የጥበብ እመቤት 📜
الذهاب إلى القناة على Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
270
المشتركون
+224 ساعات
+107 أيام
+15330 أيام
أرشيف المشاركات
270
የዋህነትሽ ስለ ሰው አርቆ አሳቢነትሽን
እንደ ሞኝነት አድርገው የሚቆጥሩ የመኖር ትርጉም ያልገባቸው ፣ ብዙ ሰዎች አሉ የማያስብልሽን እና ስላንች ግድ የሌለውን ለይተሽ ማወቅ አለብሽ ዝም ስትይ የሚሰሙሽ ዝምታሽ የሚያስጨንቃቸው ስላንች የሚያስቡ ሰዎች ናቸው ያለሽበትን ውደጅው ፣
ውድቀት ቢሆንም ምክንያቱም ፣
ውድቀት ለስኬትሽ የምትከፍይለት የቤት ኪራይ ነው ፣የሚያሳምምሽን ነገር ለመተው አታንገራግሪው ሰዎች መልሳቸው እንደሚያሳምምሽ ካወቅሽ ጥያቄሽን እርሽው ፣ ፈጣሪ ይዘሽ የማይሳካልሽ ነገር ቢኖር ተንኮል ብቻ ነው ።
በስደት ላይ ሁነሽ መከራ ቢደርስብሽም ሰዎች ሊያዝኑልሽ እጅ ህመምሽ ሊሰማቸው አይችልም ፣ስለዚህ ጉዳትሽን
ስብራቶችሽን ሁሉ ከፈጣሪሽ ጋር በሚስጢር አውሪ።
270
Repost from Never Give up!!!
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
ዕውነተኛ ደስታ የሚገኘው በመቀበል ሳይሆን በመስጠት ውስጥ ነው። ስንሰጥ፣ የሌሎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የራሳችንንም እናበለጽጋለን። መስጠት ገንዘብ ብቻ ማለት አይደለም፤ ጊዜን፣ ፍቅርን፣ ድጋፍን፣ እውቀትን ወይም ፈገግታን ሊሆን ይችላል። ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን፣ ከልብ የመጣ መስጠት ትልቅ ለውጥ የማምጣት ኃይል አለው። በዚህች አለም ውስጥ ብዙ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ተያይዘው የሚኖሩት በዚህ የመስጠትና የመቀበል ሰንሰለት ነው። የምንዘራው ፍቅር፣ እዝነትና ልግስና ተባዝቶ ወደ እኛ ይመለሳል። መስጠት የሰው ልጅ የጋራ መተሳሰር ጥበብና ውበት ነው።
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
270
በአንድ ዘመን አንድ ላይ የሚኖሩ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ ። እኚህ ጓደኛሞች ኑሯቸውን የሚገፉት የእንጨት ስራ በመስራት እና በመሸጥ ነበር ። ታዲያ አንድ ቀን እንድሁ የተለመደው ስራቸውን በመስራት ላይ ሳሉ በስህተት አንደኛው የሌላኛውን አብሯጣት ይቆርጠዋል ።
ታዲያ ጉዳቱን ያደረሰበት ጓደኛ በቶሎ አስፈላጊውን እርዳታ ካደረገለት በኋላ የእርሱን ስራ እንደሚሸፍንለት እና ይህ የሆነው ለበጎ እንደሆነ ይነግረዋል ። ጣቱ የተቆረጠው ጓደኛም ጣቱ ከመቆረጡም አልፎ ጓደኛው ለበጎ ነው ማለቱ እጅግ ያበሳጨው እና ቂም ይይዝበታል ።
ይህ አጋጣሚ ከተከሰተ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሁለቱም ወደ ሌላ ሀገር በመርከብ ይጓዛሉ ። ታዲያ ቂሙ ያልበረደለት ጓደኛም ለበጎ ነው ያለውን አስታውሶ ጓደኛውን ከመርከብ ላይ ጥሎት ጉዞውን ይቀጥላል ። ከመርከቡ ወርዶ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ በማያውቀው ሀገር ላይ እያለፈ እያለ በድንገት የአካባቢው ሰዎች ያግቱታል ። ለካ ሲያልፍበት የነበረው ሀገር የዘንዶ አምላኪዎች የነበሩ ሲሆን ለዘንዶው የሚገብሩት ደግሞ ከዚያ አካባቢ የሚያልፍ ፀጉረ ልውጥን አግቶ በመገበር ነበር ። እናም ይህ ጣቱ የተቆረጠበት ጓደኛ በመንደሩ ሰዎች ተይዞ ለዘንዶው መስዋእት ይሆን ዘንድ አሰሩት ። ነገር ግን ከማህላቸው የነበረው አንዱ የመንደሩ ሰው ይህ ታጋች ጣቱ እንደተቆረጠ ያስተውልና ይህን ሰውዬ በአስቸውኳይ እንዲለቁት ይነግራቸዋል ። እነሱም ይህ ታጋች ጣቱ እንደተቆረጠ ባስተዋሉ ጊዜ ቶሎ በአስቸውኳይ ለቀው ወደ መጣበት ይልኩታል ። ይህም የሆነበት ምክንያት እንደ እምነታቸው አካለ ጎዶሎ የሆነ ሰው መስዋእት ማድረግ ለዘንዶው ንቀት እና ክብር እንደሌላቸው ማሳያ ነው ብለው ስለሚያምኑ ነበር ይህንን ሰው የለቀቁት ።
ታዲያ ይህ ከዘንዶው የተረፈው ሰው ጓደኛው ለበጎ ነው ያለው እውነቱን እንደነበር አስተዋለ ። ከመርከቡም በመጣሉ ተጸጽቶ እሱን ከጣለበት ለማዳን መርከብ ተከራይቶ ፍለጋውን ይጀምራል ። ከጥቂት አሰሳ በኋላ ጓደኛው ላለመሞት ሲጣጣር ያገኘውና ወደመርከቡ ጎትቶ ያስገባዋል ። ከዚህ በኋላ የተፈጠረውን ሁሉ ይነግረው እና ይቅርታ ይጠይቀዋል ። ከሞት የተረፈውም ጓደኛ ይቅርታውን ተቀብሎ እሱም ከመርከቡ መጣሉ ለበጎ እንደሆነ ይነግረዋል ። ያኛው ጓደኛም ግራ በመጋባት እንዴት ብሎ ይጠይቀዋል ። እሱም ከመርከብ ባይወረውረው ኖሮና አብሮት ከእሱ ጋር ቢሄድ ኖሮ እርሱን ትተው እኔ ጤነኛውን መስዋዕት ያደርጉት እንደነበር ነገረው ይባላል ።
✍️TF
270
" ግማሽ ጨረቃ "
ባንድ በኩል ተሸሽጋ ጽልመት ተሸልማ ፣
ባንድ በኩል ጸድላ መድመቅን አልማ ።
እንደምታሳየን ግማሿ ጨረቃ ፣
ሰውም ድክመት አለችበት የምትኖር ተደብቃ ፣
ሰው ብርታትም አለው ለእይታ የሚበቃ ።
እንደ ግማሿ የተደበቀ ፣
እንደ ግማሿ የፈነጠቀ ።
ሰው ጨረቃ መሳይ ፣
ድክመቱን ደብቆ ብርታቱን የሚያሳይ ።
ሰው ጨረቃ መሳይ ።
ብርታቱ የምትታይ ድክመቱ ተደብቃ ፣
ሰው ግማሽ ጨረቃ ፡፡
270
Be firm, but don't be rude. Be kind, but not weak. Be humble, but don't be timid. Be proud of yourself, but don't be arrogant."
270
What makes a person beautiful is not his appearance or his clothes, but his personality or pride!!!
270
Repost from Never Give up!!!
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
"ልክ በራስህ ላይ እምነት ሲኖርክ እንዴት መኖር እንዳለብህ ታውቃለህ።"
በህይወት ዘመንህ ማጣት የሌለብህ ነገር ቢኖር በራስ መተማመንን፣የራስህን ሞራል፣ ክብርህን እና የስነልቦና ጥንካሬን መቼም ቢሆን የትም ብትሆን በህይወት ማጣት የሌለብህ ነገር ነው።
#በራስ መተማመን፣የራስ ሞራልን ፣ ክብርህን እና የስነልቦና ጥንካሬ ከአጣክ የራስህን ሥራ በትክክል መስራት አትችልም ። ስለዚህ አራቱንም በህይወት እንዳታጣ መጠንቀቅ የሚያስፈልግ ወሳኝ ነገር ነው።
#𝐍𝐞𝐯𝐞𝐫 𝐛𝐞 𝐥𝐨𝐬𝐞 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐨𝐧𝐟𝐢𝐝𝐞𝐧𝐜𝐞, 𝐦𝐞𝐫𝐚𝐥 𝐚𝐧𝐝 𝐩𝐬𝐲𝐜𝐡𝐨𝐥𝐨𝐠𝐢𝐜𝐚𝐥 𝐬𝐭𝐫𝐞𝐧𝐠𝐭𝐡𝐞𝐧 𝐢𝐧 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐥𝐢𝐟𝐞𝐭𝐢𝐦𝐞,
#ቻናሉን_ለወዳጆቻችሁ_ሼር_በማድረግ_እንዲቀላቀሉ_አድርጓቸው::
✍✍https://t.me/payattetion12
270
“In war, when a commander becomes so bereft of reason and perspective that he fails to understand the dependence of arms on Divine guidance, he no longer deserves victory.”
— Seneca the Younger
270
“Don't make promise when you are in joy. Don't reply when you are sad. don't take decision when you are angry.”
270
"የሰው ልጅ ውበት በፊቱ ሳይሆን በልቡ ውስጥ ባለው የፍቅር መጠን ይለካል። ልብህን ለሚያደንቅህ ሳይሆን፣ ለሚያከብርህ እና በነፃነት እንድትበር ክንፍ ለሚሆንህ ሰው ስጥ።"
270
" የሰው ልጅ ውበቱ "
የሚታየው ውበት ይረግፋል በግዜ፣
ዝናና ስልጣንም ለከንቱ ትካዜ ፣
ፈክቶ የሚኖረው ሞትን የማይፈራ ፣
መልካም ስራ ብቻ ደምቆ የሚያበራ ፣
አመታት ተሻግሮ ግዜ የማይረታው፣
የሰው ልጅ ውበቱ የልቡ መብራት ነው።
ገንዘብም አይደለም ውበትም ይቀራ፣
እውቀት ከልክ ቢያልፍ ከሞት መች ያድናል?
ዘላለም የሚደምቅ ግዜ ተሻጋሪ፣
ጨለማን እረቶ አንደ ጀንበር አብሪ፣
የሰው ልጅ ውበቱ ዘላለማዊ ቅርስ፣
በመልካም ምግባሩ ከልቡ ሲቀደስ፣
ያኔ ነው ውበቱ ሳይረግፍ የሚሻገር፣
የቁም ዘመን ስራው ሲጠመቅ በፍቅር።
270
አስተሳሰብ ከአለባበስ በላይ ሲያምር
መልካምነት ከምንቀባው ሽቶ በላይ ሲያውድ
ስነ ምግባር ከመልክ የበለጠ ውብ ሲሆን
እሱ ነው የሰውነት ልኩ::
270
ክረምት እና ፍቅር❤
ክረምት ሲመጣ ዝናቡ ምድርን ያርሳል፤ ትዝታ ደግሞ ልብን ያረጥባል። አንተን የናፈቅሁት ስለራቅከኝ ብቻ አይደለም፤ በልቤ ውስጥ የተቀመጠክ ስለሆንክ ነው።
ፍቅር ሁልጊዜ አብሮ መሆን አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ ከሩቅ ሆኖ ሰውን በትዝታ የሚያኖር ፀጥ ያለ ስሜት ነው። እንደ ክረምት ዝናብ ሳይታይ የሚያረጥብ፣ ሳይነካ የሚያሞቅ ነው።
ምናልባት አንድ ቀን ይህ ዝናብ ያቆማል፤ ግን በእያንዳንዱ ክረምት ስምህ በልቤ ላይ እንደ ዝናብ ጠብታ ይወርዳል። ምክንያቱም አንዳንድ ፍቅሮች መጨረሻ የላቸውም፤ ወቅት ብቻ ይቀየራል።💔
የጓደኛዬ ትዝታ⚔️🥀
270
ይቅር በለኝ
ንፁህ ሰው ነኝ ብለህ ራስክን ክበሃል
ደግሞም ታብየሃል
ያደፈ ገላህን ንፁህ ካባ አልብሰህ
ከፃድቃኖች ተርታ ራስህን አሰልፈህ
ደካማ አንተነትክን ስጋህን ሾመሃል
ግን ህሊና አለና ደርሶ ይከስሃል
ቅሬታ ያሰማሀል
እንቅልፍ ይነሳሃል
ያለፈ ስራህን ይመረምርና
ትዕዛዝ አልጠበቅክም
ዉለታ አልመለስክም
ታርዞ አላለበስክ ተቸግሮ አልረዳህ
ተርቦ አላበላህ፣
ታሞ ከርሞ አልጋላይ
በእግዜር እጅ ተይዞ፣
በህመም ደንዝዞ no
ወይ ምጣ ወይ ልምጣ እያለ ሲለምን፣
አምላኩን ሲማፀን
እንዳላዬ አይተህ
እንዳልሰማ ሰምተህ
ይማርህ ይግደልህ ሳትል ቆይተሃል
ሳታጠጣዉ ዉሃ ቀና አርገህ ደግፈህ
ሳታጐርሰዉ በጅህ
እያለ ይከስሃል አያርፍም ህሊናህ
አንተኮ ሰርቀሃል
የሰው ሃቅ ወስደሃል
እምነት አጉለሃል
የማታዉቀዉ ፍጥረት
የማታዉቀው ህይወት
በእጅህ አልፎብሃል
270
Indeed, this life is a test. It is a test of many things of our convictions and priorities, our faith and our faithfulness, our patience and our resilience, and in the end, our ultimate desires.”
270
የተፃፈልንን ነው የምንኖረው❓
"ህይወታችን አስቀድሞ ተፅፏል፤ ከተፃፈው ውጪ መኖር አንችልም"የ40 ቀን እድል ነው የሚሉ ብዙ አሉ። "እጣ ፈንታዬ ነው" እያሉ ባሉበት መቆየትን የሚመርጡም ጥቂት አይደሉም።
270
የማለዳ ቅኔ
የውጭው ዓለም ጎህ፣በፀሐይ ቢፈካ፣
የውስጥህ ማንነት፣ጨለማን ከተካ፤
ቀኑ ቀን አይሆንም፣ፀሐይ ስለወጣች፣
እውነተኛው ንጋት፣ሰውነትህ ላይ ነች።
የማለዳ ውበት፣ የንጋቷ ጀምበር፤
ተፈለገች ትውጣ፣ ቢሻት በዛው ትቅር፤
በውስጥህ ላይ ያለው፣ ተስፋና ደግነት፤
አብሮ ካልነቃልህ፣ አይኖርህም ሕይወት።
