en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 308
Subscribers
No data24 hours
-227 days
-8530 days
Posts Archive
🇮🇷🇦🇪ሮይተር ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገው፡ ኤሜሬት ለኢራን $10 ቢሊዮን ዶላር ለመልቀቅ የተስማማች ሲሆን፣ 3 ቢሊየን ዶላሩን በአይሮፕላን ጭና ለኢራን አራግፋለች። ኤሜሬት፣ የሮይተርን ዘገባ፣
🇮🇷🇦🇪ሮይተር ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገው፡ ኤሜሬት ለኢራን $10 ቢሊዮን ዶላር ለመልቀቅ የተስማማች ሲሆን፣ 3 ቢሊየን ዶላሩን በአይሮፕላን ጭና ለኢራን አራግፋለች። ኤሜሬት፣ የሮይተርን ዘገባ፣ መሠረተ ቢስ እና ውሸት ስትል አጣጥለዋለች።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የአናሳ ብሔር ቋንቋዎች ውስጥ፣ የሩሲያን ቋንቋ ሰረዘች። በዩክሬን፣ የሩሲያ ቋንቋ ሁለተኛ ትልቁ ቋንቋ ሲሆን፣ ከሕዝቡ ከ30-35% ለቀን ተቀን ሕይወቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የሩሲያ ቋንቋ ከትምህርት ቤቶች፣ ከሚዲያዎች፣ ከሃይማኖታዊ ሥፍራዎች፣ ከሕዝባዊ መገልገያዎች እና ከኦፊሴላዊ ቦታዎች ሕገ- ወጥ ተብሎ ጥቅም ላይ ከመዋል መታገዱ ይታወሳል። *-*-*- ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያላት ጥላቻ ሥር የሰደደ እና እጅግ የከፋ ነው። አስደንጋጭ ነው በጣም፣ ለሚያውቀው። ሕዝቡ አይደለም በነገራችን ላይ፣ መንግሥቱ ነው። ሕዝቡ በእምነቱ ከሩሲያ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ 92% የኦርቶዶክስ እምነትን ይከተላል። ለረጅም ጊዜ፣ ቤተክርስቲያኒቱ በሩሲያ ሲኖዶስ ሥር ነበረች። ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው የተሳሰረ ነው፣ ችግር የለባቸውም በዚያ። አሁን ግን የዩክሬን መንግሥት ሕዝቡ ሩሲያን እንዲጠየፍ እና እንዲጠላ 24 ሰዓት ይሰራሉ፣ በሁሉም ረገድ። ወጣቱን ዛሬም፣ የሩሲያን ሙዚቃ ያዳምጣል፣ የሩሲያን ሶሻል ሚዲያ ይከተላል፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ እንደ ሩሲያዊያን ለመሆን ይጥራል፣ እያሉ ይከሱታል። የሩሲያን ቋንቋ ማውራትን እንደ መሰልጠን አድርጎ ሕዝቡ ይወስደዋል፣ በተለይ ወጣቱ፣ በሚል መንግሥቱ በየቀኑ ያንን እንዲተው ፕሮፓጋንዳዎች ይለቃል። ከ2019 በኋላ፣ ዩክሬንን ከሩሲያ ተጽእኖ ለመገንጠል ባለመ መልኩ የዩክሬን ቤተክርስቲያን ለሁለት እንዲሰነጠቅ ተደርጓል። እርስ በእርስ በቁራኛ የሚተያዩ፣ ሁለት ሲኖዶስ፣ ሁለት ፓትሪያርክ በአንድ ሀገር ፈጥረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመጣበት ይሆናል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የአናሳ ብሔር ቋንቋዎች ውስጥ፣ የሩሲያን ቋንቋ ሰረዘች። በዩክሬን፣ የሩሲያ ቋንቋ ሁለተኛ ትልቁ ቋንቋ ሲሆን፣ ከሕዝቡ ከ30-35% ለቀን ተቀን ሕይወቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የሩሲያ ቋንቋ ከትምህርት ቤቶች፣ ከሚዲያዎች፣ ከሃይማኖታዊ ሥፍራዎች፣ ከሕዝባዊ መገልገያዎች እና ከኦፊሴላዊ ቦታዎች ሕገ- ወጥ ተብሎ ጥቅም ላይ ከመዋል መታገዱ ይታወሳል። *-*-*- ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያላት ጥላቻ ሥር የሰደደ እና እጅግ የከፋ ነው። አስደንጋጭ ነው በጣም፣ ለሚያውቀው። ሕዝቡ አይደለም በነገራችን ላይ፣ መንግሥቱ ነው። ሕዝቡ በእምነቱ ከሩሲያ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ 92% የኦርቶዶክስ እምነትን ይከተላል። ለረጅም ጊዜ፣ ቤተክርስቲያኒቱ በሩሲያ ሲኖዶስ ሥር ነበረች። ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው የተሳሰረ ነው፣ ችግር የለባቸውም በዚያ። አሁን ግን የዩክሬን መንግሥት ሕዝቡ ሩሲያን እንዲጠየፍ እና እንዲጠላ 24 ሰዓት ይሰራሉ፣ በሁሉም ረገድ። ወጣቱን ዛሬም፣ የሩሲያን ሙዚቃ ያዳምጣል፣ የሩሲያን ሶሻል ሚዲያ ይከተላል፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ እንደ ሩሲያዊያን ለመሆን ይጥራል፣ እያሉ ይከሱታል። የሩሲያን ቋንቋ ማውራትን እንደ መሰልጠን አድርጎ ሕዝቡ ይወስደዋል፣ በተለይ ወጣቱ፣ በሚል መንግሥቱ በየቀኑ ያንን እንዲተው ፕሮፓጋንዳዎች ይለቃሉ። ከ2019 በኋላ፣ ዩክሬንን ከሩሲያ ተጽእኖ ለመገንጠል ባለመ መልኩ የዩክሬን ቤተክርስቲያን ለሁለት ተሰንጥቋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመጣበት ይሆናል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የአናሳ ብሔር ቋንቋዎች ውስጥ፣ የሩሲያን ቋንቋ ሰረዘች። በዩክሬን፣ የሩሲያ ቋንቋ ሁለተኛ ትልቁ ቋንቋ ሲሆን፣ ከሕዝቡ ከ30-35% ለቀን ተቀን ሕይወቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የሩሲያ ቋንቋ ከትምህርት ቤቶች፣ ከሚዲያዎች፣ ከሃይማኖታዊ ሥፍራዎች፣ ከሕዝባዊ መገልገያዎች እና ከኦፊሴላዊ ቦታዎች ሕገ- ወጥ ተብሎ ጥቅም ላይ ከመዋል መታገዱ ይታወሳል። *-*-*- ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያላት ጥላቻ ሥር የሰደደ እና እጅግ የከፋ ነው። አስደንጋጭ ነው በጣም፣ ለሚያውቀው። ሕዝቡ አይደለም በነገራችን ላይ፣ መንግሥቱ ነው። ሕዝቡ በእምነቱ ከሩሲያ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ 92% የኦርቶዶክስ እምነትን ይከተላል። ለረጅም ጊዜ፣ ቤተክርስቲያኒቱ በሩሲያ ሲኖዶስ ሥር ነበረች። ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው የተሳሰረ ነው፣ ችግር የለባቸውም በዚያ። ከ2019 በኋላ ግን የዩክሬን ቤተክርስቲያን ለሁለት ተሰንጥቋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመጣበት ይሆናል።

🇮🇷🇺🇸 የሚገርማችሁ፣ ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኢራን ፓርላማ መሰብሰቡን አቁሟል። በነገሮች ላይ፣ በድጋፍ ወይም በተቃውሞ ለመወሰን፣ የሚችልበት ዕድል አላገኘም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብቻ፣ ከተወሰኑ አማካሪዎቹ ጋር፣ በጉዳዮች ላይ በመወያየት እየወሰኑ ናቸው። በብዙ የድርድሩ ነጥቦች ላይ ይላሉ ተንታኞች፣ ፖርላማው ቢኖር ኖሮ፣ ይቃወመው ወይም ክርር ያለ አቋም ይይዝባቸው ነበር። ፖርላማው በወግ አጥባቂዎች የተሞላ እንደመሆኑ፣ 'ድርድር' ስለሚባለው ነገር፣ ብዙ ጥርጣሬና ጥያቄ ያነሳ እንደነበር የቀጠናው ተንታኞች ያምናሉ። ሁሉም ግን፣ ለዘብተኞችም ሆኑ ወግ አጥባቂዎች፣ ተስፋቸውን የጣሉት በበላዩ አያቶላህ ላይ ነው። ምንም ይፈጠር ምንም፣ እሱ ካልፈረመበት የሚያልፍ አይኖርም። የእሱ ውሳኔ ደግሞ ለሁሉም የተሻለው ነው ይላሉ።

🇵🇰🇮🇷🇺🇸 ሸባዝ ሸሪፍ፣ የፖኪስታኑ ዋና አደራዳሪ፣ ነገሮች እያለቁ ነው፣ እንረጋጋ፣ መግባቢያዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል፣ ሥራዎች ይቀራሉ። ሚዲያውም ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት ይቆጠብ።
🇵🇰🇮🇷🇺🇸 ሸባዝ ሸሪፍ፣ የፖኪስታኑ ዋና አደራዳሪ፣ ነገሮች እያለቁ ነው፣ እንረጋጋ፣ መግባቢያዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል፣ ሥራዎች ይቀራሉ። ሚዲያውም ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት ይቆጠብ።

🇮🇷🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰይድ አባስ አራግቺን ፖስትን በገፁ አጋርቷል። … እባካችሁ ሚዲያዎች ተረጋጉ፣ ያልተጻፈ ያልተደረሰበትን ስምምነት አትለፍፉ። ጊዜው
🇮🇷🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰይድ አባስ አራግቺን ፖስትን በገፁ አጋርቷል።
… እባካችሁ ሚዲያዎች ተረጋጉ፣ ያልተጻፈ ያልተደረሰበትን ስምምነት አትለፍፉ። ጊዜው ሲደርስ እራሳችን ለሕዝብ የምናሳውቅ ይሆናል።

🇷🇺🇺🇦⚡️ - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡ ሩሲያ ጥንት ጀምሮም ጠላት የበዛባት ናት፣ ናፖሊዮን፣ ሂትለር እና አሁን ሙሉ አውሮፓ፣ በጠላትነት እየወጉን ነው።

🇷🇺❌🇺🇦🪖 - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
ኔቶ የተባለን ማህበራዊ ጥምረት ስብስብን በመቃወም፣ ሩሲያ ብቻዋን ቆማለች። ሁሉም ሀገሮች ጥረታቸውን በእኛ ላይ እያጠናከሩ ነው። ለሩሲያ ጠላት በመሆን የሚችሉትን ድርጊቶችን ሁሉ እያደራጁ ናቸው። አዳዲስ ማህበርተኞችን እየሰበሰቡ ነው። ሩሲያ በምትሸነፍበት ጊዜ "የቂጣውን ቁራጭ" ለማግኘት በመቋመጥም፣ ከ 2022 በኋላ፣ በርካታ ሀገራት ኔቶን ተቀላቅለዋል።


🇷🇺🇺🇦⚡️ - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
ለተቃዋሚዎቻችን አንድ ምክር ብቻ መስጠት እፈልጋለሁ፡ ሩሲያን አትዋጉ! ተው ብለናል! በሰላም እንኑር እና ሁሉንም ጉዳዮች በድርድር እንፍታ። ነገር ግን፣ እነዚህ ድርድሮች፣ መነጋገሮች እንጂ ማስጠንቀቂያዎች መሆን የለባቸውም።

🇷🇺🇺🇦⚡️ - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡
ጠላት፣ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን አጠቃቀም እያሰፋ መሆኑን እያየን ነው። መሠረተ ልማቶቻችንን እያጠቁ ናቸው። የጠላት ተግባር በሩሲያ ማህበረሰብ ውስጥ መከፋፈልን፣ ግራ መጋባትን መዝራት እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን ማድረስ ነው፣ ግን ምንም አይሰራም። የድሮን ጥቃቶች በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው፣ አዎ! ነገር ግን ሁሉም ነገር በፍጥነት እያገገመ ነው። የሀገሪቱን የአየር መከላከያ ሥርዓት ማጠናከር አለብን እና ይህን እያደረግን ነው።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷 - የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ሚሳኤል ጥቃትን ተከትሎ የእስራኤልን ምላሽ እንዲገድብ ጫና እንዳደረገበት ተናግሯል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ትራምፕ 'ከህዝብህ አንዱን ገድለዋል?' ብሎ ጠይቋል። ኔታንያሁም፣ እስራኤል ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ ብቻ ምላሽ የምትሰጥበትን ሁኔታ ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተናግሯል፣ በእስራኤል ግዛት ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት የበቀል እርምጃ እንደሚያስከትልም ለፕሬዝዳንቱ በአጽንኦት ተናግሯል። ኔታንያሁ ለሚኒስትሮች ንግግር ሲያደርግ፣ እስራኤል በዋሽንግተን ላይ ጥገኛ መሆኗን የሚገልጹትን አስተያየቶች ውድቅ በማድረግ 'እኛ ለአሜሪካውያን የበታች አይደለንም። እኛ አጋሮቻቸው ነን" ብሏል። - Yedioth Ahronoth

🇪🇹🇫🇷 ኢትዮጵያ፣ የእርስ በርስ ጦርነት የዘገቡትን እና ኢትዮጵያ ለሱዳን ጃንጃዊድ (RSF) አማፂ የሥልጠና ቦታ መስጠቷን ለዓለም ያጋለጡትን ፈረንሳዊያን ጋዜጠኞችን፣ ከሀገሯ አባረረች። RSF አማፂ ቡድን፣ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ጀኖሳይድ የሚፈፅም አንጃ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከኤሜሬት ንጉሥ ጋር በመጣመር አሶሳ አቅራቢያ ለዚህ ቡድን፣ የማሰልጠኛ እና የሎጀስቲክ ማዕከል እንዳስገነባ እና ይህንንም እነዚህ ጋዜጠኞች ደርሰውበት ለዓለም እንደዘገቡት ታውቋል። ይህ የኢትዮጵያ ቅሌት፣ ለዓለም ከተጋለጠ በኋላ፣ አብዛኛዎቹ የምዕራብ ሀገር መሪዎች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንዲከልሱ ተገደዋል። *-*-*-*- ይሄን ይሄን ስትሰሙ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች 'ጋዜጠኛ' ናቸው ትላላችሁ? ሕዝብ ቢፈጅ፣ ሽብርተኞች ካምፕ ገንብተው ቢንቀሳቀሱ፣ ሕዝብ በረሃብ ቢሞት፣ ሀገር ብትነድ … የውጭ ጋዜጠኛ እንጂ ዘግቦ ለዓለም በማጋለጥ ሕዝብ የሚታደገው፣ የኢትዮጵያ "ጋዜጠኞች" አይደሉም። የኢትዮጵያ 'ጋዜጠኞች'፣ ስትነዱ እና ስትታረዱ ቢያዩ፣ ዘፈን ነው የሚለቁባችሁ።

አንዳንድ ጊዜ ሳስበው፣ ህዳሴ ግድብ ከምንገነባ ይልቅ ምናለ ገንዘቡን ኒውክሌር በገዛንበት እላለሁ። አንድ ቦንብ፣ ኒውክሊየር ቢኖረን እኮ በአንድ ሌሊት Super Power ተብለን ነበር። መቼስ፣ ውሃ ማቆር ከኒውክሊየር ቦንብ ይበልጣል ብሎ የሚከራከር ጤነኛ ሰው አለ ብዬ አላስብም። ህዳሴ ምን ጠቀመ ሕዝቡን? ሀገሩንስ? ምናልባት ጤነኛ አስተዳደር ቢኖር ይጠቅም ነበር ሊባል ይችላል። ግን የፈለገ ቢሆን፣ የኒውክሊየር ባለቤት እንደመሆን አይጠቅምም። አሁን ኢራን ውስጥ ውስጡን እያሰበች ያለችው በተወሰነ የገባኝ ስለመሰለኝ ነው። እንደ ምንም ብዬ፣ ከፓኪስታን ወይም ከሰሜን ኮሪያ አንድ ቦንብ ገዝቼ … አለቀ! ከዛ ማንም ሰላቶ አረብ ተነስቶ የባስማቲ ሩዝ አፉን አይከፍትብኝም፣ ነው። በነገራችን ላይ ይሄ ፍራቻ የዛሬ አይደለም፣ ድሮ በፊት ጀምሮ ያለ የምዕራባዊያን ስጋት ነው። ሩሲያ ብትሸጥስ? ሰሜን ኮሪያ ብትሸጥስ? ፓኪስታን፣ ሕንድ ቢሸጡስ …? የሆነ ታጣቂ ቡድን አንድ ሁለቱን ቢሰርቀውስ?

🇺🇸🇮🇷 አሜሪካ እና ኢራን የመጨረሻውን መፅደቅ በመጠባበቅ ላይ ባለው ረቂቅ ስምምነት ጽሑፍ ላይ ተስማምተዋል፣ ሲል አክሲዮስ ዘግቧል። ስምምነቱ የሚከተሉትን ያጠቃልላል ። · በሊባኖስ ጨምሮ፣ በሁሉም ግንባሮች፣ ተኩስ አቁሙን ለ60 ቀናት ማራዘም። በዚህ ጊዜ ድርድሩን ማድረግ። • የሆርሙዝ ወሽመጥን ያለ ክፍያ ወዲያውኑ መክፈት እና መደበኛ የመርከብ መጠኖችን ወደ ነበረበት መመለስ። · በኢራን ላይ የአሜሪካ ማዕቀብ ይላላ ዘንድ፣ እነዚህ ነጥቦች መጀመሪያ ተፈፃሚነታቸውን ማረጋገጥ። • የኢራን የበለፀገ ዩራኒየም ጉዳይ መፍትሄ እንዲበጅለት፣ ማዕቀፍ ማዘጋጀት። • ከኳታር ጋር በሚደረግ ቅንጅት፣ ኢራን ለሰብዓዊ ግዢዎች አንዳንድ የተያዘባት ንብረት መልቀቅ።

🇮🇷⚡️ኢራን አላት ተብሎ የሚገመተው የተብላላ ዩራኒየም 4 ኩንታል ነው። ይሄን 4 ኩንታል ነው፣ እነ አሜሪካ አሳልፈሽ ካልሰጠሽ የሚሉት። አራት ኩንታል ሲባል ትንሽ እንዳይመስለን፣ አንዷ ብናኝ ሀገር ታጠፋለች።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ኢራን፣ የተብላላው ዩራኒየሟን፣ ከ60 በመቶ የጥራት ደረጃ፣ ወደ 23 በመቶ በሀገሯ ውስጥ እንድታቀጥነው ትራምፕ የተስማማ መሆኑ ተገለጸ። ከዚህ በፊት አሜሪካ የኢራን ዩራኒየም መቅጠን ካለበት ከኢራን ውጭ ሊሆን ይገባል የሚል አቋም ነበራት AXIOS *-*-*- ዩራኒየም 70 በመቶ የጥራት ደረጃ ላይ ተብላልቶ መድረስ ከቻለ፣ የኒውክሊየር ቦንብ ሊያስገነባ ያስችላል። ኢራን ከ60-63 በመቶ የጥራት ደረጃ ላይ እንዳደረሰችው ይገመታል። ትንሽ ነው የቀራት። አሁን አቅጥኚው ተብላ አብሲት ልትጥል ነው።

🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ አመሻሽ ላይ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ከኢራን ጋር ወደ ድርድር ለመግባት ስለተደረሰው የመግባቢያ
🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ አመሻሽ ላይ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ከኢራን ጋር ወደ ድርድር ለመግባት ስለተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ተነጋግረዋል። ምንም እንኳን፣ እስራኤል የመግባቢያ ስምምነቱ አካል ባትሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድርድሩ ማጠቃለያ ላይ የመጨረሻው ስምምነት ሊሆን ይገባዋል ያሉትን ምክረ ሐሳብ ለፕሬዝዳንቱ ለግሰዋል። የበለፀገውን ዩሬኒየም ማስወገድ፣ የማበልፀጊያ መሠረተ ልማቶችን ማፍረስ፣ የሚሳኤል ምርትን መገደብ እና ኢራን በክልሉ ለሚገኙ የአሸባሪ ወኪሎቿ የምታደርገውን ድጋፍ ማቆምን ያካትታል ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ላደረጉት ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ት
+2
🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ትሪሊዮን ዶላር በንኖ ጠፋ (ኪሳራ)። አረንጓዴው ሰንጠረዥ፣ የከሰዓት በኋላው ግብይት ነው። ትራምፕ ወጥቶ፣ ከኢራን ጋር ያለው ጉዳይ በመስተካከል ላይ ነው አለ፣ ያንን ተከትሎ ገበያው ደስ አለው። በዚያም ከጧት የነበረውን ኪሳራ አካክሶ $1.7 ትሪሊየን ዶላሩን አፈሰው። $600 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ወደ ኪስ፣ አይ አሜሪካ አለ ሰውዬው። ታዲያ አሜሪካ ብትደነቅ ያንስባታል ትላላችሁ?

🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ት
+1
🇺🇸 ቀዩ ሰንጠረዥ ዛሬ ጠዋት የነበረውን የአሜሪካ የገበያ ግብይት ያሳያል፣ ገበያው ቀዝቀዝ ያለ ስለነበር (ሌሊቱን በነበረው የኢራን ጦርነትና በተፈጠረው ያለመረጋጋት ሁኔታ)፣ ከገበያው $1.1 ትሪሊዮን ዶላር በንኖ ጠፋ (ኪሳራ)። አረንጓዴው ሰንጠረዥ፣ የከሰዓት በኋላው ግብይት ነው። ትራምፕ ወጥቶ፣ ከኢራን ጋር ያለው ጉዳይ በመስተካከል ላይ ነው አለ፣ ያንን ተከትሎ ገበያው ደስ አለው። በዚያም ከጧት የነበረውን ኪሳራ አካክሶ $1.7 ትሪሊየን ዶላሩን አፈሰው። $600 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ወደ ኪስ፣ አይ አሜሪካ አለ ሰውዬው። ታዲያ አሜሪካ ብትደነቅ ያንስባታል ትላላችሁ?