አረቦን
Открыть в Telegram
ይሕ ቻነል መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ አሳቦቼን የማጋራበት [የሌሎች ወንድም እህቶቼን መጣጥፎችና ምልከታዎች ማጋራቴ እንደተጠበቀ ሆኖ] እንዲሁም መጽሐፍ ተኮር ዳሰሳና ሂስ የማቀርብበት ነው።
Больше2 366
Подписчики
-224 часа
Нет данных7 дней
+230 дней
Архив постов
2 365
ከክርስትና በፊት የነበረው አረማዊው ዓለም (pagan world) ድሆች ፣ ሕሙማን እና አካል ጉዳተኞች በአማልክቱ የተረገሙ እንደሆኑና ርኅራኄ እንደማይገባቸው ያምን ነበር። ለእነዚህ የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች መራራት ለአረማዊው ዐለም እንግዳ የሆነ፣ የክርስትና ግን መሠረታዊ ተፈጥሮ ነበር። ክርስቲያኖችም ከአረማውያኑ የሚለዩበት ልዩ መታወቂያቸው ይህ ለተቸገሩትና ልዩ ልዩ ደዌ ለጸናባቸው ሰዎች የሚያሳዩት ፍቅር ርኅራኄና እንክብካቤ ነበር። በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ለነበሩ ክርስቲያኖች ምጽዋት እንደ አማራጭ በጎ ስራ (virtue) የሚደረግ አልነበረም። ይልቁንም ክርስቲያን ያደረጋቸው መሠረታዊ ማንነታቸው እንጂ። በዛሬው ቆይታችን ይህንን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ስለነዳያን የነበራትን አቢዮታዊ አቋም ፣ ዛሬ ካለው መረዳትና ልምምድ ጋር በስፋት ለማነጻጸር ሞክረናል። መልካም ቆይታ።
https://youtu.be/cy9mYo1cFw0?si=3FKQyHXn4yO_Nnvj
2 365
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዋና የትምህርት ምንጭ የሆነው የአብነት ትምህርት ቤት በየአመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በመምህርነት አስመርቆ ያወጣል። እነዚህ ተማሪዎች የሚማሩት ትምህርትና ከሦስት እና ከአራት መቶ አመት በፊት የነበሩት ሊቃውንት የተማሩበት መንገድም ሆነ የተማሩት ትምህርት ይዘት ተመሳሳይ ነው። ብዙዎች ይህን ትውፊትን እንደማስጠበቅ አድርገው ይረዱታል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ቤተክርስቲያን አድርጎ ያቆያት ዋና ቁምነገርም ይህ እንደሆነ ያስባሉ። ወደፊትም ቤተክርስቲያኒቱን ለመጠበቅ የትምህርት መንገዳችንም ሆነ ትምህርታችን መነካት የለበትም ይላሉ። ነገር ግን እዚህ ጋር መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ ይነሳል። ከአብነት ትምህርት ቤት የሚወጡ መምህራን ከዘመኑ ጋር መራመድና ዘመኑ የሚሠራበትን ፍልስፍና ያለማወቃቸው ነገር ነው። የማያውቁትን ሕመም ደግሞ ማዳን እንደማይቻል ግልጽ ነው። የመምህራን ዋና ተልእኮ ደግሞ የዘመኑን መንፈስ ማንበብና መፈወስ መቻል እስከሆነ ድረስ ትምህርታችንም ሆነ የትምህርት መንገዳችን ላይ ጥያቄ ማንሳታችን የግድ ይሆናል። ከየኔታ ኃይለማርያም ጋር ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ደፈር ብለን ለመወያየት ሞክረናል። መልካም ቆይታ።
https://youtu.be/84qnUpLiPeg?si=sA22oVkx2kT9njo_
2 365
ኤማሁስ መነኮሳትን በተመለከተ ያደረገችው ሁለተኛ ክፍል ውይይት እነሆ። የመጀመርያው ክፍል የምንኩስናን መሠረታውያን የተመለከተ ውይይት እንደሆነ የተከታተላችሁ ታስታውሳላችሁ። ይህ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ምንኩስናን በተመለከተ የቤተክርስቲያን ያልሆኑ ነገሮችን የተናገሩ ከዚያም አልፎ ትርክቱን ለመበረዝ በሚመስል መልክ ብዙ የስንፍና ንግግር ሲናገሩ የነበሩትን መምህራን ተብዮዎች የሚያሄስ ውይይት ነው። መልካም ቆይታ።
https://youtu.be/5lxbXfsp6pc?si=RMlP8xex10j0KCuU
2 365
ከሰሞኑ የመነኮሳት ነገር ሲያነጋግር እንደሰነበተ ይታወቃል። ይህን ጉዳይ መሠረት በማድረግ ዲያቆን ብንያም ፣ ቀሲስ አባተ እና መጋቤ ሐዲስ ኢዮብ እንደሚከተለው ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
እነሆ ውይይቱ ፦
https://youtu.be/AQ_z48j-rEQ?si=ev8391bFp_mIZiTf
2 365
የጌታን ሕማምና ሞት ከሕክምና አንጻር ለማየት መሞከር ሕማሙን በተለየ መንገድ እንድንረዳ የሚያደርግ ልዩ መነጽር? ወይስ ወደማያልቁ ነገር መለኮታዊ ስሕተቶች የሚመራ መንገድ?
የዛሬው ውይይታችን ይህንን ይመለከታል።
https://youtu.be/_-lSVAok52Q?si=xhL2U29qLwTmDERe
2 365
የጌታን ሕማምና ሞት ከሕክምና አንጻር ለማየት የመሞከር ዝንባሌ ባለፉት ጥቂት አመታት ብቅ ብሏል። ይህንን በተመለከተ ያደረግነውን ዘለግ ያለ ውይይት ነገ ይጠብቁን።
https://youtu.be/TCzbHx2tvEk?si=tg35UH_N5EVb7ckz
