💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
前往频道在 Telegram
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot
显示更多📈 Telegram 频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 的分析概览
频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 942 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 175,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 492 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 942 名订阅者。
根据 10 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -126,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.92%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 338 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله
ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot”
凭借高频更新(最新数据采集于 11 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
13 942
订阅者
无数据24 小时
-427 天
-12630 天
帖子存档
Repost from Abu Useymin (أبو عثيمين ابن شافي )Channel
ብር እየሰጣችሁ ወንዶችን አታቅብጡ🙌
ፍቅር እንጂ ብር አትስጡ! ሰርቶ ያስተዳድርሽ እመወይ ስሚ!🙌
=
🔴አሁን በቀጥታ ስርጭት
📚 የአልወሳኢሉል አል ሙፊዳ ሊልሀያቲ ሰኢዳ ኪታብ
ሊ
ጀ
መ
ር
ነው
ገባ ገባ በሉ ባረከሏህ ፊኩም
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestream
🔴አሁን በቀጥታ ስርጭት
📚 የአልወሳኢሉል አል ሙፊዳ ሊልሀያቲ ሰኢዳ ኪታብ
ሊ
ጀ
መ
ር
ነው
ገባ ገባ በሉ ባረከሏህ ፊኩም
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestream=f9076a5de6691d389f
👉ለሸይኽ አወል እና ለዑስታዝ ኸድር ከሚሴ ሀፊዞሁሙሏህ
«አንበሳ እና ነብሩ»
----------------------
ፈጥነው እንደ ሌሎች ክፉ አይናገሩም ፡
የኔን ብቻ የሚል ሙሪድ አያፈሩም፡
ዕውቀት ፍለጋ እንጅ ከቶ ፊትና አይመሩም፡
በማንም ላይ ቢሆን በደልን አይሰሩም፡
የፊትና አራጋቢ ውርጋጥ አይቀጥሩም፡
እኔን ተከተሉኝ ብለው አይደነፉም፡
ከዕውቀት ገበታ ጧትም ማታ አይጠፉም፡
መጓዝ የፈለገን አያወላከፉም፡
እኔን ምሰል ብለው ማንንም አይለክፉም፡
የሰለፍያ ልጅ ውድ የተውሒድ ፈርጦች
የወሎ ላይ ተክል የከሚሴ ምርጦች፡
ፈጥኖ የገባቸው የሰውነት ክብሩ፡
ጀግኖቻችን ናቸው አንበሳና ነብሩ፡
...በኑረዲን አል-ዓረብ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
በትዳርም ሆነ በጓደኝነት መካከል እየገባችሁ የምታራርቁ ምቀኛ፣ሸረኛ፣ተንኮለኛ ሰወች ተገሰፁበት ከክፉ ስራችሁ ተቆጠቡ ምንም አታተርፉበትም።
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
እያስተዋላቹህ!!ልታገባው ነበር ነገር ግን "ከታማኝ ምንጭ" ባገኘችው መረጃ ሰውዬው በገንዘቡም በጤናውም ሆነ በፀባዩ ለትዳር አይሆንም ። ከዚያም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሰውየው ማግባቱን ሰማች ። ማግባቱ አይገርምም ነገሩ ግን ወዲህ ነው ። ሰውየው ያገባው "ታማኝ ምንጯን" ነው
∙ አንዳንድ ጊዜ
መጨረሻ ነዉ ብለን እናስባለን ነገር ግን በድንገት አላህ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል።
=
t.me/https_Asselefya1Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ሚስት አለው!
~
→ በህይወት ጉዞ ላይ ልብ ያላሰበውን እንግዳ ያስተናግዳል፤ አንዳንዴም ባልተገባ ስፍራና ባልተፈቀደ ጊዜ ያርፋል። ልክ ለምለም መስክ መስሎት በጨው መሬት ላይ እንደበቀለ ዘር፣ ፍቅርሽ ወይም ፍቅርህ በሌላ ሰው የትዳር ክልል ውስጥ ሲገኝ፣ የነፍስ ጥማት ሳይሆን የህሊና እሳት ይሆናል። አንዳንዴ የራሱን ህይወት እየመራ፣ በራሱ ቃል-ኪዳን ታስሮ ለሚኖር ሰው ልባችሁን ትሰጣላችሁ። ይህ ስሜት፣ እንደማይደርሱበት ኮከብ እያዩ ሌሊቱን በናፍቆት እንደሚያነጋ ተጓዥ፣ መንገዳችሁን አጨልሞ፣ እርምጃችሁን ያግተዋል። ወይ የራሳችሁን ጎጆ አልቀለሳችሁ፣ ወይ ከዚህ የሀሳብ እስር ቤት አልተፈታችሁ። ይህ ስቃይ፣ የብቸኝነት ጩኸት ብቻ ሳይሆን፣ ከባድ የኢማን ፈተና ነው።
• ይህ ስሜት ሲጀምር ንፁህ ሊመስል ይችላል፤ የአንድን ሰው መልካም ስብዕና፣ ፈገግታ፣ ወይም አቀራረብ መውደድ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ይህ መውደድ ድንበሩን አልፎ ያ ሰው የሌላው እንደሆነ እየታወቀ ወደ ጥልቅ ፍቅር ሲቀየር፣ ጦርነቱ ይጀምራል። ይህ ጦርነት በልብህና በአዕምሮህ መካከል የሚደረግ ነው። አዕምሮህ «ይህ አይሆንም፣ ሀራም ነው፣ የሌላ ሰው ንብረት ነው» ሲል፣ ልብህ ደግሞ በስሜት ታውሮ «ግን እወደዋለሁ/እወዳታለሁ» ይላል።
በዚህ የውዥንብር ሰዓት ነው ሸይጣን እንደ ቀበሮ ሾልኮ የሚገባው። ስቃይህን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ፣ የሀራምን መንገድ በውብ ቃላት ያስውብልሃል። እንዲህ ሲል ይሸነግልሃል፦
• «ምን ችግር አለው? ፍቅርኮ ከፈጣሪ ነው። ስሜትህን መግለፅ አለብህ።»
• «ትዳሩ ደስተኛ ላይሆን ይችላል። አንተ/አንቺ ነህ/ነሽ እውነተኛ ደስታው/ደስታዋ።»
• «በጓደኝነት ስም ቀርበህ/ሽ ቀስ በቀስ የራስህ/ሽን ማድረግ ትችላለህ/ትችያለሽ።»
• «አንድ ጊዜ ብታገኘው/ኚውና ብትነጋገር/ሪ ምንም አያመጣም።»
እነዚህ ሁሉ የሸይጣን ጣፋጭ መርዞች ናቸው። አንዴ ከተቀመሱ፣ ወደ ከፋ የልብ ስብራት፣ የቤተሰብ መፍረስና ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደ አላህ ቁጣ የሚወስዱ አደገኛ መንገዶች ናቸው።
የአላህ ቃል የሆነው ቁርአን፣ ለዚህ ችግራችን ፍቱን መድኃኒት የሆነ ታሪክን ይተርክልናል። የነብዩላህ ዩሱፍ እና የዙለይኻ ታሪክ። ዙለይኻ ባለትዳር ሆና ሳለ፣ በቤቷ በሚሰራው በዩሱፍ ፍቅር ከቁጥጥሯ ውጭ እስክትሆን ድረስ ተይዛ ነበር። ፍቅሯ አይኗን አሳውሮ፣ ሀፍረቷን ገፎ፣ የተከለከለውን ነገር ለመፈፀም እስከመዘጋጀት አድርሷታል። ክፍሏን ዘጋግታ "ና" ባለችው ጊዜ፣ የነብዩላህ ዩሱፍ ምላሽ ለሁላችንም እስከ እለተ-ቂያማ ድረስ የሚደወል የኢማን ደወል ነው፦ (በአላህ እጠበቃለሁ!) ነበር ያሉት።
እርሱ የመረጠው ጊዜያዊ ደስታን ሳይሆን፣ የጌታውን ውዴታ ነበር። የዙለይኻን ውበትና ግፊት ከመከተል ይልቅ፣ የአላህን ፍራቻ አስበለጠ። በዚህም ምክንያት ለዓመታት በእስር ቤት መከራን ተቀበለ። ነገር ግን ለአላህ ብሎ በመታገሱ፣ አላህ ከእስር አውጥቶ የግብፅ ገዥ አደረገው፤ ክብርንና ጥበብን ሰጠው። ይህ የሚያሳየን ታላቅ እውነት አለ፦ "ለአላህ ብለህ አንድን ነገር የተውክ እንደሆነ፣ አላህ ከዚያ የተሻለውን ይተካልሃል።" የሚለው የውዱ የነብያችን ሐድስ።
ይህንን የልብ ምርኮኝነት አሸንፎ ወደ ነፃነት ለመውጣት፣ ልክ እንደ ነብዩሏህ ዩሱፍ በአላህ መታገዝ ያስፈልጋል። ከዚህ አይነት መጥፎ ስሜት ከምንወጣባቸው ነገሮች መካከል፦
① ዱዓ፦ ልቦች በአላህ እጅ ናቸው፤ እርሱ እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል። በእኩለ ሌሊት ተነስተሽ፣ በሱጁድ ላይ ወድቀሽ «ያ ሙቀሊበል ቁሉብ፣ ሰቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ» (አንተ የልቦች ገላባጭ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ) በማለት ዱዓ አድርጊ።
«ጌታዬ ሆይ! ይህንን ከልቤ አውጣልኝ፤ በምትኩም አንተን የምወድበትንና አንተን ለሚወድ ሰው የሚኖረኝን ሀላል ፍቅር ለግሰኝ» ብለሽ አልቅሺ።
② ሁሉንም የግንኙነት በሮች ዝጊ፦
ቁስል እንዲድን ከተፈለገ መንካትን ማቆም ግድ ነው። የዚያን ሰው ፎቶ ማየት፣ በማህበራዊ ሚዲያ መከታተል፣ ዜናውን መስማት፣ አልፎም ሊገኝበት በሚችልበት ቦታ መገኘት፣ እሳቱን እንደማራገብ ነው። ስልኩን ማጥፋት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ ማገድን ጨምሮ ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች ሙሉ በሙሉ መቁረጥ የመጀመሪያውና ዋነኛው የመድኃኒቱ አካል ነው።
③ ለአላህ ብለሽ ተይው!፦ ይህንን ስሜት የምትተይው "ስለማይረባ" ወይም "ስለማያምር" ሳይሆን፣ ለአላህ ብለሽ መሆን አለበት። ይህ ውሳኔ በራሱ ዒባዳ ነው። ወሏሂ!ይህንን ውሳኔ ስታደርጊ፣ አላህ በልብሽ ውስጥ ልዩ የሆነ የኢማን ጥፍጥናን፣ እርካታንና መረጋጋትን (ሰኪናን) ይሰጥሃሻል ። የሀራምን ደስታ ለአላህ ብሎ የተወ፣ አላህ የሀላልን ጣፋጭነት ያቀምሰዋል።
④ ልብህን በበጎ ነገር ሙላው!፦ ልብ እንደ ባዶ እቃ ነው። በበጎ ነገር ካልተሞላ፣ በክፉ ነገር መሞላቱ አይቀርም። ጊዜህን ዒባዳ ላይ አውለው። ሰላትን በወቅቱና በኹሹዕ ስገድ። ቁርአንን በተደቡር አንብብ። ዚክር አብዛ። የነብያቶችን ታሪክ አጥና። ልብህ በአላህ ፍቅር ሲሞላ፣ የሌላ ፍቅር ቦታ ያጣል።
⑤ የራስህን ህይወት ጀምር!፦ አላህ ትዳርን ትልቅ ተቋም ያደረገው እርጋታን፣ ፍቅርንና ምህረትን እንድናገኝበት ነው።አይንህን ወደ ሀላሉ በማዞር፣ ለአንተ ወደ ተፈቀደው የሕይወት አጋርህ ዞር በል። ይህንን የሀሳብ እስረኛነት ሰብረህ ስትወጣ አላህ ላንተ ያዘጋጀው የተሻለና የተባረከ የህይወት አጋር እንዳለ እመን።
በመጨረሻም ወዳጆቼ! ይህ ስሜት ሊያጠፋችሁ ሳይሆን፣ ሊያንፃችሁና ወደ ጌታችሁ ሊያቀርባችሁ የመጣ ፈተና መሆኑን ተረዱ።ማዕበሉ አልፎ የኢማናችሁ ፅናት ሲፈተን፣ ይበልጥ ጠንካሮችና ወደ አላህ የቀረባችሁ ሆናችሁ ትወጣላችሁ። የተሰበረ ልባችሁን ይዛችሁ ወደ እርሱ ተመለሱ፤ ጌታችሁ ከምንም በላይ ለተሰበሩ ልቦች ቅርብ ነውና።
📝𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧
|•|t.me/AbuSufiyan_Albenan
