
5. ለቤተሰብ ጊዜ መስጠት እና ልጆችን በኢስላማዊ ስነ-ምግባር ማሳደግ
• ሸይኽ ሙሐመድ አል-.. (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ: "ልጆችን በኢስላማዊ ስነ-ምግባር ማሳደግ የወላጆች ትልቅ ኃላፊነት ነው። ልጆቻችሁን ቁርኣንን እንዲያነቡ፣ ሶላትን እንዲሰግዱና መልካም ስነምግባር እንዲላበሱ አስተምሯቸው።
• ለልጆቻችሁ ጊዜ ስጡ፣ አብራችሁ ተጫወቱ፣ ተዝናኑ፣ ምከሯቸው። በኢስላማዊ እሴቶች ላይ ተመስርታችሁ ልጆቻችሁን ማሳደግ ለዱንያም ለአኺራ የሚጠቅም ትልቅ ትውልድ ፍጠሩ።
እነዚህን ምክሮች ተግባራዊ በማድረግ ትዳራችሁን የበለጠ ደስተኛና የተሳካ ማድረግ ትችላላችሁ። አላህ መልካም ትዳር ይወፍቃችሁ!
ይቀጥላል ....?
በወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን
ሸር በማድረግ ለወንድሞቼ አድርሱልኝ
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً
ከነፍሶቻችሁም ለእነሱ ትረኩ ዘንድ ሚስቶችን መፍጠሩ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው
🌸🌸👌✍👇
ባል ለሚስቱ ታጋሽ ይቅር ባይ በቤት ውስጥ ስራ አጋዥ ፊቱን በፈገግታ የሚያበራ እና እወድሻለሁ የሚሉ የደግነት ቃላትን የማይሰስት የልብ ጓደኛ መሆን አለበት
