fa
Feedback
አረቦን

አረቦን

رفتن به کانال در Telegram

ይሕ ቻነል መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ አሳቦቼን የማጋራበት [የሌሎች ወንድም እህቶቼን መጣጥፎችና ምልከታዎች ማጋራቴ እንደተጠበቀ ሆኖ] እንዲሁም መጽሐፍ ተኮር ዳሰሳና ሂስ የማቀርብበት ነው።

نمایش بیشتر
2 384
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
-930 روز
آرشیو پست ها
የጌታን ሕማምና ሞት ከሕክምና አንጻር ለማየት መሞከር ሕማሙን በተለየ መንገድ እንድንረዳ የሚያደርግ ልዩ መነጽር? ወይስ ወደማያልቁ ነገር መለኮታዊ ስሕተቶች የሚመራ መንገድ? የዛሬው ውይይታችን ይህንን ይመለከታል። https://youtu.be/_-lSVAok52Q?si=xhL2U29qLwTmDERe

የጌታን ሕማምና ሞት ከሕክምና አንጻር ለማየት የመሞከር ዝንባሌ ባለፉት ጥቂት አመታት ብቅ ብሏል። ይህንን በተመለከተ ያደረግነውን ዘለግ ያለ ውይይት ነገ ይጠብቁን። https://youtu.be/TCzbHx2tvEk?si=tg35UH_N5EVb7ckz

የቤተ ክርስቲያን አበው በሰፊው ካብራሯቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት፣ የሮሜ መልእክት ከቀዳሚዎቹ መሀከል ነው። በኦርቶዶክሳውያን አበው ብቻ ሳይሆን ኦውግስቲን እና ሉተርም ለሮሜ መልእክት ልዩ ፍቅር ነበራቸው። በዚያው ልክ መልእክቱ የልዩነት ምክንያትም ሆኗል። በዚህ ምክንያት የሮሜ መልእክት ጥናት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይኼ የመጋቤ ሐዲስ ኢዮብ ተከታታይ ማብራሪያ ከዚህ አንጻር በጣም ጠቃሚ ነው። ሁላችሁም በእርጋታ ተከታተሉት። ታተርፉበታላችሁ https://youtu.be/e_yqPVrTuyA?si=uJidgqtdPVBlASCL

የጎንደርን የጥምቀት አከባበር ካዩ በኋላ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ታዲያ አሁን የታለ ድምጻችሁ? ብዕራችሁ የሚሰራው ኢጃት ላይ ሲሆን ብቻ ነው ወይ? የሚል ትችት ሲሰነዝሩ አይቻለሁ። ከጥቂት ቀናት በፊት ishowspeed የተባለው streamer ሥላሴ ቤተክርስቲያን እያሟሟቀ መግባቱንና መቅደስ ውስጥ ከሮናልዶና ከሜሲ ማን ይበልጣል? ብሎ መጠየቁን በተመለከተም "ታዲያ አሁን ጥላቻ ስላለባችሁ ነው እንጂ ስለ አእላፋት ዝማሬ ያን ሁሉ ብላችሁ አንድ ዩቲዩበር መጥቶ መቅደስ ውስጥ ሲፋንን እንዴት ዝም ትላላችሁ?" ያሉም አልጠፉም ነበር። የጎንደር ጥምቀት በዚህ አመት ብቻ ሳይሆን ላለፉት ብዙ አመታት ከክርስትና ተጻራሪ በሆኑ ድርጊቶች ታጅቦ ነበር ሲያልፍ የኖረው። እውነቱን ለመናገር መጠኑ ይለያይ ይሆናል እንጂ በጎንደር ብቻ ሳይሆን በብዙ የሃገራችን ክፍሎች ጥምቀት የማንነት ኩራት መገለጫ ፣ ደምቆ መታያ እና ጥሩ ድባብ መፍጠሪያ በዐል እንደሆነ ግልጽ ነው። በዐላት እውነተኛ ትርጉማቸው ሳይታወቅ ሲቀር እንዲህ ባለው ጥፉ አካሄድ መጠለፋቸው አይቀርም። ተጠልፈውማል። ይህንንም አጥብቀን ስንኮንን የኖርነው ነገር እንደሆነ ኤማሁስን ሲከታተሉ የነበሩ ወዳጆች በሚገባ ያውቃሉ። የአእላፋት ዝማሬም ውጫዊ ከሆኑት መገለጫዎቹ ውጭ መንፈሱ በዚሁ ብልሹ የሆነና የተንሸዋረረ የኦርቶዶክሳዊነት መረዳት ውስጥ የበቀለ ችግር መሆኑን አሳይተናል። የአእላፋት ዝማሬ ለምን ችግር እንደሆነ በዝርዝር ማሳየት ያስፈለገን ብዙዎች ለማየት ባለመፈለግ/ባለመቻል ጽንተው ስለነበር ነው። የአእላፋት ዝማሬ ምንም ያህል በግልጽ የሚታይ ችግር ቢሆንም የነበረው አለመረዳት (አንዳንዶቹ በአድርባይነትና በክፋት ሆነ ብለው ላለመረዳት በመሞከርና ነገሮችን በማጣመም) የኦርቶዶክሳዊነት እና የኦርቶዶክሳዊ ሥርዐተ አምልኮ Ethos ምን ያህል ከብዙኃን ኅሊና እንደተሰደደ እና ከአደባባይ እንደተገፋ የመሰከረ አጋጣሚ ነበር። ያ ባይሆንና የአእላፋት ዝማሬና መሰል ኮንሠርታዊ ዝግጅቶች ልክ ዘንድሮ የጎንደር ጥምቀት እንደተኮነነው ቢኮነኑና ችግርነታቸው ቢታመን ኖሮ እኛም ባፍም በመጣፍም ችግርነቱን ለማስረዳት ባልደከምንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ባተኮርን ነበር። አሁንም እንዲህ ያለው የሾቀ Gotcha ውስጥ ከመንቦጫረቅ ትልቁን ምስል ለማየት መሞከር የሚበጅ ይመስለኛል።

Here is a precise and valuable article written by a Coptic priest. https://frmichaelsorial.com/2024/10/23/heartfelt-or-hype-emotions-in-worship/

በአእላፋት ዝማሬ ማግስት ያገረሸውን ውዝግብ እና ኤማሁስ ላይ የተሰነዘሩትን ትችቶች በተመለከተ የሚከተለውን ብያለሁ። መልካም ንባብ።

" ነገር ግን፥ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። " ወደ ገላትያ ሰዎች
" ነገር ግን፥ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። " ወደ ገላትያ ሰዎች 4፥4 እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ትናንት ማታ ያጋራነው ቪዲዮ የተወሰነ የድምጽ ችግር ስለነበረበት private አድርገነው ነበር። አሁን የተስተካከለውን ቪዲዮ እንደሚከተለው እናጋራችኋለን። ለተፈጠረው ስህተት ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን። https://youtu.be/vsY0_Or7aD8?si=baaovBA_a5j6dccZ