en
Feedback
ምክር ለወጣቶች

ምክር ለወጣቶች

Open in Telegram

"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
7 288
Subscribers
-524 hours
+1227 days
+79230 days
Posts Archive
ቲላወቱል  ቁርዓን🎧
ለቀልቦዎ❤️‍🩹
https://t.me/Sakinah_Quran_Post

ደርስ ላይ ጠንካራ እደሆሽው ሁላ ተግባሩ ላይም ጠንካራ ሁኚ🙌
ደርስ ላይ ጠንካራ እደሆሽው ሁላ ተግባሩ ላይም ጠንካራ ሁኚ🙌

ቢደአ እና ሽርኩ ሳይሆን ሙብተዲው እና ሙሽሪኩ ነው ጀሀነም ሚገባው ጣፋጭ መልስ ነች"ጥፋቱን ብቻ አውግዝ ሰውዬው ተወው" ለሚሉት አካሎች

👉 የነሲሓ ሙሪዶች ለራሳችሁ ታማኝ ሁኑ ! እውነተኛ ሙሪዶች ለራሳቸው ታማኞች ናቸው ። አብዛኛዎች ያብሬት ሙሪዶች ፣ የቃጥባሬና አልከሶ እንዲሁም የዳንዬና አንዬ የከረምና ጀማ ንጉስ የጌታው ሸኽዬ ሙሪዶችም የዚሁ አይነት ናቸው ። ለሙሪድነታቸው ኢኽላስ አላቸው ። ሲወዱም ሲጠሉም በግልፅ ነው ። ከኋላና ፊት የተለያየ ባህርይ የላቸውም ። ከላይ ከተገለፁት የሙሪድ አይነቶች በአካል ሲያገኙኝ ሁለመናቸው የሚቀያየርና ምናልባት ሸይጧንን በአካል ቢያዩት የማይሰማቸው አይነት ስሜት የሚሰማቸው የሚመስሉ አሉ ። የእነዚህ ሰዎች ጥላቻ መንስኤው ባህሩ ተውሒድ ተውሒድ ከሚሉ ሰዎች አንዱ ነው የሚል እይታቸው ነው ። መጥላታቸው ትክክል ይሁንም አይሁንም ግን ለሙሪድነታቸው ታማኞች ናቸው ። ምክንያታቸው ከላይ የተጠቀሱ መሻኢኾች ለጭንቅ ይደርሳሉ ፣ ይረዳሉ ፣ ሲጠሩ ይሰማሉ ፣ ለጥሪ ምላሽ ይሰጣሉ ፣ የተጨነቀን ይፈርጃሉ ፣ የደኸየን ያከብራሉ ፣ የታመመን ያሽራሉ የሚል እምነት ስላላቸው ነው ። ተውሒድ ተውሒድ የሚሉ ሰዎች ደግሞ የዚህ አይነት እምነት ያከፍራል ይላሉ !። ታዲያ ለእነዚህ ሰዎች ከባህሩና ከሱ አምሳያዎች በላይ ጠላት ማን ነው ? በእነርሱ እይታ ማንም የለም ። በመሆኑም ጠላትነታቸውን ግልፅ በማድረግ ወደ አላህ እንቃረባለን ብለው ስለሚያምኑ ግልፅ ያደርጋሉ ። የነሲሓ ዘመናዊ ሙሪዶች የነሲሓ ዱዓቶች የሰለፍዮች ተምሳሌቶች ናቸው ። ሸይኻቸው ኢልያስ አሕመድ ማለት ዒልሙ ከአንዳንድ የሰለፍ ዑለሞችም ይበልጣል የሚሉ ናቸው !። እንዴት ስትላቸው አንዳንድ የሰለፍ ዑለሞች አንድ ሐዲስን ለማግኘት በእግራቸው ከወር በላይ ይሄዱ ነበር ። ሸይኽ ኢልያስ ግን አሁን የፈለገውን ሐዲስም ይሁን የሰለፎች አሳሮች በቀላሉ ማግኘት ስለሚችል ከሱ የሚያመልጥ ነገር የለም ። ስለዚህ ሁሉንም ሐዲስና የሰለፎች አሳሮችን ያውቃል ። በመሆኑም እሱ የሚለው ነገር ሁሉ ትክክል ነው ይሉሀል ። እነዚህ የነሲሓ ሙሪዶች የሰለፍይ መሻኢኾችንና ኡስታዞች እንዲሁም ዱዓቶችን በሰዎች አእምሮ ውስጥ እንደ ሸይጧን ይስላሉ ። ምክንያታቸው ደግሞ የሰለፍዮች ተምሳሌት ናቸው የሚሉዋቸው ዱዓቶቻቸውና ፍፁም ነው የሚሉትን ሸይኻቸው ከሱና የወጡበትና ኢኽዋንይ ስሩርይ የሆኑበትን ሰለፎችን የተቃረኑባቸው መሰረታዊ የዐቂዳ ነጥቦችን በመረጃ ግልፅ አድርገው በማቅረብ ሐቅን የሚፈልጉ ሁሉ እንዲርቁዋቸው በማድረጋቸው ነው ። በጣም የሚገርመው አብዛኞች የነሲሓ ሙሪዶች ሁለት ፊት ነው ያላቸው ። ከኋላ እንደሸይጧን ይስሉሀል ሲያገኙህ ፈገግ ብለው ሰላም ይሉሃል ። ከእንደነዚህ አይነት የነሲሓ ሙሪዶች ውስጥ አንዱ ባህሩ ማለት ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ነው የምከተለው እያለ ስሜቱን የሚከተል ሰው ነው እያላ የሚያስጠነቅቅና ላገኘው ሁሉ በዚህ መልኩ ዳዕዋ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም ከሽርክና ቢዳዓ ከማስጠንቀቅ የበለጠ አጅር የሚያገኝ የሚመስልበት አይነት ሰው ነው ። ስለዚህ ሰው ብዙ በዚህ መልኩ ዳዕዋ እያደረገ ከሚያስጠነቅቃቸው ወንድሞች እሰማለሁ ። የዚህን ሰው ስም ከተለያዩ ወንድሞች ብዙ ጊዜ ስለምሰማው አንዳንዴ እየተገረምኩ እረሳውና እተወዋለሁ ። ዛሬ አል ኢስላሕ መስጂድ ላይ ከመጝሪብ ሶላት በኋላ ከአንድ ወንድሜ ጋር ቆሜ እያወራሁ ሳለሁ በአካል የማውቀውና ሁል ጊዜ ሲያገኘኝ በጥሩ ፈገግታ ሰላም የሚለኝ ሰው እንደተለመደው ባይሆንም ሰላም ብሎን አልፎን ሄደ ። ያ ከኔ ጋር ቆሞ የነበረው ወንድሜ በጣም ተገርሞ የአሁኑ እኮ እገሌ የሚባለው ሁሌ ካንተ የሚያስጠነቅቀው ሰው ነው አለኝ ። ከሱ ጋር በኔ ምክንያት ሀጅር ተደራርገው አይነጋገሩም ! ለካ የሌላ ጊዜ ፈገግታው የቀነሰው እሱ ከኔ ጋር ስለነበረ ነው ። ገርሞ ገርሞ ይገርማል !!! ። ለዚህ ወንድሜ ይህ ሰው እኮ ሁሌ ነው ፈገግ እያለ ሰላም የሚለኝ ብዬው ቶሎ ተለያይተን ፈጠን ብዬ ስወጣ ውጪ በር ላይ ተገናኘን ። እገሌ ማለት አንተ ነህ አይደል ብዬ ጠየቅሁት እሱም አው እኔ ነኝ አለኝ ። ታዲያ እገሌ ማለት አንተ ከሆንክ ባህሩ ስሜቱን ነው የሚከተለው ብለህ አይደለም እንዴ የምታምነው ? ቁርኣንና ሐዲስን ትቶ ስሜቱን የሚከተል ደግሞ ሙብተዲዕ ነው ። ሙብተዲዕን መጥላትና ማኩረፍ ደግሞ ወደ አላህ የሚያቃርብ ተግባር ነው ። እንዴት አንተ ባህሩ እንዲህ አይነት ሰው ነው ብለህ አምነህ ለሌሎች ዳዕዋ እያደረግህና እያስጠነቀቅህ ስታየኝ እንዴት ሰላም ትለኛለህ ? ላንተ እኔን ማኩረፍ እኮ ወደአላህ የሚያቃርብህ ዒባዳ ነው ብዬው ትቼው ሄድኩኝ ። ይህ ሁሉ ሲሆን መሬት መሬት ከማየት ውጪ መልስ አልነበረውም ! ዛሬስ ምልስ አነበረውም ነገስ አላህ ፊት መልስ ይኖረው ይሆን ? ለማንኛውም የነሲሓ ሙሪዶች ለራሳችሁ ታማኝ ሁኑ ያልኩት ለዚህ ነው !። http://t.me/bahruteka

አሉ ደግሞ አላህ አላህ ስራቸውንም ትዳራቸውንም በቃ ላይፋቸውን ሲያስተካክልላቸው ጓደኞቻቸውን የሚረሱ አኺ እንደዚህ አይነት ወንድ እንዳትሆን በተለይ በዲን መንገድ ላገኘሀው ጓደኛህ

የመጅሊሱ ምክትል ሱፊይ ነው እነ ኢብኑ መስኡድ ሴንተር ከእንደዚህ አይነት ሰው ጋር ሆነን ዲንን እንርዳ እያሉ ነው ከባድ ውሸት🙌

ሽርክ እየሰሩ ቢደአ እየሰሩ የሶሻል ሚዲያ ስማቸውን "እገሌ ነኝ የነቢ ወዳጅ " ይላሉ አጂብ!

እህትዋ ሁሉን ነገር ለአላህ መተው ልመጂ።ችግር ይመጣል ይሄዳል። ሶብርሽ ላይ አደራ የነገሮች መክበድ ወይም መጠንከር የሚመጣውኮ ከአላህ ነው ምንአልባት እየተፈተንሽ ቢሆንስ ??? ፈተናውን በአግባቡ
እህትዋ ሁሉን ነገር ለአላህ መተው ልመጂ።ችግር ይመጣል ይሄዳል። ሶብርሽ ላይ አደራ የነገሮች መክበድ ወይም መጠንከር የሚመጣውኮ ከአላህ ነው ምንአልባት እየተፈተንሽ ቢሆንስ ??? ፈተናውን በአግባቡ ለማለፍ ደሞ ከምንም በላይ صبر አስፈላጊ ነው። እናማ ሶብሪ እህትዋ🫰🏽 @yeselefochteketay

📌 በሶሃቢያት ዘመን የነበረው የሀያእ (የሀፍረት) ገፅታ ​በሶሃቢያት (ረዲየላሁ አንሁነ) ዘመን የነበረው የሴቶች ጥበቃ እና ሀያእ ሁል ጊዜ የሚያስደንቅ ነው። የነሲባ ቢንት ከዕብ (ኡሙ ዐማራህ) ረዲየላሁ ዐንሃ ንግግር እንዲህ ይላል፦ «በዒድ ቀን እንድንወጣ፣ አልፎ ተርፎም ቢክራ ሴቶችን ከክትክታቸው (ከመጋረጃቸው ጀርባ) እንድናወጣ እንታዘዝ ነበር።» ​«ኽድር» (ክትክታ) ማለት አንዲት ቢክራ ሴት ይበልጥ እንድትከበርና እንድትሸሸግ በቤት ውስጥ የሚደረግላት መጋረጃ ወይም የተለየ ክፍል ነው። እዚያ ውስጥ የምታድግ ሴት ከሴቶች እንኳ ስለምትሸሸግ ሀያእዋ እጅግ የላቀ ይሆናል። በየመንገዱ ከሚወጣና ከሚገባ፣ ከማያውቁት ጋር ከሚቀላቀል ሰው በተቃራኒ ይበልጥ አይን አውጣ አትሆንም። ለዚህም ነው በሀያእ ምሳሌ የምትደረገው። ​በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበው የነቢዩ ﷺ ሀያእ ሲገለፅ የመጣው ሀዲስ ይህንን ያረጋግጣል፦ ​الْحَدِيثُ: «كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَشَدَّ حَيَاءً مِنَ الْعَذْرَاءِ فِي خِدْرِهَا» [صحيح البخاري: 6119، صحيح مسلم: 2320] ​ኡሙ ዐማራህ (ነሲባ) ይህንን ስትናገር ሁሉም ሙስሊም ሳይቀር ለዒድ ሰላት መውጣት እንዳለበት ስታስረዳ፣ እነዚያ ተሸሽገው የሚኖሩት ደናግላን እንኳ እንዲወጡ መታዘዛቸውን በመጥቀስ ነው። እነሱ እንኳ ከወጡ ማንም ሰው ወደ ኋላ ሊቀር እንደማይገባ ታሳያለች፤ ምክንያቱም ክብርና ሀያእን ለመጠበቅ ሲባል ሰላት ላይ ከመገኘት ወደ ኋላ ሊቀሩ የሚችሉት መጀመሪያ እነሱ ነበሩና። ◼️​2ኛ_የኡሙል ሙእሚኒን ዓኢሻ (ረ.ዐ) አስገራሚ ሀያእ ​የነቢዩ ﷺ ውድ ባለቤት፣ የሲዲቅ ልጅ ሲዲቃዋ እናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የነበራትን ሀያእ ስታወራ እንዲህ ትላለች፦ «የአላህ መልክተኛ ﷺ እና አባቴ (አቡበከር) የተቀበሩበት ቤት ውስጥ ልብሴን አውርጄ (ዘና ብዬ) እገባ ነበር፤ "እነሱ እኮ ባሌና አባቴ ናቸው" እል ነበር። ነገር ግን ዑመር አብሯቸው ሲቀበር በአላህ እምላለሁ! ከዑመር በማፈር ልብሴን በደንብ (ሳልሸፈን) ገብቼ አላውቅም።»ትላለች ⚪️​እስኪ አስቡት! እናታችን ዓኢሻ መሬት ስር ከተቀበረ አስከሬን ነው ያፈረችው! ለዚህም ስትል በገዛ ክፍሏ ውስጥ ልብሷን ጠቅልላ ትለብስ ነበር። ሀዲሱ እንዲህ ይላል፦ ​: «كُنْتُ أَدْخُلُ بَيْتِي الَّذِي دُفِنَ فِيهِ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَأَبِي، فَأَضَعُ ثَوْبِي، وَأَقُولُ: إِنَّمَا هُوَ زَوْجِي وَأَبِي، فَلَمَّا دُفِنَ عُمَرُ مَعَهُمْ، فَوَاللَّهِ مَا دَخَلْتُهُ إِلَّا وَأَنَا مَشْدُودَةٌ عَلَيَّ ثِيَابِي؛ حَيَاءً مِنْ عُمَرَ» [مسند أحمد: 25660، المستدرك على الصحيحين للحاكم: 4399 - وقال: صحيح على شرط الشيخين] ◼️​3ኛ_የጀናዛ አልጋ (ነዕሽ) አመጣጥ ታሪክ ​ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ የጀናዛ አልጋ (ሰዎች ሞተው ሲሸከሟቸው ሰውነታቸው እንዳይታይ በላዩ ላይ የሚደረግ ቅርፅ) ታሪክ ነው። ለመሆኑ ይህ ለምን እንደተሰራ ያውቃሉ? ፋጢማ አል-ዘህራእ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ለአስማእ ቢንት ዑመይስ የተናገረችውን ድንቅ ንግግር ላስቀምጥላችሁ፦ ​«አስማእ ሆይ! ነገ እኔ ስሞት በራሴ ላይ ስለሚሆነው ነገር እያስብኩ ነው። በአላህ እምላለሁ! በጠራራ ፀሃይ በወንዶች ፊት በካፈን ብቻ ተጠቅልዬ (የሰውነቴ ቅርፅ ታይቶ) ለመውጣት እጅግ አፍራለሁ!» ስትል አስማእ (ረ.ዐ) በሐበሻ ምድር (ኢትዮጵያ) ስትሰደድ ያየችውን፣ ከእንጨት ተሰርቶ የሴቶችን አስከሬን የሚሸፍነውንና የሰውነት ቅርፅ እንዳይታይ የሚያደርገውን የጀናዛ አልጋ (ነዕሽ) ገለፀችላት። ​ፋጢማ (ረ.ዐ) ስትሞት እንኳ ቅርፅዋ እንዳይታይ ያላትን ጨክኖ የቆመ ሀያእ ተመልከቱ! የሞተች ሴት ማንም ላይ ፈተና አትሆንም፣ ማንም አይመኛትም፣ እሷም ማንንም አታይም፤ በዚያ ላይ ሙሉ በሙሉ በካፈን ተሸፍናለች። ይህ ሆኖ ሳለ ግን የሰውነቷ ውጫዊ ቅርፅ እንኳ ለወንዶች እንዳይታይ ፈቀደች። ​ይህንን አልጋ መጀመሪያ የተጠቀመችው የነቢዩ ﷺ ልጅ ሩቀያህ (ረ.ዐ) እንደነበረችም በሌላ ዘገባ ተጠቅሷል። አስማእ ቢንት ዑመይስ ለነቢዩ ﷺ እንዲህ አለች፦ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሐበሻ እያለሁ ክርስቲያኖቹ ለሴት ልጅ በላዩ ላይ ቅርንጫፎች ያሉት አልጋ (ነዕሽ) ሲሰሩ አይቻለሁ (የሰውነቷ ቅርፅ እንዳይገለጽ ይጠላሉ)፤ ለልጅዎ እንዲህ አይነት አልጋ ልስራላት?» ኣለቻቸው ነቢዩም ﷺ፦ «አዎ ስሪላት» አሉ። ​ عَنْ أَسْمَاءَ بِنْتِ عُمَيْسٍ أَنَّ رُقَيَّةَ بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لَمَّا تُوُفِّيَتْ... قَالَتْ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنِّي رَأَيْتُ بِالْحَبَشَةِ شَيْئًا يَصْنَعُونَهُ لِنِسَائِهِمْ، جَعَلُوا النَّعْشَ فَوْقَهُ الْأَضْلَاعُ، أَفَلَا أَجْعَلُ لِابْنَتِكَ نَعْشًا مِثْلَهُ؟ قَالَ: «اصْنَعِيهِ» [المعجم الأوسط للطبراني: 9127] (ፋጢማህ መጀመሪያ የተጠቀመችበት ዘገባም በሱነን አል-በይሀቂ ቁ. 6916 ላይ በሰፊው ተወርቷል)። ​ ◼️​የሶሃቢያትን ሀያእ እና ሞተው እንኳ ለመሸፈን የነበራቸውን ጉጉት ልብ ይበሉ። ከነቢያት በመቀጠል ምርጥ ፍጡራን በነበሩት ሶሃቦች ፊት እንኳ ለመሸሸግ የነበራቸውን ጥንቃቄ ተመልከቱ። በመሞት ጭንቅ ውስጥ ሆነው እንኳ ያሳሰባቸው የሀያእ እና የሂጃብ ጉዳይ ነበር። ​የሚያስደንቀው ግን በዚያ ዘመን የነበረው ማህበረሰብ በሙሉ የሴቶችን ክብርና ሀያእ ለመጠበቅ የተባበረ ነበር። አንድም ሶሃቢይ የቤተሰቡን ሴቶች ያለ በቂ ምክንያት አጊጠውና ተኳኩለው ከቤት ሲወጡና ሲገቡ ዝም ብሎ የሚመለከት አልነበረም። ሶሃቢያትም ለራሳቸውም ሆነ ለሴት ልጆቻቸው እድሜያቸው ትንሽም ቢሆን ይህንን አይፈቅዱም ነበር። ⚪️​ስለሆነም በዘመናችን ያሉ ወንዶች በሴቶቻቸው፣ በራሳቸውና በማህበረሰቡ ላይ አላህን ሊፈሩ ይገባል። የልጆቻቸውን ክብር ሊጠብቁና ትክክለኛውን ሂጃብ በደረጃው እንዲለብሱ ሊያዟቸው ይገባል። ምክንያቱም በቤት ውስጥ መረጋጋት ከሁሉ የላቀው የሂጃብ መገለጫ ነውና። ሴቶችም ክብራቸውን፣ ሀያአቸውንና ስተራቸውን ሊጠብቁ ይገባል፤ ይህም የኢማንና የتقوى (አላህን የመፍራት) መገለጫ ነውና። ሼር ማድረግ እንዳይረሳ t.me/abduselam_addalochy11 t.me/abduselam_addalochy11

🎈ሁለተኛ ማግባት ማለት ልክ እንደ እስልምና ዳዕዋ ጅማሮ ነው . 🎈በድብቅ ትጀምራል ከዛ ሲሰማ ትሰደዳለህ ከዛ ፊት ለፊት ትጋፈጣለህ ከዛ ወይ ድል ታገኛለህ ወይ ሺሂድ ትሆናለህ Copy

"ያልተጋቡ ወጣቶችን የምመክረው፤ እራሳቸውን ለጋብቻ እንዲያዘጋጁ፣ የትዳር ድንጋጌዎችን (ህጎችን)፣ በወንድና በሴት መካከል ያለውን ግንኙነት ህግጋት፣ ለእሱ የተፈቀደለትንና የተከለከለውን፣ በእሱ ላይ ግዴታ የሚሆነውን፣ የሚወደድለትን (ሱና የሆነውን) እና የመሳሰሉትን እንዲያውቁ ነው። ይህን የሚያደርጉት በትዳር ህይወታቸው በአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ፍርሃት (ተቅዋ) ላይ እና የላቀውና ከፍ ያለው የአላህን ሸሪዓ በመጠበቅ ላይ ለመመስረት እንዲችሉ ነው።"ይላሉ ሸይኽ አል-ሉሀይዳን 📚الأحكام المتعلقة بالزواج በዘመናችን ዑለማኦች ብቻ በዚህ ረገድ የተፃፉ ኪታቦች ከ 100 በላይ መሆኑን ደርሼበታለሁኝ::አሏህ ከሰጠህ ግዜ ቀነሰ አርገህ አጥና t.me/abduselam_addalochy11 t.me/abduselam_addalochy11

🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ

ጣፋጭ ስቃይ ብሎ ማለት በአላህ መንገድ ላይ ስትሆን የሚገጥምህ የሆነ ስቃይ ነው ይህ ስቃይ ዛሬ ላይ ሊመር ነገ ላይ ግን ትላልቅ የዲን ስኬቶች ላይ እንድትነግስ መሰረት ይሆንልሃል
إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
አብሽሩ ሰለፊዮች🙌 https://t.me/Abu_Umer1

የሶሻል ሚዲያ አንበሳ ሳይሆን የተውሂድ የሱና አንበሳ ሁኚ🙌
የሶሻል ሚዲያ አንበሳ ሳይሆን የተውሂድ የሱና አንበሳ ሁኚ🙌

ሁለተኛ ሚስት አገባሁ አትበል እህት አመጣሁልሽ በል

የማዳ ስንቅ ለቀልብዎ🫀🎧 @NasihaLishebab

አላህ ጀነትን የሚያስገባህ ተውሂድህን አይቶጂ በፖለቲካ ላይ ያለህን ብስለት ወይም አቋም አይቶ አይደለም ኢኽዋኒዝም❌

እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ! ይህ ቻናል የሱና ኡለማዎች ለተለያዩ ኢስላማዊ ጥያቄዎች በቁርኣንና በሐዲስ ማስረጃነት የሰጧቸውን ፈትዋዎች(መልሶች) የሚያገኙበት መድረክ ነው። ትክክለኛውን የዲን እውቀት ለማግኘት እና ለጥያቄዎችዎ መልስ ለማግኘት ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ። 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDX7r_ao1Y-79yIOZKj4YFA የቴሌግራም ቻናል 👇 https://t.me/Sunnah_Fatawa https://t.me/Sunnah_Fatawa

#ሸይኽ_ረቢዕ ረሒመሁሏህ።
#ሸይኽ_ረቢዕ ረሒመሁሏህ።

ዋናው ዲና ነው🙌