ʜᴀʟᴀʟ™
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 ʜᴀʟᴀʟ™ 的分析概览
频道 ʜᴀʟᴀʟ™ (@halal_post) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 069 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 8 296,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 026 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 069 名订阅者。
根据 03 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -198,过去 24 小时变化为 -4,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.60%。内容发布后 24 小时内通常能获得 5.97% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 952 次浏览,首日通常累积 661 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 19。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“خُذ ماشئت ، لا تستأذن بنشر الخير🤍.
Cross @Ifendim”
凭借高频更新(最新数据采集于 04 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
11 069
订阅者
-424 小时
-537 天
-19830 天
帖子存档
11 069
Repost from N/a
📣 እንዴዴዴዴ ኧረ ፍጠኑ ጥያቄ እና መልስ ጀምረናል ⌛
❓ጥያቄ❓1,ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እናታቸው ሲሞቱ የስንት አመት ልጅ ነበሩ❓ Free promoter😏 @Smile_waverbot
11 069
ኢብኑል ቀይም 🤎 እንዲህ ይላሉ:
"ነፍስህ ልክ እንደ ጠላትህ ናት፤ ቁርጠኛ መሆንህን ካወቀች ትታዘዝልሃለች። ከአንተ በኩል ድክመትን ካየች ግን ምርኮኛ ታደርግሃለች።"— [በዳኢ አል-ፈዋኢድ፣ ቅጽ 3፣ ገጽ 1202]
11 069
Dear የባድ ወልድስ & ሸምሱአያመተሽሪቅ ዛሬ ያልቃል እና ነገ ሱቅ እንምትከፍቱ ተስፋ አደርጋለው እኛ ተማሪዎች ሞትንባቹኮ😭 pls ነገ በጠዋት ክፈቱ እሺ🥹
11 069
የጉልበተኛውና የብልሁ ሰው እውነተኛ ታሪክ!" 😂 #የተቀነጨበ
በእውነት አስቂኝና አስተማሪ የሆነ እውነተኛ ታሪክ ነውና ተጋበዙልኝ፦
□ አንድ የየመን ተወላጅ ሳዑዲ ዓረቢያ ሄዶ በስደት እየለፋ ቆንጆ ገንዘብ ያከማቻል። ወደ ሀገሩ ተመልሶም ሰንዓ (የየመን ዋና ከተማ) ውስጥ አንድ መሬት ገዝቶ ያጥርና እንደገና ወደ ስደት ይመለሳል።
ከዓመታት በኋላ ከስደት ሲመለስ፣ አንድ ትልቅ ባለጉልበት ቀማኛ መሬቱን በሃይል ነጥቆ ህንጻ እየገነባበት እንደሆነ ያያል። የአካባቢው ሰዎች "ይህ ሰው በጣም ጉልበተኛ ነው አትችለውም፤ ይልቅ ነገሩን ለአላህ ተወው ይሉታል። ምስኪኑ ሰውዬም ራሱን ነቅንቆ ነገሩን ወደ ፈጣሪ ያስጠጋና የመሬቱን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ይዞ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ስደት ይጓዛል።
ቀማኛው ሰውዬ ህንጻውን ባለ ሁለት ፎቅ ሰርቶ አጠናቆና አሳምሮ ለኪራይ እስኪያወጣው ድረስ ባለመሬቱ ከስደት አይመለስም። እርግጥ ነው፣ ይህ ጉልበተኛ መሬቱን በሃይል ቀማ እንጂ እውነተኛው ባለቤት ማን እንደሆነ አያውቅም ነበር።
ባለመሬቱ በረሃብ እንደተጠቃ ሰው መስሎ ወደ ቀማኛው ዘንድ ይሄድና ህንጻውን ሙሉ የዓመት ኪራይ በ"ካሽ" ከፍሎ ይከራየዋል።
ከዚያ በኋላ የሆነውን ስሙ! ይህ ብልህ ሰው የህንጻውን ቁልፍ በእጁ ካስገባ በኋላ፣ የድሮውን የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶቹን ይዞ ይነሳና... ከቀማኛው ሰውዬ የሚበልጥ ወደሚገዝፍ ሌላ "ትልቅ ባለጉልበት" ዘንድ ይሄዳል። መሬቱንና በላዩ ላይ የተሰራውን ፎቅ በሙሉ ድፍን አድርጎ ይሸጥለታል! ሙሉ ገንዘቡን በ"ካሽ" ተቀብሎ፣ ሻንጣውን ጠቅልሎ በሰላም ወደ ስደት ይመለሳል።😅
ያለ ምንም ጠብና ጩኸት፣ መሬቱንም ሸጦ በላዩ ላይ የተሰራውን ፎቅ ጭምር ደርቦ በላበት! በእውነት ወንድም ዓለም... ሰውዬው መብቱን "በደብል" አስከብሮ ተገላገለ! 😅
አያስቅም ግን ለሞራሌ ሳቁ😭
11 069
ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል።
ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል።
በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት።
ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው...
我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急匆匆地冲进家门时,果然不出所料,她正一边被浓烟包围着剧烈咳嗽,一边在翻看我的手机。最终,我把她和手机一起救了出来。
አቻ ትርጉም ከትንሽ ቅመም ጋር
"ስልኬንና ሚስቴን ብቻቸውን እቤት ውስጥ መተው ፈጽሞ አልችልም! 'የተላላኩትን መልዕክት እያነበበች ይሆን?' የሚለው ስጋት እረፍት ነሳኝ። ዘልዬ እቤት ውስጥ ስገባ ልክ እንደፈራሁት፤ በጭስ ተከባ የቀሚሷ ጫፍ በእሳት እየተቀጣጠለና እያሳለች ስልኬን ስትፈትሽ አገኘኋት! በጨዋነት ስልኬን ተቀብየ ልወጣ ስሞክር 'ዢዋን ማናት? ለምንስ የልብ ኢሞጂ ላክህላት?' እያለች በዚያ ጭስ ውስጥ መጨቃጨቅ ጀመረች። ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ ከነስልኩ አንጠልጥዬ ይዣት ወጣሁ።"
ክፉ ጊዜ ላይ ነን እ? 😁
11 069
"መቼ ይሁን እኛም እንደ ሌሎች ሰዎች የልጃችንን እጇን ይዘን ጁምዓ የምንሄደዉ "
አለኝ አንዱ መንገደኛ እየሄድን🥲
ለማንኛውም ሰለዋት አብዙ ጁምዓ ነው
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد
11 069
ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ይላሉ
አንድ በእድሜ ገፋ ያለች እናት
ዙህር ሳይደርስ ከደቂቃዎች በፊት
ውዱእ ስታደርግ አየኋትና አዛን አለ እንዴ? አልኳት‥
እኔ አላህ ሳይጠራኝ ነው ወደ አላህ
የምሄደው ብላ መለሰችልኝ ።
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
