en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 295
Subscribers
No data24 hours
-217 days
-9130 days
Posts Archive
🇪🇹⚡️🇪🇬 የኢትዮጵያ መንግሥት ግብፅ፣ ቀይ ባሕርን እንዳልጠቀም ደንቃራ እንቅፋት ሆናብኛለች፣ በማለት ግብፅን የከሰሰ መሆኑን ተከትሎ፣ ግብፃዊያን በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ላይ meme እና catroon በመሥራት በቴሌግራም እና X ላይ ሲሳለቁበት ተስተውሏል። ሌሎች በቁጣ መልስ ሰጥተዋል። በቴሌግራም ካሉ ታዋቂ ግብፃዊያን አንዱ እንዲህ ሲል ጽፏል፡
የኢትዮጵያ መሪ ነኝ የሚለው ሰው፣ የራሱን ሕዝብ ያጠፋል፣ የጅምላ የጎሳ ጭፍጨፋ ይፈጽማል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቅላል፣ ከዚያ *እኔ እኮ* ሀገሬን ልጠብቅ ነው የሞከርኩት ይላል። እንዲህ ዓይነት ዋሾ አይታችሁ ታውቃላችሁ? እና ዞሮ ክፉ አረቦች በእውነቱ የኢትዮጵያን ፌደራላዊ አንድነት ለማበላሸት እየሞከሩ ነው ይላል፣። ከዚያ ደግሞ ወረራ በመመኘት ኢትዮጵያ ከአሁን በኋላ ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት እንደምትሄድ ያመለክታል። የኖቤል የሰላም ሽልማት ሰጥተውታል፣ ታውቃላችሁ? ለሕዝብ ጨፍጫፊ! ለምን ይህን እንደሚያደርግ ሲጠይቁት፣ *እራሳቸው በግልጽ በእሱ ላይ በማመፅ ላይ ባሉት* በአማራውያን ጀርባ ይደበቃል፣ ከእስራኤል የአይሁድ ርህራሄን እና ድጋፍን ይጠይቃል፣ በኦርቶዶክስ ክርስቲያን ቡድኖች ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ይሞክራል፣ ይህም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደል ሰማያዊ እንደሆነ አድርጎ እንዲታይ ያደርጋል። እሱ ፈርቷል፣ ወይም ምናልባት አብዷል። እብድ ውሾች ደግሞ መወገድና መገደል አለባቸው፣ የኛ ዝምታ ነው የሚገርመው፣ በጣም አሳፋሪ ነው! እኛ በጭራሽ ጠበኛ አይደለንም፣ ከዚህ ውሻ ጋር መሆን ያለብን እንደዚያ ነው፣ በጣም ተገዥ ነን።


🇮🇷🇺🇸🇵🇰❌❗️— የሳዑዲ ሚዲያ አንድ ከፍተኛ ምንጭን በመጥቀስ፡ የኢራኑ የበላይ መሪ፣ ሙጅተባ ኻመኒይ፣ የተብላላውን ዩራኒየም ወደ ዋሽንግተን ላለማድረስ የመጨረሻ ውሳኔ እንደወሰነ ዘግቧል።
🇮🇷🇺🇸🇵🇰❌❗️— የሳዑዲ ሚዲያ አንድ ከፍተኛ ምንጭን በመጥቀስ፡ የኢራኑ የበላይ መሪ፣ ሙጅተባ ኻመኒይ፣ የተብላላውን ዩራኒየም ወደ ዋሽንግተን ላለማድረስ የመጨረሻ ውሳኔ እንደወሰነ ዘግቧል። በሌላ ዜና፣ የፖኪስታኑ ወታደራዊ አዛዥ እና የኢራኑ አደራዳሪ፣ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር፣ ዛሬ ምሽታ ወደ ኢራን የሚያደርገውን ጉዞ መሰረዙ ተሰምቷል።

🇦🇫❗️በአፍጋኒስታን፣ ታሊባን ሴት ልጆች የሚያገቡበትን ዕድሜ ከ16 ዓመት ወደ 9 ዓመት ዝቅ አድርጓል የከዚህ በፊቱ ዝቅተኛው ዕድሜ ከጉርምስና ጅማሬ ጋር የተያያዘ ነበር። አሁን ላይ ግን 'ከሸሪ
🇦🇫❗️በአፍጋኒስታን፣ ታሊባን ሴት ልጆች የሚያገቡበትን ዕድሜ ከ16 ዓመት ወደ 9 ዓመት ዝቅ አድርጓል የከዚህ በፊቱ ዝቅተኛው ዕድሜ ከጉርምስና ጅማሬ ጋር የተያያዘ ነበር። አሁን ላይ ግን 'ከሸሪዓ' ባሉት ድንጋጌ መሠረት፣ 'የጉርምስናን ዕድሜ በማውረድ 9 ዓመት አድርገዋል። ድንጋጌው በእስላማዊው እንቅስቃሴ "ታሊባን" መሪ በሐይባቱላህ አኩንዛዳ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ ሆኗል። BBC በዘገበው ሌላኛው ዘገባ፣ በድህንነት ምክኒያት ህፃን ሴት ልጆቻቸውን ለባርነት የሚሸጡ አፍጋኒስታዊያን ቁጥር፣ ጨምሯል።

— 🇺🇸/🇮🇷 ለድርድር ቡድኑ ቅርብ የሆነ የኢራን ምንጭ፦ 1. የጽሑፎች ልውውጥ እስካሁን ወደ የመጨረሻ ረቂቅ ፅንሰ-ሀሳብ አልደረሰም። 2. የአሜሪካ በኒውክሌር ድርድሮች ላይ ያላት ጽኑ አቋም ውይይቶቹ ወደ ፊት እንዳይራመዱ፣ ወደ መዘጋት አስገብቷቸዋል። 3. ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአሜሪካ ማስፈራሪያዎች ኢራንን አስቆጥተዋታል፣ እና ቴህራን ድርድሩን ለመቀጠል ብዙም ፍላጎት አላሳየችም። 4. ግጭት የመጀመር እድሉ በማንኛውም ጊዜ ሊኖር ይችላል።

🇺🇸🇮🇷⚡️— የFOX NEWS የሕዝብ አስተያየት ግምገማ እንደሚያሳየው፣ 60% የሚሆኑት አሜሪካውያን አሁን በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ መወሰድን ይቃወማሉ።
🇺🇸🇮🇷⚡️— የFOX NEWS የሕዝብ አስተያየት ግምገማ እንደሚያሳየው፣ 60% የሚሆኑት አሜሪካውያን አሁን በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ መወሰድን ይቃወማሉ።

— 🇺🇸/🇮🇷 ሪፖርተር፦ 'በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በልጅዎ ሠርግ ላይ ይገኛሉ?' ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'መሄድ እፈልጋለሁ፣ ነገር ግን አሁን በጣም ጥሩ ጊዜ እንዳልሆነ ነግሬዋለሁ። 'ኢራን' የሚባል ነገር አለብኝ።

— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'እንደምታውቁት የሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር አለን። የኢራንን የባሕር ኃይል አጥፍተናል፣ የአየር ኃይላቸውን አጥፍተናል፣ 85% የሚሆነውን የድሮን እና የሚሳይል አቅማቸውን አጥፍተናል። ነገር ግን፣ ተመልከቱ፣ ኢራን የኑውክሌር መሳሪያ እንዳይኖራት እናረጋግጣለን፣ በሰላም። ያ ሳይሆን ከቀረ በጣም ከባድ ነገር ማድረግ ይኖርብናል።'

— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'ኢራን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የምንፈልገውን ትሰጠናለች።'

— 🇮🇷/🇺🇸 ትኩስ ዜና፦ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ዳግም አዲስ ግጭት የሚፈጠር ከሆነ፣ ኢራን በግሪክ፣ በሮማኒያ እና በጀርመን የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ማዕከላትን ዒላማ ማድረግን ከግምት ውስጥ ታስገባለች -- IRGC.

🇺🇸🤝🇮🇷🕊🇵🇰— አስቸኳይ ዜና፦ አል አረቢያ እንደገለጸው፣ በፓኪስታን አደራዳሪነት የተደረሰው የአሜሪካ-ኢራን ስምምነት የመጨረሻ ረቂቅ እጄ ገብቷል ብሏል። በጥቂት ሰዓታትም ውስጥ ኦፊሴላ
🇺🇸🤝🇮🇷🕊🇵🇰— አስቸኳይ ዜና፦ አል አረቢያ እንደገለጸው፣ በፓኪስታን አደራዳሪነት የተደረሰው የአሜሪካ-ኢራን ስምምነት የመጨረሻ ረቂቅ እጄ ገብቷል ብሏል። በጥቂት ሰዓታትም ውስጥ ኦፊሴላዊ መግለጫዎች ከሦስቱም ወገኖች ይጠበቃል፣ ብሏል። ▶️ የተደረሰበት ስምምነት በሁሉም ግንባሮች ላይ በፍጥነት የተኩስ ማቆምን ይደነግጋል፣ መሠረተ ልማትን ዒላማ ከማድረግ የሚከላከል የጋራ ዋስትናን ይሰጣል፣ በባሕሩ መግቢያዎች እና በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ጥበቃ፣ እና የጋራ የክትትል ዘዴን ማቋቋምን ያካትታል፣ ብሏል። ▶️ የማዕቀብ እፎይታው ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች መፈፀማቸውን ተከትሎ የሚጀምር ሲሆን፣ እንዲሁ መፍትሄ ባልተገኘባቸው ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ድርድሮች ስምምነቱ በሥራ ላይ ከዋለ በሰባት ቀናት ውስጥ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። *** ይሄ አል አረቢያ እጄ ገባ ያለው የድርድሩ ረቂቅ ነው። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ይገለጣል ያለውን መግለጫ እንጠብቃለን። ኦፊሴላዊው መግለጫ አል አረቢያ እንዳለው የሚሆን ከሆነ፣ በድርድሩ ኢራን የምትፈልገውን አግኝታለች ወይም በድርድሩ በበላይነት ወጥታለች ብለን መደምደም እንችላለን። በሌላ በኩል፣ በተለይ እስራኤል፣ በብዙ የሚያስኮርፋት ይሆናል።

⚡️🇸🇦— ሳውዲ ዓረቢያ እያደገ ያለውን የገንዘብ ጉድለቷን (ከገቢ ወጪዋ በዝቷል) እና የጦርነቱን ተጽዕኖ ለማካካስ ስትል፣ ከአሁን በኋላ የምዕራባውያን አማካሪ ድርጅቶችን መቅጠር ማቆሟን እና አዳ
⚡️🇸🇦—  ሳውዲ ዓረቢያ እያደገ ያለውን የገንዘብ ጉድለቷን (ከገቢ ወጪዋ በዝቷል) እና የጦርነቱን ተጽዕኖ ለማካካስ ስትል፣ ከአሁን በኋላ የምዕራባውያን አማካሪ ድርጅቶችን መቅጠር ማቆሟን እና አዳዲስ ውሎችን እንደማትፈራረም አስታወቀች። ከዚያም ባለፈ፣ ያሉባትን የዕዳዎች ክፍያ አራዝማለች። ሳዑዲ ዓረቢያ $405 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ያለባት ሲሆን፣ ይህም ከሀገሪቱ አጠቃላይ GDP 31.7% ይይዛል።

ሩሲያ የኒውክሌር ጦር ኃይሎቿን ስልታዊ እና ታክቲካዊ ልምምድ ታሻሽላለች - ፑቲን ​ፕሬዚዳንቱ ከቤላሩስ ጋር በተካሄደው ልምምድ ማጠቃለያ ላይ ካስተላለፏቸው መግለጫዎች መካከል ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​◻
ሩሲያ የኒውክሌር ጦር ኃይሎቿን ስልታዊ እና ታክቲካዊ ልምምድ ታሻሽላለች - ፑቲን ​ፕሬዚዳንቱ ከቤላሩስ ጋር በተካሄደው ልምምድ ማጠቃለያ ላይ ካስተላለፏቸው መግለጫዎች መካከል ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​◻️ ሩሲያ ስልታዊ ሚሳኤል ኃይሎቿን በአዳዲስ የሚሳኤል ሥርዓቶች ታስታጥቃለች፣ ​◻️ የሩሲያ ጦር ሠራዊት በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ካገኘው ልምድ በመነሳት የውጊያ ግዳጆችን ይለማመዳል፣ ​◻️ ሩሲያ ወደ ጦር መሣሪያ እሽቅድምድም ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም፣ ​◻️ በሩሲያ እና ቤላሩስ መካከል የሚደረጉ የጋራ የኒውክሌር ልምምዶች ወታደራዊ ወንድማማችነትን እንዲሁም የክፍለ-ጦሮች ቅንጅትን ያጠናክራሉ። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልነቷን እንድታጣ ጠየቀች። "ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባልነቷን እንድታጣ የፖለቲካ እና የሕግ ዘዴ መፈለግ አስፈላጊ ነው" ሲሉ የዩክሬን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ ተወካይ አንድሬ ሜልኒክ ተናግረዋል።

🇪🇺🇮🇷⚡️— በሎስ አንጀለስ ፖስት ዘገባ መሠረት፣ በኢራን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ከፍ በማለቱ፣ በአውሮፓ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት አሻቅቧል። የአዳዲስ እና አሮጌ ኤሌክትሪክ መ
🇪🇺🇮🇷⚡️— በሎስ አንጀለስ ፖስት ዘገባ መሠረት፣ በኢራን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ከፍ በማለቱ፣ በአውሮፓ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት አሻቅቧል። የአዳዲስ እና አሮጌ ኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጮች እያደገ ሲሆን፣ ይህም ለኢንዱስትሪው አዲስ ሕይወትን ዘርቷል። ➡️ ጦርነቱ አውሮፓውያን ስለ ኢነርጂ ደህንነት ያላቸውን አስተሳሰብ በመሠረታዊነት ቀይሯል፣ ይህም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ከ"ምናልባት አንድ ቀን" ወደ "አሁኑ ወዲያውኑ" እንዲቀይሩ አድርጓቸዋል። ** ያልገባቸው ነገር፣ ኤሌክትሪኩን የሚያመነጨው ነዳጅ መሆኑ ነው። መኪናው ኤሌክትሪክ ለማግኘት ኤሌክትሪኩ መጀመሪያ ነዳጅ ማግኘት አለበት። ነዳጅ ከሌለ ኤሌክትሪክ አይኖርም። የቀረው ነዳጁን መኪና ውስጥ መቅዳቱ ብቻ ነው፣ እንጂ መኪናው ያው ዞሮ ዞሮ ነዳጁን በኤሌክትሪክ በኩል ያገኘዋል። በአሜሪካ ከ70% በላይ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ከድንጋይ ከሰል (20-25%) እና ከነዳጅና ጋዝ ነው (50%-55%).

🇹🇷🇺🇸⚡️— በብሉምበርግ መረጃ መሠረት፡ የቱርክ ኢኮኖሚ በኢራን ጦርነት ምክኒያት እየከሰረ ነው። በመጋቢት ወር ቱርክ በአሜሪካ ግምጃ ቤት የነበራትን ሰነድ (ንብረቶቿን) በከፍተኛ ሁኔታ በመቀ
🇹🇷🇺🇸⚡️— በብሉምበርግ መረጃ መሠረት፡ የቱርክ ኢኮኖሚ በኢራን ጦርነት ምክኒያት እየከሰረ ነው። በመጋቢት ወር ቱርክ በአሜሪካ ግምጃ ቤት የነበራትን ሰነድ (ንብረቶቿን) በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ከ16 ቢሊዮን ዶላር ወደ 1.8 ቢሊዮን ዶላር አውርደዋለች። ➡️ እርምጃው የተወሰደው አንካራ ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ በገበያ መዋዠቅ ወቅት (ሊራ) የቱርክ ብርን ለመደገፍ በሞከረችበት ወቅት ሲሆን፣ ማዕከላዊ ባንኩ ደግሞ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የውጭ ምንዛሪ እና የወርቅ ክምችትን አሟጦ ተጠቅሟል። ➡️ እርምጃዎቹ ቢወሰዱም ግን፣ የቱርክ ሊራ አሁንም ጫና ውስጥ ነው፣ የዋጋ ግሽበት ወደ 32.4% ከፍ ብሏል።

🇮🇱⚡️— በኢየሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ ዘገባ መሠረት፡ በጦርነት ምክንያት በተፈጠረው የሥነ-ልቦና ችግር እና ለረጅም ጊዜ በብሔራዊ የስሜት ቀውስ ምክንያት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ በእስራኤል ውስጥ የ
🇮🇱⚡️— በኢየሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ ዘገባ መሠረት፡ በጦርነት ምክንያት በተፈጠረው የሥነ-ልቦና ችግር እና ለረጅም ጊዜ በብሔራዊ የስሜት ቀውስ ምክንያት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ በእስራኤል ውስጥ የአእምሮ ጤና ህክምና ፍላጎት በ240% ገደማ ጨምሯል።

— 🇺🇸/🇮🇷 በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ የወደሙ ወታደራዊ አቅሞችን፣ ኢራን በፍጥነት መልሳ መገንባት ጀምራለች፣ ይህም በአሜሪካ የስለላ ተቋሞች የተረጋገጠ መሆኑ ተነግሯል ። ከእነዚህ አቅ
— 🇺🇸/🇮🇷 በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ የወደሙ ወታደራዊ አቅሞችን፣ ኢራን በፍጥነት መልሳ መገንባት ጀምራለች፣ ይህም በአሜሪካ የስለላ ተቋሞች የተረጋገጠ መሆኑ ተነግሯል ። ከእነዚህ አቅሞች መካከል፣ ሁለት ምንጮች ለCNN  እንደገለጹት፣ ኢራን በሚያዝያ መጀመሪያ ላይ በጀመረው የስድስት ሳምንት የተኩስ አቁም ወቅት፣ ድሮንና ሚሳዬሎችን በአዲስ መልክ ማምረት መጀመሯን ተናግረዋል። እነዚሁ ምንጮች አክለውም፣ እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ወታደራዊ አቅም ላይ በጠበቁት ልክ ውድመት አላደረሱም፣ ሲሉ ለCNN ተናግረዋል።

— 🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ፦ የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ ሙጅተባ ኻመኒይ የኢራንን የተብላላ የዩሬኒየም ክምችት ወደ ማንኛውም የውጭ ሀገር ቦታ ማዛወርን እንዳገደ ሮይተርስ ዘግቧል። ኢራን በግምት 400
— 🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ፦ የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ ሙጅተባ ኻመኒይ የኢራንን የተብላላ የዩሬኒየም ክምችት ወደ ማንኛውም የውጭ ሀገር ቦታ ማዛወርን እንዳገደ ሮይተርስ ዘግቧል። ኢራን በግምት 400 ኪ.ግ የዩራኒየም ክምችት አብላልታ ከመሬት በታች በሚገኝ ዋሻ ውስጥ እንደሸሸገችው ይነገራል። ባለፈው ሳምንት፣ ሩሲያ፣ የኢራን ዩሬኒየም ወደ ሦስተኛ ሀገር መዛወር ካለበት፣ ለመውሰድ እና በአደራ ራሷ ጋር ለማስቀመጥ ፈቃደኝነቷን አሳይታ ነበር። አሜሪካ ግን፣ ሩሲያ፣ ኢራን በምትፈልገው ሰዓት መልሳ ትሰጣታለች በሚል ስጋት፣ ያንን ሐሳብ ሳትፈልግ ቀርታለች። የአሜሪካ ፍላጎት፣ ኢራን ዩሬኒየሙን ለእሷ ብቻ እንድታስረክባት ነው።

🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇷 ሳውዲ ዓረቢያ በኢራን ላይ ማንኛውንም ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ እስከ ሐጅ ወቅት ማብቂያ ድረስ እንዲያራዝም፣ የትራምፕ አስተዳደርን መጠየቋ ተነገረ። ሐጅ፣ እንደ ፈረንጆች፣ ሜ
🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇷 ሳውዲ ዓረቢያ በኢራን ላይ ማንኛውንም ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ እስከ ሐጅ ወቅት ማብቂያ ድረስ እንዲያራዝም፣ የትራምፕ አስተዳደርን መጠየቋ ተነገረ። ሐጅ፣ እንደ ፈረንጆች፣ ሜይ 25 ተጀምሮ በሜይ 30 ይጠናቀቃል።

🇺🇸🇨🇺⚡️ — የዋይት ሃውስ የፖሊሲ ሥራ አስፈፃሚ Stephen Miller፦ 'ብዙ አሜሪካውያን ላያውቁ ይችላሉ፣ ነገር ግን ማወቅ ያለባቸው ከአሜሪካ ዳርቻዎች በበረራ 45 ደቂቃ ርቀት ላይ የምትገኘው ኩባ፣ ለአስርተ ዓመታት ለአሜሪካ ተቀናቃኞች ዋሻ እና መነሻ ሆና ቆይታለች። የኮሚኒዝም እና የቀዝቃዛው ጦርነት የመጨረሻ ጦር ሰፈር ናት። የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ለትውልዶች ችግሩን ለመፍታት ሞክረዋል፣ ከአሜሪካ ዳርቻዎች በጥቂት ማይሎች ርቀት ላይ የሚገኘው የዚህ የኮሚኒስት መሠረት ስጋት ሆኖ ቆይቷል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ በአመራሩ እና በራዕዩ አማካኝነት፣ ኩባ ነፃ የምትሆንበት እና ኩባ ከአሁን በኋላ ለአሜሪካ ስጋት የማትሆንበት ነገር ግን ኩባ ለአሜሪካ ጓደኛ እና አጋር የምትሆንበት ቀን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቀርቦልናል፣ ይህም ለብሔራዊ ደህንነታችን አስፈላጊ ነው።'