(የወጣቶች አለም)🌏 عَالَمُ الشَّبَاب
Open in Telegram
🌟 እንኳን ወደ "የወጣቶች አለም" በሰላም መጣችሁ! 🌟 በኢስላማዊ እሴቶች፣ በአኽላቅ፣ በቁርኣን እና በሐዲሥ ብርሃን የወጣቶችን የዱንያ እና የአኺራ ስኬት ለማጎልበት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ። 💡 ኢስላማዊ እውቀት | 🚀 አነቃቂ ምክሮች | 📚 የመልካም ስነ-ምግባር መመሪያዎች💥1ታሪክ 💥2የትዳር ተሞክሮዎች 💥3ኢስላማዊ የእውቀት ፈተና ተቀላቀሉን፤ በእስልምና ብርሃን አብረን እንደግ! 🌙✨
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
330
Subscribers
+124 hours
+57 days
+4630 days
Posts Archive
በትልቅ ጭንቀት ውስጥ ሆነሽ፣ ነገሮች ሁሉ ተደራርበውብሽ ልክ እንደ ጥልቅ ጨለማ ክፍል ውስጥ የጠፋሽ ሲመስልሽ፣ ወይም በራስሽ ስህተት ምክንያት የጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ ሆነሽ "እኔ እኮ..." እያልሽ ራስሽን እየወቀሽ ከሆነ..
ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) በአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ ሆነው የጠሩትንና አላህም ሰምቶ ያዳናቸውን ያንን ተአምራዊ ዚክር አስታውሺ፡-
لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ
«...ከአንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበደለኞቹ ነበርኩ...» (ሱረቱ አል-አንቢያእ 21:87)
ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) በወቅቱ የነበሩበትን ሁኔታ አስቢው፤ የሌሊቱ ጨለማ፣ የባህሩ ጥልቀት ጨለማ፣ እና የአሳ ነባሪው ሆድ ጨለማ... በሶስት ደራራቢ ጨለማዎች ውስጥ ነበሩ። በሰዋዊ ስሌት ከዚያ መውጣት ፍጹም የማይቻል ነበር። ነገር ግን እሳቸው አላህን አልተቆጡም፣ "ለምን እኔ?" አላሉም። ይልቁኑ የአላህን ታላቅነት መሰከሩ፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ጥፋታቸውን አመኑ። ይህ ዱዓ የትኛውንም የጨለማና የጭንቀት ግንብ ሰባብሮ የአላህን ራህመት የመሳብ ተአምራዊ ኃይል አለው። አላህም ቀጥሎ ባለው አያህ "ዱዓቸውን ተቀበልን፣ ከጭንቀትም አዳናቸው፤ አማኞችንም እንደዚሁ እናድናለን" ብሏል።🥰
So, ኡኽታዬ...🤍
አሁን ያለሽበት የጭንቀት ማዕበል የቱንም ያህል ከባድና ጨለማ ቢሆን፣ ልክ እንደ ነብዩ ዩኑስ ይሄንን ዱዓ በሱጁድሽና በብቸኝነትሽ ደጋግሚው። አሳ ነባሪውን አዞ ነብዩን በሰላም ምድር ላይ ያስፋፋው አምላክ፣ አንቺንም ካለሽበት ከባድ የጭንቀት ባህር ማውጣቱ ፈጽሞ አይሳነውም።
just ልብሽን በዚህ ዚክር አርጥቢው.... ጨለማው ተገፎ ንጋቱ መምጣቱ የማይቀር ነው 🩹
🍂 ከ ቁርአን አያህ...
💜 እንስሣ ሲርበው እጅግ በጣም አደገኛ
እና መርዛማ ይሆናል፥ የሰው ልጅ ግን መጥፎና አደገኛ የሚሆነው ሲጠግብ ነው::
share & join👇👇
https://t.me/yemuslimwetatochdimts
ቁስል የሚያደርቅ
ህመም የሚያጠፋ
ጠባብ አቅል ቀዶ ቀልብን የሚያሰፋ
ካንተ በቀር ረሂም ማን ይሰጣል
ተስፋ❤️🩹
share & join 👇👇
https://t.me/yemuslimwetatochdimts
─── ⋆ 💎 بِسْمِ اللهِ الرَّحْمٰنِ الرَّحِيْمِ 💎 ⋆ ───
ወጣትነት ለአላህ አደራ የተሰጠ ውድ ሀብት ነው! ✨
ወጣትነት በህይወት ዘመናችን ውስጥ አንዴ ብቻ የምናገኘው ትልቅ ፀጋ ነው። ይህንን ጊዜ በአላህ መንገድ፣ በእውቀትና በመልካም ስራ ካላሳለፍነው ነገ የምንቆጨው ትልቅ ቁጭት ይሆናል።
💡 ዛሬ ላይ የምትዘራውን መልካም ነገር ነገ በቂያማ ቀን ታጭደዋለህ/ሽ።
join & share 👇👇
https://t.me/yemuslimwetatochdimts
─── ⋆ 💎 بِسْمِ اللهِ الرَّحْمٰنِ الرَّحِيْمِ 💎 ⋆ ───
ነቢዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
ከእናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተማሮ ያስተማረ ነው።
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
🌿 አላህ ከቁርአን ሰዎች ያድርገን 💫
share 👇👇
https://t.me/yemuslimwetatochdimts
السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ! ✋
እንኳን ወደ የሙስሊም ወጣቶች ድምፅ የቴሌግራም ቻናል በሰላም መጡ
ይህ ገጽ ወጣቶችን በኢስላማዊ እውቀት፣ በሥነ-ልቦና እና በበጎ ሥነ-ምግባር ለማነፅ የተዘጋጀ ማዕድ ነው።
በዚህ ቻናል፦
🔹 አነቃቂ ኢስላማዊ ማስታወሻዎች
🔹 የወጣቶች ሕይወትና የሥነ-ልቦና ምክሮች
🔹 አጫጭር ትምህርቶች፣ ዚክሮችና ዱዓዎችን ያገኛሉ።
💡 ወደ ቀጥተኛው መንገድ አብረን እንጓዝ
ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ የኸይር ሥራው ተካፋይ ይሁኑ! 🌿
👇👇Join Us: https://t.me/yemuslimwetatochdimts
