ch
Feedback
አረቦን

አረቦን

前往频道在 Telegram

ይሕ ቻነል መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ አሳቦቼን የማጋራበት [የሌሎች ወንድም እህቶቼን መጣጥፎችና ምልከታዎች ማጋራቴ እንደተጠበቀ ሆኖ] እንዲሁም መጽሐፍ ተኮር ዳሰሳና ሂስ የማቀርብበት ነው።

显示更多
2 366
订阅者
-224 小时
无数据7 天
+230 天
帖子存档
ከክርስትና በፊት የነበረው አረማዊው ዓለም (pagan world) ድሆች ፣ ሕሙማን እና አካል ጉዳተኞች በአማልክቱ የተረገሙ እንደሆኑና ርኅራኄ እንደማይገባቸው ያምን ነበር። ለእነዚህ የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች መራራት ለአረማዊው ዐለም እንግዳ የሆነ፣ የክርስትና ግን መሠረታዊ ተፈጥሮ ነበር። ክርስቲያኖችም ከአረማውያኑ የሚለዩበት ልዩ መታወቂያቸው ይህ ለተቸገሩትና ልዩ ልዩ ደዌ ለጸናባቸው ሰዎች የሚያሳዩት ፍቅር ርኅራኄና እንክብካቤ ነበር። በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ለነበሩ ክርስቲያኖች ምጽዋት እንደ አማራጭ በጎ ስራ (virtue)  የሚደረግ አልነበረም። ይልቁንም ክርስቲያን ያደረጋቸው መሠረታዊ ማንነታቸው እንጂ። በዛሬው ቆይታችን ይህንን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ስለነዳያን የነበራትን አቢዮታዊ አቋም ፣ ዛሬ ካለው መረዳትና ልምምድ ጋር በስፋት ለማነጻጸር ሞክረናል። መልካም ቆይታ። https://youtu.be/cy9mYo1cFw0?si=3FKQyHXn4yO_Nnvj

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዋና የትምህርት ምንጭ የሆነው የአብነት ትምህርት ቤት በየአመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በመምህርነት አስመርቆ ያወጣል። እነዚህ ተማሪዎች የሚማሩት ትምህርትና ከሦስት እና ከአራት መቶ አመት በፊት የነበሩት ሊቃውንት የተማሩበት መንገድም ሆነ የተማሩት ትምህርት ይዘት ተመሳሳይ ነው። ብዙዎች ይህን ትውፊትን እንደማስጠበቅ አድርገው ይረዱታል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን አድርጎ ያቆያት ዋና ቁምነገርም ይህ እንደሆነ ያስባሉ። ወደፊትም ቤተክርስቲያኒቱን ለመጠበቅ የትምህርት መንገዳችንም ሆነ ትምህርታችን መነካት የለበትም ይላሉ። ነገር ግን እዚህ ጋር መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ ይነሳል። ከአብነት ትምህርት ቤት የሚወጡ መምህራን ከዘመኑ ጋር መራመድና ዘመኑ የሚሠራበትን ፍልስፍና ያለማወቃቸው ነገር ነው። የማያውቁትን ሕመም ደግሞ ማዳን እንደማይቻል ግልጽ ነው። የመምህራን ዋና ተልእኮ ደግሞ የዘመኑን መንፈስ ማንበብና መፈወስ መቻል እስከሆነ ድረስ ትምህርታችንም ሆነ የትምህርት መንገዳችን ላይ ጥያቄ ማንሳታችን የግድ ይሆናል።  ከየኔታ ኃይለማርያም ጋር ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ደፈር ብለን ለመወያየት ሞክረናል። መልካም ቆይታ። https://youtu.be/84qnUpLiPeg?si=sA22oVkx2kT9njo_

ኤማሁስ መነኮሳትን በተመለከተ ያደረገችው ሁለተኛ ክፍል ውይይት እነሆ። የመጀመርያው ክፍል የምንኩስናን መሠረታውያን የተመለከተ ውይይት እንደሆነ የተከታተላችሁ ታስታውሳላችሁ። ይህ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ምንኩስናን በተመለከተ የቤተክርስቲያን ያልሆኑ ነገሮችን የተናገሩ ከዚያም አልፎ ትርክቱን ለመበረዝ በሚመስል መልክ ብዙ የስንፍና ንግግር ሲናገሩ የነበሩትን መምህራን ተብዮዎች የሚያሄስ ውይይት ነው። መልካም ቆይታ። https://youtu.be/5lxbXfsp6pc?si=RMlP8xex10j0KCuU

ከሰሞኑ የመነኮሳት ነገር ሲያነጋግር እንደሰነበተ ይታወቃል። ይህን ጉዳይ መሠረት በማድረግ ዲያቆን ብንያም ፣ ቀሲስ አባተ እና መጋቤ ሐዲስ ኢዮብ እንደሚከተለው ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። እነሆ ውይይቱ ፦ https://youtu.be/AQ_z48j-rEQ?si=ev8391bFp_mIZiTf

የጌታን ሕማምና ሞት ከሕክምና አንጻር ለማየት መሞከር ሕማሙን በተለየ መንገድ እንድንረዳ የሚያደርግ ልዩ መነጽር? ወይስ ወደማያልቁ ነገር መለኮታዊ ስሕተቶች የሚመራ መንገድ? የዛሬው ውይይታችን ይህንን ይመለከታል። https://youtu.be/_-lSVAok52Q?si=xhL2U29qLwTmDERe

የጌታን ሕማምና ሞት ከሕክምና አንጻር ለማየት የመሞከር ዝንባሌ ባለፉት ጥቂት አመታት ብቅ ብሏል። ይህንን በተመለከተ ያደረግነውን ዘለግ ያለ ውይይት ነገ ይጠብቁን። https://youtu.be/TCzbHx2tvEk?si=tg35UH_N5EVb7ckz

አረቦን - Telegram 频道 @mitshaf 的统计与分析