ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 326
订阅者
+224 小时
+87 天
+9730 天
帖子存档
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ በ2017 ዓ.ም የሚካሄደውን 4ኛ ዙር የክህሎት ውድድርን አስመልክቶ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የተለያዩ ኢንደስትሪዎችና ተቋማት ለተወጣጡ ውድድሩን በዳኝነት ለሚመሩ ዳኞች የኦረንቴሽን መድረክ አዘጋጀ፡፡ በዚህም ግልጽ የዳኝነት አሰራር ማስረጽና ቅሬታዎችን መቀነስ ብሎም እንዳይኖሩ መስራት የውድድሩ ዋንኛ ተግባርና ኃላፊነት በመሆኑ የዳኞች መመልመያ ተግባርና ኃላፊነት መመሪያ ለክህሎት ውድድሩ በማዘጋጀት በውድድሩ ሂደት ቅሬታዎች እንዳይፈጠሩ በመስራት ለተወዳዳሪዎች የዳኝነት አሰጣጥ ላይ የሚከናወኑ ሂደቶችን በማሳወቅና ግንዛቤ በመፍጠር በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚመራ የዳኝነት ክትትልና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት መረጃዎችን በተደራጀ ሁኔታ ለውሳኔ አሰጣጥ በሚያመች ሁኔታ ከማወዳደሪያ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በየደረጃው ለሚገኙ አካላት ውጤቱን በማደራጀት ማስረከብ እንዲሁም በዳኝነት ስራቸው ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች ከአስፈላጊው መረጃ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ ለቅሬታ ኮሚቴ ምላሽ መስጠት በሚያስችላቸው አግባብነት ላይ ተገቢ የሆነ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ውድድሩ ከፊታችን መጋቢት 16/2017 ዓ.ም ጀምሮ የኮሌጆች ሰልጣኝ ተማሪዎችን በማሳተፍ በክላስተር ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን በተለይም መሰል ውድድሮችን ማካሄድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ በውድድር ከማሸነፍ በላይ የክህሎት እና እውቀት ሽግግሩ ወሳኝ መሆኑን የቢሮው ም/ኃላፊና የኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ለድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በየሳምንቱ ሀሙስ ቀን በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተከታታይ እያካሄደ የሚገኘውን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በማጠናከር በድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚገኙ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘርፉን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል:: በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተማሪዎች ስለ ቴክኒክና ሙያ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ ከማደረግ አኳያና እንደ ሀገር ከተያዘው የትኩረት አቅጣጫም አንፃር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለወጣቱ በተለይም ከዚህ በኃላ ወደ ዘርፉ ለሚቀላቀሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብዙ መልካም እድሎችን የያዘ ዘርፍ መሆኑን በማስገንዘብ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ተችሏል:: የግንዛቤ ማስጨበጫውን ለተማሪዎች የሰጡት የኮሌጁ ዲኖች እንዲሁም አሰልጣኝ መምህራን ሲሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ከወዲሁ በአስተሳሰብም ሆነ ለዘርፉ ባላቸው አረዳድ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን ምክረ ሀሳብና በኮሌጁ ያለውን ምቹ አጋጣሚ ለተማሪዎች በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን የህይወት ልምዳቸውንም አካፍለዋል:: በቀጣይም ተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳቸውን የቴክኒክና ሙያ (STEM) ክበብ በየትምህርት ቤቶቹ በመቋቋም ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ይህም የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ቀደም ብለው ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና በሲስተም ውስጥ እንዲያልፉ እድል እንደሚፈጥርላቸውም ተገልፇል:: በተጨማሪም በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሴት ተማሪዎች ቁጥር አብላጫውን እንደሚይዝና ነገር ግን የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ውስን በመሆኑ ሴቶች በዘርፉ በስፋት እንዲሳተፉ ማበረታታትና መደገፍም እንደሚገባ ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 12/2017 ዓ.ም

#ዜና| የአሰልጣኞችን የክህሎት ክፍተት በየጊዜው መሙላት ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ከመስጠት በዘለለ ለሚሰሩት ቴክኖሎጂዎች ጥራትና ያላቸውና ውጤታማ የሆነ የፈጠራ ስራ እንዲኖራቸው ያስችላል ተባ
+5
#ዜና| የአሰልጣኞችን የክህሎት ክፍተት በየጊዜው መሙላት ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ከመስጠት በዘለለ ለሚሰሩት ቴክኖሎጂዎች ጥራትና ያላቸውና ውጤታማ የሆነ የፈጠራ ስራ እንዲኖራቸው ያስችላል ተባለ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ የትምህርት ክፍል ለተውጣጡ መምህራን በAutocad እና በsolid work ላይ ትኩረቱን ያደረገ ለ15 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ፡፡ ስልጠናው በዋናነት በተለየው የክህሎት ክፍተት መሰረት የአሰልጣኝ መምህራኑን የዲዛይን ክህሎት ለማዳበር የታለመ እንደሆነ የገለጹት የኮሌጁ ም/ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽግግር ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ አያይዘውም በየጊዜው ለአሰልጣኝ መምህሩ የሚደረጉ ስልጠናዎች በትምህርትና ስልጠናው ላይ ብቻ ሳይሆን በሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች ላይ ለውጥ እያሳየ እንዳለ ገልጸዋል፡፡ም/ዲኗ በመቀጠልም በዚህ ስልጠና በተገኘው ግብአት መሰረት በቀጣይ በእጅ ከሚሰራው የዲዛይን ስራ ወደ ኮምፒዩተራይዝድ የዲዛይን ስራ ለማሳደግ እንዲሁም ኮሌጁ በቀጣይ የቴክኖሎጂ ማእከል እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ ምርቶችን እያመረተ ለማህበረሰቡ ብሎም ለኢንዱስትሪዎች የሚያቀርብ ስለሆነ የሚሰሩት ስራዎች በሙሉ በኮምፒውተር በተደገፈ አይነት መልኩ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ለተከታታይ 15 ቀኛት የተሰጠው ይህ ስልጠና በAutocad 2D ፣3D Drawing እንዲሁም በsolid work ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲሰጥ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መጋቢት 13/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና| በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለምረጥ የታለመ የክህሎት ውድድር ማከናወን ጀመረ፡፡ በዘንድሮ በጀት ዓመት ለ4
+8
#ዜና| በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለምረጥ የታለመ የክህሎት ውድድር ማከናወን ጀመረ፡፡ በዘንድሮ በጀት ዓመት ለ4ኛ ጊዜ ‹‹ ብሩህ አዕምሮዎች ፣በክህሎት የበቁ እጆች!››በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ያለመ ከኮሌጅ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ የሚሄድ የተለያዩ የምዘና ስራዎች በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተሰሩ ሲሆን በዚህም በICT ፣በTextile and Garment በElectrical Electronics፣በ Automotive ፣በManufacturing ፣በHotel Truism ትምህርት ክፍሎች ለበርካታ ሰልጣኝ ተማሪዎች ምዘናዎች ተደርገዋል፡፡ ይህ የክህሎት ውድድር ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ወደ ተግባር በመለወጥ ሂደት የበቁ ዜጎችን ለመፍጠር የሚያስችልና የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ መሬት አውርደው ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ውድድር እንደሆነ በውድድሩ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በትናንትናው እለት የተጀመረው ይህ ውድድር በኮሌጅ ደረጃ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ በክላስተር ደረጃ የተለያዩ ውድድሮች የሚደረጉ ይሆናል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከ3 ሚሊየን በላይ የስራ ዕድሎችን መፈጠራቸውን ገለጹ አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 8 ወራት ከ3 ሚሊየን በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከ3 ሚሊየን በላይ የስራ ዕድሎችን መፈጠራቸውን ገለጹ አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 8 ወራት ከ3 ሚሊየን በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠር መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ባለፉት 8 ወራት በተመዘገበ መረጃ በሀገር ውስጥ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከ300 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸው፤ ከ45 ሺህ በላይ ዜጎች በሪሞት ጆብ ወይም በዲጂታል መንገድ ስራ ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ የግብርናው ዘርፍ 40 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 20 በመቶ፣ ሰርቪስ 38 በመቶ የስራ ዕድሎች የተገኙባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከሴክተሮች በተጨማሪ በኮሪደር ስራዎች እና ልዩ ልዩ ኢኒሼቲቮች በርካታ የስራ ዕድሎችን ፈጥረናል ብለዋል፡፡ ካለው አምራች ሀይል አንፃር አሁን ያለው የስራ ዕድል በቂ አለመሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቀጣይም ያለውን የስራ ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ዜጎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡ FBC

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? ***** የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል . በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው? . የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ፤ በትግራይ ዳግም ጦርነት እንዳይነሳስ ምን እየተሠራ ነው? . የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል? . በሰላም እጦት ሳቢያ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እንግልት ከመሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው? . በአምራች ዘርፉ ያለውን የጥሬ ዕቃ እና የሌሎች የአቅርቦት ችግሮ ለመፍታት መንግሥት ምን እየሠራ ይገኛል? . የ10 ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ማሳካት መቻላችንን የሚያመላክቱ መስፈሪያዎች ምንድን ናቸው? ፤ ሴክተሮችስ ከዚህ ዕቅድ ጋር ምን ያህል ተናበው እየሰሩ ነው? . መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ምን አይነት ጠንካራ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው? . በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በኑሮ ውድነት እየተቸገሩ ባሉበት ሁኔታ እንዴት የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ሊባል ይችላል? . የቁጥጥር ተቋማት ነጻ ሆነው በትክክል ኃላፊታቸውን እንዲወጡ ምን አይነት ሥራዎች እየተሰሩ ነው? . የባሕር በር ለማግኘት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነቶች በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? . ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ያላቸውን የቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ለማጣጣም ምን እየተሰራ ነው? . የኮሪደር ልማትን ተከትሎ የሚነሱ የአፈጻጸም ችግሮችን እና ቅሬታዎችን ለመፍታት እየተወሰዱ ያሉ ርምጃዎች ምን ይመስላሉ? . የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ላይ መዘግየት እንዳይፈጠር ምን እየተሰራ ነው? . የመሬት አቀማመጣቸው ወጣ ገባ በሆኑ እና ለሜካናይዜሽን በማይመቹ አካባቢዎች ምርታማነት ለማሳደግ ምን እየተሠራ ነው? . እስካሁን የተፈጠረው የሥራ ዕድል ካለው ፍላጎት ጋር ምን ያክል የተመጣጠነ ነው?

የትኩረት አቅጣጫ በሆኑ የሙያ ዘርፎች ላይ የሴት ሰልጣኞችን ተሳፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት ሴቶችን ተፈላጊ በሆኑ የሙያ ዘርፎች ለማሳተፍ በሚደረግ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ ከዲፓርትመቶች ከተወጣጡ ሴት ሰልጣኝ ተማሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ:: መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ የሴቶችና ህፃናት ክፍል ተጠሪ ወ/ሮ ራሄል እሸቱ ሲሆኑ በንግግራቸውም ሴት ሰልጣኞች በአብዛኛው Soft Skill የሚባሉ ሙያዎች ላይ ጥገኛ እንደሚሆኑ አስታውሰው በዛው መጠንም ተምረው ሲጨርሱ ስራ የማግኘት እድላቸው በጣም አናሳ እንደሆነ ይስተዋላል ያሉ ሲሆን ሴቶች ኢንዱስትሪው በሚፈልገውና ብዙ እድሎች ያሉባቸው ዘርፎች ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባልም ብለዋል:: በፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መድረኩ ላይ ለሰልጣኞች ግንዛቤ የሰጡት የEASE ፕሮጀክት የሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን አስተባባሪ ኢንጂነር ህይወት እሸቱ ሲሆኑ በመልእክታቸውም ሴቶች የኢንጂነሪንግ ዘርፎች ላይ ደፈር ብለው ተሳታፊ ቢሆኑ ተጠቃሚ የሚያደርጏቸው ብዙ እድሎች እንዳሉ አስታውሰው ይህ በኮሌጁ የሚዘጋጀው ጥናትም የችግሩን መንስኤ ከስር መሰረቱ በመለይትና ለሴቶች እስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ወቅቱ በሚጠይቀው የሙያ ዘርፍ ላይ በሚፈለገው ደረጃ እንዲሳተፉ ለማድረግ እንደሆነም ገልፀዋል:: በመድረኩ ሴት ሰልጣኞቹን በቡድን ተክፍለው የሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ እንዲወያዩ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም ሴቶች Hard Skill የሚባሉ የሙያ ዘርፎችን ደፍረው እንዳይቀላቅሉ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን መንስኤዎች በዝርዝር አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል:: በቀጣይም ከመድረኩ በተገኙ ግብዓቶች እንዲሁም ተጨማሪ በሚደረጉ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቶች መሰረት የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ወደ ትግበራ እንደሚገባም ተገልፇል:: በEASE ፕሮጀክት በአለም ባንክ በሚደርግ ድጋፍ ለቀጣይ 5አመት በሚቆየው ፕሮጀክት ውስጥ የትኩረት ዘርፍ ተብለው በተመረጡ 3 የሙያ መስኮች (Manufacturing, Electrical/Electronics, Automotive) ላይ በትኩረት የሚሰራ ሲሆን ሴቶች በነዚህ ዘርፎች ላይ ተሳትፎ ቢያደርጉ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸውም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ አመራር ኮሚቴ በዛሬው እለት በካሄደው ስብ ሰባ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሃሳብ ያስተላለፈ ሲሆን በተለይም በቀጣይ እንደ ቢሮ በትኩረት የሚፈጸሙ አቅጣጫዎችን ከዚህ እንደሚከተለው አስቀምጧል፡- 1.  መለየት፡- የአካባቢን ጸጋ በአግባቡ መለየት፤ የሥራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞችን መለየት፤ ከልምድ የተገኘ ክህሎት ያላቸውን መለየት፤ በኢ መደበኛ የተቀመጡ ኢንተርፕራይዞችን መለየት፤ 2.  ማዘጋጀት፤- አመራሩ በሚናው ዙሪያ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ፤ አቅም የሚፈጥሩ ኢንዱስትሪዎችን ለይቶ ማዘጋጀት፤ ሥራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞች በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ማዘጋጀት፤ 3.  መደገፍ፡- ተቋማትን መለየት ማዘጋጀትና መደገፍ፤ ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን መስራት፤ 4.  ማሸጋገር፡- ከሥራ አጥነት ወደ ተወዳዳሪ ዜጋ ማሸጋገር፤ የተመዘገቡ ሥራ አጦችን ከLMIS ላይ በተጨባጭ መውሰድና ማሸጋገር፤ ኢንተርፕራይዞችን ማሸጋገር፤ ከኢ መደበኛ ወደ መደበኛ ማሸጋገር፤ ኢ መደበኛ አንቀሳቃሾችን በአንድ ቦታ በማደራጀት ማሸጋገር፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

"ብሩህ አዕምሮዎች፣በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መካሄድ ጀመረ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዘንድሮ አመት የሚካሄደው 4ኛው የክህሎት ውድድር ጋር ተያይዞ በተቋም ደረጃ የሚደረገውን ውድድር በዛሬው እለት አስጀምሯል:: በተቋም ደረጃ በዛሬው እለት በተካሄደው ውድድር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አሰልጣኝ መምህራን እና ሰልጣኝ ተማሪዎችን ያሳተፈ ውድድር ሲሆን በመጀመርያው ቀን የውድድሩ ውሎም.... በAuto mechanics በAutomotive body repair & painting wor በBuilding Electrical Installation በIndustrial Electrical/Electronic control technology በFinishing Construction work በPlumping installation በStructural construction work በWood work technology.... የሙያ ዘርፎች ውድድሮች ተካሂደዋል:: ይህ በተቋም ደረጃ የተጀመረው ውድድር በቀጣይ ቀናትም በቀሩት የሙያ መስኮች የክህሎት ውድድሩ የሚደረግም ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

ኮሌጁን ዘመናዊና ለስራ ምቹ እንዲሆን የኮንስትራክሽን ትምህርት ክፍል እንደሚሰራ ገለጸ፡፡ የትምህርት ክፍሉ ተጠሪ አሰልጣኝ መምህር ተሾመ ሸለመ በዛሬው እለት እንደገለጹት ኮሌጁ ለስራ ምቹ እንዲሆንና
+4
ኮሌጁን ዘመናዊና ለስራ ምቹ እንዲሆን የኮንስትራክሽን ትምህርት ክፍል እንደሚሰራ ገለጸ፡፡ የትምህርት ክፍሉ ተጠሪ አሰልጣኝ መምህር ተሾመ ሸለመ በዛሬው እለት እንደገለጹት ኮሌጁ ለስራ ምቹ እንዲሆንና ዘመናዊ ይዘት እንዲኖረው ትምህርት ክፍሉ እየሰራ እንዳለ የገለጹ ሲሆን ያይዘውም ለኮሌጁ የተለያዩ ገቢ ማስገኛ ስራዎችን ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት በዘለለ ምርቶችን ለማምረትና ለኮሌጁ ማህበረሰብ ብሎም ለአካባቢው ማህበረሰብ ለማቅረብ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ ይህንንም ምርት ለማምረት የቦታ መረጣ፣ለማሽነሪዎች ምቹ ቦታ በመምረጥ የማስቀመጥ ስራዎች እንዲሁም ለምርት የሚያገለግሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች ጥገና ስራ አከናውነናል ብለዋል፡፡ ለዚህ ስራ ደግሞ መሳካት ሁሉም የትምህርት ክፍል አባላቶች በስራው ላይ አመርቂ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መጋቢት 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ