የጥበብ እመቤት 📜
Open in Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
271
Subscribers
-124 hours
+77 days
+15230 days
Posts Archive
271
ያ የምንወደው ትናት እንደቀልድ አለፈ
ዛሬንም አስመስለን አለፍነው!!!
ደግሞ በስስት የምንናፍቀውም ነገ ምናልባት
ላንኖርበት እንችለን-----!?
271
'' አለማወቅ ተስፋ መሆኑን ዘነጋን፡፡ ሰው በተስፋ የሚኖረው ስለማያውቅ ነው፤ ብዙው ነገር የሚሆን የሚመስለን ለዚያ ነዉ፡፡ መንግስት የሚሻሻል የሚመስለን፣ ሌላው ሁሉ ሠው ልብ የሚገዛ የሚመስለን፥ በተስፋ በታጀለ የውሽት እምነት ውስጥ ስንኖር ነው፡፡ የተስፋ ተቃራኒው ተስፋ መቁረጥ መሰለን፤ የተስፋ ተቃራኒው ግን እውነት ነው፡፡ ይህንን ባለማወቃችን በተስፋ ከመኖር አፈነገጥን። እዉነትን አወቅን፡፡ የእውነት ችግሯ ምንድነው?' ብዬ ጠየቅሁት፤....
''የእውነት ችግሯ መልከ ብዙ መሆኗ ነው የሚመስለኝ፥ ቢያንስ ሁለት ፊት አላት፡፡ ሁልጊዜ በጎ አይደለችም፡፡ መራራነቷ ጣዕሟ ነው፡፡....
📚አለማወቅ
271
ህይወት አንደንድ ጊዜ እጅግ ዉስብስብ ፈታኝ እና ግራ የሚያጋባ
ትመስላለች አንደንድ ቀናት እንደ ተራራ ከባድ ሌሎች ቀናት ደግሞ
እንደ ወንዝ የሚፈሱ ሆነዉ ይሰማሉ
ህይወት በምታቀርብልን ፈተናዎች ዉስጥ መማርን ከመረጥን
ምንም ያህል ካባድ ቢሆንም ወደፈት መኀዝ እንችላለን
271
ሕይወት የምትፈትንህ በሸክምህ አይደለም ሸክምህን ተሸክመህ እስከ መጨረሻ መጓዝህን ነው።
ይህን መኪና ስታይ መጀመሪያ የምታስተውለው የተጫነበት ከባድ ሸክም ነው ነገር ግን ሸክሙ ብዙ ስለሆነ ጉዞውን አላቆመም አሁንም መንገዱን ቀጥሎ እየተጓዘ ነው።
እኛም እንደዚሁ ነን የቤተሰብ ኃላፊነት የኑሮ ጫና ያልተነገረ ህመም ያልታየ እንባ... ሁሉንም ተሸክመን በፈገግታ የምንጓዝ ሰዎች ነን።
ሰዎች የሚያዩት ሸክምህን ነው ፈጣሪ ግን የሚያየው ጽናትህን ነው ሰዎች የወደቅክበትን ቀን ሊረሱ ይችላሉ ከወደቅህ በኋላ እንዴት ተነስተህ እስከ መድረሻህ እንደደረስክ ግን ፈጽሞ አይረሱም።
ሸክምህ ቢከብድም ጉዞህን አታቁም ምክንያቱም መድረሻህ ከሸክምህ ይበልጣል።
271
የመጀመሪያ ስህተት ትምህርት ነው…
ሁለተኛው ግን ግዴለሽነት ነው።
ካለፈው ስህተት መማር ካልቻልክ
በገዛ እጅህ ለውድቀትህ እየፈረምክ ነው።
271
ገና ነኝ
ብዙ ዘምርያለሁ ብል ስለ ጌታ ብዙ በአንደበቴ ተናገርያለሁ ብዙ ቅኔ ተቀኝቻለሁ ስለ እርሱ ብዙ ፅፊያለሁ ነገር ግን ገና ነኝ እርሱን በማወቅ ደረጃ ገና ነኝ ምክንያቱም ይሄ ጌታ ከነገር ሁሉ በላይ የሆነ የጠበብ አባት በፍጥረቱ በመግቦቱ በአባትነቱ ያህል ገና አልተረዳሁትም የፍቅር ጅማሬ የሆነውን ጌታ አውቄዋለሁ እል ይሆናል ነገር ግን ገና ነኝ አውቄ አልጨረስኩም
ያን በቃል መግለፅ የማይቻል ጌታ እወድሃለሁ እለዋለሁ እንጂ ከመወደድ ገና ዘግይቻለሁ። ለነገር ሁሉ ገና ነኝ
እኔ ሙሉ ነኝ የምለው እርሱን ለማወቅ በይበልጥ ስተጋ እርሱን በህይወቴ ለመግለጥ ስተጋ ብቻ የእርሱን መልካም ፈቃድ በህይወቴ እንዲገለጥ ስፈቅድ ያኔ ሙሉ ሰው ነኝ
አሁን ግን ገና ነኝ ምንም ትንሽዬ መንፈሳዊእወቀት። ቢኖረኝም ገና ነኝ አዎ ገናነኝ
የ አ ብ
ዕለተ ቅዳሜ በሀሳብ ሰሌዳ ላይ ተፃፈ📜
271
የሰው ልጅ "እሱማ ምን አለበት " አይባልም
ይህች አጭር ቃል በብዙዎቻችን አንደበት ላይ በቀላሉ የምትመላለስ ነገር ግን በሰሚው ልብ ውስጥ ትልቅ ስብራት የምትፈጥር ከባድ ቃል ናት።
ሸክሙን የሚያቀው ባለቤቱ ነው
እያንዳንዱ ሰው እኛ በማናውቀው የሕይወት አውድማ ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተዋጋ ነው።
please ሰዎችን ውጫዊ ገጽታቸውንና ሳቃቸውን ብቻ በማየት "አንተማ ምን አለብክ" አትበሉ 😊
271
የዋህነትሽ ስለ ሰው አርቆ አሳቢነትሽን
እንደ ሞኝነት አድርገው የሚቆጥሩ የመኖር ትርጉም ያልገባቸው ፣ ብዙ ሰዎች አሉ የማያስብልሽን እና ስላንች ግድ የሌለውን ለይተሽ ማወቅ አለብሽ ዝም ስትይ የሚሰሙሽ ዝምታሽ የሚያስጨንቃቸው ስላንች የሚያስቡ ሰዎች ናቸው ያለሽበትን ውደጅው ፣
ውድቀት ቢሆንም ምክንያቱም ፣
ውድቀት ለስኬትሽ የምትከፍይለት የቤት ኪራይ ነው ፣የሚያሳምምሽን ነገር ለመተው አታንገራግሪው ሰዎች መልሳቸው እንደሚያሳምምሽ ካወቅሽ ጥያቄሽን እርሽው ፣ ፈጣሪ ይዘሽ የማይሳካልሽ ነገር ቢኖር ተንኮል ብቻ ነው ።
በስደት ላይ ሁነሽ መከራ ቢደርስብሽም ሰዎች ሊያዝኑልሽ እጅ ህመምሽ ሊሰማቸው አይችልም ፣ስለዚህ ጉዳትሽን
ስብራቶችሽን ሁሉ ከፈጣሪሽ ጋር በሚስጢር አውሪ።
271
Repost from Never Give up!!!
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
ዕውነተኛ ደስታ የሚገኘው በመቀበል ሳይሆን በመስጠት ውስጥ ነው። ስንሰጥ፣ የሌሎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የራሳችንንም እናበለጽጋለን። መስጠት ገንዘብ ብቻ ማለት አይደለም፤ ጊዜን፣ ፍቅርን፣ ድጋፍን፣ እውቀትን ወይም ፈገግታን ሊሆን ይችላል። ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን፣ ከልብ የመጣ መስጠት ትልቅ ለውጥ የማምጣት ኃይል አለው። በዚህች አለም ውስጥ ብዙ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ተያይዘው የሚኖሩት በዚህ የመስጠትና የመቀበል ሰንሰለት ነው። የምንዘራው ፍቅር፣ እዝነትና ልግስና ተባዝቶ ወደ እኛ ይመለሳል። መስጠት የሰው ልጅ የጋራ መተሳሰር ጥበብና ውበት ነው።
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
271
በአንድ ዘመን አንድ ላይ የሚኖሩ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ ። እኚህ ጓደኛሞች ኑሯቸውን የሚገፉት የእንጨት ስራ በመስራት እና በመሸጥ ነበር ። ታዲያ አንድ ቀን እንድሁ የተለመደው ስራቸውን በመስራት ላይ ሳሉ በስህተት አንደኛው የሌላኛውን አብሯጣት ይቆርጠዋል ።
ታዲያ ጉዳቱን ያደረሰበት ጓደኛ በቶሎ አስፈላጊውን እርዳታ ካደረገለት በኋላ የእርሱን ስራ እንደሚሸፍንለት እና ይህ የሆነው ለበጎ እንደሆነ ይነግረዋል ። ጣቱ የተቆረጠው ጓደኛም ጣቱ ከመቆረጡም አልፎ ጓደኛው ለበጎ ነው ማለቱ እጅግ ያበሳጨው እና ቂም ይይዝበታል ።
ይህ አጋጣሚ ከተከሰተ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሁለቱም ወደ ሌላ ሀገር በመርከብ ይጓዛሉ ። ታዲያ ቂሙ ያልበረደለት ጓደኛም ለበጎ ነው ያለውን አስታውሶ ጓደኛውን ከመርከብ ላይ ጥሎት ጉዞውን ይቀጥላል ። ከመርከቡ ወርዶ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ በማያውቀው ሀገር ላይ እያለፈ እያለ በድንገት የአካባቢው ሰዎች ያግቱታል ። ለካ ሲያልፍበት የነበረው ሀገር የዘንዶ አምላኪዎች የነበሩ ሲሆን ለዘንዶው የሚገብሩት ደግሞ ከዚያ አካባቢ የሚያልፍ ፀጉረ ልውጥን አግቶ በመገበር ነበር ። እናም ይህ ጣቱ የተቆረጠበት ጓደኛ በመንደሩ ሰዎች ተይዞ ለዘንዶው መስዋእት ይሆን ዘንድ አሰሩት ። ነገር ግን ከማህላቸው የነበረው አንዱ የመንደሩ ሰው ይህ ታጋች ጣቱ እንደተቆረጠ ያስተውልና ይህን ሰውዬ በአስቸውኳይ እንዲለቁት ይነግራቸዋል ። እነሱም ይህ ታጋች ጣቱ እንደተቆረጠ ባስተዋሉ ጊዜ ቶሎ በአስቸውኳይ ለቀው ወደ መጣበት ይልኩታል ። ይህም የሆነበት ምክንያት እንደ እምነታቸው አካለ ጎዶሎ የሆነ ሰው መስዋእት ማድረግ ለዘንዶው ንቀት እና ክብር እንደሌላቸው ማሳያ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነበር ይህንን ሰው የለቀቁት ።
ታዲያ ይህ ከዘንዶው የተረፈው ሰው ጓደኛው ለበጎ ነው ያለው እውነቱን እንደነበር አስተዋለ ። ከመርከቡም በመጣሉ ተጸጽቶ እሱን ከጣለበት ለማዳን መርከብ ተከራይቶ ፍለጋውን ይጀምራል ። ከጥቂት አሰሳ በኋላ ጓደኛው ላለመሞት ሲጣጣር ያገኘውና ወደመርከቡ ጎትቶ ያስገባዋል ። ከዚህ በኋላ የተፈጠረውን ሁሉ ይነግረው እና ይቅርታ ይጠይቀዋል ። ከሞት የተረፈውም ጓደኛ ይቅርታውን ተቀብሎ እሱም ከመርከቡ መጣሉ ለበጎ እንደሆነ ይነግረዋል ። ያኛው ጓደኛም ግራ በመጋባት እንዴት ብሎ ይጠይቀዋል ። እሱም ከመርከብ ባይወረውረው ኖሮና አብሮት ከእሱ ጋር ቢሄድ ኖሮ እርሱን ትተው እኔ ጤነኛውን መስዋዕት ያደርጉት እንደነበር ነገረው ይባላል ።
✍️TF
271
" ግማሽ ጨረቃ "
ባንድ በኩል ተሸሽጋ ጽልመት ተሸልማ ፣
ባንድ በኩል ጸድላ መድመቅን አልማ ።
እንደምታሳየን ግማሿ ጨረቃ ፣
ሰውም ድክመት አለችበት የምትኖር ተደብቃ ፣
ሰው ብርታትም አለው ለእይታ የሚበቃ ።
እንደ ግማሿ የተደበቀ ፣
እንደ ግማሿ የፈነጠቀ ።
ሰው ጨረቃ መሳይ ፣
ድክመቱን ደብቆ ብርታቱን የሚያሳይ ።
ሰው ጨረቃ መሳይ ።
ብርታቱ የምትታይ ድክመቱ ተደብቃ ፣
ሰው ግማሽ ጨረቃ ፡፡
271
Be firm, but don't be rude. Be kind, but not weak. Be humble, but don't be timid. Be proud of yourself, but don't be arrogant."
271
What makes a person beautiful is not his appearance or his clothes, but his personality or pride!!!
271
Repost from Never Give up!!!
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
"ልክ በራስህ ላይ እምነት ሲኖርክ እንዴት መኖር እንዳለብህ ታውቃለህ።"
በህይወት ዘመንህ ማጣት የሌለብህ ነገር ቢኖር በራስ መተማመንን፣የራስህን ሞራል፣ ክብርህን እና የስነልቦና ጥንካሬን መቼም ቢሆን የትም ብትሆን በህይወት ማጣት የሌለብህ ነገር ነው።
#በራስ መተማመን፣የራስ ሞራልን ፣ ክብርህን እና የስነልቦና ጥንካሬ ከአጣክ የራስህን ሥራ በትክክል መስራት አትችልም ። ስለዚህ አራቱንም በህይወት እንዳታጣ መጠንቀቅ የሚያስፈልግ ወሳኝ ነገር ነው።
#𝐍𝐞𝐯𝐞𝐫 𝐛𝐞 𝐥𝐨𝐬𝐞 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐨𝐧𝐟𝐢𝐝𝐞𝐧𝐜𝐞, 𝐦𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐚𝐧𝐝 𝐩𝐬𝐲𝐜𝐡𝐨𝐥𝐨𝐠𝐢𝐜𝐚𝐥 𝐬𝐭𝐫𝐞𝐧𝐠𝐭𝐡𝐞𝐧 𝐢𝐧 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐥𝐢𝐟𝐞𝐭𝐢𝐦𝐞,
#ቻናሉን_ለወዳጆቻችሁ_ሼር_በማድረግ_እንዲቀላቀሉ_አድርጓቸው::
✍✍https://t.me/payattetion12
271
“In war, when a commander becomes so bereft of reason and perspective that he fails to understand the dependence of arms on Divine guidance, he no longer deserves victory.”
— Seneca the Younger
271
“Don't make promise when you are in joy. Don't reply when you are sad. don't take decision when you are angry.”
