en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 292
Subscribers
+524 hours
-137 days
-8430 days
Posts Archive
በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሳቢያ አገር አቀፍ የተሽከርካሪዎች አድማ እና የትራንስፖርት መቋረጥ ተከሰተ - የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለሥልጣን ግንቦት 6 ቀን የናፍጣ ዋጋን በአንድ ሊትር በ46.29 የኬንያ ሺሊንግ (ወደ 0.36 ዶላር ገደማ) ለመጨመር ባስተላለፈው ውሳኔ ተከትሎ፣ የሚኒባስ ባለቤቶች ማኅበርን፣ የቱሪስት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችን እና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን ጨምሮ በትራንስፖርት ዘርፍ ጥምረት ሥር ያሉ 14 ቡድኖች ይህንን የሥራ ማቆም አድማ ጠርተዋል። በጥምረቱ የቀረቡት ጥያቄዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ 🟠 የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለሥልጣን በግንቦት 6 ያደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዲሰረዝ፤ የቤንዚን እና ናፍጣ ዋጋ በአንድ ሊትር ወደ 152 የኬንያ ሺሊንግ (ወደ 1.17 ዶላር ገደማ) እንዲቀንስ፣ 🟠 በመንግሥታት መካከል የሚደረገው የነዳጅ ግዥ ሥርዓት እንዲቀር እና ተወዳዳሪ የገበያ ሥርዓት እንዲመለስ፣ 🟠 የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ካቢኔ ጸሐፊ (ሚኒስትር) ኦፒዮ ዋንዳዪ ከሥራቸው እንዲለቁ፤ ባለሥልጣኑ እንዲፈርስና ገለልተኛ ተቆጣጣሪ ተቋም እንዲቋቋም፣ 🟠 የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች እንዲቃጠሉ ምክንያት የሚሆኑ የገንዘብ ዝርፊያዎችን እና “የመንጋ ፍርድ” እርምጃዎችን ለማስቆም ደህንነት እንዲጠናከር። በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዋና ዋና አካባቢዎች፦ 1️⃣ ቲካ ሱፐርሃይዌይ፦ ተቃዋሚዎች ሮይሳምቡ እና ኪሁ ንጉሮ/ሩይሩ ባይፓስን ጨምሮ የተወሰኑ የመንገድ ክፍሎችን ዘግተዋል፡፡ 2️⃣ ናይሮቢ፦ አሽከርካሪዎች ሞይ አቬኑ እና ቶም ምቦያ ጎዳናዎችን ከአገልግሎት አግደዋል፡፡ 3️⃣ የናይሮቢ የከተማ ዳርቻዎች፦ በኪቴንጌላ፣ ኦንጋታ ሮንጋይ እና ኪኑ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል፡፡ 4️⃣ ምስራቃዊ ክፍሎች፦ በካሪዮባንጊ፣ አውተር ሪንግ ሮድ እና በምዊኪ መስመር ላይ ከፍተኛ የትራፊክ መዘጋት አጋጥሟል፡፡ 5️⃣ ሌሎች ማዕከላት፦ ናኩሩን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የመንገድ መዘጋቶች እና የትራንስፖርት እጥረቶች መከሰታቸው ተዘግቧል። 👉 የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ የፀጥታ ኃይሎችን ስምሪት ያሳደገ ሲሆን፣ ሁከት በሚፈጥሩ ድርጊቶች እና ሕገ-ወጥ የመንገድ መዝጋት እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

🇺🇸🇮🇱️ — AIPAC (በአሜሪካ የአይሁድ ለጋሾች ማህበር) እና ሌሎች የእስራኤል ደጋፊ ቡድኖች ኮንግረስማን ቶማስ ማሴን በኬንተኪ በመጪው የሪፐብሊካን ምርጫ ለማሸነፍ ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ
🇺🇸🇮🇱️ — AIPAC (በአሜሪካ የአይሁድ ለጋሾች ማህበር) እና ሌሎች የእስራኤል ደጋፊ ቡድኖች ኮንግረስማን ቶማስ ማሴን በኬንተኪ በመጪው የሪፐብሊካን ምርጫ ለማሸነፍ ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል፣ ይህም በውድድሩ አጠቃላይ ወጪን ከ32 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ውድ የሆነው የኮንግረስ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሂደት እንዲሆን አድርጎታል፣ እንደ POLITICO ዘገባ። ከታዋቂ የእስራኤል ሪፐብሊካን ለጋሾች የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ፣ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ የእስራኤልን ረጅም እጅ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚህ በፊት በድብቅና በሹክሹክታ ይደረግ የነበረው የድጋፍ ተሳትፎአቸው፣ አሁን ላይ በአደባባይ ወጥቶ መነጋገሪያ እንዲሆን ሆኗል። ይህ ከመሆኑ ጋር በተያያዘም፣ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ፀረ- አይሁድ እንቅስቃሴ በስፋት እየተስተዋለ ይገኛል። ተመሳሳይ ስሜት በሕዝቡ ዘንድም ተፈጥሯል። በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ የእስራኤልን ጣልቃ ገብነት ከሚቃወሙ ድምፆች መካከል ደግሞ የሪፐፕሊካኑ የኮንግረስ ዕጩ ቶማስ ማሲ ዋነኛውና ትልቁ ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጥቷል። ማሴ፣ ከአብዛኛው ለእስራኤል ከሚሰግዱት የኮንግረስ አባላት አፈንግጦ የቆየ ሲሆን፣ በቅርቡም AIPAC እንደ ባዕድ ሀገር ወኪል እንዲመዘገብ የሚያስገድድ የሕግ አንቀጽ በመቅረፅ፣ በኮንግረስ ፊት ለምርጫ አቅርቧል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሶሻል ሚዲያው ግራ የገባ የ AI ነገሮችን መለጠፉን ቀጥሏል።
+3
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሶሻል ሚዲያው ግራ የገባ የ AI ነገሮችን መለጠፉን ቀጥሏል።

ትራምፕ

🇺🇸⚡ሁለት የአሜሪካ F-18 ወታደራዊ ተዋጊ ጄቶች፣ በ Idaho የአየር ትርዒት እያሳዩ ባሉበት ተጋጭተው ፈንድተዋል። የጀቶቹ ፖይለቶች ተርፈዋል።

🇺🇦🇷🇺 ዩክሬን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞስኮ ከተማ ላይ በወሰደችው መጠነ -ሠፊ ጥቃት በርካታ ዒላማዎች መምታቷን አስታውቃለች። ከዩክሬን የተነሱ የተባሉ ድሮኖች በሞስኮ ከተማ ጠልቀው በመግባት ዒላማዎችን መምታት የቻሉ ሲሆን፣ ጉዳዩ ብዛት ያላቸውን የሩሲያ ተንታኞችን አስደንግጧል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሩሲያ የዩክሬን ጥቃት እያየለ የመጣ ሲሆን፣ አጠቃላይ የጦርነቱን አቅጣጫና መልክ በመቀየር ላይ ነው። በዚህ የዩክሬን ጥቃት መባባስ አውሮፓዊያን መንግሥታት በርግጥም ሩሲያ ልትሸነፍ ካልሆነም ልትሽመደመድ ትችላለች የሚል አስተሳሰብ እንዲያዳብሩና ዩክሬንን ግፊ በማለት እርዳታቸው እንዲጨምሩ እያደረጋቸው ይገኛል።

🇸🇦🤝🇦🇪-ሳዑዲ አረቢያ በአልዳፍራ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባራካህ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመውን የድሮን ጥቃት "የአካባቢውን ደህንነት እና መረጋጋት አደጋ ላይ
🇸🇦🤝🇦🇪-ሳዑዲ አረቢያ በአልዳፍራ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባራካህ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመውን የድሮን ጥቃት "የአካባቢውን ደህንነት እና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል" በማለት በጽኑ አውግዛለች።

!!️🇺🇸🇮🇷 ዩ ኤስ ኢራን ድርድሩን መቋጨት የምትችለው እነዚህን አምስት ቅድመ ሁኔታዎችን ስታሟላ ነው ብላለች - ፋርስ። ️የዋሽንግተን ቅድመ- ሁኔታዎች: ➖ US ምንም አይነት ካሳ ወይም ጉዳ
!!️🇺🇸🇮🇷 ዩ ኤስ ኢራን ድርድሩን መቋጨት የምትችለው እነዚህን አምስት ቅድመ ሁኔታዎችን ስታሟላ ነው ብላለች - ፋርስ። ️የዋሽንግተን ቅድመ- ሁኔታዎች: ➖ US ምንም አይነት ካሳ ወይም ጉዳት ለመክፈል ፈቃደኛ አትሆንም። ➖400 ኪሎ ግራም ዩራኒየም ከኢራን ወደ አሜሪካ መላክ እና ማስተላለፍ ያስፈልጋል። ➖በኢራን ውስጥ የአንድ የኑክሌር ተቋም ብቻ ሥራ እንዲሠራ ይፈቀዳል። የቀሩት ሁሉ መዘጋት ይኖርባቸዋል። ➖የታገዱ የኢራን ንብረቶችን 25% እንኳን ለመመለስ ፈቃደኞች አንሆንሞ። ➖በሁሉም ግንባሮች ጦርነት ማቆም የሚቻለው ድርድሩ ከተጀመረ በኋላ ብቻ ነው። ** ኢራን እነዚህን ሁኔታዎች ብታሟላ እንኳ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል የጥቃት ስጋት ይቀንሳል ተብሎ አይገመትም። በዛ በኩል ዋስትና ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም። የኢራን አቋም የዚህ ግልባጭ ነው። በዋነኝነት በአራት ሁኔታዎች ዙሪያ ያተኩራል። ኢራን፡ አሜሪካ ከአካባቢው ሙሉ ለሙሉ ለቅቃ እንድትወጣ ትፈልጋለች፣ የታገዱባት ንብረቶች በሙሉ እንዲመለስላት ትሻለች፣ አሜሪካና እስራኤል ዳግመኛ እጃቸውን ኢራን ላይ ላለ ማንሳት እንዲፈርሙ እና እስራኤል ከሊባኖስ ለቅቃ እንድትወጣ በዋነኝነት የሚጠይቋቸው ናቸው። ኢራን የሚሰማት ጦርነቱን በበላይነት እንደተወጣችው ነው፣ በመሆኑም የምታቀርባቸው ቅድመ ሁኔታዎቿ ያንን የሚያሳዩ ናቸው። (እነ አሜሪካ White Flag እንዲያውለበልቡ ትፈልጋለች)። የትራምፕ መንግሥት ኢራን ይሄን አቋማን እንድታንፀባርቅ ክፍተት የከፈተ መሆኑ በሀገር ቤት ብዙ ትችቶች እንዲነሱበት፣ በእርግጥም ኢራን በበላይነት ጦርነቱን ተወጥታለች እንዲባል ሆኗል። እናም ይህ አዲሱ የአሜሪካ ቅድመ ሁኔታ ያንን ትችት ለማዳፈን የታሰበ ነው።

🇺🇸🇮🇷⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social በኩል፦ ለኢራን፣ ሰዓቱ እየጠበበ ነው፣ እናም በፍጥነት ቢንቀሳቀሱ ይሻላቸዋል። ያ ካልሆነ፣ ከእነሱ ምንም ነገር እንዳይቀር ይሆናል። ጊዜ
🇺🇸🇮🇷⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social በኩል፦ ለኢራን፣ ሰዓቱ እየጠበበ ነው፣ እናም በፍጥነት ቢንቀሳቀሱ ይሻላቸዋል። ያ ካልሆነ፣ ከእነሱ ምንም ነገር እንዳይቀር ይሆናል። ጊዜ ወሳኝ ነው!

🇮🇱⚡- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ወታደራዊ አመራሮች የተካተቱበት ዝግ የካቢኔ ስብሰባ መምራት ጀምሯል።

🇺🇸🇮🇱⚡️- ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ማታ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ አላቸው።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ጋዜጠኛ፡ 'ስለዚህ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት እንዲደረግ እየጠየቁ ነው?' ሊንድሲ ግራሃም፦ 'አዎ፣ ይህንን አገዛዝ ለመጉዳት ጥሪ እያቀረብኩ ነው።' 'በበቂ ሁኔታ በደንብ ከጎዳችኋቸው ምናልባት ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ።'

🇸🇦ሳዑዲ ድሮኑን ብታየውም እንኳ፣ ወደ ኤሜሬት የሚያልፍ እስከሆነ ድረስ የምትነካው አይመስለኝም።
🇸🇦ሳዑዲ ድሮኑን ብታየውም እንኳ፣ ወደ ኤሜሬት የሚያልፍ እስከሆነ ድረስ የምትነካው አይመስለኝም።

—❗🇨🇺/🇮🇷/🇺🇸 ይህ አሜሪካውያን ሦስተኛ ዙር የኢራን ጦርነትን ለአሜሪካ ህዝብ ለመሸጥ እየሞከሩ ሊሆን ይችላል። ከመጨረሻው የረመዳን ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት፣ AXIOS እንዲሁ ኢራን አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ አህጉራዊ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን እየሠራች መሆኑን ዘግቦ ነበር። በነገራችን ላይ፣ የአይሁዶች የሻቩኦት በዓል ከአራት ቀናት በኋላ ነው።

❗️❗️🇺🇸❗️ትራምፕ ዛሬ ይገኝባቸዋል ተብለው የሚጠበቁትን ሁሉንም ይፋዊ ዝግጅቶችን መሰረዙ የታወቀ ሲሆን፣ በምትኩ፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በኢራን ላይ በሚደረግ የደህንነት ስብሰባ ላይ ይሳተፋል።

—❗🇨🇺/🇮🇷/🇺🇸 ትኩስ፦ ኩባ ከ300 በላይ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ተቀብላለች፣ ምናልባትም ከኢራን እና ከሩሲያ የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እናም በደሴቲቱ ላይ የአሜሪካ ጥቃት ቢደርስ፣ በጓንታናሞ ቤይ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ማዕከልን ጨምሮ፣ በአሜሪካ ወታደራዊ መርከቦች እና በፍሎሪዳ የባህር ዳርቻ ላይ ለመጠቀም እየተዘጋጀች ነው – Axios

🇦🇪 | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 3 ድሮኖች “ከምዕራብ” ወደ ግዛቷ መግባታቸውን እና አንድ ድሮን በአል ዳፍራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ውጫዊ ወሰን ውስጥ የኤሌክትሪ
🇦🇪 | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 3 ድሮኖች “ከምዕራብ” ወደ ግዛቷ መግባታቸውን እና አንድ ድሮን በአል ዳፍራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ውጫዊ ወሰን ውስጥ የኤሌክትሪክ ጄነሬተሬ መምታቱን ተናግራለች። ጠዋት በዚሁ አካባቢ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ተከስቶ የነበር ሲሆን እስከ አሁን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር እየጣሩ ናቸው። የ"ምዕራብ ክልል" ማለት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ ወይም የመን ሊሆን ይችላል።

🇮🇷⚡️የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ ዛሬ፣ እስራኤልን "በሽብር የምትኖር ሽብርተኛ ሀገር" ብሎ በጠራበት ደብዳቤው፣ የሐማስን መሪ ግድያ በጽኑ አውግዟል።
🇮🇷⚡️የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ ዛሬ፣ እስራኤልን "በሽብር የምትኖር ሽብርተኛ ሀገር" ብሎ በጠራበት ደብዳቤው፣ የሐማስን መሪ ግድያ በጽኑ አውግዟል።

🇮🇷🇺🇸🇮🇱 (ኢራን) The Wall Street Journal፦ በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት በዓለም ላይ የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን ጨምሯል። 🔹የሆርሙዝ መተላለፊያ ወሽመጥ መዘጋት ጋር የኃይ
🇮🇷🇺🇸🇮🇱 (ኢራን) The Wall Street Journal፦ በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት በዓለም ላይ የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን ጨምሯል። 🔹የሆርሙዝ መተላለፊያ ወሽመጥ መዘጋት ጋር የኃይል አማራጭ ምንጮችን ሲፈልጉ የነበሩ ሀገራት፣ አሁን ፊታቸውን ወደ ድንጋይ ከሰል አዙረዋል፣ በዚህም ፍላጎቱ ጨምሯል። የአሜሪካ የድንጋይ ከሰል አውጪ ኩባንያዎች፣ የገበያው ፍላጎት አጨናንቋቸው ይገኛል፣ ከሀገር አቅርቦት ውጭ፣ የሚልኩት እጥፍ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል። በአሜሪካ ከተፈጥሮ ጋር ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ የድንጋይ ከሰል እንደሆነ ይታወቃል።