en
Feedback
Abu Hayder Aliy

Abu Hayder Aliy

Open in Telegram

نشرالكتاب والسنة وقول العلمآء بائذن الله الباري بأبي حيدر علي إبن سليمان إبن أحمد الولغاوي

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
571
Subscribers
No data24 hours
+287 days
+6030 days
Posts Archive
AnimatedSticker.tgs0.19 KB

✅የጁሙዓ ቀን ሱናዎች 〰〰〰〰〰〰〰〰 ①) ገላን መታጠብ ②) ሲዋክ መጠቀም ③) ጥሩ ልብስ መልበስ ④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት ⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች) ⑥) ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ ⑦) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ ⑧) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት ⑨) ዱአ ተቀባይነት ያለበት ሰአት ስላለ ዱዓ ማድረግ https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

በውሸት የታወቀ ሰው እንኳን ጥንቃቄና የአላህ ፍራቻ እጅግ በሚያስፈልግበት "ጀርሕ እና ተዕዲል" ይቅርና በማንኛውም ተራ ጉዳይ ምስክርነቱ በኢጅማዕ ተቀባይነት የለውም። ምክኒያቱም ለምስክርነት "ዓዳለህ" ያስፈልገዋል። ውሸት ደግሞ "ዓዳለህ"ን ያጓድላል። ሸይኽ ዓብዱልሐሚድ እንዲህ ይላሉ፦ "ኢብኑ መስዑድ ችግር የለበትም እያሉ ነው አይደል!? ኢልያስ ችግር የለበትም እያሉ ነው አይደል!? ፍፁም ናቸው ነው አይደለ!? ፍፁም ናቸው መቶ በመቶ እንከተል እያሉ ነው! ከአንደበታቸው የተወራ ነው።..." እስኪ ልጠይቅዎትና "ፍፁም ናቸው መቶ በመቶ እንከተል ብለው የተናገሩት እነማን ናቸው? ማስረጃ ማቅረብ ይችላሉ? የዚህን ንግግር ክብደት ግን በቅጡ ተገንዝበዋል? የሚናገሩትን የተረዱት አይመስለኝም። ከነቢያት ውጭ ያለን አካል መቶ በመቶ ፍፁም ነው ስህተት የለበትም ማለትኮ ኩፍር (ክህደት) ደረጃ ሊደርስ ይችላል። በዚህ መሰረት የምትናገሩት እውነት ከሆነ ሙመይዕ የምትሏቸውን ሰዎች ከሱና ብቻ ሳይሆን ከኢስላምም ማስወጣት ይጠበቅብዎታል። ነው ወይስ የእርስዎች ብይን አለመቀበል "ችግር የለባቸውም ፍፁም ናቸው እንከተላቸው" ነው ትርጉሙ? አጥፊ ላይም ቢሆን እንኳ እርምት ሲሰጥ ፍትሓዊ መሆንና ወረዕ አያስፈልግም ወይ? ሰዎች ያልተናገሩትን ብለዋል ብሎ መዋሸት የራስን ጭፍን ጥላቻ ከማጋለጥ ውጭ ምን የሚያመጣው ጥቅም አለ? ነው ወይስ እርስዎን የተቃረነ ሰው ላይ ውሸትም ቢሆን ይፈቀዳል? ደግሞ በጣም የሚገርመው በዚህ መልኩ እየተናገሩ "እኔ ጋ የረድ ብቃት የምትፈልጉ ከኔ ጋር ተቀመጡ! አለዚያ ይከብዳቹኋል!..." አላህ እንዲህ ይላል፦ {فَلَا تُزَكُّوۤا۟ أَنفُسَكُمۡۖ} {ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ} = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

በህይወት ጉዞችን ላይ የስኬታችን መገንቢያ መሠረት፣ የለውጣችንም መጀመሪያ «መወሰን» መቻል ነው ብየ አስባለሁ። ብዙዎቻችን የትኛው መንገድ እንደሚበጀን፣ የትኛው ስራ እንደሚያተርፈንና የትኛው ግንኙነ
በህይወት ጉዞችን ላይ የስኬታችን መገንቢያ መሠረት፣ የለውጣችንም መጀመሪያ «መወሰን» መቻል ነው ብየ አስባለሁ። ብዙዎቻችን የትኛው መንገድ እንደሚበጀን፣ የትኛው ስራ እንደሚያተርፈንና የትኛው ግንኙነት ለህይወታችን እንደሚበጀን ጠንቅቀን እናውቃለን። ይሁንና እውቀቱ እያለን፣ ጥበቡ ሞልቶን ሳለ ግን አንዲት እርምጃ ወደፊት ለመራመድ እንቸገራለን። ለምን?የመወሰን ድፍረት ስለሚያጥረን! «ቢያከስረኝስ? ባይሳካልኝስ? ሰዎች ምን ይሉኝ ይሆን?» የሚሉ የፍርሃት ሰንሰለቶች እግራችንን አስረው ከቆምንበት ንቅንቅ እንዳንል ያደርጉናል። አንዳንዴ ካለመወሰን የተነሳ የምናጣው ዕድል፣ ወስነን ከሚደርስብን ኪሳራ በላይ እጅግ የከፋ ነው። ጊዜው ካለፈ በኋላ «ምነው በወሰንኩ ኖሮ» የሚል የቁጭት እንባ ከማፍሰስ በላይ ምን የሚያም ነገር አለ? ውሳኔ በመዘግየቱ ብቻ ስንት ታላላቅ ህልሞች ሳይቀበሩ ሞተዋል? ስንት የንግድ በሮች ተዘግተዋል? ሐቢቢ ስራ ከመጀመርህ በፊት ኪሳራን አትቁጠር፤ ይልቁንም ለመጀመር ባለመወሰንህ የምታጣውን ዕድሜና ጊዜ አስብ።ዛሬ የምትወስነው ትንሽ ውሳኔ፣ ነገ ለምታገኘው ትልቅ ስኬት መነሻ ናት።አትፍራ! ወስን! የአላህ እገዛ የሚመጣው መንገዱን በውሳኔ ለጀመሩት ብቻ ነውና። |•| t.me/AbuSufiyan_Albenan

ኢማሙል_አልባኒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ልክ ከአላህ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ ሁሉ፥ በእውነት የሚከተሉትም የለም ረሱል ﷺ ብቻ ቢሆኑ እንጂ።» 📚 ۞ متفرقات شريط رقم【6】۞ https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye

ውድ የሙልተቃ ቤተሰቦች ይህንን በጉጉት የሚጠበቅ ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም በዚህ ፕሮፋይል ደምቀንና አሸብርቀን መልዕክቱን ለሌሎች ተደራሽ እናድርግ። الوقت: الساعة 2:30 مساءً بتوقيت
ውድ የሙልተቃ ቤተሰቦች ይህንን በጉጉት የሚጠበቅ ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም በዚህ ፕሮፋይል ደምቀንና አሸብርቀን መልዕክቱን ለሌሎች ተደራሽ እናድርግ። الوقت: الساعة 2:30 مساءً بتوقيت إثيوبيا. رابط مجموعة التليغرام: t.me/Multeka_Selefiyin t.me/Multeka_Selefiyin

ሸይኽ_ሷሊህ_አልፈውዛን ሐፊዞሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «አግብተህ፣ ነፍስህን (ከዝሙት) መጠበቅህ፣ ሴቲቱንም እንዲሁ መጠበቅህ እና ዝርያዎችንም መተካትህ ትርፍ ዒባዳዎችን ለመፈፀም ለብቻህ ከመገለልህ የበለጠ ነው።» 📚 ۞ شـرح إغاثـة اللهفـان【25/6/1437】۞ https://t.me/abu_haider_aliye https://t.me/abu_haider_aliye