ch
Feedback
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

前往频道在 Telegram

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) is a national Lutheran church with more than 10 million members.

显示更多
3 519
订阅者
+424 小时
+157 天
+4430 天
帖子存档
#የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተ_ክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ_2017_ዓም #አዲሱን_ዓመት_አስመልክቶ_ከቤተ_ክርስቲያኒቱ_ፕሬዚዳንት_ለአገሪቱ_ሕዝቦችና_ምዕመናን_የተላለፈ_መልዕክት በስመ አብ፤ በስመ ወልድ፤ በስመ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ፤ አሜን! በጌታ የተወደዳችሁ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ምዕመናን በያላችሁበት ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፡፡ ፍጥረታት ይወለዳሉ፤ ያድጋሉ፤ ይሞታሉም፡፡ ዘመናትም ይመጣሉ፤ ይሄዳሉም፡፡ ሁሉ ነገር ጊዜውን ጠብቆ ይለወጣል፡፡ 2016 ዓመተ ምህረትም ተጠናቅቆ 2017 ዓመተ ምህረትን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሁሉን አሳልፎ የሚኖረውና የሁሉ ፈጣሪ የሆነው ቅዱስ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ እርሱን ሊለውጠው የሚችል አንዳችም ኃይል የለም፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች የሆኑት ፍጥረታት ሲለወጡ እርሱ ግን ምን ጊዜም የማይለወጥ ዘላለማዊ አምላክ መሆኑን ሲገልጽ በመዝሙር 102፡12 ላይ ‹‹አንተ ግን ለዘላለም ትኖራለህ፤ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው›› ይላል፡፡ ቀጥሎም በቁጥር 27 ላይ ‹‹አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል›› በማለት እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ የሚኖር ዘለዓለማዊ አምላክና ብቸኛ ፈጣሪ መሆኑን ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስም ‹‹አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው (ሰቆ. 5፡19) ይላል፡፡ እንግዲህ ባለፈው 2016 ዓመተ ምህረት የነበሩና አሁን ግን ከዘመኑ ጋር ያለፉ በርካታ ነገሮች ቢኖሩም እኛ ግን እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ አገር 2017 ዓመተ ምህረትን ለመቀበል እየተዘጋጀን የምንገኘው ከቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ጥበቃና ቸርነት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም እስከ ዛሬ ድረስ በነገር ሁሉ የረዳንና የጠበቀንን አምላካችን እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ በማለት በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና በራሴ ስም መልካም ምኞቴን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ ባለፉት ዓመታት በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በነበረው የዝናብ እጦት ምክንያት ከደረሰው ድርቅ የተነሳ በርካታ ዜጎቻችን በምግብና በውኃ እጥረት መጎዳታቸውን እናስታውሳለን፡፡ በዚያን አስቸጋሪ ጊዜ ከዳር እስከ ዳር ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ያቀረበው ጸሎት ተሰምቶ አካባቢው ዝናብ በማግኘቱ ሕዝቡ በደስታ ኑሮውን ቀጥሎአል፡፡ ለዚህም በዚህ አጋጣሚ እግዚአብሔርን ላመሰግን እውዳለሁ፡፡ በሌላ በኩል ግን የዓለማችን የሰላም እጦት አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአገራችንም ከተለመደው የሰላም እጦት በተጨማሪ የኢኮኖሚ ጫናና ሙሰኝነት በዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሯል፡፡ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ከተፈጠረው የመሬት ናዳ (Land Slide) የተነሳም ብዙ ዜጎቻችን ለድንገተኛ ሞት ተዳርገዋል፡፡ በዚሁ ሰበብ በርካቶች ከቤት ንብረታቸውን ተፈናቅለው በችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ አሁንም ቢሆን ከጎረቤት አገራት ጋር የተያያዙ የአገሪቱን ሰላም የሚፈታተኑ እንቅስቃሴዎች ይታያሉ፡፡ በመሆኑ መላው የአገሪቱ ሕዝብ እግዚአብሔር እነዚህንና የመሳሰሉትን ችግሮች እንዲቆጣጠርና ለአገራችን ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲያሰፍን መጸለይ ይገባል፡፡ የተከበራችሁ ውድ የአገራችን ህዝቦችና መላው ህዝበ-ምዕመናን፤ 2016 ዓመተ ምህረት ዳግመኛ ላይመለስ ሄዷል፤ 2017 ደግሞ አዲሱ ዘመን ተብሎ ተተክቷል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ አዲሱ ዓመት ከመግባታችን በፊት ባለፈው ዓመት እንደ ግለሰብ፤ እንደ ቤተሰብ፤ እንደ ማህበረሰብ፤ እንደ የሀይማኖት ተቋማት፤ እንደ አገርና እንደ ህዝብ በአገሪቱ ስንኖርና ተግባሮቻችንን ስናከናውን ጉዞአችን እንዴት ነበር? በማለት የሄድንባቸውን መንገዶችና ያከናወንናቸውን ተግባራት መገምገም ይገባናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህም ባለፈው ዓመት የታዩብንን ደካማና ጠንካራ ጎኖቻችንን በመለየት ድክመቶቻችንን አስተካክለን ጥንካሬዎቻችንን በማጎልበትና አዳዲስ ራዕዮችን በመሰነቅ በ2017 ዓ/ም በምንሰማራባቸው ሥራዎች ሁሉ ለራሳችንም ሆነ ለዜጎቻችን ኑሮ መሻሻል በሚደረገው ጥረት የየራሳችንን ድርሻ በትጋትና በታማኝነት መወጣት እንድንችል ይረዳናል፡፡ ለዚህም ያለፈውን ዓመት ሥራችንን መገምገምና ራይዕ ሰንቀን ዕቅዶችን ማዘጋጀት ብቻ በቂ አይሆንም፡፡ ለመልካም ሥራ ሁሉ መሰረት ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ የቅዱሱ አምላካችን ቃል ‹‹ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደህና ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል›› (መዝ 111፡10) ይላል፡፡ እንግዲህ በአገራችን ብሎም በዓለማችን ሰዎች የሚጠበቅባቸውን መልካም ተግባር እንዳይፈጽሙ፤ የሰው ልጆች በሰላም አብረውና ተባብረው እንዲሁም ተፋቅረው እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ችግሮች የሚከሰቱት በዋነኛነት ሰው እግዚአብሔርን ባለመፍራቱ በባልንጀራው ላይ ከሚፈጽማቸው ክፉ ተግባራት የተነሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአገራችንም በማናቸውም ደረጃ የሚታዩት የእግዚአብሔር አምላክን ክብር እንዲሁም የሰውን ልጅ ጥቅምና ክብር የሚነኩ ተግባራት እግዚአብሔርን ካለመፍራት የተነሳ የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ማስተዋል ያመጣል፤ ለእግዚአብሔር ክብርና ለባልንጀራችን ጥቅም ከማይሆን ማንኛውም ድርጊት እንድንርቅ ያደርጋል፡፡ መዝሙረኛው ዳዊትም ‹‹ ከትዕዛዝህ የተነሳ አስተዋልኩ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ›› (119፡104) ይላል፡፡ በመሆኑም በአዲሱ ዓመት በየዕለቱ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማስተዋል የማያልፈውን ከሚያልፈው፤ የከበረውን ከተዋረደው፣ መልካሙን ከክፉ በመለየት በተጠያቂነት መንፈስና በታማኝነት ኃላፊነታችንን ለመወጣት መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር አምላካችን በ2017 ዓ/ም ለአገራችን ሕዝቦች በተለያዩ የአመራር ደረጃዎች ለሚያገለግሉ መሪዎች፣ ለኃይማኖት አባቶችና አገልጋዮች እንዲሁም ለመላው ሕዝበ-ምዕመናን እግዚአብሔርን የመፍራት ልብ ይስጥ፤ አገራችንን በሰላሙ ይጠብቅ፤ የምንሰራውን ሥራ ሁሉ ይባርክ፤ እያልኩ አዲሱን ዓመት ስናከብር በተለያዩ ምክንያት የተጎዱና የተቸገሩ፣ ድሆችና በሽተኞች፣ ወገኖቻችንን በማሰብና ካለን በማካፈል አብረናቸው እንድናሳልፍ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያን ይባርክ! እግዚአብሔር ይባርካችሁይጠብቃችሁ፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራላችሁ ጸጋውንም ይስጣችሁ! እግዚአብሔር ፊቱን ይመልስላችሁ ሰላሙንም እለት እለት ያብዛላችሁ! በስመ አብ፤ በስመ ወልድ፤ በስመ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ! አሜን! ቄስ ዶር/ዮናስ ይገዙ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት

#Qaammee_4 #Biyya_Keenyaaf #mata_duree_Kadhataa_fi_Galataa 1. Biyyi keenya biyya haraaraa fi nagaa; biyya nagfaa, kan misoomaa fi kan gammachuu akka ta’uuf; 2. Walitti bu’iinsi fi Wal dhabdeen akka dhaabbatu; Dhiiga walii dhangalaasuun, wal ajjeechaan raawwatee akka hafuuf; 3. Bulchiinsi gaariin bakka hundumaatti hojii irra akka ooluuf, seerrii fi naamuusni akka eegamuuf, malaamaltummaanii fi gochaawwan badoon haf akka hafaniif.

#ጳጉሜ_4 #ስለ_ሀገራችን #የፀሎት_እና_የምስጋና_ርዕሶች 1. አገራችን የዕርቅ እና የሠላም፤የልማት እና የደስታ ምድር እንዲሆን፤ 2. ጠብ፣ የጎሳ ግጭትና አለመግባባት ከአገራችን እንዲወገድ፤ የደም
#ጳጉሜ_4 #ስለ_ሀገራችን #የፀሎት_እና_የምስጋና_ርዕሶች 1. አገራችን የዕርቅ እና የሠላም፤የልማት እና የደስታ ምድር እንዲሆን፤ 2. ጠብ፣ የጎሳ ግጭትና አለመግባባት ከአገራችን እንዲወገድ፤ የደም መፋሰስ፣ የመገዳዳል ታሪክ እንዲያበቃ፤ 3. መልካም አስተዳደር በሁሉም የአስተዳደር ክልሎች እንዲኖር፣ ህግና ሥርዓት እንዲከበር፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራር እንዲወገድ መፀለይ፡፡

ለ34 አገልጋዮች በሆሳዕና ከተማ የቅስና ሹመት ተሠጠ * * * * * * በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መአከላዊ ደቡብ ሲኖዶስ ለቃሉና ቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት ያግዝ ዘንድ ለ34 አገልጋዮች የቅስና ሹመት በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል። ሲኖዶሱ ከተመሠረበት 1963 ዓ.ም ጀምሮ ላፉት 53 ዓመታት ቤተክርስቲያኒቱ ሰፊ የወንጌል እና የልማት ሥራዎችን በአከባቢው ሲያካሂድ ቆይቷል። በአሁኑም ሰዓት ሲኖዶሱ በ7 ዞኖች የወንጌል ሥራን እየሰራ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወደ አገልግሎት ከተሰማሩ የ21ኛ ዙር ተሿሚ አዳዲስ ቀሳውስት ውጪ 540 ቄሶች በሲኖዶሱ በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ። በሹመት ሥነ-ሥርዓቱም ላይ ሰፊ መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን አዳዲስ ቀሳውስት ወደ ማህበረ ምዕመኖቻቸው ሲመለሱ ለቃሉና ቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት ልዮ ትኩረት በመስጠት እና በትጋት ቡዙ ፍሬን እንዲያፈሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል። የቤተክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳ የቅስና ሃላፊነት የሰጡ ሲሆን የሚስዮን እና ቲኦሎጂ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር የሆኑት ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል ቃለ እግዚአብሔር አስተምረዋል። በሥፍራውም የቤተክርስቲያኒቱ የአስተዳደር እና ፋይናንስ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ማቴዎስ፣ የሲኖዶሷ መሪዎች እና የእጩ ቀሳውስት ቤተሰቦች ተገኝተዋል። ለመከሩ ሥራ አገልጋዮችን እያበዛልን ያለ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! - - - Magaalaa Hosaanaa keessatti tajaajiltoota 34f muudamni Lubummaa kennameefii jira. * * * * * * Waldaa Warra Wangeelaa Makana Yesuus Itiyoophiyaa Sinodoosii giddu galeessaa Kibbaa keessatti tajaajiltoonni 34 Dubbii Waaqayyo fi tajaajila Iccitiiwwan Qulqullootaa akka gargaaranif Lubummaadhaan guyyaa har’aa muudamnii Kennameefiraa. Sinodoosichi bara 1963 hundeeffamee kaasee waggoota 53 darbaniif hojiiwwan wangeelaa fi misooma bal’aa naannoo sanatti gaggeessaa turte. Yeroo ammaa kana Sinodoosiin hojii wangeelaa zoonii 7 keessatti hojjechaa kan jiru yoo ta’u, yeroo ammaa Luboota haaraa marsaa 21ffaa irraa kan hafe luboonni 540 Sinodoosicha keessatti tajaajilaa jiru. Sirna muudamaa kana irratti ergaawwan bal’aan kan dabarfaman yoo ta’u, Luboonni haaraan gara waldaa isaaniitti yeroo deebi’an tajaajila Dubbii Waaqayyo fi iccitiiwwan qulqulluu xiyyeeffannoo akka kennan fi ciminaan firii akka godhatan yaadachiifamaniiru. Itti aanaan pireezidaantii mana kiristaanaa Luba Dr. Taarikuu Tolosaa itti gaafatamummaa Lubummaa kan kennan yoo ta’u, Daayreektarri kutaa Ergamaa fi Ti’ooloojii Luba Dr. Lalisaa Daani’eel sagalee Waaqayyoo barsiisaniiru. Daarektarri bulchiinsaa fi faayinaansii mana kiristaanaa obbo Gammachiis Matewoos, hoggantoota Sinoodoosii fi maatiin Luboota kaadhimamaani dabalatee argamaniiru. Hojii tajaajilaaf tajaajiltoota nu baay'isaa jiruuf galanni Waaqayyof haa ta'u! - - - EECMY ordained 34 ministers in Hossana city * * * * * * In the Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus, South Central Synod, for the service of the Word and Sacrament, 34 ministers got ordained today. Since the establishment of the Synod in 1963 EC, the Church has engaged in extensive missional and developmental activities in the area for the past 53 years. Currently, the Synod is working in 7 Zones. Apart from the newly ordained pastors of the 21st round, 540 senior pastors are actively serving in the Synod. During the service, several messages were conveyed from church leaders. When the newly ordained ministers go back to their congregations, they are reminded to pay attention to the service of the Word and Sacrament and bear fruits of ministry with diligence. The vice president of the Church, Rev. Dr. Tariku Tolessa bestowed the responsibility for the ministers and DMT director of the Church, Rev. Dr. Lalisa Daniel shared the word of God. Including leaders of the synod, the church’s Department of Administration and Finance Director, Mr Gemechis Matewos, and families of candidate pastors attended the service. Thanks be to God for continuously sending ministers to His filed of harvest!

ጳጉሜ 3.jpg6.20 KB

ጳጉሜ 3(2).jpg6.00 KB

#Qaammee_3 #Waldaa_Keenyaaf #mata_duree_Kadhataa_fi_Galataa 1. Tokkummaa ishee akka eeggattuuf; 2. Qabeenyaadhaan akka guddattuuf; 3. Bakka Wangeelli hin ga’iiniin Wangeela akka geessuuf; Hojii Misiyoonummaa caalchiftee akka hojjettuuf፣ ፤ 4. Tajaajila Guutuu waldattiif; Ijaarsa Kaateediraaliif፤ Gutummaan Amantootaa fi Geggeessitootaa jireenya fakkeenyummaa qabu akka jiraataniif; 5. Sochii Waldattiin Gootu Hundumaa Keessatti Kiristoos Akka Mul’atuuf.

#ጳጉሜ_3 #ስለ_ቤተ ክርስቲያን #የፀሎት_እና_የምስጋና_ርዕሶች 1. አንድነቷን እንዲጠበቅ፤ 2. በኢኮኖሚ እንድታድግ፤ 3. ወንጌል ላልደረሳቸው ሰዎች ወንጌልን እንድታደርስ፣ የሚስዮን ሥራ ተጠናክሮ
#ጳጉሜ_3 #ስለ_ቤተ ክርስቲያን #የፀሎት_እና_የምስጋና_ርዕሶች 1. አንድነቷን እንዲጠበቅ፤ 2. በኢኮኖሚ እንድታድግ፤ 3. ወንጌል ላልደረሳቸው ሰዎች ወንጌልን እንድታደርስ፣ የሚስዮን ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ 4. ለቤተ ክርስቲያንቱ ሁለንተናዊ አገልግሎት፤ የካቴድራል ግንባታ፤ የምዕመናን እና የመሪዎች መልካም ምሳሌነት፤ 5. በሁሉም አቅጣጫ የክርስቶስን ምሳሌነት እንድታንጸባርቅ፡፡