ch
Feedback
Assaye Derbie

Assaye Derbie

前往频道在 Telegram

📈 Telegram 频道 Assaye Derbie 的分析概览

频道 Assaye Derbie (@asayede) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 351 名订阅者,在 博客 类别中位列第 2 648,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 352

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 351 名订阅者。

根据 21 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -144,过去 24 小时变化为 -1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 37.49%。内容发布后 24 小时内通常能获得 11.78% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 382 次浏览,首日通常累积 1 691 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 40

📝 描述与内容策略

尚未提供频道描述。

凭借高频更新(最新数据采集于 22 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 博客 类别中的关键影响点。

14 351
订阅者
-124 小时
-387
-14430
帖子存档
ከስር ባለው ሊንክ ገብተው የቀጥታ ሥርጭታችንን መከታተል ይችላሉ።👇 https://www.youtube.com/live/192YrJpxdOE?feature=share

በሸዋ፣ በጎጃምና በወሎ አማራ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ዋነኛ ዓላማው የአማራ ሕዝብን ሕልውና እና ስነ ልቦና ማንኮታኮት ሲሆን ሁለተኛው ዓላማ ደግሞ ተረኛው አካል ከተባረረው ኃይል ጋር ተባብሮ በጎንደር አማራ ላይ ሊፈጽም ያሰበውን መጠነ ሰፊ የክሕደት ዘመቻ የማያደናቅፉ ሦስት ዞኖች መፍጠር መቻል ነው። እናም እልኻለሁ... የጋራ ጥቃታችንን በወረፋ ማስተናገድ እስካላቆምን ድረስ ዋጋ መክፈላችን ይቀጥላል።

photo content

ብልጽግናዎች ፓርቲያቸውን የሚቃወሙባቸው ፌክ አካውንቶች ▬▬▬▬ "ጥቅመኛ" የሚል ኮሜንት የሚያስገኙ ጽሑፎችን እየጻፈ በትክክለኛ አካውንቱ ሲለጥፍ የነበረው ልጅ ባለፈው ሰይጣን አሳስቶት ብልጽግናን ለመተቸት ደፈረ። በማግስቱም በታጣቂዎች ታፍኖ አንድ ሳምንት ታሠረ። ከእስር ቤት በወጣ ማግሥትም በማይታወቅ ሰው ሥም ባወጣው ሐሰተኛ አካውንቱ "ትክክለኛ ሐሳብ" የሚል ኮሜንት የሚያስገኙ ሐሳቦችንና መረጃዎችን ማቀበል ጀመረ።😆 ምን ለማለት ፈልጌ ነው? ➔በትክክለኛ አካውንታቸው ገዢውን ፓርቲ የሚተቹ አስር አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ሲታሠሩ አስር ሺህ ፌክ አካውንቶች ተከፍተው ያድራሉ። ➔ለስሜት ሕዋሳት የሚሰቀጥጥ ግፍ በምታስተናግድ አገር ውስጥ ግፍን ተቃወማችሁ ተብለው የሚታሠሩ ይቅርና ግፍን ይደግፉ ዘንድ የሚከፈሉ ካድሬዎች እንኳን ብሶታቸውን የሚተነፍሱበት ፌክ አካውንት ለማውጣት ይገደዳሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለምሳሌ ባለፈው አንዱን "የኮንዶሚኒየም ምርኮኛ" መንገድ ላይ አገኘሁትና "አንት የማትረባ" ማለት ስጀምር የሆዱን በሚቀባጥርበት ፈንታ የልቡን የሚተነፍስበትን ሐሰተኛ አካውንት ከፍቶ የኔን ትክክለኛ አመለካከት ማወቅ ከፈለግክ በዚህኛው አካውንት ፎሎው አድርገኝ" ይለኝ ጀመር።😆 አሁንም ምን ለማለት ፈልጌ ነው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሱ ብልጽግናን የሚቃወምበት ፌክ አካውንት እንደሚኖረው አልጠራጠርም 😂

photo content

ሕዝብን መፈተን ጥሩ ስላልሆነ አርበኛውን ልቀቁት።
+1
ሕዝብን መፈተን ጥሩ ስላልሆነ አርበኛውን ልቀቁት።

photo content

photo content

photo content

አርበኛ ዘመነ ካሴን ፍርድ ቤቱ ነጻ ሰው ነህ ብሎታል። Yalelet Wondye የንጹሑ ወንድማችን ንጽሕና በፍርድ ቤት የተረጋገጠው ግን በርካታ ሙስሊም በተጨፈጨፈበት፣ የጎጃም አርሶ አደር አመጽ በጀ
አርበኛ ዘመነ ካሴን ፍርድ ቤቱ ነጻ ሰው ነህ ብሎታል። Yalelet Wondye የንጹሑ ወንድማችን ንጽሕና በፍርድ ቤት የተረጋገጠው ግን በርካታ ሙስሊም በተጨፈጨፈበት፣ የጎጃም አርሶ አደር አመጽ በጀመረበትና ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በጄኖሳይድ በተከሰሰበት ወቅት መሆኑን ልብ ይሏል።

photo content

ለዶክተር ለጤናህ እጅጉ አሳዬ ደርቤ በማዳበሪያ ፋብሪካው ዙሪያ የሚከተሉትን ሐሳቦች መስጠት ፈለግሁ። ➼ማዳበሪያ ከውጭ አስገብቶ መሸጥ ያልቻለ ሥርዓት የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታን ያሳካል ተብሎ አይገመትም። ➼ባዶ ካዝና ተሸክሞ የሚንገታገተውን ሥርዓት በማዳበሪያ ፋብሪካ ሥም ስልሳ ቢሊዮን ብር ላመጣልህ ነው" ስትለው እንቢ ይላል ተብሎ አይታሰብም። ➼የማዳበሪያ ፋብሪካው ግንባታ ለይስሙላ ያክል ቢጀመር እንኳን "እኔ ከወረድኩ ይሄን ፋብሪካ ጨርሶ የሚያስረክብህ አይኖርም" እያለ ብአዴን አስር ዓመት ዘና ብሎ ፖለቲካ እንደሚሰራበት አያጠራጥርም። ➼የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት እንደ ሌሎች አክሲዮኖች ቀላል ተግባር አይደለም። ለዚያም ነው በርካታ የውጪና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በሲሚንቶ ዘርፍ ሲሰማሩ የማዳበሪያ ፋብሪካን ያልሞከሩት። ካላመንክ ያዮ ሔምስፌር ላይ ሄደህ ሳይጀመር የቆመውን የማዳበሪያ ፋብሪካ ተመልከት። ➼ነዳጅ መኖሩ ሳይረጋገጥ የነዳጅ አውጪ አክሲዮን ማሕበር እንደማይመሠረት ሁሉ ለማዳበሪያ ምርት እንደ ዋና ግብዓትነት የሚያገለግሉት እንደ Phosphate rock,sulfur and Ammonia ያሉ ግብአቶች መኖራቸው በጥናት ሳይረጋገጥ ስለ ማዳበሪያ ፋብሪካ አይወራም። እናም በጥድፊያ የተሞላ ፕሮጀክትህ ወደ ብልጽግና ካዝና ስልሳ ቢሊዮን ብር ገቢ ከማድረግ የዘለለ ግብ አይኖረውም። በተረፈ ወገንህን በኢኮኖሚ ለማሳደግ ለምትሠራው በጎ ተግባር ሁሉ ትልቅ አክብሮት አለኝ።

ያልተዘመረላቸው ጀግኖች ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ " " ሰለሞን ገዛኸኝ " " አዲሱ ጌታነህ " " ቤተማርያም አለማየው " " አዲሱ አርጋው " " እታለማው ➔ጭቆናን እና ባርነትን በመቃወም
ያልተዘመረላቸው ጀግኖች ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ " " ሰለሞን ገዛኸኝ " " አዲሱ ጌታነህ " " ቤተማርያም አለማየው " " አዲሱ አርጋው " " እታለማው ➔ጭቆናን እና ባርነትን በመቃወምህ የተነሳ በገዢው ፓርቲ አፋኝ እጆች ተጠፍንገህ ከእስር ቤት ስትወረወር ከቤተሰቦችህ ባልተናነሰ መልኩ ጠያቂ ቤተሰብ ሆነው የምታገኛቸው፤ ➔"ጠበቆች" ከሚለው መጠሪያ ይልቅ "የነጻነት ታጋዮች" የሚለው ሐረግ የሚገልጻቸው፤ ➔ከእስር ቤት በላይ ችሎት ላይ መገኘት እጅግ አሰልች ቢሆነም ዓመቱን ሙሉ ችሎት ላይ የማታጣቸው፤ ➔ማንኛውም የፖለቲካ እስረኛ ያለምንም ክፍያ ጥብቅና የሚያቆማቸው፤ ➔ሕዝባዊ እውቅናም ሆነ ግላዊ ጥቅም በሌለው የትግል መስመር ውስጥ ተሰማርተው ብሎም ለፍትሕ ለሚሟገቱ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች፤ ጸሐፊዎችና ፖለቲከኞች ተሟጋች ሆነው ችሎት ለችሎት መንከራተት የማይደክማቸው፤ . . . ሼር እና ፖስት በማድረግ አክብሮታችንን እንግለጽላቸው።

በገበሬዎች ምናብ ትናንትና ሲታሰብ!! አሳዬ ደርቤ በዘመነ ኢሕአዴግ ለብአዴን አመራሮች እጅግ ከባዱ ተግባር ለማዳበሪያ ግዢ ከፍተኛ የበጀት ድጎማ በማድረጉ የሚታወቀው የግብርና ሚኒስትር ከክልሉ የግዢ ፍላጎት በላይ በሆነ መልኩ በኮታ ደልድሎ በዝቅተኛ ዋጋና በብድር በገፍ የሚልከውን ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ማሠራጨት መቻል ነበረ። የአርሶ አደሩም ቅሬታ "ሁለት ኩንታል ማዳበሪያ ጠይቄ አራት ኩንታል አምጥተው አሸከሙኝ" የሚል ነበረ። ዛሬሳ? ➼ዛሬማ...ግብርና መር ፖሊሲው ቀርቶ "መናፈሻና ፓርክ መር ፖሊሲ" እውን በመሆኑ ምርጥ ዘር በኩንታል ሲከፋፈሉ የኖሩ አርሶ አደሮች በስንት ፍለጋ ከገበያ ያገኙትን ምርጥ ዘር በፍሬ ቆጥረው እየተከፋፈሉ ነው። ➼ዛሬማ..... ከምርምር ጣቢያዎች የሚወጡ ምርጥ ዘሮችን ሲያባዙ የነበሩ የዘር ብዜት ጣቢያዎች ፈርሰው ዘርን መሠረት ባደረገ ጥቃት የሚሳደዱ አርሶ አደሮች የመኸር እርሻቸውን ጥለው መከራቸውን እየበሉ ነው። ➽ዛሬማ....በተፈጥሮ ሐብት ዘመቻ ሲሰሩ የኖሩ የውሃ ማቆር ትሬንቾች ምሽጎች ሆነው ደም እየታቆረባቸው ነው። ➼ዛሬማ... የክልላቸው መንግሥት ቀበሌያቸው ድረስ አጓጉዞ ማዳበሪያ ሲያቀርብላቸው የኖሩ ገበሬዎች ክልል ድረስ ሄደው "የማዳበሪያ ያለህ" እያሉ ነው። ➼ዛሬማ...በመከላከያ ኢንጂነሪንግ የሚመረቱና እንደ ታይሬጀርና BBM ያሉ የተሻሻሉ የእርሻ ቴክኖሎጂዎችን ሲወስዱ የነበሩ አርሶአደሮች በBM እና ሞርታር እየተንገበገቡ ነው። ➼ዛሬማ... ከማሳቸው የተፈናቀሉ፣ በርሐብ አለንጋ የሚቆሉና 'እሕል እሕል' የሚሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች "በመኸር ለሚያመርተው አርሶ አደር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ማቅረብ ያልቻለው መንግሥት በበጋ ያመረተውን ስንዴ Export ማድረጉን ሲያወራ ርሐብ ያደረቀውን ከንፈራቸውን በግርምት ከፍተው "ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ" እያሉ ነው። Share

በቀጣይ ደግሞ ቪላ ቤቶችን አፍርሶ "የጽንፈኞች ማዕከል ስለሆኑ ነው" "ይልኻል። 😁 መስጊዶችስ የፈረሱት ስለምን ይሆን?
በቀጣይ ደግሞ ቪላ ቤቶችን አፍርሶ "የጽንፈኞች ማዕከል ስለሆኑ ነው" "ይልኻል። 😁 መስጊዶችስ የፈረሱት ስለምን ይሆን?

ዶክተር ሐይለ ማሪያም ይባላል። "ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ባለማቅረብ ፥ የአማራ ገበሬዎችን ማስራብ" የሚለውን የብልጽግና ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደርግ ዘንዳ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆኖ የተሾመ
ዶክተር ሐይለ ማሪያም ይባላል። "ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ባለማቅረብ ፥ የአማራ ገበሬዎችን ማስራብ" የሚለውን የብልጽግና ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደርግ ዘንዳ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆኖ የተሾመ ሰው ነው። እናም እንላለን.... "የአማራ ገበሬ ጅራፉን ይዞ እየመጣልህ ስለሆነ ሥልጣንህን አስረክበህ ተሰወር።

photo content

አገዛዙ ቤተክርስቲያንን እና ገዳማትን የሚመዘብረው ሲኖዶሱን ከመዳፉ ውስጥ አስቀምጦ ነው። መስጊድ የሚያፈርሰው መጅሊሱን ተቆጣጥሮ ነው።
አገዛዙ ቤተክርስቲያንን እና ገዳማትን የሚመዘብረው ሲኖዶሱን ከመዳፉ ውስጥ አስቀምጦ ነው። መስጊድ የሚያፈርሰው መጅሊሱን ተቆጣጥሮ ነው።

አቢሲኒያ ባንክ የማይካድራ ቅርንጫፍን በመቀሌ ዲስትሪክት ስር አድርጎ ያወጣው የሥራ ማስታወቂያ...
+1
አቢሲኒያ ባንክ የማይካድራ ቅርንጫፍን በመቀሌ ዲስትሪክት ስር አድርጎ ያወጣው የሥራ ማስታወቂያ...

ጌታቸው ረዳ "ህውሓት ትጥቅ አስረከበ የሚለው ዜና ድራማ መሆኑን.... ጥበብ በተሞላበት መንገድ የአማራን ልዩ ሃይል ማፍረስ መቻሉን... እንዲሁም ባሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ምንም አይነት የተደራጀ
ጌታቸው ረዳ "ህውሓት ትጥቅ አስረከበ የሚለው ዜና ድራማ መሆኑን.... ጥበብ በተሞላበት መንገድ የአማራን ልዩ ሃይል ማፍረስ መቻሉን... እንዲሁም ባሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ምንም አይነት የተደራጀ ሃይል አለመኖሩን..." ተናገረ የሚል መረጃ ሲንሸራሸር እያየሁ ነው። እኔ ግን እላለሁኝ... የአማራ ልዩ-ሃይልን ያፈረሰው ብአዴን የተባለ ጸረ ሕዝብ ድርጅት እንጂ የጌታቸው ረዳ ጥበብ አይደለም። ፋኖን በከባድ መሣሪያ የሚያስደበድበውም የኦነግ ቅጥረኛ የሆነው የብአዴን አመራር እንጂ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስላልሆነ የዶክተር ይልቃል ካድሬ በክልሉ ሕዝብ ሕልውና ላይ የፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት ነጥቆ ጌታቸው ረዳ ማቅራራቱ ልክ አይደለም። በተረፈ ልዩ ሃይል ሲበተን ሕዝባዊ ሃይል እንደሚወለድ አያጠራጥርም።