6 848
订阅者
-724 小时
+447 天
+15930 天
数据加载中...
标签云
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服。
进出提及
---
---
---
---
---
---
吸引订阅者
七月 '26
七月 '26
+249
在0个频道中
六月 '26
+237
在0个频道中
Get PRO
五月 '26
+219
在0个频道中
Get PRO
四月 '26
+224
在0个频道中
Get PRO
三月 '26
+92
在1个频道中
Get PRO
二月 '26
+631
在3个频道中
Get PRO
一月 '26
+116
在0个频道中
Get PRO
十二月 '25
+95
在0个频道中
Get PRO
十一月 '25
+77
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+109
在0个频道中
Get PRO
九月 '25
+120
在2个频道中
Get PRO
八月 '25
+134
在1个频道中
Get PRO
七月 '25
+146
在1个频道中
Get PRO
六月 '25
+212
在2个频道中
Get PRO
五月 '25
+159
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+196
在1个频道中
Get PRO
三月 '25
+240
在3个频道中
Get PRO
二月 '25
+263
在1个频道中
Get PRO
一月 '25
+364
在1个频道中
Get PRO
十二月 '24
+772
在2个频道中
Get PRO
十一月 '24
+547
在4个频道中
Get PRO
十月 '24
+368
在1个频道中
Get PRO
九月 '24
+272
在2个频道中
Get PRO
八月 '24
+280
在1个频道中
Get PRO
七月 '24
+672
在3个频道中
Get PRO
六月 '24
+213
在1个频道中
Get PRO
五月 '24
+44
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+32
在1个频道中
Get PRO
三月 '24
+64
在2个频道中
Get PRO
二月 '24
+415
在1个频道中
Get PRO
一月 '240
在3个频道中
Get PRO
十二月 '230
在0个频道中
Get PRO
十一月 '23
+32
在0个频道中
Get PRO
十月 '23
+39
在0个频道中
Get PRO
九月 '23
+28
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+2 553
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 30 七月 | +6 | |||
| 29 七月 | +2 | |||
| 28 七月 | +10 | |||
| 27 七月 | +6 | |||
| 26 七月 | +9 | |||
| 25 七月 | +10 | |||
| 24 七月 | +16 | |||
| 23 七月 | +13 | |||
| 22 七月 | +4 | |||
| 21 七月 | +16 | |||
| 20 七月 | +2 | |||
| 19 七月 | +10 | |||
| 18 七月 | +10 | |||
| 17 七月 | +9 | |||
| 16 七月 | +5 | |||
| 15 七月 | +11 | |||
| 14 七月 | +4 | |||
| 13 七月 | +11 | |||
| 12 七月 | +5 | |||
| 11 七月 | +9 | |||
| 10 七月 | +10 | |||
| 09 七月 | +9 | |||
| 08 七月 | +8 | |||
| 07 七月 | +14 | |||
| 06 七月 | +5 | |||
| 05 七月 | +4 | |||
| 04 七月 | +7 | |||
| 03 七月 | +8 | |||
| 02 七月 | +12 | |||
| 01 七月 | +4 |
频道帖子
`` When Life does not find a singer to sing her
heart she produces a philosopher to speak her mind.``
`` ህይወት የልቧን የሚዘፍንላት ዘፋኝ ስታጣ ሀሳቧን የሚናገር ፈላስፋ ታፈራለች ``
#Kahlil_gibran
፦ from Sand and Foam 📖 (1926)| 2 | <ይሄን ብር ያዝልኝ እኔ ጋር ከሆነ አጠፋዋለሁ> ብላችሁ ለሰው ሰጥታችሁ ገንዘባችሁን ቢያጠፉባችሁ ምንድን ነው የምትሉት? አንደኛ ያው ምነው ባልሰጠሁት ብላችሁ ቁጭት እና ፀፀት ውስጥ ትገባላችሁ። ግን ከዛ በላይ ጥያቄ አይፈጥርባችሁም? ምን የሚል?...
<ገንዘቡን እኔ ጋር ባስቀምጠው ኖሮ የምር ጨክኜ አጠፋው ነበር?> የሚል ጥያቄ ሽው አይልባችሁም?
ቀለል አድርጌ ነገርየውን ገንዘብ አደረኩት እንጂ የሆነ የራሳችንን ነገር ከእኛ በላይ ሊጠነቀቁለት ይችላሉ ብለን አስበን ለሰዎች አሳልፈን እንሰጣለን። ነፃነታችንን.. ጊዜያችንን.. ህልማችንን.. እድሜያችንን.. እና እነዚህን በዋጋ የማይተመኑ ነገሮችን አሳልፈን ሰጥተን ልክ ነፋስ ላይ እንደተበተነ ዱቄት ብንንንን አድርገው ሲያጠፉት ምንድን ነው መልሳችን?
እምነትን ያህል ነገር ሰጥተን ወሽመጥን ቁርጥ የሚያደርግ ክህደት.... እድሜን ያህል ጊዜ ሰጥተን <እንዴ> የሚያስብል ቸልተኝነትን እንቀበላለን። ልባችንን አሳልፈን ሰጥተን እነሱ ግን ስብር አድርገውት ሲሄዱ ምንም እስካይመስላቸው ነው ድንዳኔያቸው። ለቅሷችን... ናፍቆታችን... ትኩረት መስጠታችን ሁሉ ለእነሱ ኢምንት ሆኖ ስናገኘው ... ምነው በቀረብኝ ያስብላል።
እኔ ልቤ ያሳዝነኛል ፤ ሰፍ ብሎ ሄዶ ተጋጭቶ እየደማ ሲመለስ ያሳዝነኛል። እርፍ ሊል ሄዶ ኮስኩሶት ሲመለስ ያሳዝነኛል። ተው እያልኩት አምኖ ስላቅን ተቀብሎ ሲመለስ እና ክፍት ሲለው ያሳዝነኛል። ከዛ በላይ ልቤን ማስታመም እኔን ያደክመኛል።
ህመምን እንደማይችል ስለማውቅ እና ሲደማ ስለሚያሳዝነኝ እንዲህ አደርጋለሁ.. ልክ አንዲት እናት ተደባዳቢ ልጇን እስር አድርጋ ከቤት እንዳይወጣ እንደምትከለክለው ሁሉ .. አይምሮዬም ልቤን ቆንጠጥ አድርጎ አርፎ እንዲቀመጥ ያደርገዋል።
ግን ደግሞ ጥልጥል ብሎ ማረፊያ ፍለጋ ክርትት ሲል መልሶ ደግሞ ያሳዝነኛል። ልቤን ስገድበው ያሳዝነኛል .. እየፈለገ ተው ስለው ያሳዝነኛል። <እስኪ ልሞክር > እያለኝ .. ጭክን ስልበት ያሳዝነኛል
ስሜቱ እንዴት መሰላችሁ... ብቻ የመሆን ልብን የመከልከል ስሜቱ... በሃይለኛው ውሃ ጠምቶን <ቆይ ትንሽ.. > እያሉ እንደማስታገስ ነው። በመንገድ የዛለ ሰውነታችንን <ቆይ ደርሰናል..> እያሉ እንደማስጓዝ ነው። ያለምንም ተስፋ ተስፋ እንደመስጠት ነው። ይከብዳል።
እንዴት እንደሆነ ባላውቅም አደራን ጠብቆ ራስ ጋር ማቆየትም ፤ አደራን ለሰው መስጠትም ከባድ ነው።
Fantu emu | 810 |
| 3 | " I live my life as I want not what other people expect me to be. This way makes me happier. "
" ህይወትን የምኖራት እንደምፈልገው አድርጌ እንጂ . . . ሌሎች ሰዎች እንድሆን እንደሚጠብቁኝ አይደለም፤ ይህኛው መንገድ ይበልጥ ደስተኛ እንድሆን ያደርገኛል። "
፦ Osho | 899 |
| 4 | ልክ እግሮቿን በዳበስኩኝ ቅፅበት የተሰማኝን ጉድለት ከዛ በኋላ አልደገምኩትም።
ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ እጇን ነክቼው ነበር.. ቻዎ ልላት ስጠጋት በህመሟ ምክንያት ግንባሯ ብቻ ሳይሆን ትንፋሿም ያቃጥል እንደነበር አስታውሳለሁ። ያው ከታመመች ሰዓት ጀምሮ ሁሌ እንደጋለች ነው። ለሊት ላይ ተኝተን ልታቅፈኝ እጇን ስትዘረጋ እና የተራቆተው ወገቤ ላይ ስታሳርፈው
<እማ እጅሽ ያቃጥላል አውርጂው> እላታለሁ
<እሺ> ብላ እጇን ሰብሰብ ታደርገዋለች
እና ጠዋት እንደዛ ግላ ተለይቻት ሄጄ... አሁን በነጭ አቡጀዲ ከተጠቀለለው ሰውነቷ ስር እንደምንም እጄን አሾልኬ የነካሁት እግሯ ቅዝቃዜው ክው አድርጎኛል።
ግን ግን ያስደነገጠኝ ቅዝቃዜው አይመስለኝም.. እንዳው የተሰማኝም ድጋጤ አይመስለኝም። ድንጋጤን ስሜቱን አውቀዋለሁ... ስመለስ ውጪ እንዳላገኝሽ ብላኝ ስትመለስ እየተራገጥኩ ስታገኘኝ እንደምደነግጠው አይደለም የተሰማኝ... የቤት ስራ እንደተሰጠኝ ረስቼው ሳልሰራ ሄጄ አስተማሪ <ደብተራችሁን አውጡ> ሲል እንደሚሰማኝ አይደለማ የተሰማኝ...
አሁን ካደኩ በኋላ ሰው ሞቶ መርዶ ስሰማ እንደተሰማኝ አልነበረም የተሰማኝ.. እንደሚያፈቅረኝ ያመንኩት ሰው <መለያየት አለብን> ሲለኝ እንደደነገጥኩት አልነበረም ስሜቱ... እጅግ የማምናት ሴት አሳልፋ የሰጠችኝ እለት እንዲ አልነበረም የተሰማኝ ... አልነበረም
የዛች ቀን የተሰማኝ.. የቅዝቃዜውን ልክ እስካሁን ባላገኘሁለት መጠን የቀዘቀዘኝን እግሯን ስነካው የተሰማኝ ... ድንጋጤ አልነበረም... ፍርሃትም አልነበረም ... ብዙ ፈርቼ አውቃለኋ .. በማላውቀው መንገድ ሊያውም በጨለማ እየፈራሁ ተጉዤ አውቃለሁ.. የማላውቀው ቢሮ ውስጥ ተቆልፎብኝም ያውቃል... ብዙ ትልልቅ የስራም የትምህርትም ፈተናዎችን ልፈተን ተዘጋጅቻለሁ... ብዙ ፈርቻለሁ... ስለዚህ ስሜቱ እንደሱ አልነበረም።
ይልቅ የተሰማኝ ጉድለት ይመስለኛል... አበቃ አይደል? አይነት... መንገድ እንደጠፋበት ሰው ቆም አልኩ.. ምንም አይነት የመንገድ ምልክት የሌለበት መሐል በረሃ ላይ እንደመቆም... አይ በቃ አይገለፅም ተውት ብቻ እንደዛ ነው...
እና ከስንት ጊዜ በኋላ ዛሬ አየኋት በህልሜ። መልኳን እየረሳሁት ነበር መጥታ አስታወሰችኝ። ያንን ጉድለት በምኑም በምኑም ልሞላው እየሞከርኩ ግን ይበልጥ እያጎደልኩት ነበር ፤ ዛሬ ሳያት የሆነ ደስታ ተሰማኝ። እንዳዲስ ናፈቀችኝ የእውነት።
<እጅሽ ያቃጥላል አውርጂልኝ> እንዳላልኳት .. እንደ እሳት ብትንቦገቦግ ላቅፋት ፈለኩ።
<አስር ጊዜ እማ እማ አትበይ አታድክሚያት> ያሉኝን ሰዎች ረገምኳቸው .. የሚበቃኝን ያህል በጠራኋት .. የትም ከእሷ ውጪ አልሄድም <እዚም እዛም አትጎተቺላት እሷ እኮ ልጅ ናት ለልጅ ትጎተቺያለሽ?> እያሏት <ዝም በያቸው በኋላ እንሄዳለን> ብላ ትጠቅሰኝ ነበር። የትም እንሂድ ካልኳት ትሄዳለች።
ነይ እንሂድ ልላት ፈለኩ... ልንገርሽ የተፈጠረውን ልላት ፈለኩ... ልጅ እያለሁ አርቲቡርቲውን ስነግራት የምትሰማኝን አይነት አሁን ሴት ከሆንኩ በኋላ የደረሰብኝን ሁሉ ልነግራት ፈለኩ... ቡና እያፈላሁላት ሚስጢሮቼን ላማክራት ፈለኩ... <እንዴት መሰለሽ ይሄን ያለፍኩት...> እያልኩ ያለፍኩትን ሁሉ ላናግራት ፈለኩ... ግን በህልሜ ነው ማውራት አልቻልኩም። ዝም ብዬ ሳያት ቆየሁ... አጋብታብኝ የሄደችውን ሳቅ ብቻ እየሳቀች አየችኝ።
በመጨረሻም <ልምጣ?> አልኳት <ፊትሽን አዙሪ አለችኝ> ታዘዝኳት .. ቆይቼ ስዞር የለችም። ለምን ፊትሽን አዙሪ ላለችኝ ታዘዝኩ? ለምን ሳያት አልቆየሁም?
Fantu emu | 54 |
| 5 | ``Having a good home , eating good food , wearing good clothes , are a means to living well ; they are not the goals of our life . The quality of your life is decided by how peaceful and joyful you are .``
`` ጥሩ ቤት መኖር ፥ ጥሩ ምግብ መብላት ፥ ጥሩ ልብስ መልበስ ጥሩ ኑሮ መኖር። እነሱ የሕይወታችን ግቦች አይደሉም! የህይወት ጥራት የሚወሰነው እናንተ ምን ያህል ሰላማዊ እና ደስተኛ መሆኖ ላይ ነው። ``
🧘🏽♂
#Sadhguru | 1 070 |
| 6 | ሳላውቅህ በፊት ጨለማ እፈራ ነበር። ጨረቃ ወጣች፣ መሸ፣ ነጋ... ግድ የሚሰጠኝ ምንም አልነበረም። ለኔ ምሽትና ንጋት የቀን መለዋወጥ ብቻ ነበሩ፣ ትርጉም የለሽ ዑደት።
አንተ ግን በህይወቴ ገብተህ ሁሉንም ለወጥከው። አሁን መስኮቴን ከፍቼ ጨረቃዋንና ጨለማውን ሳያቸው "ይሄን ያህል ተጉዘን ነበር?" እላለሁ።
ትዝ ይልሃል? እጅ ለእጅ ተያይዘን ማርጀት ነበር ፍላጎታችን። ለልጆቻችን የምንተርክላቸውን ተረት የሚመስል ታሪካችንን ስትተርክልኝ፣ ድምጽህ አሁንም ድረስ በጆሮዬ ያስተጋባል። መድረስ የምትፈልግበትን ቦታ ስትነግረኝ፣ እጄን ይዘህ ላግዝህ ስጣጣር የነበርኩበት ስሜት አሁንም በአእምሮዬ ይዋልላል።
ብቻ... ልክ ኮምፓስ እንደጠፋበት መርከብ፣ አሁን ወዴት እንደምሄድ አላውቅም። እጄን ይዘህ ያደረስከኝ ቦታ ላይ ቆሜ መንገዱን ከማማተር ውጪ ምን አማራጭ አለኝ?
አዎ... አንተ ኮምፓሴ ነበርክ! 🧭
አሁን ጨረቃን ሳያት አንተ ትዝ ትለኛለህ። አንዳንዴ ካለህበት ጎትቼ ላወጣህ እፈልጋለሁ፣ ግን አልችልም። ምናልባት. . . ጥላ ከለላ የሆኑን ሰዎች ሲርቁን ነው፣ የህይወት ዱላዋ በትክክል የሚሰማን።
ዛሬም ጨረቃዋ ወጥታለች። ግን ዛሬ... ብቻዬን ሆኜ ነው የማያት።
121(አኮብ) | 2 890 |
| 7 | በሲኒማ ታሪክ ውስጥ በጣም ሃያል ከሆኑ ንግግር አንደኛው የዚህን አለም እውነታ ያጠቃልላል። 🎬 The Godfather ዶን ቪቶ ኮርሊኒ ለልጁ ሚካኤል ኮርሊኒ እንዲህ ሲል ይመክረዋል፦
«እኔ ስሞት ካንተ ጋር የሰላም ውል ጠይቀው ስምምነት ላይ ይደርሳሉ። የምታምነውን አንድ ሰው ከእኛ ጉባኤ ወይም ከቤተሰብህ መካከል አንዱን መርጠው ወደአንተ ይልኩታል። የተላከው ሰውም ለሰላም ስምምነት እና ለአንተ የበለጠ ሹመት ልታገኝ እንደሆነ በመንገር ስብሰባው መች እንደሚከናወን የቀጠሮ ቀኑን ያሳውቅሃል። በዚህ ስብሰባ ወቅት ግን አንተ ትገደላለህ!። ለዛም ነው ይሄን የምልህ፤ ያ ለሰላም እና ለሹመት የሚልኩት ሰው ማንም ይሁን ማን አስወግደው ከሃዲ ነው!።»
| 3 354 |
| 8 | https://t.me/Nazrawit38 | 2 969 |
| 9 | "የድሮ ደብተሬን ስገለጥ፣ 'ፍቅር እያደር ወጣት ይሆናል እንጂ እንደ ሰው አያረጅም' የሚል ጽሁፍ አገኘሁ። የኔስ ፍቅር የት ደረሰ? እንደ እድሜ ጠገብ አዛውንት መቋሚያ ተደግፎ ይሆን ወይ? 'ገና አልሞትኩም' እያለ ለማትረፍ የሚታገል...
አንዳንዴ በውስጥ ያለን ስሜት አለመናገር፣ ከልብ የማይጠፋ የዘወትር ጠባሳ ሆኖ ይቀራል። እናንተስ? የውስጣቹን ሳትናገሩ ግዜ የሸበለለባቹ ነገር አለ?"
አኮብ(121) | 3 626 |
| 10 | ሬድዮ አዳምጬ ማቅባቸው ቀናቶች በጣት የሚቆጠሩ ትንሽ ናችው ዛሬ ግን መክፈት ፈለኩ መስማት ፈለኩ የሆነ ምስሉን የማላየው ድምጽ ፈለኩ እሱነቱን በለበሰው ጨርቅ ሳይሆን በንግግሩ መመዝን ፈለኩ አንዳንዴ ምናለ የዘመኑ social mediaዋች በድምጽ በሆኑ እላለሁ ብቻ ከፈትኩት አንድ ሰው በደስታ ተሞልቶ ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው ሲል ይደመጣል ታሪካዊ ቀን ማለት የማይረሳ በጥሩ ም በመጥፎም የሚታወስ አደል እንዲ ካልን ስንቱ በልቡ ከትቦ የያዘው ታሪካዊ ቀን አለው የማይረሳው. . . የማይዘክረው. . . የማይረግመው. . . ሊፍቀው ቢሞክር የማይፋቅ በልቡ የተነቀሰው ጥቁቁር የጠለሹ የህይወቱ ቅንጥብጣቢዋች ሆነው ለመንቀል ያዳገቱ ብቻ እግዜር መቶ ለሁሉም ብእር ወርቀት የታሪካዊ ቀናቹን ገጠመኝ አስፍሩ ቢል ወረቀቱ ይበቃቸዋል? እንጃ የኔዋ ታሪካዊ ቀን ግን ታሪከ ብዙ ናት ቢጨልፏት የማታልቅ ውቅያኖስ የናተስ? ስንት ታሪካዊ ቀን . . . አላቹ ?
አኮብ(121) | 65 |
| 11 | አሁንኮ ድንገት ትዝ ብለኸኝ…እንዲሁ በኑሮ በኑሮ መሀል አንዳንዴ አስብሀለሁ።ትዝታ ግን አይገርምህም?
.
ትዝታ ጎበዝ የሒሳብ ሊቅ ነው።
ይሔ ሲደመር ይሔ ..ሲደመር ይሔ…ነው እዚህ ያደረሳችሁ ይለኛል። እሺ እላለሁ።
ይሔ ሲቀነስ ይሔ…ሲቀነስ ይሔ ነው…ልብሽን ባዶ ያደረገው ይለኛል። እሺ እላለሁ።
ይሔ ሲባዛ ይሔ …ሲደመር ይሔ ..እኩል ይሆናል ይሔ መለያት ይለኛል። እሺ ነው መቼስ ለትዝታ ምን ይመልሱለታል?
.
ትዝታ የአለም አንደኛ ዲፕሎማትም ነው። ይሔ ሆኗል ይሔም ተደርጓል ቢሆንም ፍቅርን የሚያህል የታል? ይላል። ያኔ ልብም አዕምሮም ለዘብ ረገብ ይሉለታል። የተኩስ አቁም ስምምነት ይፈርሙለታል። እንዲያ እያሞኘ ድል ይረታል። እንጂ እኔ አሁን አንተን ላስብ ይገባል? በፍፁም!
.
ትዝታ እግዜር የጎበዝ ዕድሜ በደላችንን ያይደል የልጅነት የወተት ጥርሳችን እያሰበ ይቅር እንደሚለን ለማስታወስ በልብ ያስቀመጠው ህቡዕ ቋንቋም ይመስለኛል።
ለዛ ነው መሰል ሰው ነፍሱ ስጋውን ስትሰናበት ለሰከንድ በህይወት ሳለ የሰራው ዋና ዋና ነገር summary ይቀርብለታል አሉ። ችግሩ ያኔ ‘take me back to the night we met’ን እየዘፈኑ መመለስ የለም።
.
ስለዚህ ዛሬ አስብሀለሁ። ስለማስብህም ብዙ አይደብረኝም። ወደተዋወቅንበት ፀደይ ዘመን እየሔድኩ ደግ ደግህን እደግማለሁ።
አንተ ግን በቃ እረሳኸኝ እንደዛ የሰው limited edition ነሽ እንዳላልከኝ። እንግዲህ ምን አደርጋለሁ ከቴዲ ታደሰ ጋር ከመጮህ ውጪ
ከተስማማህ ከደላህ ምን አለ ከደላህ
ከሞላልህ ከደላህ ምን አለ ከደላህ…..🎧
ቤቴልም እንደ ከተበችው | 4 075 |
| 12 | «አንድ ሰው ይህ ያጋጥመዋል፤ ከእንቅልፉ ሲነሳ በጥልቅ ድንጋጤ ራሱን ይጠይቃል፦ እውነት ሃያ ሞላኝ? ሰላሳ፣ አርባ? እናስ ህይወት እንዴት አለፈች?!»
―ኢቫን ቶርጌኔቭ
| 3 733 |
| 13 | °°
እኛ የቀትር ህልሞች ነን ቀን የተፋነውን እንቅልፍ ማታ የምናላምጥ 🎈
| 3 322 |
| 14 | በወሬ መሀል እንደቀልድ በዋዛ ፈዛዛ ስምሽን ሲያነሱ ድንገት ነበር ሳቄ ከገፄ ላይ የተራገፈው... ድንገት ነበር ጨዋታ የጠፋብኝ... ድንገት ነበር በዝምታ ባህር ውስጥ የሰጠምኩት... ብቻ ከምሸሸው እኔነቴ ጋር ነው ያላተሙኝ.. አላወቁትም እንጂ ማባርያ ከሌለው ዶፍ ትዝታ ውስጥ ነበር የዘፈቁኝ...
"!አንዳንዴ የተዳፈነ ትዝታ ሰው ፊት ሲነቃ አንገት ያስደፋል ''
121 | 3 702 |
| 15 | አባት ሁሉ ወታደር ነው. .አንዳንዱ የገዛ ልጁን ሲገድል፤ አንዳንዱ ግን ልጁን ለማኖር እራሱን ያጠፋል!።
| 3 565 |
