የጥበብ እመቤት 📜
Open in Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
270
Subscribers
+224 hours
+107 days
+15330 days
Number of Posts
Data loading in progress...
Reactions
Comments
Telegram Stars
TOP posts by
Data loading in progress...
Publication analysis
Posts | Views dynamics | |||||
*_<<ተወዳጆች>>_*
*(ስለ ልብ መታወክና ስለ እምነት)*
*"ልጄ ሆይ፣* በውስጥህ የጭንቀትና የፍርሃት ማዕበል ሲነሳብህ አትደንግጥ።
የነፍስ ጠላት ሰይጣን አንተን ተስፋ ለማስቆረጥና ካለህበት መስመር ለማውጣት በትዝታዎች፣ በጥርጣሬዎችና በትልልቅ የጭንቀት ሐሳቦች ልብህን ይወጋዋል።
በእነዚህ ሐሳቦች ላይ አትደገፍ፣ አትከራከራቸውም።
ልብህ ግራ ሲጋባ ‘ *ጌታ ሆይ* ፣ እኔ ደካማ ነኝና አንተ እርዳኝ፣ አንተ ጠብቀኝ’ በማለት ራስህን ዝቅ አድርግ። ሰይጣን አንተን ሊያጠፋህ ሲመጣ፣ አንተ ወደ እግዚአብሔር ስትሸሽ ያኔ ኃይሉ ይደክማል።
ጭንቀትህ የቱንም ያህል ታላቅ ቢሆን፣ የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ከዚያ በላይ ሰፊ ነው።
ዛሬ የምታየው ጨለማ ነገ ብርሃን ሆኖ ያልፋል። ጽኑ ሁን፣ በትዕግሥትም ጠብቀው።" | 34 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
የሚያጽናናሽ ሁሉ ራሱ ቁስል የሌለበት አይደለም"
የሚሰጥሽም ሁሉ ከአንቺ የበለጠ ያለው ሰው አይደለም
መስጠት ገንዘብ ወይም ንብረት ብቻ መካፈል አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች የቀራቸውን ትዕግስት ያካፍሉሻል በልባቸው የቀረውን ተስፋ ይሰጡሻል
ከራሳቸው ረጅም ሀዘን በፊት የመጨረሻዋን ፈገግታ እንኳ ከአንቺ ጋር ይካፈላሉ "
ስለዚህ ለሚያሳዩሽ ፍቅርና ደግነት አክብሮት ስጪ'
#ያ በእውነት ውድ ነውና» | 33 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
ሕይወት ብርሃንና ጥላ ድብልቅልቅ ያለባት መድረክ ናት። አስደሳች ጊዜያት እንደ ብርሃን ሆነው ሲታዩን፣ ፈተናዎች ደግሞ የጥላውን ክፍል ይወክላሉ። ብዙውን ጊዜ ብርሃኑን ብቻ እንፈልጋለን፣ ጥላውን እንሸሸዋለን። ነገር ግን፣ ብርሃን ያለ ጥላ ትርጉም አይኖረውም፤ ጥላም ያለ ብርሃን ሊኖር አይችልም። ጨለማ የብርሃንን ዋጋ ያስታውሰናል፣ ፈተናዎች ደግሞ ውስጣዊ ጥንካሬያችንን ያጎለብቱታል። እያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፍ፣ መልካምም ይሁን አስቸጋሪ፣ የራሱ የሆነ ትምህርት ይዞ ይመጣል። እነዚህን ሁለቱን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ስንቀበል፣ ሕይወትን በሙሉ ምሉዕነቷ የመኖር ጥበብ ይገለጥልናል።
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12 | 27 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
ትርጉም የለሽ ግቦች ካላቸው መሀከል አትሁን👌
አንድ ገበሬ ሁልጊዜ በመንገድ ዳር እየተቀመጠ መኪና እስኪያልፍ የሚጠብቅ ውሻ ነበረው። አንድ መኪና ብቅ ሲል ብቻ ውሻው እየጮኸና ለመቅደም እየሞከረ በመንገዱ ላይ ይሮጥ ነበር።
አንድ ቀን ጎረቤቱ ገበሬውን፣ "ለመሆኑ ውሻህ መኪና ደርሶ የሚይዝ ይመስልሃል?" ብሎ ጠየቀው።
ገበሬውም፣ "የሚያስጨንቀኝ እሱ አይደለም። የሚያስጨንቀኝማ አንድ ቀን መኪናውን ቢይዘው ምን ሊያደርገው ነው?" ብሎ መለሰለት።
በህይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች ልክ እንደ ውሻው በትርጉም የለሽ ግቦችን ይኖራሉ። | 35 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
"ጠንካራ ስዎች ግን እንዴት ደስ ይላሉ የማንም ሙገሳ የማንም ወቀሳ ከፍ ዝቅ የማያደርጋቸው እራሳቸዉን ሆነው የሚኖሩ ከመጣዉ መአበል ጋር የማይሽራተቱ ጀግኖች ያስድስቱኛል::🌸💜🦋 | 32 | 1 | 0 | 0 | Loading... | |
አንዳንዱ ጋር ቸኩዬ አንዳንዱ ጋ ዘግይቼ ዋጋ ከፍያለሁ ።
አንዳንዱ ጋር ጥጋቤ አንዳንዱ ጋ ትህትናዬ አስገምቶኛል።
አንዳንዱ ጋር መጠየቄ አንዳንዱ ጋ ዝምታዬ ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ አንዳንዱ ጋ ግዴለሽነቴ አስመርምሮኛል ።
አንዳንዱ ጋር ጨዋነቴ አንዳንዱ ጋ ብልግናዬ ረብሿል።
አንዳንዱ ጋር አማኝነቴ አንዳንዱ ጋ አህዛብነቴ አጠያይቋል።
አንዳንዱ ጋር ቸርነቴ አንዳንዱ ጋ ስስቴ አስገርሟል !! | 35 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
እኛው ነን ጠላትሽ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሀገሬ ዘመንሽ በጠመንጃ ገዝፎ
ሰክኖ በመነጋገር ሰላም ፍቅር ሰንፎ
ሁሉም ለወንበሩ ሲሞተና ሲገደል
በየቦታው ሲወድቅና ሲጣል
ጠላቶችሽ ሁነን ልጆችሽ በጋራ
ከሩቅ ሳይሆን ፍዳሽ የቅረቡ ጎመራ
ዘመን እየሄደ ዘመን እየመጣ
ቢለያይም ቅሉ ሁሌም ያንቺ ጣጣ
ከእኛ ነው መነሻው የሰላምሽ ጥልመት
ከጎራዴም አያልፍም የሩቅማ ጠላት ።
እኛ ነን ጠላትሽ🇪🇹🇪🇹😢 | 44 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
ናፍቀሺኛል ብየ
ናፍቀሺኛል ብየ ለመጮህ አልወጣ
ሰውም ቢያፌዝ እንጂ አንቺን ይዞ አይመጣ
ናፍቀሺኛል ብየ እኔም ግጥም አልፅፍ
ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ
ብቻ ናፍቀሺኛ.....ናፍቀሺኛል በጣም | 47 | 1 | 0 | 0 | Loading... | |
ስርዝ ድልዝ ደብዳቤ
እዚ ደብዳቤ አይ
ልነገርህ ያሰብኩ
አስቤ የፃፍኩት
ፅፌ የሰረዝኩት
ሰርዤ የላኩት
ስርዝ ድልዝ ሁኖ አልነበብ ካለህ
ሳልሰርዘው በፊት ምን ይላል መሰለህ
መግቢያው መደምደምያው ሀተታ በሞላ
ሌላ አይናገርም ከናፍቀከኝና ከፍቅርህ ሌላ። | 40 | 1 | 0 | 0 | Loading... | |
Screenshot_20260708_191208_com_einnovation_temu_ContainerMaskActivity.jpg | 1 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
የት ነህ ስትባል የምታፍርበተ
ቦታ ላይ በፍፁም አትገኝ 🤘 | 39 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
ህይወት ስታስጠላህ እና ስትሰለችህ ታሪክህን ለሁሉም አትዘርዝር።ነገር ግን ለእውነተኛ ጓደኛ አማክር። ሲደብርህ የፊትህ ፈገግታ ጠፍቶ ሴለሚታይ ብዙ አስመሳይ ሰወች ምን ሁኖ ነው አያሉ ሊስልሉህ ይችላሉ በዚያ ስአት የህይወት ታሪክህንና ገመናህ ለሁሉም ሰው አትዘርዝር የሳቁልህ ሁሉ ከውስጥ አይደለም። ይሉቁን ያንተን ዋጋ ለሚያውቅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለሚረዳህ ለአንድ እውነተኛ ወዳጅ ወይም ለቤተሰብ ደውለህ ተጨዋውት ልብህን በፈገግታ ከሚመርዙ ሳይሆን ካንተ ጋር በቁርጠኝነት ከሚቆሙት ጋር አድርገው። | 42 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
የፍላስፎቾ ንግግር... 🗣️
ሀብታም የደከያል ሀኪም ይሞታል
ጎበዝ ይሸነፋል ብልህ ይሳስታል
የበራውን ጠፍቶ የሰሩትን ይፈርሳል
የቆመው ወደቆ የሳቀ ያለቅሳል
ግጥም ሆነ #ጥበብ 💫
ውበት ሆነ ክብርም
ያማረበት ነገር ማስቀየሙ አይቀርም ✨ | 44 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
Voice message | 41 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
Voice message | 45 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
ሁሉ ሴት የብር ወይ የጥቅም አይደል እንደዝቺ አይነት ልባም ሴት አፍቃሪ አለቺ።
ፍቅር በምንም አይነት አይገዛም አይለወጥም 🥰
እግዚአብሔር የተባረከ ትዳር ያደርግላችኋል
ትክከለኛ ፍቅር ማለት እንደዚህ ነው 🙏❤🥰 | 50 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
ሁሉን ነገር ለፈጣሪ መስጠት የሚያመጣው ትልቁ ስጦታ ሰላም ነው።
መለወጥ የማትችለውን በፀጋ ተቀብለህ ለፈጣሪ ስትሰጠው፣ ልብህ ይረጋጋል፣ እንቅልፍህ ይጣፍጣል፣ ደስታህም ይሞላል።
ሁሉን ነገር መቆጣጠር አይጠበቅብህም፤ መታመን ብቻ ይበቃል።
ለፈጣሪ የተሰጠ ሸክም ይቀላል፤ ለፈጣሪ የተሰጠ ልብ ደግሞ በሰላም ይኖራል። የከበዳቹህ ነገር ካለ ለፈጣሪ ስጡት | 46 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል
የአንድ ሰው ጥንካሬ የሚለካው በወደቀበት ብዛት ሳይሆን፣ በወደቀ ቁጥር ተመልሶ በመነሳቱ ነው። ማንም ሊያቆምህ አይችልም — አንተ ራስህ ካላቆምክ በስተቀር። ድንጋይ ለመሆን አትሞክር፣ በቀላሉ ይሰበራል፤ ይልቅስ እንደ ውኃ ሁን — ውኃ የገጠመውን አለት አልፎ፣ ሰርጎና ፈልፍሎ መንገዱን ያበጃል። ለስላሳ ሁን ነገር ግን የማይበገር።
#ቻናሉን_ለወዳጆቻችሁ_ሼር_በማድረግ_እንዲቀላቀሉ_አድርጓቸው::
#Never_give_up | 57 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
"ህይወት እንደ መፅሀፍ ናት፤ አንዳንድ ምዕራፎች ያስለቅሳሉ፣ አንዳንዶቹ ያስደስታሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እጅግ ይፈትናሉ። ነገር ግን አንድ ምዕራፍ መጥፎ ስለሆነ ብቻ የመፅሀፉ ታሪክ አበቃ ማለት አይደለም። ዛሬ ያለህበት ቦታ መጨረሻህ አይደለም፤ የጉዞህ
አንድ አካል እንጂ። በርታ! ታሪክህ ገና አላለቀም።" | 35 | 0 | 0 | 0 | Loading... | |
, | 1 | 0 | 0 | 0 | Loading... |

