ፍኖተ-ሎዛ መዝሙር
前往频道在 Telegram
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዓለምገና ደ/ሲ/ቅ/ኪ/ምሕረት ቤ/ክ ፍኖተ-ሎዛ ሰ/ት/ቤት የመዝሙር ክፍል የቴሌግራም ገጽ ነው ሀሳብ ፣ አስተያየት ፣ ጥያቄ ካሎት በዚህ ያድርሱን👇 @Fenotelozaaaaa_bot
显示更多1 461
订阅者
无数据24 小时
+17 天
-430 天
帖子存档
1 459
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ማስታወሻ🗣
⭐️አርብ (03/11/18) የመዝሙር ጥናት መርኃ ግብር የሚቀጥል ሲሆን 11:00 እንድንገኝ ይሁን
ሰናይ ጊዜ
1 459
684. ግበር ታቦተ
ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኀግበር ታቦተ በዘትድኅን /2/
ትርጉም፡- ሥላሴ ኖህን የምትድንበትን ታቦት (መርኅ) መርከብ ሥራ አሉት
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 ( አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: ምድብ ማርቆስ (ሐዋርያተ ሰላም)
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት684. ግበር ታቦተ 685. በጸሎቱ ለኖኅ 686. ወጽአ እምድረ ካራን 688. ሰላም ዘአብ 689. እንዘ ይብሉ 690. አአትብ ወእትነሳእ 691. ስብሐት ለሥላሴ 692. በመምሬ አድባር ስር
1 459
683. ጴጥሮስኒ ወጳውሎስ (0:00)
ጴጥሮስኒ ወጳውሎስ ጸንዑ በእምነቶሙ
ወበእምነቶሙ /3/ ወረሱ መንግሥተ ሰማያት
ትርጉም፡- ጴጥሮስና ጳውሎስ በዕምነታቸው ጸንተው መንግስተ ሰማያትን ወረሱ
893. ድንቅ ነው (1:00)
ድንቅ ነው ልዩ ነው ልዑል የእኛ ጌታ
ምስጋና ይድረሰው ከጧት እስከ ማታ
የማይመረመር በሰው ልጅ ኅሊና
ረቂቅ ባህርይ ገናና ነውና
ያለ የነበረ ከዘመናት በፊት
ለዘለዓለም ኗሪ ፈጣሪ ዓለማት
በፍጥረታት ሁሉ የሚመሰገነው
ኃያሉ ጌታችን በእውነት ግሩም ነው
በፍጹም ልዩ ነው የእርሱ ጌትነቱ
አልፋና ዖሜጋ ጽኑ ነው መንግሥቱ
በመላእክት ዓለም በሰማይ ከተማ
ለክብሩ ሲዘመር ማኅሌት ሲሰማ
ያለምንም እረፍት በቀንና ሌሊት
ንጹሐን መላእክት የሚያመሰግኑት
አዳምን ለማዳን ፍጹም በመውደዱ
የማይሞተው አምላክ ሞተ በፈቃዱ
ምስጢሩ ረቂቅ ነው ለሰዎች አዕምሮ
ፍቅሩ ያስደንቃል ስናየው በአንክሮ
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 ( አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: ሐረገ ወይን (ያርኁ ክረምተ፣ የወደደኝ ጌታ)
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት667. በመንፈስ የሐውር 668. ወአንተኒ ሕፃን 669. ምን ሰማህ ዮሐንስ 677. እስመ አሐዱ 679. ከዋው እገሪሆሙ 683. ጴጥሮስኒ ወጳውሎስ 893. ድንቅ ነው 932. የወደደኝ ጌታ
1 459
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
⭐️የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት እንኳን በደህና መጣችሁ እያልን በመደበኛ የዝማሬ ጥናት እንድትገኙ እንዲሁም የአገልግሎት ምድባችሁን በመጠየቅ አገልግሎታችሁን እንድትቀጥሉ ይሁን
ሰናይ ጊዜ
1 459
672. ሕዝብ ቅዱሳን (0:00)
ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተ ክርስቲያን
ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ትርጉም፡- የክርስቲያን ህዝቦች የቤተክርስቲያን ምሰሶዎች የተከበሩ ሐዋርያት ጴጥሮስ እና ጳውሎስ የብርሃን ልጆች ብለው ሰየሟቸው።
674. ሚ መጠን (1:00)
ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ ለኢየሩሳሌም
እምደመ ጳውሎስ ሐዋርያ እስከ ደመ ጴጥሮስ ወልደ ዮና /2/
ትርጉም፡- ከቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ እና ከዮና ልጅ ጴጥሮስ በኢየሩሳሌም ላይ ምን ያህል ደም ፈሰሰ።
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 ( አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: ማኅደረ ስብሐት (ሐነጽዋ)
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት665. ሰርዐ ሰንበተ 666. ያርኁ ክረምተ 672. ሕዝብ ቅዱሳን 674. ሚ መጠን 894. ማን እንደ እርሱ 920. እናመስግነው ጌታችንን 930. አማኑኤል ናና
1 459
ዝማሜ ዘነሐሴ ኪዳነ ምሕረት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ
እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤
ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ፤
ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤
ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ
ትርጉም:
(መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት)
ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ማኅደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሰማእት ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኩልነ ኀበ ማርያም እምነ
አመላለስ
ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ ፤
በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ
1 459
650. እስመ ኪያሆሙ (0:00)
እስመ ኪያሆሙ ብነ እለ ይጸልዩ በእንቲአነ
አባ ገሪማ ወአባ ይምዓታ ብነ ቅዱሳን
ትርጉም:- በፈጣሪ ፊት ቆመው ስለ እኛ የሚጸልዩ የእኛ ቅዱሳን አባቶቻችን አባ ገሪማ እና አባ ይምአታ ናቸው፡፡
655. ይትባረክ እግዚአብሔር (2:15)
ይትባረክ እግዚአብሔር /2/
ዘአልዓላ ለጽዮን አምኲሉ ዓለማት /2/
ትርጉም፡- ጽዮንን ከዓለማት ሁሉ በላይ ከፍ ያደረጋት እግዚአብሔር ይባረክ፡፡
657. ሕንፄሃ አዳም (4:17)
ሕንፄሃ አዳም /2/ ሕንፄሃ ቤተክርስቲያን
ሐመልማለ ወርቅ /2/ ገበዋቲሃ ሐመልማለ ወርቅ
ትርጉም፡- የቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ የሚያምር ዙሪያዋም የወርቅ ሐመልማል ነው።
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 ( አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: አንቀጸ ብርሃን (ወደ ቤተ እግዚአብሔር)
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት648. ጸሎትከ ትባርከኒ 650. እስመ ኪያሆሙ 652. ለቤተ ክርስቲያን 653. ተቀደሲ 654. ለዛቲ ቤት 655. ይትባረክ እግዚአብሔር 657. ሕንፄሃ አዳም 658. ሐነጽዋ 885. በልዑል መጠጊያ 899. ሳይገባኝ አምላክ
1 459
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
ማስታወሻ🗣
⭐️ፈተና ያልተፈተናችሁ አባላት እሑድ (07/10/18) ጠዋት ፈተና የሚኖራችሁ ይሆናል
⭐️ነገ ሐሙስ (04/10/18) ወርኃዊ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ የሰርክ ጉባኤ አገልግሎት በአንቀጸ ብርሃን አባላት የሚሸፈን ሲሆን በጊዜ እንድንገኝ ይሁን
ዝማሬ: (እልል በሉ ፣ ሰአል ወጸሊ)
ማሳሰቢያ💥
⚡️ስማችሁ ከላይ የተጠቀሰ አባላት በግንቦት ወር በነበሩ የጥናት እና የአገልግሎት ቀናት በተገቢው መንገድ ያልተገኛችሁ ሲሆን ከቅዳሜ 06/04/18 እስከ እሑድ 07/04/18 በአካል በመቅረብ የቀራችሁበትን ምክንያት እንድታስረዱ ፤ ማስጠንቀቂያ እንድትወስዱ ይሁን፡፡
1 459
645. አመ ይሰቅልዎ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ
ትርጉም፡- አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ጊዜ ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤልም ተደነቀ
775. ነዐ ሚካኤል
ነዐ/2/ ሚካኤል ማዕከሌነ ቁም
በበዓልከ ባርከነ/2/ ዮም
ትርጉም: ና ሚካኤል በመሀከላችን ቁም ዛሬ በበዓልህ ባርከን
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 ( አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: ሐረገወይን (እኔስ እዘምራለው)
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት645. አመ ይሰቅልዎ 646. ባሕራንኒ ይቤ 647. ፈተና ቢገጥማት 756. ሚካኤል ወገብርኤል 758. ከመ ትባርከነ 759. ዓይኑ ዘርግብ 762. ተወከፍ ጸሎተነ 763. መልአከ ሰላምነ 765. ሀበነ ሰላመከ 770. ሰአል ወጸሊ 771. ረዳኤ ምንዱባን 773. ተወከፍ ጸሎተነ 775. ነዐ ሚካኤል 933. ዘምር ዘምር አለኝ 934. ወዶናልና
1 459
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
ማስታወሻ🗣
⭐️ከላይ የተያያዘው የተስተካከለ የአገልግሎት ምድብ ሲሆን አባላት በተመደባችሁበት ምድብ እንድታገለግሉ ይሁን
⭐️በምድብ ያልተካተታችሁ አባላት መዝሙር ክፍሉን እንድታናግሩ ይሁን
የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
1 459
677. እስመ አሐዱ
እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘተሰውጠ ላዕለ ሐዋርያት
በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኩሉ በሐውርት በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ
ትርጉም፡-በሐዋርያት ላይ የተዋሓደው
መንፈስቅዱስ አንድ ነውና
679. ከዋው እገሪሆሙ
ከዋው እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ
ዘእግዚአብሔር ፈነዎ /2/ ይነግር ቃለ እግዚአብሔር
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 (አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: ማርቆስ ምድብ
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት670. ሐዋርያተ ሰላም 675. ስምዖን ጴጥሮስ 676. ትዕግሥቶሙ 677. እስመ አሐዱ 678. እስመ ዝንቱ 679. ከዋው እገሪሆሙ 681. ውስተ ኩሉ ምድር 926. ተመስገን ጌታዬ 927. በምን ደስ ላሰኝህ 928. እኔስ እዘምራለሁ ለሥላሴ 929. ቸርነትህ ነው 931. በዘባነ ኪሩብ
1 459
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
ማስታወሻ🗣
⭐️ቅዳሜ በ22/09/18 10:00 የጽሁፍ ፈተና የሚኖረን ሲሆን ተዘጋጅተን በሰዓቱ እንድንመጣ ይሁን
⭐️ ፈተናውን ለመፈተን ያልተመዘገባችሁ አባላት እስከ ሐሙስ ማታ ድረስ ስማችሁን በ @Fenotelozaaaaa_bot ምዝገባ የሚለውን በመጫን እንድትልኩ ይሁን
⭐️በፈተናው ቀን መገኘት የማትችሉ አባላት ከወዲሁ እንድታሳውቁ ይሁን
ሰናይ ጊዜ
1 459
920. እናመስግነው ጌታችንን (0:00)
እናመስግነው /2/ ጌታችንን እንደ ቅዱስ ዳዊት /2/
መንፈስ ቅዱስ ይቃኘን /2/ ያስተምረን
አምላካችን እንደ ቅዱስ ዳዊት /2/
እናመስግነው /2/ ጌታችንን እንደ አባቶቻችን/2/
መንፈስ ቅዱስ ይቃኘን /2/ ያስተምረን /3/
አምላካችን እንደ አባቶቻችን /2/
930. አማኑኤል ናና (3:25)
አማኑኤል ናና መድኃኔዓለም ናና አማኑኤል ናና
በቀኝህ ለመቆም እንሻለንና አማኑኤል ናና
እግዚአብሔር አምላክ አማኑኤል ናና
በገሀድ ይመጣል መድኃኔዓለም ናና
የሚያቃጥል እሳት አማኑኤል ናና
በፊቱ ይነዳል መድኃኔዓለም ናና
ፍሬ እና ገለባን አማኑኤል ናና
በሥልጣኑ ይለያል መድኃኔዓለም ናና
ጌታ ሰትመጣ አማኑኤል ናና
በሚያስፈራ ግርማ መድኃኔዓለም ናና
መላእክት ሲነጉዱ አማኑኤል ናና
ከሰማይ ከራማ መድኃኔዓለም ናና
ማነው የሚቆመው አማኑኤል ናና
ከጻድቃን ከተማ መድኃኔዓለም ናና
ለአንተ የሚያስደስት አማኑኤል ናና
ምግባርን ሳልሰራ መድኃኔዓለም ናና
ምን ትመልስ ይሆን አማኑኤል ናና
ነፍሴ ስትጠራ መድኃኔዓለም ናና
ኰናኔው በርትዕ ነህ አማኑኤል ናና
ፈታሄ በጽድቅ መድኃኔዓለም ናና
ባለፀጋ ድሀ አማኑኤል ናና
ብለህ የማትንቅ መድኃኔዓለም ናና
ቸርነትህ ይርዳኝ አማኑኤል ናና
ሲዖል እንዳልወድቅ መድኃኔዓለም ናና
ትናፍቀኛለች አማኑኤል ናና
መንግሥተ ሰማያት መድኃኔዓለም ናና
ዘለዓለም በሙሉ አማኑኤል ናና
ሰላም ያለባት መድኃኔዓለም ናና
ከእመብርሀን ጋር አማኑኤል ናና
የምኖርባት መድኃኔዓለም ናና
@fenotelozaaaa
@fenotelozaaaa
@Fenotelozaaaaa_bot
1 459
የዚህ ሳምንት ጥናትቅዳሜ 10:00-12:00 (አዳራሽ) እሑድ 5:00-6:00 (አዳራሽ) የሰንበት አገልግሎት: ሰራተኛ ጉባኤ (ዝናው በዓለም፣ መንፈስ ቅዱስ)
በዚህ ሳምንት የሚጠኑ መዝሙራት659. መንፈስ ቅዱስ ወረደ 660. በትፍሥሕት 661. ዘአጽናእኮሙ 662. ጰራቅሊጦስሃ 918. የኃያላን ኃያል 920. እናመስግነው ጌታችንን 923. ምስጉን ነው 924. አስፈሪው ነበልባል 925. ኃይሌ ብርታቴ 930. አማኑኤል ናና
