1 326
订阅者
+224 小时
+87 天
+9730 天
帖子存档
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ከመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ የተወጣጣ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሌጅ የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ አካሄደ::
ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታም አጠቃላይ የኮሌጁን እንቅስቃሴ እና ያለበትን ደረጃ በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፊ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን እንዲሁም በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በትብብር ሊሰሩ በሚችሉበት አግባብ ላይ የሁለትዮሽ ውይይት ተካሂዷል::
በነበረው የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ ልዑካን ቡድኑ ከተደረገላቸው ገለፃ በተጨማሪ በቀጣይ በምን ዘርፍ በትብብር ለመስራት ያስችላል ሚለውን ለመለየት ኮሌጁ ያለውን ፋሲሊቲ እና ማሰልጠኛ ወርክሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ኮሌጁ በዚህ መልኩ ራሱን በማራጀራጀቱም አድናቆታቸውን ለግሰዋል::
በቀጣይም ልዑካን ቡድኑ በኮሌጁ ባገኙት የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ መሰረት ሁለቱ ተቋማት በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ወደ ተግባር እንደሚገቡም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
#ዜና| በድሬዳዋ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በምግብ ዋስትና መርሀግብር በማቀፍ ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ የሚሸጋገሩበትን እድል ለመፍጠር አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ከንቲባ ከድር ጁሀር ገለጹ።
#Diretv አማርኛ መጋቢት 6/2017
የሁለተኛው ዙር የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ተጠቃሚ የምረቃ ሥነስርዓት ተካሂዷል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት (upsnjp)
ተጠቃሚ ቤተሰቦች የምረቃ እና የርክክብ ፕሮግራም ተካሂዷል ።
የከተሞች ምግብ ዋስትና ፕሮግራም በኢትዮጵያ መንግስት በሚመደብ በጀትና እና ከአለም ባንክ በተገኘ የብድር ገንዘብ በሁለተኛው ምዕራፍ በሀገሪቱ በሚገኙ በተመረጡ 88 ከተሞች እና ክልሎች ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ከተማችን ድሬደዋ አንዷ ተጠቃሚ ናት።
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተጠቃሚ ከሆኑ በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች መካከል አንዱ ሲሆን በፕሮግራሙ የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ምዕራፍ ብዙ ሺ ዜጎች ከድህነት እና ስራ አጥነት እንዲላቀቁ ምቹ እድል ተፈጥሮላቸዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት ሲያስፈፅም የቆየዉ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት የስራ ፕሮጀክት በሁለተኛ ምእራፍ አንደኛ ዙር ተጠቃሚ ቤተሰቦች ከ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው የደሃ ደሃ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በስድስት የከተማ ወረዳዎች ማለትም በ04፣ 05፣ 06፣ 07፣ 08 እና 09 በድምሩ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አራት (1724) ቤተሰቦችን በአካባቢ ልማት ንኡስ ፕሮግራሞች በመታቀፍ ለሶስት አመታት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲደረግ ቆይቷል።
የፕሮግራሙ ተጠቃሚ የነበሩና የዛሬ ተመራቂዎችም ከዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ከሶስት አመት ቆይታ በኋላ ወደ መደበኛ ስራ እድል ፈጠራ የተሸጋገሩ ሲሆን ካሉበት የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻሉ ከማገዝ ባለፈ የከተማዋን ማጽዳትና ዉበት በማሻሻል ÷ የከተማ ግብርና እንዲጠናከር እንዲሁም የተለያዩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ይበልጥ እንዲስፋፋ የበኩላቸዉን ድርሻ የተወጡ መሆናቸዉን ከመድረኩ ተገልጿል ።
በመድረኩ ተገኝተዉ ለተመራቂዎች መልዕክታቸዉን ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የዜጎች የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል በማድረግ የበለፀገች እና ለሁሉም የምትመች ሀገርን ዕዉን ለማድረግ መንግስታቸዉ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዉ በድሬዳዋ አስተዳደርም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም በማቀፍ ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ የሚሸጋገሩበትን እድል ለመፍጠር አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አንስተዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጅነር ጀማል ኢብራሂም በበኩላቸዉ በፕሮጀክቱ ሶስት አመታት በ21 የስልጠና ርእስ የተከፋፈለ የገንዘብ አጠቃቀምና አያያዝ፣የህይወት ክህሎት፣ የንግድ ስራ አመራር፣ የንግድ ሥራ ዕቅድ የክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠና እና ተከታታይነት ያለዉ የድጋፍና ምክር አግኝተዋል ብለዋል ።
ወ/ሮ ብርቱካን አስራትና ወ/ሮ ጡርዬ በየነ የ08 እና 04 ወረዳ ነዋሪዎች ናቸው፤ በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተጠቃሚ በመሆናቸው ከተረጂነት እራሳቸዉን ችለዉ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲገኙ እንዳስቻላቸዉ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በቀጣይ በሚኖራቸው የቦታ፣የገንዘብ ይሁን የስራ ምችችት ማንኛውም ነገር በተመለከተ በስራና ክህሎት ቢሮ በኩል እንዲሆን የሰነድ ፊርማ ተፈራርመዋል ።
©️ ድሬ ቲቪ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ዜና | በሀገራችን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳድር መካኒክ አሽከርካሪዎችን በማፈራት የትራፊክ አደጋን መቀነስ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ አሽከርካሪዎችን ማፍረት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መካኒክ አሽከርካሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ፡፡
የትራፊክ አደጋ አምራች ኃይሉ ላይ ጉዳት የሚያደርስና ማህበረሰቡንም የሚጎዳ አስከፊ አደጋ ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ የትራፊክ አደጋ በመንገድ ብልሽት፣በተሸከርካሪ ብልሽት፣ በእግረኛ የመንገድ አጠቃቀም ስህተት እንዲሁም በአሽከርካሪዎች ቸልተኝነት የሚደርስ ነው ስለዚህ ይህን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ደግሞ ኮሌጁ አሽከርካሪዎችን በመካኒክነት ሙያ እንዲሁም በስነ ባህሪ በማብቃት አደጋውን መቀነስ በሚቻልበት ዙሪያ ስልጠናዎችን እየሰጠ ክፍተቶችን እየሞላ ይገኛል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ለከተማችን ብሎም ለሃገራችን ብቁና ተወዳዳሪ አሽከርካሪዎችን ለማፍራት ቀጣይነት ባለው መልኩ በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናዎችን በመስጠት አሽከርካሪዎችን የማብቃት ስራ ኮሌጁ በሰፊው የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡በመጨረሻም እንኳን ለምርቃት ቀናችሁ አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
በምርቃቱ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ አሰልጣኝ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታሪኩ ለገሰ እንዳሉት ይህ ስልጠና ብቃት ያለው መካኒክ አሽከርካሪዎችን በማፈራት የትራፊክ አደጋን መቀነስ ዋናው አላማ ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ ይህንን ስልጠና በዘመናዊ መኪኖች መስጠት እንዲቻል የአሰልጣኞችን ብቃት የማሳደግ እና የማሰልጠኛ እቃዎችን የማሟላት ስራ ከኮሌጁ ጋር በመሆን ይሰራል ብለዋል፡፡
መካኒክ አሽከርካሪዎች ስልጠና ይህ የሁለተኛ ዙር ሲሆን በዚህም ስልጠና ከ47 በላይ አሽከርካሪዎች የተሳተፉበት እንደሆነና ሶስተኛ ዙር ስልጠናም በቀጣይ እንደሚጀመር በእለቱ ተገልጿል ፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 6/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ወጣቶችን በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ የሚፈጠሩ በርካታ እድሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ የወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሚና የላቀ መሆኑ ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ የወላጅ ኮሚቴዎች እንዲሁም በየወረዳው ለተመረጡ የመንደር ኮሚቴዎች በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ::
የግንዛቤ መስጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ስተላፉት በመልዕክታቸው በተለምዶ ያደጉ እያልን የምጠራቸው ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት እድገት መነሻ የሆናቸው በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ያሳደሩት እምነትና ዘርፉ ላይ በሰሩት ጠንካራ ስራ መሆኑን ጠቅሰው ወጣቱን በዚህ ረገድ ግንዛቤው ተፈጥሮለት የክህሎት ስልጠናዎች ላይ እንዲሰማራ እንዲሁም እንዱስትሪውን እንዲያንቀሳቅስ የማድረጉ ተግባርና ሀላፊነት ከወላጆች ጀምሮ የሁላችንም ድርሻ ነውም ብለዋል::
ወጣቶች አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማስቻል እና እየተፈጠሩ ያሉ እጅግ በርካታ እድሎችን ተጠቃሚ ለመሆን የመጀመርያ መግቢያ በሩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እንደሆነ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ አክለውም ወጣቶች ወደ ዘርፉን በሚፈለገው መጠን እንዳይቀላቀሉ ቴክንክና ሙያ ላይ በተለምዶ ያልተገባ ስም ተልጥፏል ያሉ ሲሆን እንደ ኮሌጅ ይህንን አመለካከት ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ገልፀው ወላጆችን ጨምሮ ህብረተሰቡ ውስጥ ተሰሚነት ያላችሁ ሰዎች በተገኘው አጋጣሚ ለወጣቶች ግንዛቤ የመፍጠሩን ስራ ላይ መረባረብ ያስፈልጋልም ብለዋል::
በመድረኩ የተሻሻለውን የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ ሰነድ ለተሳታፊዎች ያቀረቡት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ ባቀረቡት ሰነድም የቴክኒክና ሙያ እስፈላጊነት ጨምሮ ነባሩ ፖሊሲ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንዲሁም የፖሊሲውን መሻሻል አስፈላጊነትን በዝርዝር ለመድረኩ ተሳቲፊዎች አቅርበዋል::
የEASE ፕሮጀክት ከአለም ባንክ ጋር የ5 አመት ፕሮጀክት እንዳለው የገለፁት ደግሞ የEASE ፕሮጀክት ዋና ኮርድኔተር ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ አያይዘውም ኮሌጁ መሰል ፕሮጀክቶችን በማፈላለግ አስፈላጊ የሚባለውን ሁሉ የሚያሟላው በከተማችን ያሉ ወጣቶችን አሰልጥኖ ከስራ ጋር ለማስተሳሰር እንደሆነም ጠቅሰው ወጣቶችን ወደዚህ እንዲመጡ ማበረታታት ያስፈልጋልም ብለዋል::
በመጨረሻም ከመድረኩ የተነሱ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ በቅንጅት በሚሰሩ ተግባራት ላይ ከመግባባት በመድረስ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 5/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
#ዜና| ኮሌጁን ዘመናዊና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ ለማድረግ በተለያዩ ሁነቶች የተገኙ ልምዶችን ለኮሌጁ ማህበረሰብ በማካፈል ምርጥ ተሞክሮ ያለው ተቋም እንዲሆን እየተሰራ እንዳለ ተገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንትና የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ከኢትዮጵያ አቬይሽን አካዳሚ የተቋም አሰራር ስርአት ያገኙትን መልካም ተሞክሮ ለተቋሙ ትምህርት ክፍልና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ተጠሪዎች አካፈሉ፡፡
ኮሌጃችን ብዙ ለሌሎች እንደ ተሞክሮ የምንሰጣቸው መልካም ጎኖች አሉን ነገር ግን ወጥነት ያለው አተገባበር ባለመኖሩ የተለያዩ ክፍተቶች ይስተዋላሉ ያሉት የኮሌጁ ም/ዲንና የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ ም/ዲኗ አያይዘውም በዛሬው እለት የምናደርገው ይህ የልምድ ልውውጥ በተለያዩ ተቋማት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመውሰድ እንዲሁም ለተቋማችን እንዲሆን በማድረግ ልንተገብራቸው ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ኮሌጃችንን ዘመናዊና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ ተቋም እንዲሆን ሁሉም አካላት በርብርብ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት ልምዳቸውን ያካፈሉት የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላትና የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ከዚህ ቀደም ለ5 ቀናት በኢትዮጵያ አቬይሽን አካዳሚ የTvT leadership and management system ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መውሰዳቸው የሚታወስ ነው፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ኮሌጁ በ2017 ዓ.ም "ብሩህ አዕምሮዎች ፣በክህሎት የበቁ ዜጎች!" በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አጠናቆ ከመጋቢት 9 2017 ዓ.ም ጀምሮ ውድድሩ እንደሚካሄድ የገለፁት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ከመለየት አንስቶ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በሟሟላት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውንም ገልፀዋል::
በዘንድሮ ውድድር ኮሌጁን እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩን በሀገር አቀፍ ውድድር ላይ የሚወክሉ አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እንዲሁም ኢንተርፕራይዞችን አወዳድሮ ለመለየት በኮሌጅ ደረጃ ከመጋቢት 9 ጀምሮ የሚደረግ ሲሆን ውድድሩም በ7 የሙያ ዘርፎች ተወዳዳሪዎችን እንደሚያሳትፍ ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ዜና| የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብየዳ እና የምህንድስና ብቃት ማእከል ለመሆን እየሰራ እንዳለ ተገለጸ፡፡
ከኢትዮጵያ የምህንድስና ብቃት ማእከል(CEE) የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብየዳ እና የምህንድስና ብቃት ማእከል የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡
ከፍተኛ ባለሙያዎችን የተቀበሉትና የተቋሙን እንቅስቃሴ ያስረዱት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት ኮሌጁ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የልህቀት ማእከል ለመሆን አልሞ እየሰራ ይገኛል ከነዚህም መካከል አንዱ ለምስራቁ የሃገራችን ክፍል ማገልገል የሚችል የብየዳ የልህቀት ማእከል አንዱ ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም ይህ የብየዳ ማእከል በተቋማችን መኖሩ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል ለሚኖሩ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን በሙያና በክህሎት የዳበሩ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡ኮሌጁ በአስተዳደሩ በኩልም እንደ ተርኒኪ አይነት ፕሮጀክቶችን ተረክቦ እየሰራ እንዳለ ለባለሙያዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በኮሌጃችን በተለያዩ ደረጃዎች የበቁ ከፍተኛ የብየዳ አሰልጣኞች ያሉት ኮሌጅ ነው ያሉት ደግሞ የኮሌጁ የማኑፋክቸሪንት ትምህርት ክፍል ተጠሪ አሰልጣኝ መምህር ዮሃንስ ተካ ሲሆኑ አያይዘውም ይህን በኮሌጁ ያለውን መልካም እድል በመጠቀም ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በርከት ያሉ ድጋፎችን መስጠት ችላል እንዲሁም ለባለሙያዎቻቸው ደግሞ በየጊዜው ስልጠናዎችን መስጠት ችለናል ብለዋለል፡፡
የመስክ ምልከታውን መሰረት በማድረግም የልኡካን ቡድኑ ጋር በነበረው የጋራ ውይይት ወቅት የተሳተፉ የልኡክ ቡድኑን አባላት እንዳሉት አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባልና በተለያዩ መስኮች የልህቀት መአከል ለመሆን እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታነው በቀጣይ ደግሞ የብየዳ ማእከሉ ሙሉ እውቅና አግኝቶ በኮሌጁ ውስጥ ሲቋቋም ድግሞ ተጨማሪ አቅምን ይፈጥራል ያሉ ሲሆን፡፡ ትምህርት ክፍሉም እየሰራ ያለው ስራ ለከተማው ብቻ ሳይሆን ለምስራቁ የሃገራችን ክፍል የሚተርፍ ስራ ነው ስራውም ለሌሎች ኮሌጆች እንደ አርአያ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡
የመስክ የስራ ጉብኝቱ ዋናው አላማ ኮሌጁን የምህንድስና ልህቀት ማእከል ለማድረግ ያሰበ እንደሆነ በውይይቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሰራውን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በማጠናከር በማርያም ሰፈር እና በመድሀንያለም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ ለሚገኙ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘርፉን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ::
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማደረግ አኳያና እንደ ሀገር ከተያዘው የትኩረት አቅጣጫም አንፃር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለወጣቱ በተለይም ከዚህ በኃላ ወደዘርፉ ለሚቀላቀሉ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብዙ መልካም እድሎችን የያዘ ዘርፍ መሆኑን በዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት ሰፋ ያለ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መስራት ተችሏል::
የግንዛቤ ማስጨበጫውን ለተማሪዎች የሰጡት የኮሌጁ ዲኖች እንዲሁም የዲፓርትመንት ተጠሪዎች ሲሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ከወዲሁ በአስተሳሰብም ሆነ ለዘርፉ ባላቸው አረዳድ ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን ምክረ ሀሳብና በኮሌጁ ያለውን ተሞክሮ ለተማሪዎች አካፍለዋል::
በቀጣይም የፈጠራ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳቸውን የቴክኒክና ሙያ (STEM) ክበብ በየትምህርት ቤቶቹ በመቋቋም ላይ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ይህም የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ቀደም ብለው ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና በሲስተም ውስጥ እንዲያልፉ እድል እንደሚፈጥርላቸውም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” በሶስተኛው ዙር ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን ወደ ትግበራ ለማስገባት እንዲያስችል ለመልማይ እና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተዘጋጀ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በዚህ ዓመት ቀበሌዎች ለሚተገበረው ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” ውስጥ መሳተፍ ያለባቸውን ወጣት የሆኑ ነዋሪዎችን በመምረጥ በኩል የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባበቡ መወጣት እንደሚገባቸው ከየቀበሌው ለተመረጡ መልማይና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ገለጻ ተደርጓል፡፡
በሁለተኛው ዙር ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” ተግባራዊ ተደርጎ እንደ አስተዳደር የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል ከተጠቃሚዎች ምልመላ ጀምሮ የታዩ የአሰራር ክትተቶችን በማሻሻል ወደ ምዝገባ መገባቱ ይታወቃል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 4/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
