ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 307
المشتركون
-124 ساعات
-217 أيام
-8630 أيام
أرشيف المشاركات
የሊባኖስ መንግሥት ጦር ሽሽት፣ የአሁኑን ጊዜ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊትን አቋም ያስታውሳል። እነሱስ እሺ፣ በዓለም ስመ ጥር ጦር ሰራዊት ከሆኑት መካከል አንዱ ከሆነው ከእስራኤል ጦር ነው የሚሸሹት። ወቅታዊው የኢትዮጵያ ጦር ግን ከደቡብ ሱዳን አማፂያንም ይሮጣል። ለዚያም ነው፣ ሙሉ ዞን የሚያህል ስፋት ያለው መሬት፣ 'ደቡብ ምዕራብ ክልል' ከሚባለው የኢትዮጵያ ግዛት የተቀደደ ሱሪና ሁለት ዓይነት የተቦረተፈ ጫማ ያደረጉ አማፂያን የኢትዮጵያን ሰራዊት እስከዛሬ የያዙት።

🇮🇱⚡️🇱🇧 እስራኤል ትናንት ምሽት በደቡብ ሊባኖስ ወታደራዊ የእግረኛ ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ፣ የሊባኖስ መንግሥት ጦር ደቡብ ሊባኖስን በመልቀቅ ላይ ነው። ኢራን፣ ሊባኖስ የስምምነቱ አካል መሆን እንዳለባት በተደጋጋሚ ስትገልፅ ቆይታለች።

🇵🇰🇮🇷🇺🇸 የፖኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ዋና አደራዳሪ፣ ሻባዝ ሸሪፍ፣ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ፣ ስንለፋበት የቆየነው መቋጫውን ያገኛል ብለን እናስባለን እና እንረጋጋ እያለ ነው።
🇵🇰🇮🇷🇺🇸 የፖኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ዋና አደራዳሪ፣ ሻባዝ ሸሪፍ፣ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ፣ ስንለፋበት የቆየነው መቋጫውን ያገኛል ብለን እናስባለን እና እንረጋጋ እያለ ነው። ፖኪስታን የፊርማውን ሥነ ስርዓት በዲጂታል እንደምታሳልጥም ተናግሯል። በአካል ተገኝቶ የሚፈረም ነገር አይኖርም። ከዚያም የ60ው ቀን ድርድር በይፋ ይጀመራል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰይድ አባስ አራግቺ፣  በኢራን መገናኛ ብዙሃን በLive ቃለ-መጠይቅ በማድረግ ላይ ነው። የኢራን ሕዝብ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ለተከታታይ ቀናቶች፣ አሁን መቶኛ ቀኑን ተሻግሯል፣ በአደባባይ ጦሩን በመደገፍ መሰለፉን ቀጥሏል። እንደሚሰማው ከሆነ፣ ሚንስትሩ፣ ሊፈረም ጫፍ የደረሰው ስምምነት ለኢራን ትልቅ ድል እንደሆነ በመናገር ላይ ይገኛል። አሁን ላይ በስምምነቱ ውስጥ ስላሉ ነጠቦች ብዙ ብዥታዎች እና ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ያሉ መሆኑና የትኛውም ሀገር ግልፅ ለማድረግ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ እየታየ ነው። ጋዜጠኛው፣ አስር ግዜ አራግቺ የስምምነቱን ዝርዝሮች እንዲናገር ቢገፋፋውም፣ ሚንስትሩ ለመናገር ፍቃደኛ እንዳልሆነ ይሰማል።

🇮🇷🇺🇸 The New York Times አሁን እንደዘገበው፡ የኢራኑ የበላይ መሪ፣ አያቶላህ ሙጅተባ ኸመነይ፣ የስምምነቱን ረቂቅ ከከፍተኛ አማካሪዎቻቸው ጋር እያጤኑት ይገኛል፣ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

🇺🇸 ኢላን መስክን እንኳን ደስ ያለህ እንበለው ሄደን፣ የዓለም የመጀመሪያው ትሪሊየነር ሆኗል። የዓለም የመጀመሪያው ቢሊየነር አሜሪካዊው ራከፊለር በ1916 ነበር -- The New York Times
🇺🇸 ኢላን መስክን እንኳን ደስ ያለህ እንበለው ሄደን፣ የዓለም የመጀመሪያው ትሪሊየነር ሆኗል። የዓለም የመጀመሪያው ቢሊየነር አሜሪካዊው ራከፊለር በ1916 ነበር -- The New York Times

🇪🇹 በአርሲ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በመንግሥት የሚደገፉ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች የተጨፈጨፉት የንፁሃን ሲቪሊያኖች ፎቶ፣ በሶሻል ሚዲያዎች እየወጣ ነው። ከዚህም በተጨማሪ፣ የመንግሥት አካላት የሆኑ ባለስ
+3
🇪🇹 በአርሲ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በመንግሥት የሚደገፉ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች የተጨፈጨፉት የንፁሃን ሲቪሊያኖች ፎቶ፣ በሶሻል ሚዲያዎች እየወጣ ነው። ከዚህም በተጨማሪ፣ የመንግሥት አካላት የሆኑ ባለስልጣኖች፣ ለእነዚህ ታጣቂዎች ሕዝቡን ሳይመርጡ በጅምላ እንዲገድሉ ትዕዛዝ ሲሰጡ የሚያሰማ የድምፅ ቅጂም በሚዲያዎች ሲዘዋወር ታይቷል። በርካታ ሴቶችና ሕፃናት ያለቁበት ይህ ጭፍጨፋ፣ ብሔር እና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ ሲሆን፣ የዐማራ ተወላጆችን እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮችን ዒላማ ያደረገ እንደነበር የዓይን እማኞች ገልፀዋል። በኢትዮጵያ፣ በተለይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ፣ የንፁሐን ሕዝብ ጭፍጨፋ እየተበራከተ የመጣ ሲሆን፣ እንደ ቀጠናው ተንታኞች፣ እነዚህ ግድያዎች የተቀነባበሩና የገዢው መንግሥት እጅ በስፋት የሚታይባቸው ናቸው ይላሉ።

🇦🇪🇮🇷 ለኢራን ያስተላለፍኩትም፣ ለማስተላለፍ ያለምኩትም ብር የለም። ሮይተርስ ይያዝልኝ፡ ኤሜሬት።
🇦🇪🇮🇷 ለኢራን ያስተላለፍኩትም፣ ለማስተላለፍ ያለምኩትም ብር የለም። ሮይተርስ ይያዝልኝ፡ ኤሜሬት።

🇮🇷🇦🇪ሮይተር ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገው፡ ኤሜሬት ለኢራን $10 ቢሊዮን ዶላር ለመልቀቅ የተስማማች ሲሆን፣ 3 ቢሊየን ዶላሩን በአይሮፕላን ጭና ለኢራን አራግፋለች። ኤሜሬት፣ የሮይተርን ዘገባ፣
🇮🇷🇦🇪ሮይተር ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገው፡ ኤሜሬት ለኢራን $10 ቢሊዮን ዶላር ለመልቀቅ የተስማማች ሲሆን፣ 3 ቢሊየን ዶላሩን በአይሮፕላን ጭና ለኢራን አራግፋለች። ኤሜሬት፣ የሮይተርን ዘገባ፣ መሠረተ ቢስ እና ውሸት ስትል አጣጥለዋለች።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የአናሳ ብሔር ቋንቋዎች ውስጥ፣ የሩሲያን ቋንቋ ሰረዘች። በዩክሬን፣ የሩሲያ ቋንቋ ሁለተኛ ትልቁ ቋንቋ ሲሆን፣ ከሕዝቡ ከ30-35% ለቀን ተቀን ሕይወቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የሩሲያ ቋንቋ ከትምህርት ቤቶች፣ ከሚዲያዎች፣ ከሃይማኖታዊ ሥፍራዎች፣ ከሕዝባዊ መገልገያዎች እና ከኦፊሴላዊ ቦታዎች ሕገ- ወጥ ተብሎ ጥቅም ላይ ከመዋል መታገዱ ይታወሳል። *-*-*- ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያላት ጥላቻ ሥር የሰደደ እና እጅግ የከፋ ነው። አስደንጋጭ ነው በጣም፣ ለሚያውቀው። ሕዝቡ አይደለም በነገራችን ላይ፣ መንግሥቱ ነው። ሕዝቡ በእምነቱ ከሩሲያ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ 92% የኦርቶዶክስ እምነትን ይከተላል። ለረጅም ጊዜ፣ ቤተክርስቲያኒቱ በሩሲያ ሲኖዶስ ሥር ነበረች። ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው የተሳሰረ ነው፣ ችግር የለባቸውም በዚያ። አሁን ግን የዩክሬን መንግሥት ሕዝቡ ሩሲያን እንዲጠየፍ እና እንዲጠላ 24 ሰዓት ይሰራሉ፣ በሁሉም ረገድ። ወጣቱን ዛሬም፣ የሩሲያን ሙዚቃ ያዳምጣል፣ የሩሲያን ሶሻል ሚዲያ ይከተላል፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ እንደ ሩሲያዊያን ለመሆን ይጥራል፣ እያሉ ይከሱታል። የሩሲያን ቋንቋ ማውራትን እንደ መሰልጠን አድርጎ ሕዝቡ ይወስደዋል፣ በተለይ ወጣቱ፣ በሚል መንግሥቱ በየቀኑ ያንን እንዲተው ፕሮፓጋንዳዎች ይለቃል። ከ2019 በኋላ፣ ዩክሬንን ከሩሲያ ተጽእኖ ለመገንጠል ባለመ መልኩ የዩክሬን ቤተክርስቲያን ለሁለት እንዲሰነጠቅ ተደርጓል። እርስ በእርስ በቁራኛ የሚተያዩ፣ ሁለት ሲኖዶስ፣ ሁለት ፓትሪያርክ በአንድ ሀገር ፈጥረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመጣበት ይሆናል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የአናሳ ብሔር ቋንቋዎች ውስጥ፣ የሩሲያን ቋንቋ ሰረዘች። በዩክሬን፣ የሩሲያ ቋንቋ ሁለተኛ ትልቁ ቋንቋ ሲሆን፣ ከሕዝቡ ከ30-35% ለቀን ተቀን ሕይወቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የሩሲያ ቋንቋ ከትምህርት ቤቶች፣ ከሚዲያዎች፣ ከሃይማኖታዊ ሥፍራዎች፣ ከሕዝባዊ መገልገያዎች እና ከኦፊሴላዊ ቦታዎች ሕገ- ወጥ ተብሎ ጥቅም ላይ ከመዋል መታገዱ ይታወሳል። *-*-*- ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያላት ጥላቻ ሥር የሰደደ እና እጅግ የከፋ ነው። አስደንጋጭ ነው በጣም፣ ለሚያውቀው። ሕዝቡ አይደለም በነገራችን ላይ፣ መንግሥቱ ነው። ሕዝቡ በእምነቱ ከሩሲያ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ 92% የኦርቶዶክስ እምነትን ይከተላል። ለረጅም ጊዜ፣ ቤተክርስቲያኒቱ በሩሲያ ሲኖዶስ ሥር ነበረች። ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው የተሳሰረ ነው፣ ችግር የለባቸውም በዚያ። አሁን ግን የዩክሬን መንግሥት ሕዝቡ ሩሲያን እንዲጠየፍ እና እንዲጠላ 24 ሰዓት ይሰራሉ፣ በሁሉም ረገድ። ወጣቱን ዛሬም፣ የሩሲያን ሙዚቃ ያዳምጣል፣ የሩሲያን ሶሻል ሚዲያ ይከተላል፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ እንደ ሩሲያዊያን ለመሆን ይጥራል፣ እያሉ ይከሱታል። የሩሲያን ቋንቋ ማውራትን እንደ መሰልጠን አድርጎ ሕዝቡ ይወስደዋል፣ በተለይ ወጣቱ፣ በሚል መንግሥቱ በየቀኑ ያንን እንዲተው ፕሮፓጋንዳዎች ይለቃሉ። ከ2019 በኋላ፣ ዩክሬንን ከሩሲያ ተጽእኖ ለመገንጠል ባለመ መልኩ የዩክሬን ቤተክርስቲያን ለሁለት ተሰንጥቋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመጣበት ይሆናል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የአናሳ ብሔር ቋንቋዎች ውስጥ፣ የሩሲያን ቋንቋ ሰረዘች። በዩክሬን፣ የሩሲያ ቋንቋ ሁለተኛ ትልቁ ቋንቋ ሲሆን፣ ከሕዝቡ ከ30-35% ለቀን ተቀን ሕይወቱ የሚጠቀምበት ቋንቋ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ፣ የሩሲያ ቋንቋ ከትምህርት ቤቶች፣ ከሚዲያዎች፣ ከሃይማኖታዊ ሥፍራዎች፣ ከሕዝባዊ መገልገያዎች እና ከኦፊሴላዊ ቦታዎች ሕገ- ወጥ ተብሎ ጥቅም ላይ ከመዋል መታገዱ ይታወሳል። *-*-*- ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያላት ጥላቻ ሥር የሰደደ እና እጅግ የከፋ ነው። አስደንጋጭ ነው በጣም፣ ለሚያውቀው። ሕዝቡ አይደለም በነገራችን ላይ፣ መንግሥቱ ነው። ሕዝቡ በእምነቱ ከሩሲያ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ 92% የኦርቶዶክስ እምነትን ይከተላል። ለረጅም ጊዜ፣ ቤተክርስቲያኒቱ በሩሲያ ሲኖዶስ ሥር ነበረች። ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው የተሳሰረ ነው፣ ችግር የለባቸውም በዚያ። ከ2019 በኋላ ግን የዩክሬን ቤተክርስቲያን ለሁለት ተሰንጥቋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት ሌላ ጊዜ በሰፊው እንመጣበት ይሆናል።

🇮🇷🇺🇸 የሚገርማችሁ፣ ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኢራን ፓርላማ መሰብሰቡን አቁሟል። በነገሮች ላይ፣ በድጋፍ ወይም በተቃውሞ ለመወሰን፣ የሚችልበት ዕድል አላገኘም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብቻ፣ ከተወሰኑ አማካሪዎቹ ጋር፣ በጉዳዮች ላይ በመወያየት እየወሰኑ ናቸው። በብዙ የድርድሩ ነጥቦች ላይ ይላሉ ተንታኞች፣ ፖርላማው ቢኖር ኖሮ፣ ይቃወመው ወይም ክርር ያለ አቋም ይይዝባቸው ነበር። ፖርላማው በወግ አጥባቂዎች የተሞላ እንደመሆኑ፣ 'ድርድር' ስለሚባለው ነገር፣ ብዙ ጥርጣሬና ጥያቄ ያነሳ እንደነበር የቀጠናው ተንታኞች ያምናሉ። ሁሉም ግን፣ ለዘብተኞችም ሆኑ ወግ አጥባቂዎች፣ ተስፋቸውን የጣሉት በበላዩ አያቶላህ ላይ ነው። ምንም ይፈጠር ምንም፣ እሱ ካልፈረመበት የሚያልፍ አይኖርም። የእሱ ውሳኔ ደግሞ ለሁሉም የተሻለው ነው ይላሉ።

🇵🇰🇮🇷🇺🇸 ሸባዝ ሸሪፍ፣ የፖኪስታኑ ዋና አደራዳሪ፣ ነገሮች እያለቁ ነው፣ እንረጋጋ፣ መግባቢያዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል፣ ሥራዎች ይቀራሉ። ሚዲያውም ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት ይቆጠብ።
🇵🇰🇮🇷🇺🇸 ሸባዝ ሸሪፍ፣ የፖኪስታኑ ዋና አደራዳሪ፣ ነገሮች እያለቁ ነው፣ እንረጋጋ፣ መግባቢያዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል፣ ሥራዎች ይቀራሉ። ሚዲያውም ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት ይቆጠብ።

🇮🇷🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰይድ አባስ አራግቺን ፖስትን በገፁ አጋርቷል። … እባካችሁ ሚዲያዎች ተረጋጉ፣ ያልተጻፈ ያልተደረሰበትን ስምምነት አትለፍፉ። ጊዜው
🇮🇷🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰይድ አባስ አራግቺን ፖስትን በገፁ አጋርቷል።
… እባካችሁ ሚዲያዎች ተረጋጉ፣ ያልተጻፈ ያልተደረሰበትን ስምምነት አትለፍፉ። ጊዜው ሲደርስ እራሳችን ለሕዝብ የምናሳውቅ ይሆናል።

🇷🇺🇺🇦⚡️ - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡ ሩሲያ ጥንት ጀምሮም ጠላት የበዛባት ናት፣ ናፖሊዮን፣ ሂትለር እና አሁን ሙሉ አውሮፓ፣ በጠላትነት እየወጉን ነው።

🇷🇺❌🇺🇦🪖 - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
ኔቶ የተባለን ማህበራዊ ጥምረት ስብስብን በመቃወም፣ ሩሲያ ብቻዋን ቆማለች። ሁሉም ሀገሮች ጥረታቸውን በእኛ ላይ እያጠናከሩ ነው። ለሩሲያ ጠላት በመሆን የሚችሉትን ድርጊቶችን ሁሉ እያደራጁ ናቸው። አዳዲስ ማህበርተኞችን እየሰበሰቡ ነው። ሩሲያ በምትሸነፍበት ጊዜ "የቂጣውን ቁራጭ" ለማግኘት በመቋመጥም፣ ከ 2022 በኋላ፣ በርካታ ሀገራት ኔቶን ተቀላቅለዋል።


🇷🇺🇺🇦⚡️ - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
ለተቃዋሚዎቻችን አንድ ምክር ብቻ መስጠት እፈልጋለሁ፡ ሩሲያን አትዋጉ! ተው ብለናል! በሰላም እንኑር እና ሁሉንም ጉዳዮች በድርድር እንፍታ። ነገር ግን፣ እነዚህ ድርድሮች፣ መነጋገሮች እንጂ ማስጠንቀቂያዎች መሆን የለባቸውም።

🇷🇺🇺🇦⚡️ - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡
ጠላት፣ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን አጠቃቀም እያሰፋ መሆኑን እያየን ነው። መሠረተ ልማቶቻችንን እያጠቁ ናቸው። የጠላት ተግባር በሩሲያ ማህበረሰብ ውስጥ መከፋፈልን፣ ግራ መጋባትን መዝራት እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን ማድረስ ነው፣ ግን ምንም አይሰራም። የድሮን ጥቃቶች በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው፣ አዎ! ነገር ግን ሁሉም ነገር በፍጥነት እያገገመ ነው። የሀገሪቱን የአየር መከላከያ ሥርዓት ማጠናከር አለብን እና ይህን እያደረግን ነው።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷 - የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ሚሳኤል ጥቃትን ተከትሎ የእስራኤልን ምላሽ እንዲገድብ ጫና እንዳደረገበት ተናግሯል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ትራምፕ 'ከህዝብህ አንዱን ገድለዋል?' ብሎ ጠይቋል። ኔታንያሁም፣ እስራኤል ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ ብቻ ምላሽ የምትሰጥበትን ሁኔታ ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተናግሯል፣ በእስራኤል ግዛት ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት የበቀል እርምጃ እንደሚያስከትልም ለፕሬዝዳንቱ በአጽንኦት ተናግሯል። ኔታንያሁ ለሚኒስትሮች ንግግር ሲያደርግ፣ እስራኤል በዋሽንግተን ላይ ጥገኛ መሆኗን የሚገልጹትን አስተያየቶች ውድቅ በማድረግ 'እኛ ለአሜሪካውያን የበታች አይደለንም። እኛ አጋሮቻቸው ነን" ብሏል። - Yedioth Ahronoth