ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 293
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-217 أيام
-9130 أيام
أرشيف المشاركات
🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ የንፁሃኖች ፍጅት እንደቀጠለ ነው። 12 ተሳፋሪዎች ተገድለዋል! በኦሮሚያ ክልል ከጎሀፅዮን ቱሉ ሚልክ መሀከል - በአንድ የሕዝብ ባስ ሲጓዙ በታጣቂዎች ከታገቱት ተሳፋሪዎች መካከል፣ 12ቱ፣ መኪና ውስጥ እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን እንዳጡ ተገልጿል! የንፁሃን ፍጅት በኢትዮጵያ በአብዛኛው ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት የሚፈጸም ነው። በዚህ ግድያ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት፣ የመንግሥት ሚሊሺያ መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች በግድያዎቹ ሲሳተፉ እና ለገዳዮቹ ሽፋን ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል። እንዲህ ያሉ ክሶች ከዓይን እማኞች እና ከተጎጂ ቤተሰቦች ሲመጡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዚህም፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም በፍጅቶቹ የመንግሥቱን ሚና የሚያሳይ ነው። በኢትዮጵያ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን እና በሚያስደነግጥ ሁኔታ "የግል ሚዲያዎች"ም ጭምር፣ ይህን መሰል የንፁሃን ግድያዎችን ሲዘግቡ አይታዩም፣ ከዘገቡም በዘገባቸው ብሄርን ይመርጣሉ። እነዚህ የሕዝብ እልቂቶች እየተፈፀሙ ያሉት በሰሜን በሚኖሩ የሀገሩ ሕዝብ ላይ ነው፣ በዋናነት በዐማራ ሕዝብ ላይ፣ በመሆኑም ዜናውን ከመዘገብ ይቆጠባሉ። እንዲህ ያሉ የንፁሐን እልቂቶች የሕዝብ ብሶትን በማባባስ ለውጥን ቢያፋጥኑ እንጂ አያዳፍኑም!

⚡️🇮🇱🇺🇸🇮🇷 ኔታንያሁ፦ የኢራንን ስጋት ለማስቆም በማሰብ በየቀኑ ከትራምፕ ጋር እነጋገራለሁ።

— 🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ ዜና፦ ኢራን በቡሸህር ግዛት በጃም አቅራቢያ የአሜሪካን ድሮን ጥላለች -- እንደ ኢራን መገናኛ ብዙሃን Tasnim ዘገባ።

🇱🇧⚡️🇮🇱 በ$100 ዶላር ድሮን፣ $100 ሚሊዮን ዶላር መሳሪያን ማውደም። ሂዝቦላ፣ ዛሬ በለቀቀው አዲስ ቪዲዮ፣ በደቡብ ሊባኖስ ቀጠና ውስጥ ሁለት የIron Dome መሳሪያ ሲስተሞችን በFPV ድሮን ሲያጠቃ ታይቷል።

— 🇮🇷/🇦🇲 አርሜኒያ፣ የኢራን ሥሪት የሆነውን ‘መጂድ’ AD-08 የተባለውን የአየር መቃወሚያ መሳሪያን መግዛቷ ታወቀ። ትናንት በነበረው የአርሜኒያ ጦር ሠራዊት ትዕይንት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ
— 🇮🇷/🇦🇲 አርሜኒያ፣ የኢራን ሥሪት የሆነውን ‘መጂድ’ AD-08 የተባለውን የአየር መቃወሚያ መሳሪያን መግዛቷ ታወቀ። ትናንት በነበረው የአርሜኒያ ጦር ሠራዊት ትዕይንት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ይህ የአየር መቃወሚያ፣ የአሜሪካንን F-15 የጦር ጀት በኢራን አየር ላይ መትቶ መጣል የቻለ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የዚህ መሳሪያ ዝና በዓለም አቀፍ ደረጃ ንሯል። በተመሳሳይ ክስተት ፔንታገንን ያስደነገጠ ነበር። **

⚡️🇮🇱 “ትራምፕ የዘመነ መሲህነት ሂደቱን ጀምሯል።” – ራባይ ሜንደል ኬሲን በመሲሃዊው ዘመን፣ ራቢ ኬሲን እንደሚያብራሩት፣ ኤሳቭ (ማለትም፣ ነጭ ክርስቲያኖች) የአይሁድን ዘር ማገልገል [ኤሩቪን 43B] እና በማንኛውም ፍላጎታቸው ላይ መርዳት አለባቸው። ትራምፕም በተደጋጋሚ፣ የኢራን ጦርነት በተጀመረ ሰሞን፣ 'የመጨረሻው ዘመን ማብሰሪያ ጦርነት (አርማጌዶን)' እያለ ይገልጸው እንደነበር ይታወሳል።

🇺🇸 ትራምፕ፣ መጪውን የአሜሪካ 250ኛ የልደት በዓልን በተመለከተ፣ በ$250 ዶላር ላይ ፎቶዬ ይለጠፍ ማለቱን ገፍቶበታል። የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ይህን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
🇺🇸 ትራምፕ፣ መጪውን የአሜሪካ 250ኛ የልደት በዓልን በተመለከተ፣ በ$250 ዶላር ላይ ፎቶዬ ይለጠፍ ማለቱን ገፍቶበታል። የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ይህን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

🇺🇸🇮🇷🇴🇲⚡- "የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ፣ ትራምፕ የሆርሙዝ ባሕር ቀረጥ ቁጥጥርን በተመለከተ፣ ኦማን እንደ ጎረቤቶቿ አረቦች አርፋ ለአሜሪካ ካልተገዛችና ካልተቀመጠች፣ ሀገሪቱን 'ለማፍረስ' መዛቱን ተከትሎ ኢራን ከኦማን ጎን በአንድ እንደምትቆም ተናገረ" - አል-ጀዚራ።

🇸🇩⚡️የሱዳን መንግሥት ጦር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በኤሜሬት የሚደገፉ አማፂያን ላይ በብዙ ቦታዎች ድል ቀንቶአቸዋል። በጠቅላይ ሚንስቴሩ የሚደገፉት በዘር ማጥፋት የተከሰሱ
🇸🇩⚡️የሱዳን መንግሥት ጦር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በኤሜሬት የሚደገፉ አማፂያን ላይ በብዙ ቦታዎች ድል ቀንቶአቸዋል። በጠቅላይ ሚንስቴሩ የሚደገፉት በዘር ማጥፋት የተከሰሱት አማፂያን፣ ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ናቸው።   የመንግሥት ኃይሎች ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው ኩርሙክ ከተማ እየተቃረበ መሆናቸውን ገለጸዋል‼️   የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በብሉ ናይል ግዛት ሥር ወደ ምትገኘው ኩርሙክ ከተማ እየተቃረበ መሆኑን ሐሙስ ዕለት አስታወቀ። የሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው፤ ጦሩ ወደ ሥፍራው እያመራ ያለው በአካባቢው ያሉና “የአማፂያን የመጨረሻ ምሽጎች” ሲል የገለጻቸውን ቦታዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው።   የሱዳን ጦር “ከአጋር ኃይሎች” ጋር በመሆን “በኩርሙክ ዙሪያ የነበሩትን የመጨረሻዎቹን የአማፂያን ምሽጎች ማውደማቸውን እና ከተማዋን ለመቆጣጠር መቃረባቸውን” ገልጿል።    ጦሩ አክሎም፤ ከኩርሙክ በስተደቡብ በሚገኘው አል-ባርካ ጣቢያ ላይ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) የተሰነዘረውን ጥቃት ማክሸፉን አስታውቋል። በጥቃቱ ወቅት በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ላይ “ከፍተኛ የሰው ኃይል ጉዳት” ማድረሱን እንዲሁም በርካታ የጦር ተሽከርካሪዎችንና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መማረኩን ገልጿል።    እንደ ዘገባው ከሆነ፤ የሱዳን ጦር ኃይሎች በከተማዋ ውስጥ ያሉ ተዋጊዎችን ለመክበብ አልመው በዘረጉት ባለ ሁለት አቅጣጫ ስትራቴጂካዊ ጥቃት ከሰሜን እና ከደቡብ አቅጣጫዎች "ወደ ኩርሙክ እየገሰገሱ" ይገኛሉ።    

🇺🇸⚡️🇮🇷🇴🇲 ኦማን ድጋሜ ከአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷታል፡ 'ኦማን፣ አርፈሽ ብትቀመጪ ይሻላል፣ ከኢራን ጋር ባሕሩ ላይ ኬላ ዘርግቼ ቀረጥ እሰበስባለው ብትይ፣ ዋ! ትመቻለሽ' የአሜሪካ የ
🇺🇸⚡️🇮🇷🇴🇲 ኦማን ድጋሜ ከአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷታል፡ 'ኦማን፣ አርፈሽ ብትቀመጪ ይሻላል፣ ከኢራን ጋር ባሕሩ ላይ ኬላ ዘርግቼ ቀረጥ እሰበስባለው ብትይ፣ ዋ! ትመቻለሽ' የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር።

+1
🇮🇱❗️በአሜሪካ ለእስራኤል በመሰለል ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው እና 30 ዓመት በአሜሪካ እስር ቤት ታስሮ በቅርቡ በእስራኤል ውትወታ የተፈታው ሰላይ ጆናታን ፖላርድ፣ ኢራንን፣ ጋዛን እና ሊባኖስን ካጠናቀቅን በኋላ እስራኤል ከቱርክ እና ከግብፅ ጋር ጦርነት መግጠም እንደሚኖርባት ተናግሯል። “አውሎ ነፋሱ እየመጣ ነው፣ ዓለም ከዚህ በፊት ከተመለከተችው ከማንኛውም ነገር የተለየ" ይላል። “ለሚቀጥለው ጦርነት ዝግጁ መሆን አለብን፣ ይህም ምናልባት በቱርክ እና በግብፅ ላይ ሊሆን ይችላል” ሲል ተናግሯል። ፖላርድ፣ ለእስራኤል በመሰለል እስከታሰረበት ጊዜ ድረስ የአሜሪካ የደህንነት ባለሙያ ነበር። ባለፈው ዓመት ወደ እስራኤል የተመለሰ ሲሆን፣ ዛሬ ላይ ለእስራኤል ፓርላማ ወንበር እየተወዳደረ ነው።

🇳🇬 የናይጄሪያ ፓስተር ባሕሩን ለመክፈል ሞክሮ ሳይሳካለት ቀረ።

—❗️🇮🇷/🇺🇸 የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ ሙጅተባ፣ ከአሜሪካ ጋር ተደረሰ የተባለውን የመግባቢያ ሰነድ ነጥቦች አንዱንም አልተቀበለም። ለዚህ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን ማዘግየት ባይፈ
—❗️🇮🇷/🇺🇸   የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላህ ሙጅተባ፣ ከአሜሪካ ጋር ተደረሰ የተባለውን የመግባቢያ ሰነድ ነጥቦች አንዱንም አልተቀበለም። ለዚህ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን ማዘግየት ባይፈልግም፣ እያዘገየ ያለው። ምክኒያቱም ሙጅተባ በምንም ነጥቦች ላይ ለመስማማት አልፈቀደም-- i24ዜና

🇷🇺❌🇺🇦🇪🇺🇺🇸— የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌ ሾይጉ፦ "
የውጭ አምባሳደሮች ኪየቭን እንዲለቁ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ፍጹም ከባድ እና ሊፈጸም የሚገባው ነው... ሩሲያ ያስጠነቀቀችበት በኪየቭ ላይ የሚደረግ ጥቃት በማንኛውም ጊዜ ሊፈጸም ስለሚችል ነው፣ ስለዚህ ለቅቃችሁ ብትወጡ የተሻለ ይመስላል"
 አሜሪካ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ አክብራ ከቀናት በፊት አምባሳደሯን እና የኤምባሲው ሠራተኞቿን ማስወጣቷ የሚታወቅ ነው። በሌላ በኩል አውሮፓዊያን ሀገሮች ሩሲያን 'ምንም አታመጪም' በማለት ማስጠንቀቂያዋን ወደ ጎን ትተውታል።

—❗🇮🇱/🇱🇧፦ እንደ ዕብራይስጥ ሚዲያ ዘገባ፣ የግድያው ሙከራው ሳይሳካ መቅረቱ ተገልጿል። ከየካቲት ወር ጀምሮ በተከሰተው አዲሱ የግጭት መባባስ፣ ሁለቱ በሂዝቦላ መሪ በሼክ ናኢም ቃሴም ላይ የተደረጉትን ጥቃቶች ጨምሮ፣ ሁሉም ከፍተኛ የእስራኤል የግድያ ሙከራዎች ማለት ይቻላል፣ አልተሳኩም። ሂዝቦላ በ2023-2024 ጦርነት ወቅት ከገጠሙት የስለላ ውድቀቶች የተማረ ይመስላል።

—❗🇮🇱/🇱🇧 ሰበር ዜና፦ ከተኩስ አቁም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በደቡብ ቤሩት ዳርቻ፣ እስራኤል ከፍተኛ የሂዝቦላ መሪ ላይ የግድያ ጥቃት አከናውናለች። ጥቃቱ የተፈለገውን አመራር በመግደል ላይ የተሳካ ይሁን አይሁን አልታወቀም።

የሐማስ ተዋጊዎች፣ ትናንት በጋዛ የአረፋ በዓል ገበያ ላይ በጥበቃ ሥራ ላይ ታይተዋል።

🇷🇺 🗣🇮🇷የሩሲያ የደኀንነት አለቃ፣ ምዕራቡ ዓለም የ ISIS ተዋጊዎችን በኢራን ላይ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። የሩሲያ የፌዴራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) ዋና ኃላፊ፣ አሌክሳንድር
🇷🇺 🗣🇮🇷የሩሲያ የደኀንነት አለቃ፣ ምዕራቡ ዓለም የ ISIS ተዋጊዎችን በኢራን ላይ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። የሩሲያ የፌዴራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) ዋና ኃላፊ፣ አሌክሳንድር ቦርትኒኮቭ ፣ የምዕራብ ሀገራት የስለላ ኤጀንሲዎች የቀድሞ የአይሲስ ታጣቂዎች እና የሌሎች የታጠቁ ቡድኖችን አባላት፣ ከሶሪያ እስር ቤቶች አውጥተው ወደ ኢራቅ በመውሰድ በልዩ ካምፖች ውስጥ በማሰልጠን ኢራን ላይ ያነጣጠረ ኃይል እንደገና ለማደራጀት ዕቅድ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን አስጠንቅቋል። 🗣ቦርትኒኮቭ፣ ታጋዮቹ ቀደም ሲል በሶሪያ ከመታሰራቸው በፊት ለISIS እና ለሌሎች የታጠቁ ቡድኖች የተዋጉ እንደነበሩ አስታውሶ፣ የምዕራቡ የስለላ ተቋማት እነዚህን ተዋጊዎች ወደ ኢራን አስርገው በማስገባት ሀገሪቱን ከውስጥ እንዲያምሱ ስልጠና እየወሰዱ ናቸው ብሏል። “በተገኘው መረጃ መሠረት፣ የምዕራብ የስለላ ኤጀንሲዎች ከሶሪያ የመጡ አሸባሪዎችን ከኢራን ጋር በሚደረግ ጦርነት ውስጥ እንደ ወኪል ኃይሎች ለመጠቀም ጥረታቸውን ቀጥለዋል” ብሏል።

—❗️🇮🇷/🇰🇼/🇺🇸 አራን በኩዌት የአሜሪካን የጦር ሰፈር መምታቷን አስታወቀች። ይሄ የሆነው ከጥቂት ሰዓታት በፊት የአሜሪካ ጦር የኢራንን ወታደራዊ ዒላማዎችን መምታቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። የIRGC መግለጫ፦
'የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት በንጋት በባንዳር አባስ አውሮፕላን ማረፊያ ዳርቻ ላይ ባለው ቦታ ከተከሰተ በኋላ፣ የዚህ ጥቃት መነሻ ነጥብ የነበረው፣ በኩዌት ያለው የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል ማእከል ከሌሊቱ በ10:50 ላይ ዒላማ ተደርጎ ነበር። ይህ ምላሽ፣ ጠላት በኢራን ላይ ለሚያደርገው ማንኛውም ጥቃት መልስ ማግኘቱ እንደማይቀር እንዲያውቅ እንደ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ያገለግላል፣ ከተደጋገመም፣ የእኛ ምላሽ የበለጠ ወሳኝ ይሆናል። ለሚያስከትለው መዘዝ ተጠያቂው አጥቂው ብቻ ይሆናል።'

🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ አዲስ የተቋቋመው የኢራን የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር ላይ ማእቀብ ጣለ።
🇮🇷⚡️🇺🇸 የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ አዲስ የተቋቋመው የኢራን የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር ላይ ማእቀብ ጣለ።