249
Subscribers
-324 hours
+137 days
+1530 days
Posts Archive
250
...ፍቅር መሸነፍ ነው ፍቅር መያዝ ነው
ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው
ፍቅር ከምክንያት ውጭ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው
ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጭ መሆን ነው” ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው ያስፈራል ፍቅር የማይታከሙት ህመም፣ የማይጠገን ቁስል፣ የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል።”
የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን፤ ማፍቀር ራሱ ነው። ካፈቀርሽ በኋላ “እኔ” የምትይው ሁሉ ይጠፋል። ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።”
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋት፣ በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ
ከ አለመኖር መፅሐፍ
250
Repost from Never give up
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(((ይህ ነው ላንቺ ፍቅር)))
ውዴ.....
እኔ ፍቅር ያልኩት
በአንቺ አጠራር ደግሞ....
ለፍቅር የማይቀርብ
መልመድ የተባልኩት...
....................
እኔ አፈቀርኩሽ ስል
ለካ ይሄ ፍቅር...
መፋቀር አይደለም...
ላፈቀሩት መኖር
መታደል ባይሆንም....
................
እንዲያውም እንዲያውም
ስም ስጪልኝ ስልሽ
ግንኙነታችን....
ይህ ፍቅር አይደለም
መላመድ ብቻ ነው...
የነበሩን ግዜ
እነዚያ ወረቶች
ለካ ውሸት ናቸው
ተላመድን እንጂ
መቼ ተፋቀርን
ብለሽ ባልሽባቸው
እነዚያ አፎችሽ....
እንዴትስ ሌላ ወንድ
ወደድኩህ ትያለሽ....
ባቀፋኝ እጆችሽ
ሌላውን ታቅፊያለሽ....
በሳሙኝ ከንፈሮች
ልትስሚባቸው....
የለመዱት ገላ
ሊቀየርባቸው...
በውሸት ~ በሀሰት
ደግመሽ ሌላ ክህደት
ልትፈፅሚባቸው...
ባዘጋጀሻቸው
እነዚያ ልቦችሽ.....
ሌላ ትለምጃለሽ....
በወደድሽው መጠን
ትላመጂዋለሽ....
ተላምደሽ.....
ተላምደሽ....
........
ጊዜያት ሲበሩ...
ከሱ የተሻለ
ያማረ ሲመጣ...
ደግሞ ሊቀየሩ
በሌላ ብልጭልጭ
ጨርቃጨርቅ ሊተኩ.....
....................
ካዲያ ይህ ነው ፍቅር፤
ይሄ ነው ንፁህ ልብ፤
ግራ በቸጋባ ባደፈ ማንነት፤
በተቆራረጠ በቆሻሻ እውነት፤
በዛ ውስጥ መኖር....
.
.
.
ይህ ነው ላንቺ ፍቅር??
250
Reposting‼️
ሽንኩርት ሲከትፍ ቢላዋ የቆረጠዉ እና እንጨት ሲፈልጥ እጁ የተቆረጠ ሰዉ ሁለቱም “ምን ሆነህ ነዉ?” ቢባሉ “እጄ ተቆርጦ ነዉ” ይላሉ፥
.
ባለ ሽንኩርቱም፡ ባለ መጥረቢያዉም ይደማሉ፣ ይቆስላሉ፡ ቁስላቸዉን ያስታምማሉ፥
250
በነገራችን ላይ ከቅርብ ከጓደኞቻችን ና ከቤተሰቦቻችን በላይ ባህሪያችንን የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎሞች ያውቃሉ. እንዴት ??
በሰፊው በሌላ ጊዜ እንዳስሳለን
