የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 290
Subscribers
-1224 hours
-267 days
-9530 days
Posts Archive
4 291
🇦🇪⚡️ 🇸🇩 ዩናይትድ አረብ ኤሜሬት ከደቡብ አሜሪካ ኮሎምቢያዊያንን እየከፈለች በማምጣት በሱዳን ጦርነት ውስጥ እያሳተፈች ነው ተብላ ተከሰሰች። የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋም እንዳለው፣ ኤሜሬት የኮሎምቢያ ተዋጊዎችን በዳርፉር ጀኖሳይድ በመፈፀም ከተፈረጀው ጃንጃዊድ ወይም RSF ጎን በማሰለፍ እያዋጋች እንደሆነ ከሷል። ከዚህ በፊት የተባበሩት መንግሥታት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኤሜሬት በሱዳን እልቂት ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሆነች ሲናገሩ ቆይተዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድም በሱዳን ጭፍጨፋ ዋነኛ ተዋናኝ የሆነውን RSFን በመደገፍ እና የኤሜሬትን ተከፋይ ገዳዮች በሀገሩ በማሰልጠን እና መጠለያ በመስጠት፣ ክፉኛ ሲወቀስ መሰንበቱ ይታወቃል።
**
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዓለም ላይ የጦርነት አራጋቢ እና የአለመረጋጋት ምንጭ ሆናለች፣ በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ። በእኛም ሀገር ይሄን የሚያግዛት ጥሩ መሪ አግኝታለች። በዚህና በሌሎችም ብዙ ምክኒያቶች ነው የኢራንን በኤሜሬት ላይ መነሳትን ብዙዎች የሚደግፉት። የገንዘብ ምንጫቸው ሲደርቅ፣ ወደራሳቸው ይሰበሰባሉ።
4 291
🇺🇸📞🇮🇷— የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ድርድሮች ላይ፦
አሁን ላይ ኢራን ስምምነት ማድረግ ብቻ ነው የምትፈልግ የሚመስለው። ለስምምነት ቋምጠዋል።ኢኮኖሚያቸው ያለ ገደብ በነፃነት እየተንደባለለ ነው። 250% የዋጋ ግሽበት አላቸው። ገንዘባቸው ምንም ዋጋ የለውም። መላው የኢኮኖሚ ስርዓታቸው ተበላሽቷል።
4 291
🇮🇶 የኢራቅ ሱኒ ጎሳ መሪ ሼክ አሊ ሀቲም፦
ከኢራን አገዛዝ ጋር አብሮ መኖር አይቻልም፤ ትራምፕ በክልሉ የአሜሪካን ስህተቶች ለማረም መጣ፤ ኢራን የአረቦች እውነተኛ ችግር ናት – እስራኤል ደግሞ የፈጣሪ ችግር ናት።
**
በሌላ አባባል፣ ኢራንን እንመታታለን፣ በዛ በኩል ችግር የለብንም፣ እስራኤል ግን የኛ ችግር አይደለችም፣ አምላክ ራሱ ይቆጣጠራት፣ ነው።
የባሕረ ሰላጤው ፔትሮ ዶላር አረብ አገዛዞች እና በስልጣን ሥፍራ ያሉ የሃይማኖቱ መሪዎች፣ በኢራን ላይ ጥላቻቸው አብዛኛው ከሃይማኖት የሚመነጭ ነው። ኢራን ሺዓ በመሆኗ አይወዷትም። ሕዝባቸው ይቃረናቸዋል። አብዛኛው ኢራንን ይደግፋል።
4 291
+2
🇮🇱❌🇵🇸— IDF የሐማስን ወታደራዊ ክንፍ አዲስ መሪ፣ ሙሐመድ አውዳን፣ ሞት አረጋግጧል።
በሥራው ላይ ሳምንት አልቆየም። ገና ጫጉላ ቤት በሉት። በጋዛ፣ ለእስራኤል ብዙ መረጃ አቀባይ አለ፣ ውጤቱ ይህን ይመስላል። በሕይወት የቀረ አመራር የለም።
4 291
🇮🇱🇺🇸🇮🇷🇵🇰- በእስራኤል ቻናል 12 መሠረት፣ ማንኛውም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሁሉም የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከቴል አቪቭ ቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው ወደ አውሮፓ ወደሚገኙ ካምፖች እንደሚዛወሩ ለእስራኤል ባለስልጣናት ተነግሯቸዋል።
4 291
🇮🇷🤝🇸🇦 በሺዎች የሚቆጠሩ ጦርነቱ ያላስቆማቸው ኢራናዊያን የሐጅ ተጓዦች፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ደርሰዋል፡ Financial Times
'በየዓመቱ ከኢራን ይሄዱ ከነበሩ 87 ሺ የሐጅ ተጓዦች መካከል፣ ዘንድሮ መሄድ የቻሉት 30 ሺዎቹ ብቻ ናቸው። ለዚህም ምክኒያቱ፣ ጦርነቱ እና የጦርነቱ መዘዝ ነው።'
ሳዑዲ ዓረቢያ በጦርነቱ ወቅት በመቶዎች በሚቆጠሩ የኢራን ሚሳዬሎች እና ድሮኖች ተደብድባለች። ኢራንም ብትሆን ከሳዑዲ ምድር በተነሱ አሜሪካዊያን ስትመታ መክረሟ ይታወቃል።
4 291
🇺🇸🇰🇪⚡- ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኢቦላ የተጋለጡ አሜሪካውያንን ወደ ኬንያ እየላኩ ነው። በኮንጎ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በኢቦላ እንደተለከፉ ይታወቃል፣ ትራምፕም እስኪድኑ ድረስ ወደ አሜሪካ እንዳይመለሱ ባለፈው ሳምንት እገዳ መጣሉ የሚታወስ ነው።
4 291
🇩🇰 ዴንማርክ የሰዎችን የትውልድ ሀገራት የሚያሳዩ የወንጀል ስታቲስቲክስ መረጃዎችን ከሚያወጡ ጥቂት የምዕራባውያን ሀገሮች አንዷ ናት።
በዴንማርክ፣ ከሶማሊያ እና ከፍልስጤም የመጡ ስደተኞች በአብዛኛዎቹ የወንጀል ምድቦች ውስጥ ግንባር ቀደምነትን ይይዛሉ።
4 291
⚡️🇺🇸🇨🇺 የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮድሪገዝ ፓሬላ፣ ኩባ በአሜሪካ ላይ ስጋት እንደምታመጣ በአሜሪካ ባለስልጣናት የሚነዛውን ወሬ ያስተባበሉ ሲሆን፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮን ደግሞ ውሸት በመናገር ከሰዋል።
"ደህና፣ ኩባ ትንሽ ደሴት እንደሆነች አስብ፣ 100,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሆነች እና 10,000,000 ነዋሪዎች ያሉዋት ናት። በምን አይነት አመክንዮ ላይ በመመስረት ነው ኩባ የኒውክሌር ኃያል ባለቤት የሆነችውን አሜሪካ እያስፈራራች ነው የሚባለው? ኒውክሊየር ባለቤት ሀገርን ማስፈራራት ትችላለች የሚለው ሀሳብ ከጤናማ አእምሮ የመነጨ ነው? በሁለተኛ ደረጃ፣ ማንኛውም ማስረጃ ካለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን መጠየቅ ይኖርብናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ ሲዋሽ ሰምቻለሁ።”
4 291
#ሰበር | 🇮🇳 🇫🇷 — ሕንድ ከፈረንሳይ 114 የራፋዬል ተዋጊ አውሮፕላኖችን በ39 ቢሊዮን ዶላር በሚገመት ወጪ ለመግዛት ያቀረበችው ጥያቄ፣ ከፈረንሳይ በኩል ተቀባይነት ወደማግኘት ደረጃ ደርሷል።
90 ጀቶች በሁለቱ አጋርነት በሕንድ ውስጥ ይመረታሉ፣ 24ቱ ደግሞ በቀጥታ ከፈረንሳይ ይላካሉ። ለጥያቄው የመጨረሻ መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በጁን ወር ወደ ፈረንሳይ ከመጓዛቸው በፊት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይጠበቃል።
4 291
🇱🇧❌🇮🇱 — የ$100 ዶላሯ ድሮን
ሂዝቦላ በደቡብ ሊባኖስ በቢንት ጅቤይል የIDF ወታደሮችን የያዘ የእስራኤል ወታደራዊ ተሽከርካሪን በቀጥታ ሲመታ የሚያሳይ የFPV ድሮን ቪዲዮ፣ አሁን ለቋል።
4 291
🇮🇱⚡️የሚገርመው ነገር በፍልስጤም ውስጥ ለእስራኤል የሚሰራ ብዙ ሕዝብ አለ። ለ$50 እና ለ$100 ዶላር ብለው ለእስራኤል ደህንነት መረጃ በማቀበል የሚሰሩ የፍልስጤም እናቶች፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎች እና አዛውንቶች አሉ። መገናኛ ሬዲዮ ከእስራኤል ይቀበላሉ፣ ያንን ይዘው አንድ ነገር ሲያዩ ይደውላሉ። በዚህ ሄደ፣ እዚያ ቤት ገብቷል ይላሉ። ሁሉም ለምስር ወጥ።
4 291
—❗️🇮🇱/🇵🇸 ሰበር ዜና፣ ባለፈው ሳምንት ተሹሞ የነበረው የሐማስ አዲሱ መሪ፣ መሐመድ አውዳ፣ ዛሬ ምሽት በእስራኤል በተሰነዘረበት ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተነገረ።
የእስራኤል ምንጮች መሪው እንደሞተ እርግጠኞች ሆነዋል።
4 291
🇪🇹⚡️የIMF ልዑክ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ነበር፣ እናም ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ደህይታ መላው ሕዝብ የሚበላው እንዲያጣ በሚመስል መልኩ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ አውርዶ ሄዷል።
እንደሚታወቀው የሦስተኛው ዓለም፣ የአፍሪካ፣ ደሃ ሀገር መሪዎች፣ የፈረንጅ ትዕዛዝን ከማክበር ዝንፍ አይሉም፣ በዚህም መንግሥቱ ትዕዛዙን ለማስፈጸም ዝግጁነቱን አሳይቷል።
1. መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመንን ለገበያ ይተው (ገበያው አንድ ዶላር በ300 ብር ካለ፣ ይበል። ጣልቃ መግባት አይቻልም። አሁን ካለው ውድቀት በላይ ብሩ ይውደቅ)
2. መንግሥት ለሕብረተሰቡ እና ለሕዝብ ተቋማት የሚሰጠውን ድጎማ ሁሉ ያንሳ (አንድ ብናኝ እንጀራ 20 ብር የሆነው መንግሥት ለጤፍ አምራች ማሕበራት ድጎማ በማድረጉ ከሆነ፣ ድጎማው ሲነሳ፣ 20 ብር የነበረው 40 ብር፣ 100 ብርም ሊገባ ይችላል ማለት ነው።)
3 መንግሥት ግብር መሰብሰቡን ከዚህም በላይ ያሳድግ (የሚቀረጡ አዳዲስ ነገሮችን በመፈለግና በመፍጠር ላይ ይበርታ፣ እየቀረጣቸው ያሉ ነገሮች ላይም ግብሩን ይጨምር።)
ይሄ ሁሉ ነገር፣ ሕዝቡን እና ሀገሩን አሁንም ካለው በላይ በአጥንቱ አስቀርቶ የሚያስኬደው መንገድ ነው። ይሄ እንዲሆን የሚባለው already 'የደሃ-ደሃ' ተብላ በተመደበችው ሀገራችን ነው።
ነገ፣ ባለስልጣናቱ ወጥተው ሀገራችን እንዴት ያለ ቆንጆ ነገር እንደገጠማት ያወራሉ፣ የሦስተኛ ዓለም ደሃ ሀገር መሪዎች የሚሉትን የሁል ጊዜ ዲስኩር ይላሉ። በስልጣን ለመቆየት ስለሚፈልጉ፣ እንዲህ ከማለትና ትዕዛዛቱን ከማውረድ ውጭ ምርጫ የላቸውም
4 291
— 🇺🇸/🇮🇷 IRGC ትናንት ማታ በባንዳር አባስ አቅራቢያ የአሜሪካ MQ-9 'Reaper' ድሮንን በኢራን የአየር መቃወሚያ መትቶ ሲጥል የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል።
የMQ-9 Reaper ድሮን ዋጋ $30 ሚሊዮን ዶላር ነው።
4 291
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቼ በሙሉ፣ እንኳን ለኢድ አል አረፋ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እላለሁ።
መልካም በዓል እመኝላችኋለሁ 🐏
4 291
⚡️🇺🇸🇮🇷 የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ የአሜሪካ የባህር ኃይል በሆርሙዝ በኩል የንግድ መርከቦችን መሸኘት ወይም መርዳት እንደገና እንደጀመረ የሚገልጹ የሚዲያ ዘገባዎችን ውድቅ አድርጓል።
“ፕሮጀክት ፍሪደም እንደገና አልተጀመረም፣ የአሜሪካ ኃይሎችም በአሁኑ ጊዜ የንግድ መርከቦችን በሆርሙዝ በር እያጀቡ አይደለም” ሲል CENTCOM ተናግሯል።
CENTCOM ዜናውን ውድቅ ማድረጉ የተሰማው Wall Street Journal የባር ኃይሉ ፕሮጀክት ፍሪደምን እንደገና ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው ብሎ ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ነው።
4 291
— 🇮🇷/🇶🇦 ኢራንን መጥፎ ጎረቤት ለሚሉ የባሕረ ሰላጤው አረቦች…
ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ባህሬን ከኳታር ጋር ግንኙነታቸውን ሲያቋርጡ እና የኢኮኖሚ እገታን ሲጥሉ፣ ምግብ እና ሰብአዊ እርዳታዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ በመላክ በሕይወት እንዲቆዩ ያደረገችው ኢራን ነበረች።
እ.ኤ.አ ከ2017-2021, ለአራት ዓመታት በዘለቀ ሳዑዲ መራሽ ማዕቀብ፣ የአረብ ሀገሮች፣ ኳታርን አክራሪዎችን ትደግፊያለሽ፣ አልጀዚራ የተሰኘው የዜና ማሰራጫ ጣቢያሽም ስማችንን እያጠፋ ነው በሚል ሰበብ፣ በየብስም፣ በአየርም የትራንስፖርት እቀባና የኢኮኖሚ ማዕቀብ በመጣል አሽተዋት ነበር።
ኳታር ልትሰበርና በረሃብ ልትጠበስ ትችል ነበር፣ ለኢራን ባይሆን ኖሮ። ኢራን ከዓለም መገናኛ በሮችን በሷ በኩል ለኳታር በመክፈትና የምግብ ፍጆታዎችን በየቀኑ በነፃ በመላክ ሕይወቷን አስቀጥላለች።
1100 ቶን አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 60 ቶን የበሬ ሥጋ በየቀኑ ለአራት ዓመታት ልካላታለች።
