💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
前往频道在 Telegram
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot
显示更多📈 Telegram 频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 的分析概览
频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 941 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 175,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 492 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 941 名订阅者。
根据 10 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -126,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.92%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 338 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله
ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot”
凭借高频更新(最新数据采集于 11 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
13 941
订阅者
无数据24 小时
-427 天
-12630 天
帖子存档
በጣም ደስ የሚል ሀቂቃ ኮንቦልቻ ሲባል በአህባሽ ነበረ የምትታወቅ እንዲህ ያለ ሲሰማ በጣም ነዉ ደስ የሚል እዛ ያላችሁ በሉ መሻይኾችን እየሄዳችሁ ተጠቀሙባቸዉ ትልቅ እድል ነዉ የመጣላችሁ። የሰለፍያ መሻይኾች አላህ ያብዛቸዉ። ወጣቶች ንቁ ጠንክራችሁ ቅሩ። እናንተ ከጠነከራችሁ ብዙ የመቀየር ሀይል ይኖራል ቢድዐ ይጠፋል ሱና ይበራል። በርቱ እናንተ ሰበቡ እርሱ አላህ ይረዳችኋል !
=
አንዳንዴ ሳንፈልግ የግድ የሚያስቁን አሉ እኮ ....
የምርም በጣም ነዉ እንዴ ቡለኑ የላላዉ ?
በጣም ነው እንዴ ቡለኑ የላላው!!
ምን ቢቀምስ ነው እንዲህ የሚተረተረው? ብዙ የአእምሮ እክል አጋጥሞት ይሆን እንዴ? በጣም ጉዳት ደርሶብሃል እንዴ?
አሏሁል ሙስተአን!
አቡ ኡበይዳ
t.me/AbuOubeida
አንድ ሴት ከአንድ ወንድ ጋር ተዋወኩ ብላ፡ገና እውነተኝነቱ ላልታመነበት ትዳር ይሄን ያክል ዋጋ ትክፍላለች፡ይሄን ያክል ዝንጉነትና ቡልሃነት ያጠቃታል ብየ አላምንም ነበር፡በዚህ ልክ ተላላ መሆናቸውን ገና ዘግይቶ ነው የገባኝ።ሰው እንዴት፡ውጭ ሀገርን የሚያክል ነገር ስንት ዋጋ ከፍሎበት የቆረጠውን ሀገር ላልታመነበት ሒወት ሓላል ላልሆነ ትዳር እንዴት ስራ አበላሽቶ ይመጣል? ሰው እንዴት ትምህርት ብሎ ቀየውንና ሰፈሩን ለቆ ከሄደበት ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ዋልጌ ወንድ ብሎ ከትምሀርት ይሰናከላል? እንዴት እንደ ቀላል ቤተሰቡ ዋጋ የከፈለበትን ነገር በቀላል አፈርድሚ ያበላል።ያውም ለማይታሰር ትዳር ተጨባጭ ለሌለው?! አሏሁል ሙስተአን አረ አላህ ፍሩ!
አቡ ኡበይዳ
t.me/AbuOubeida
إِنَّا كُنَّا مِنْ قَبْلُ نَدْعُوهُ إِنَّهُ هُوَ الْبَرُّ الرَّحِيمُ
╭┈──── ••⇣⇣
╰┈➢
ተዉእንጅ ወንዶችዬ ሴቶች አትፈትኑ ተከናነቡ ትሉናላችሁ ማነዉ ወንድ ብቻ ይፈተናል ያለዉ እናንተም በልክ አድርጉት ወደ ዉጭ ስትሄዱ መቆነጃጀቱን ..... እንተዛዘን¡ በተለይ የሱና... ፂማችሁ በጠር ጀለብያችሁ አጠር ከዛ ጥምጣማችሁ ጣል አድርጋችሁ ሽቶ ረጨት አድርጋችሁ.....ተዋ በልክ ይሁን እንተዛዘን ማለቴ ነዉ¡ ጠብቁን እንጠብቃችሁ 🖐
#አማን ያሳድራችሁ
=
~
ከምንም ከማንም በፊት የዉስጥ ሰላማችሁን ጠብቁ ዉስጥ ሰላም ከሆነ ሁሉም ሰላም ነዉ። ዉስጣችሁ ላይ የሚረብሽ ነገር አታስቀምጡ ቶሎ አስወግዱት !
#የዉስጥ ሰላማችሁ ይብዛ
=🔴 👉ቀጥታ ስርጭት ኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➡️
ደስተኛ ህይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች...!!
🎙በአቡ ሒበቲላህ ሁሰይን
ተ
ጀ
መ
ረ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestreamRepost from قَنَاةُ بَصْمَة سَلَفيّة
ሌሎችን ማወቃችሁ ብልሕነት ነው፧
እራስን ማወቅ እውነተኛ ጥበብ ነው፤
እራስን ማስተዋል የራስን ሀይል ለመገንዘብ እና ሠዎችን ለመረዳት ትልቅ ጥንካሬ ይሠጣል።
||
t.me/Basmat_Salafiya1
ከጅንጅን አለም ሰላም የሆናችሁ አላህን አመስግኑ! ጅንጅን እንቅልፍ አሳጥቷል ፣ ምግብ ከልክሏል ፣ ቤተሰብ አርቋል፣ጓደኛ አርቋል! ትልቁ ክስረት ከአላህ አርቋል...እና ከዚህ ሙሲባ የተጠበቃችሁ አላህን አመስጎኑ ! በዚህ በሺታ የተጠመዳችሁ አላህ ያሺራችሁ ወደ እራሳችሁ ይመልሳችሁ !
#ዘወር ዘወር ስንል ከታዘብነዉ ተሟጨረ¡
=
Repost from 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
አልቻልንበትም እንጂ አንዳንዴ ከሰው መገለል ( መልካም ስራዎችን ከመስራት ጋር ) ቀልብን ከሚያለሰልሱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው !!!
https://t.me/Muhammedsirage
👉ቁጥብ ጥንቁቅ እህቶቼን አይመለከትም!!
#ከልክ_አትለፉ__!!
---------------------------
የወንድን ልጅ ጉድለት የሞላች በሀሴት፡
አይናፋር የሆነች እርሷ ናት ቁጥብ ሴት።
በኒቃቧ አጊጣ በመንሀጅ የፀናች፡
ምክሯ ሰበብ ሆኖ ብዙ ሰው ያቀናች፡
ሁሉ የሚያከብራት በፀባይ በእምነቷ፡
ከሩቁ የሚታይ አይናፋርነቷ፡
ይህች አይነቷ እህቴ ወደት ተሰወረች!?
በኒቃብ ተውባ እዚህ አልነበረች!?
ማን ምን አላትና እንድህ ሆና ቀረች!?
#ኸረ_እህቶቻችን_!!
--------------------------------------------
ስቶዱም ስትጠሉም ከልክ አትለፉ፡
በሌለበት ነገር ሰውን አትዝለፉ፡
ወረት አትልመዱ ሁሉን አትልከፉ፡
የዋሆችን ሁሉ አታድርጉ ክፉ፡
-----------------------------------
ስቶዱ አደብ የለ ይዛችሁ ልቀቁኝ፡
ስጠሉ አቅል ማጣት በገመድ እነቁኝ፡
እጅግ ስትረብሹ ይዘው ሲለቋችሁ፡
ለሰው ሰላም አይሰጥ ይሔ ምላሳችሁ፡
ስትጠሉ
ለአስተሳሰባችሁ መርህ አብጁለት፡
ቅርፅ አትቀያይሩ ሁልጊዜ እለት ከእለት፡
ሞትኩልህ ሔድኩልህ ብለሽ ሳትጨርሽ፡
እስኪ ተረጋጊ ኪዳን አታፍርሽ፡
ሚስቱ መሆንሽን ፈፅመሽ ሳትርሽ፡
ተጣላን ተያለሽ በተራ አሉባልታ፡
ከዚያም ረስተሽው ያን ሁሉ ውለታ፡
ስሙን ታጠፋለች በሚዲያ መጥታ፡
ነገር ትሰካለች ለላይክ ፍጆታ፡
ስቶዱ ቸኳላ ያዙኝ ልቀቁኝ ባይ፡
ስትጠሉ መዋሸት ያውም ባደባባይ፡
እንድህ አትሁኑ እጂጉን ያስጠላል፡
ግርማ ሞገሳችሁ ይወርዳል ይቀላል፡
---------------------------------------
ስትወዱ ምክንያት ሰበብ ይኑራችሁ፡
ስትጠሉ በወጉ ሁኑ አስተንትናችሁ፡
ለምን ከዚያ ከዚህ ትጣደፋላችሁ!?
#ለምንስ_ሌሎቹን_ታሰድባላችሁ!?
አቦ ተረጋጉ ስርዐት ይኑራችሁ!?
👉#ስትወዱ__!!
እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ዘመን ሲያልፉ፡
ድንግል ነበር ልቤ ያልተገኘ ቁልፉ፡
ለመውደድ ለፍቅር በሩን ያልከፈተ፡
ከማንም ወንድ ጋር ያልተከላፈተ፡
በሀሳብ በናፍቆት እሩቅ ያልዘመተ፡
ወዶ ያልተጎዳ ያልተቆራመተ፡
እንደዚህ ብላችሁ ስትፅፉ ከርማችሁ፡
በስምንተኛው ቀን ከተለያያችሁ!?
ልክ እንደ አባት ገዳይ ትፋለማላችሁ!?
#እንዴ_ምንድን_ነው?
ትዳር ፍቅር ማለት ምላስኮ አይደለም፡
ትልቅ ቃል ኪዳን ነው ለመኖር ዘላለም፡
በናንተ ምክንያት ትዳር ጠላንኮ፡
በስንቱ እንፈተን ስንቱ ሆኖን ታኮ፡
ያኔኮ ስቶጂው የግሉ ሲያደርግሽ፡
እንዲያ ስትፈልጊው እሱም ሲፈልግሽ፡
ነፃ ነበር ውስጤ አየር ብቻ ያለው፡
ፍቅር አረገዘ ዘንድሮ ላይችለው!?
ልቤ ነበረኮ ሀሳብ የለሽ ጀግና፡
ዛሬ ተሸነፍኩኝ በዛ ልጅ ቁንጅና፡
ብለሽ ብዙ አውርተሽ ለወዳጅ ለጠላት፡
በሰባተኛው ቀን በነገር መባላት፡
ይህ የበሽታ እንጂ የሰላም አይደለም፡
ነገ ልንፋታ ብሎ ትዳር የለም፡
👉#ኸረ_ይደብራል...!!
የታየውን ሁሉ በመንጋ ስቶዱ፡
ደግሞ ወረቱ ሲያልቅ በበደል ስትፈርዱ፡
ሰቅላችሁ ከጣራ ብላችሁ ሞትኩለት፡
ስትፅፉ ዘወትር ስትሉን ሔድኩለት፡
ሀላሌ ብላችሁ ፕሮፋይል መስቀል፡
አርማ ማዘጋጀት መትከልና መንቀል፡
------------------------------------------
ልባችን በፍቅር ፈፅሞ አልተቃኘም፡
ለሱ ነበር እንጂ ለሌላ አልተሞኘም፡
ከርሱ በቀርኮ ወንድን አልተመኘም!!
ልቤ ነበርኮ በፍቅር ያልተቦካ፡
ውስጡ ያልተቃኘ ምንም ያልተነካ፡
ሰው ወዶ የማያውቅ ጭራሽ ያልተለካ፡
በህይወት ዘመኑ ወንድን ያልወደደ፡
በናፍቆት ተጉዞ ርቆ ያልሔደ፡
ለርሱ ግን ተገዝቶ በፍቅር አበደ፡
ይህንን ባላችሁ በሶስተኛው ማግስት፡
ፍቅራችሁ አብቅቶ መቀየር እንደስስት!!
---------------------------------------------
ወደድኩት የኔ ነው እንደናት አባቴ፡
እርሱ ነው ከንግድህ ወንድምም እህቴ፡
እንደዚህ ብላችሁ በአለም አደባባይ፡
ስትለዩ ደግሞ አንተም ባይ እኔም ባይ፡
ከሰአት በኋላ ሁላችሁም ዋይዋይ!!
አልገባንምኮ ምንድን ነው ነገሩ፡
ትዳር ረከሰ ጠፋብን ሚስጥሩ!!?
#ስቶዱ__!!
ልቤ ግንድ ነበር ልብሱ ያልተላጠ፡
ለናፍቆት ሰጠብኝ ሲያየው ደነገጠ፡
ማንነቱን ሁሉ መክፈቻውን ሰጠ፡
ልቤ ቢክራ ነበር ውስጡ ያልተቃኘ፡
አልሀምዱ ሊላሒ ዛሬ አንተን አገኘ፡
አልፈልግም ፍጥረት ወንድ ካንተ ሌላ፡
በቃኝ በቃ እንግድህ ቃልና መሐላ፡
እንደዚህ ብላችሁ ወሬውን ሳንጠግብ፡
በሚዲያው አለም ሆነሽለት እርግብ፡
ገንዘብ አልፈልግም መንሀጅ ነው መስፈርቴ፡
አይዞህ ሀላሌ እምነትህ ነው ሀብቴ፡
ብለሽ ብዙ አውርተሽ ካፍሽ ሳታበቂ፡
ድጋሜ አቋም ቀየርሽ እንደ ጠጣ አረቂ፡
-----------------------------------------------
ስቶዱ ለፍቅር ድንበር ገድቡለት፡
በመጠኑ ይሁን እስከሚለይለት፡
ስትጣሉ ደግሞ የሌለ አትፍጠሩ፡
ፊትና ለማራገብ ዘበኛ አትቅጠሩ፡
እስኪ በልክ ይሁን ፍቅር ጥላቻችሁ፡
ለፈራጅ ቸገረን ግሩም ሁኔታችሁ፡
ውደታ ጥላቻን በውስጣችሁ ያዙት፡
ከሀያዕ አትራቁ መርከሱን አታብዙት፡
-----------------------------------------
በየሚዲያው ላይ ብሶትን መናገር፡
የግል ወሬወችን ተራ ርካሽ ነገር፡
ያለ የሌለውን መቀበጣጠሩ፡
ወዶ ጠላኝ ብሎ ቂምን መቋጠሩ፡
ለቀጣህ ህይወትሽ አደጋ ስላለው፡
እስኪ ዝም በሉ እሱ ነው ሚሻለው፡
ኮሽ ባለ ቁጥር ሰውን አትዝለፉ፡
ስቶዱም ስትጠሉም ከልክ አትለፉ፡
--------------------------------------------
✍️በኑረዲን አል አረቢ
-------------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
أغيثوا قلوبكم بذكر الله، ولا تَحبسوا عنها ماء الحياة: (سبحان الله، والحمد لله، ولا إله إلَّا الله، والله أكبر).
#تغريد_العصيمي
