2 130
订阅者
-124 小时
-17 天
+330 天
帖子存档
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ጉዳዩ፡- የክረምት ማጠናከሪያ ት/ት (SummerTutorial class) ይመለከታል፤ ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ት/ት ከሐምሌ 6/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 አምስት ክ/ጊዜ የሚማሩ ሲሆን በፕሮግራሙ ውስጥ ሁሉንም ተማሪዎች በማካተት ከመደበኛው የት/ት ይዘት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የተከታታይ የሶስት የክፍል ደረጃዎችን ትምህርት በጥልቀት በመስጠት፣ የተለያዩ የሀገር አቀፍ ፈተናና ሞዴል ጥያቄዎችን በመስራት በቂ ዕውቀት፣ ክህሎት እና ግንዛቤ በመፍጠር ለቀጣይ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) በቂ ዝግጅት አድርገው እንዲቀርቡ እና ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ታስቦ የተዘጋጀ ፕሮግራም መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በፕሮግራሙ የሚሰጠው የት/ት አይነትለNatural Science ተማሪዎች English, Maths, Physics, Chemistry, Biology and Scholastic Aptitude test (SAT) ለSocial science ተማሪዎች English, Maths, History, Geography, Economics, and (SAT) ይሆናል፡፡ ማሳሰቢያ፡- ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክረምት ት/ት መርሃ ግብሩ በክላስተር የተመደቡ ቀራኒዮ መድሐኒያለም ቁ-1 ት/ቤት እና በት/ቤት ለተመደቡ በሬነሳንስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሁሉም ግዴታ መሆኑን የአ.አ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በላከው የአፈፃፀም መመሪያ ላይ የተገለፀልን በመሆኑ ውድ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎቹን በወቅቱ ወደ ት/ቤት እንድትልኩ እያሳወቅን ከሐምሌ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ክረምት ት/ቱ የማይመጣ ተማሪ ካለ ለመደበኛው ትምህርት መመዝገብ እንደማይችል ት/ቢሮ እና ተማሪው ት/ቤት ለመቀየር ፈልጎ እንኳን መሸኛ ቢጠይቅ የማይሰጠው መሆኑን አሳውቆናል፡፡ በመሆኑም ከሰኞ ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ልጆዎትን ወደ ፕሮግራሙ እንዲልኩ እንገልፃለን፡፡ - የክረምት ት/ት የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡ - ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመጡ አስፈላጊውን የት/ት ግብዓት በማሟላት የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው እና የት/ቤት መታወቂያ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ት/ቤቱ
2 130
🎉🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አለን ፤ ደስ አላችሁ 🎉🎉🎉🎉
የሬነሳንስ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም የክልል አቀፍ የ6ተኛ እና የ8ተኛ ክፍል ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ (100%) ማሳለፉን በደስታ እንገልፃለን!
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ12ተኛ ክፍል ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ቅዳሜ ሐምሌ 4/2018 የፈተና ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ ጠዋት 2፡00 ሰዓት የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሳችሁ የት/ቤት እና የፋይዳ መታወቂያ የዛችሁ በሬነሳንስ ት/ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
2 130
Renaissance School Kindergarten Graduation Event
🎓 Congratulations to this year’s graduates! 🎉
2 130
🎉🎉🎉 እንኳን ለ 2018 ዓ/ም የት/ት ማጠናቀቂያ የወላ ጆች ቀን አደረሳችሁ! 🎉🎉🎉* ቅዳሜ ሰኔ 27/2018 ዓ/ም የቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች ምርቃት ይሆናል። * እሁድ ሰኔ 28/2018 ዓ/ም የወላጆች ቀን ክብረ በዓል እና የተማሪዎች ሪፖርት ካርድ መስጫ ዕለት በመሆኑ ወላጆች ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ በሬነሳንስ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲገኙ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:- እሁድ ሰኔ 28/2018 ዓ/ም በት/ቤቱ መገኘት ያለባቸው ወላጆች እና ተሸላሚ ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሁሉም ወላጅ በአካል በመገኘት የልጆቹን ውጤት እንዲወስድ እንገልፃለን::
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ12ተኛ ክፍል የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ነገ አርብ(26/10/2018) ሁለተኛ ዙር ESSLCE ፈተና ሰለሚጀምር ጠዋት 1፡20 የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሳችሁ የት/ቤት እና የፋይዳ መታወቂያ ፤ አድሚሽን ካርድ ይዛችሁ በሬነሳንስ ት/ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ12ተኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ሰኞ(22/10/2018) 7፡00 ሰዓት የፈተና ኦረንቴሽን አይኖርም። ኦረንቴሽኑ የሚሰጥበትን ጊዜ እዚሁ እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኞ(22/10/2018) የፈተና ኦረንቴሽን ስ ጠዋት 1፡30 1ኛ እና 2ኛ ዙር የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ፤ ከሰዓት 7፡00 የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሳችሁ የት/ቤት እና የፋይዳ መታወቂያ የዛችሁ በሬነሳንስ ት/ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን። ት/ቤቱ
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች የESSLCE Mock Exam ለውጥ ስለተደረገ ዛሬ አርብ(19/10/2018) ጠዋት 3፡30 የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ፤ ከሰዓት 7፡00 የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሳችሁ የት/ቤት እና የፋይዳ መታወቂያ የዛችሁ በሬነሳንስ ት/ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለ12ተኛ A ክፍል ተማሪዎች ነገ አርብ(19/10/2018) የESSLCE Mock Exam በቢኮሎስ ት/ቤት ስለምትወስዱ 7፡00 ሰዓት ላይ የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሳችሁ የት/ቤት እና የፋይዳ መታወቂያ የዛችሁ በሬነሳንስ ት/ቤት ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለተማሪ ወላጆች ነገ ሐሙስ(17/10/2018) የ አራተኛ ዕሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ስለሚሰጥ ተማሪዎች የ ት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሰው 2:30 - 6:00 ሰዓት ውጤታቸውን መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ
2 130
ሬነሳንስ ት/ቤት አዲስ አበባለተማሪ ወላጆች ነገ ሐሙስ(17/10/2018) የ አራተኛ ዕሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ስለሚሰጥ ተማሪዎች የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሰው 2:30 - 6:00 ሰት ውጤታቸውን መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ
2 130
Repost from Berbir Mereja / በርብር መረጃ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ ይሰጣል‼️
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
📌የተፈጥሮ ሳይንስ፡ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 3 ቀን (306,708 ተማሪዎች)
📌የማኅበራዊ ሳይንስ:- ከሐምሌ 6 እስከ ሐምሌ 16 ቀን (257,150 ተማሪዎች)
በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሐረር ሙሉ በሙሉ በኦንላይን (በኢንተርኔት) ይሰጣል።
በሌላ በኩል ከሰኔ 4 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ከ224 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በ88 ማዕከላት እየተሰጠ ይገኛል።
ለአጠቃላይ ፈተናዎቹ ከ600 በላይ ማዕከላት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጾ፤ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተአሳስቧል።
@berbirmereja
@berbirmereja
