የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 330
Subscribers
-624 hours
-317 days
-7230 days
Posts Archive
4 328
🇺🇦⚡️ዩክሬን የነዳጅ ማደያዎችን ከድሮኖች መጠበቅ ጀምራለች በፕሬዝዳንቱ አማካሪ ሰርሂ ፍላሽ ዘገባ መሠረት።
በእርግጥ እንደዚህ ያሉ እርምጃዎች የመሠረተ ልማት ተቋማትን ከሸሂድ ድሮኖች መጠበቅ አይችሉም፣ ነገር ግን ኦፕቲክስ ካላቸው የFPV ድሮኖች፣ በሬዲዮ ከሚቆጣጠሯቸው ሚጢጢዬ ድሮኖች እና ትናንሽ ክንፍ ካላቸው ሌሎች ዓይነት ድሮኖች በመጠበቅ ላይ ውጤታማ ይሆናሉ።
4 328
🇺🇸🇮🇷 — የአሜሪካ የባሕር ኃይል በሆርሙዝ መተላለፊያ ውስጥ ቦንቦችን የማጽዳት ተግባርን በሚስጥር ለአራት ወራት አከናውኗል።
የባሕር ኃይል ጠላቂዎች፣ የሮቦት ጀልባዎች እና የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪዎች ያሉባቸው ትናንሽ ቡድኖች፣ የኢራን የባሕር ቦንቦችን እየፈለጉ ሲያመክኑ ሰምብተዋል፣ ከዚያም በፈንጂ አውድመዋል። የኦፕሬሽኑ አብዛኛው ክፍል የተካሄደው በሌሊት ነበር።
ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፈንጂዎቹ እንደተወገዱ ቢናገሩም፣ የመርከብ ኩባንያዎች ኢራን ወሽመጡን እንደገና ፈንጂ ልትጥልበት ትችላለች የሚል ስጋት ስላላቸው ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፣ የሚሳይል እና የድሮን ስጋቶች ደግሞ ቀጥለዋል።
ኢራን በበኩሏ፣ በአሜሪካ ጥበቃ ሥር ምንም መርከብ በአካባቢው እንዳያልፍ ማገዷ፣ ከተጠበቀው በላይ ስኬት እንዳስገኘ ትናገራለች።
— ፋይናንሺያል ታይምስ |
4 328
❗️🇸🇦/🇾🇪 ሰበር፦ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የጃዛን አራምኮ የኃይል ተቋም በየመን ባሊስቲክ ሚሳይሎች እና ድሮኖች ተመቷል።
የሳተላይ ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ በሦስት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ እሳት ይታያል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ፣ በርካታ የሳውዲ ድሮኖችም በየመን ተመትተው ወድቀዋል።
4 328
🇷🇺 "የመስቀሉ ጉዞ" በመባል የሚታወቀው ሐይማኖታዊ በዓል ሰልፍ፣ ዛሬ በመቶ ሺዎች በተሳተፉበት በሞስኮ ተካሂዷል።
ዝናብ እየዘነበ ቢሆንም፣ ሕዝቡን ያስተጓጎለው አይመስልም።
በጉዟቸው፣ “እኛ ሩሲያውያን ነን — እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!” የሚል ቃል ያሰማሉ።
4 328
🇮🇷 IRGC የአሜሪካን የስለላ ፊኛ በኢርቢል ላይ አፈነዳ፦
➡️ የእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፕስ (IRGC) በኢራቅ ኩርዲስታን የአሜሪካ ወታደራዊ የስለላ ፊኛን እንዳወደመ አስታውቋል።
➡️ በኢራን መረጃ መሠረት፣ እስከ 900 ኪግ የሚደርስ የጭነት አቅም ያለው ይህ የ35 ሜትር ውስብስብ መዋቅር፣ ለአሜሪካ ኃይሎች የሬዲዮ-ኤሌክትሮኒክ ስለላ ማስኬጃ፣ የኤሌክትሮኒክ ጦርነት ማሰላጫ፣ የመረጃ ማፈኛ (Jamming) እና ደህንነቱ የተጠበቀ የግንኙነት ማስተላለፊያ በመሆን የረጅም ጊዜ የአየር ላይ command and control ሆኖ አገልግሏል።
➡️ ዋጋው እስከ አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፣ እንደ IRGC መረጃ።
4 328
🔴⚡️⚡️⚡️⚡️ ባለስልጣናት እንደተናገሩት፣ እሁድ ዕለት የአማዞን የጭነት አውሮፕላን በማያሚ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ከወደቀ በኋላ አምስት ሰዎች እንደሞቱ፣ በርካታ ሌሎች ደግሞ እንደቆሰሉ ተናግረዋል።
4 328
+1
🇺🇦🇺🇸 ዊትኮፍ እና ኩሽነር በሩሲያ ከተያዘው ክራይሚያ ባህላዊ ምግቦች አንዱን በምሳ ሰዓት ከዘለንስኪ ጋር ጋብዘናቸዋል።
ኩሽነር በተለይ ሙጥጥ አርጎ ነው የበላው፣ ጣፍጦት።
4 328
🇷🇺🇺🇦🇺🇸 በኪየቭ ያሉ አሜሪካውያን፦ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማምተዋል። እንደገና።
የትራምፕ መልዕክተኞች ወደ ኪየቭ ያደረጉት ጉብኝት፣ ምክክሮችን ለመቀጠል በስምምነት ተጠናቋል፣ ነገር ግን ለሠላም ስምምነት ምንም የተጨበጡ ውሎች አልተገለጹም።
ዊትኮፍ እና ኩሽነር ከለሌንስኪ እና ከዩክሬን የድርድር ቡድን አባላት ጋር ተገናኝተዋል። በመቀጠል፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን መሪዎች አማካሪዎች በውይይቱ እንዲቀላቀሉ ሆኗል።
ከአንድ ቀን በፊት፣ እነዚህ አሜሪካውያን ከፑቲን ጋር በሞስኮ ውይይት አድርገዋል።
*-*-**
አውሮፓዊያን በድርድሩ ጣልቃ መግባታቸውን እስካላቆሙ ወይም እንዲያቆሙ እስካልተደረጉ፣ ጦርነቱ አይቆምም!
4 328
— 🇺🇸/🇮🇷 በኢራን ጦር ሰራዊት ውስጥ ያለ አንድ ኮሎኔል፦ '
የአሜሪካ የጦር መርከብን ደረማምሼ እንዳፈነዳው፣ በቦምብ የታጨቀ ጀልባ እና የአጥፍቶ ጠፊ ቀበቶዎች እንዲሰጠኝ ስል፣ ታላቁን መሪ በትህትና እጠይቃለሁ።'
4 328
🇷🇺🇺🇦🇺🇸 በኪየቭ ያሉ አሜሪካውያን፦ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማምተዋል። እንደገና።
የትራምፕ መልዕክተኞች ወደ ኪየቭ ያደረጉት ጉብኝት፣ ምክክሮችን ለመቀጠል በስምምነት ተጠናቋል፣ ነገር ግን ለሠላም ስምምነት ምንም የተጨበጡ ውሎች አልተገለጹም።
ዊትኮፍ እና ኩሽነር ከለሌንስኪ እና ከዩክሬን የድርድር ቡድን አባላት ጋር ተገናኝተዋል። በመቀጠል፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን መሪዎች አማካሪዎች በውይይቱ እንዲቀላቀሉ ሆኗል።
ከአንድ ቀን በፊት፣ እነዚህ አሜሪካውያን ከፑቲን ጋር በሞስኮ ውይይት አድርገዋል።
*-*-**
አውሮፓዊያን በድርድሩ ጣልቃ መግባታቸውን እስካላቆሙ ወይም እንዲያቆሙ እስካልተደረጉ፣ ጦርነቱ አይቆምም!
4 328
🇷🇺🇺🇦🇺🇸 በኪየቭ ያሉ አሜሪካውያን፦ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማምተዋል። እንደገና።
የትራምፕ መልዕክተኞች ወደ ኪየቭ ያደረጉት ጉብኝት፣ ምክክሮችን ለመቀጠል በስምምነት ተጠናቋል፣ ነገር ግን ለሠላም ስምምነት ምንም የተጨበጡ ውሎች አልተገለጹም።
ዊትኮፍ እና ኩሽነር ከለሌንስኪ እና ከዩክሬን የድርድር ቡድን አባላት ጋር ተገናኝተዋል። በመቀጠል፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን መሪዎች አማካሪዎች በውይይቱ እንዲቀላቀሉ ሆኗል።
ከአንድ ቀን በፊት፣ እነዚህ አሜሪካውያን ከፑቲን ጋር በሞስኮ ውይይት አድርገዋል።
*-*-**
አውሮፓዊያን በድርድሩ ጣልቃ መግባታቸውን እስካላቆሙ ወይም እንዲያቆሙ እስካልተደረጉ፣ ጦርነቱ አይቆምም!
4 328
🇺🇦 🇷🇺 የዩክሬን ድሮን ጥቃት በሶቺ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያስከተለውን ውጤት የሚያሳዩ አዳዲስ የሳተላይት ምስሎች ታይተዋል።
የMi-28s፣ Ka-52s እና Mi-8s በሚቀመጡበት የሄሊኮፕተር ማቆሚያ ላይ የቃጠሎ ምልክቶች ይታያሉ።
ሁለት የጥቃት ሄሊኮፕተሮች ሙሉ በሙሉ የወደሙም ይመስላሉ።
ሶቺ (Sochi) በ2014 እንደፈረንጆቹ ኦሎምፒክን ያስተናገደች እና የፑቲን እረፍቱን የሚያሳልፍባት ተወዳጅ ከተማ ናት።
ከዩክሬን ድንበር 1472 KM ትርቃለች።
4 328
+2
🇺🇸 ትራምፕ ዛሬ ደብሮታል ትንሽ፣ እስኪ በኋላ ሄጄ አብሬው ቲቪ አያለሁ።
ምን ይዤ ልሂድ ነው ችግሩ፣ ብርቱካን ይዤ ልሂድ? በለጬ ይዤ ልሂድ?
4 328
🇮🇷 በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኘውን የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፕስ የባሕር ኃይል የመሬት ውስጥ ቤዝ አንድ ክፍልን የሚያሳይ ቪዲዮ፣ የኢራን ጦር ለቋል።
*-*-*-*
ሰዎቹ ላለፉት 40 ዓመታት ሲዘጋጁ ነው የኖሩት። በባቦሰጡኝ የሚዋጉት ጦርነት አይደለም።
ኢራን፣ እንደ ኢትዮጵያ፣ በአብዛኛው ተራራማ ሀገር ናት። በዚህም፣ ሙሉ ሀገሩን በሚባል ደረጃ የሚያካልልና እንደ መቀነት የሚጠመጥም የዋሻ ኔትወርኮችን በከፍተኛ ደረጃ ገንብታ አለች።
መሳሪያዋም፣ ጦሯም የተቀመጡት በእንዲህ ያሉ ዋሻዎች ነው። ወጥተው ጥቃት አድርሰው የሚመለሱትም ወደነዚሁ ነው። እንዲሁ በዘልማድ የአይሮፕላን ቦንቦች እና የመርከብ ሚሳዬሎች የሚሰበሩም አይደሉም።
በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ አሜሪካ በዓለም ከባድ በተባለለት ቦንቦች በተደጋጋሚ የደበደበችው መሰል ዋሻ፣ ምንም እንዳልሆነ እና እንዳልተሰበረ ታይቷል።
ተራራን ብትደበድበው ምን ይሆናል?
4 328
🇺🇸🇷🇺🇺🇦 በአሁኑ ሰዓት 🇫🇷ከፈረንሳይ፣ 🇬🇧ከታላቋ ብሪታንያ እና 🇩🇪ከጀርመን የመጡ ተወካዮች በኪየቭ ውስጥ ናቸው።
ዩክሬን ከእነሱ ጋር የተለየ የድርድር ክፍለ ጊዜ ይኖራታል።
**
አሜሪካን እግር በእግር እየተከታተሉ ጦርነቱን ለማቆም የምታደርገውን ጥረት የሚያደናቅፉት አውሮፓዊያን ናቸው። እነዚህ ሦስት ሀገሮች።
ሩሲያ ተሸንፋ ግዛቶቿን እስኪቀራመቱ ድረስ፣ ጦርነቱን የማቆም ምንም ሓሳብ የላቸውም። በዚህ ምክኒያት ነው፣ ጣልቃ እየገቡ ስላስቸገሩ ነው፣ አሜሪካ በተደጋጋሚ ከአውሮፓ ጋር በኢኮኖሚውም በፖለቲካውም እየተጋጨች ያለችው። ለዚህም ነው ትራምፕ በተደጋጋሚ ከኔቶ እንወጣለን የሚለው።
አውሮፓዊያን በሩሲያ ላይ ደም አሽትተዋል፣ ክፍተት አይተዋል። ድክመትን በፑቲን ላይ አስተውለዋል። በዚሁ መንገድ ሌላ አምስት ዓመት ብንገፋ፣ ሩሲያ እጃችን ትገባለች የሚል ጠንካራ እምነት አላቸው።
ዘለንስኪ በራሱ ውሳኔ ብቻ ቢመራ ኖሮ፣ ጦርነቱን በድርድር ድሮ አቁሞት ነበር፣ ነገር ግን ከአሜሪካ እና ከሩሲያ ጋር ከተነጋገረ በኋላ አውሮፓዊያን ጋር ሲሄድ፣ "በአማካሪነት" ስም ሁሉንም ስምምነቶቹን እና እሺታዎቹን እምቢ እንዲል ያደርጉታል።
አሁንም እነዚህ ሦስት ሀገሮች በኪየቭ የተገኙት ለዚህ ነው፣ የአሜሪካን መንገድ ላይ እንቅፋት ለመጣል ነው።
4 328
🇺🇦🇺🇸🇷🇺⚡️ — የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ፦
ቡድኖቻችንን እና የአሜሪካን ልዑካን ማመስገን እፈልጋለሁ። ለሁሉም ቡድኑ አመሰግናለሁ። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንትን ማመስገን እፈልጋለሁ። አስቀድመን ሁለት የውይይት ፓናሎችን አድርገናል፣ ትንሽ ቆይተን ወደ ፕረሱ እንወጣለን እና ከሁሉም አካላት ጋር እንነጋገራለን። እዚህ ያለነው ሁላችንም ፍላጎታችን አንድ ነው፣ በአንድ ወገን ነን እና ሁላችንም በእውነት ጦርነት እንዳይኖር፣ መከራ እንዳይኖር፣ ሰዎች እንዳይሞቱ፣ ይህ ጦርነት ለሁላችንም በፍትሃዊ መንገድ እና በፍትሃዊ ሰላም እንዲያበቃ እንፈልጋለን።
4 328
+1
🇺🇸🇺🇦 🇺🇦🇺🇸 በፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እና በአሜሪካ ልዩ መልዕክተኞች፣ ዊትኮፍ እና ኩሽነር፣ መካከል ከተደረጉት ውይይቶች የመጀመሪያ ፎቶዎች።
*-*-*-
ዛሬ እንኳ እዚህ አልገባሁም።
4 328
🇺🇦🇺🇸🇷🇺⚡️ — የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ፦
አየር ማረፊያዎቻችን ዝግጁ ቢሆኑም፣ ሩሲያውያን የአሜሪካ ልዑካን በአውሮፕላን እንዲመጡ አልፈቀዱላቸውም።*-***- ዘለንስኪ ሲያካብድ እንጂ ወደ ዩክሬን በአውሮፕላን መጥቶ የሚያውቅ መሪ አለ እንዴ? ፖላንድ አርፈው በባቡር ነው የሚገቡት። ያበደ መሪ ካልሆነ በስተቀር በዩክሬን ሰማይ ላይ ደፍሮ በአውሮፕላን የሚመጣ መሪ የለም። እብድ ከሆነ ሊመጣ ይችላል።
