Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 741
Obunachilar
+224 soatlar
+37 kunlar
-730 kunlar
Postlar arxiv
Repost from N/a
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግዢና ፋይናንስ ስራ ሂደት አዲስ በተገነባው ቢሮው በዛሬው እለት ስራውን ጀምሯል::
ኮሌጁ በሪፎርም ስራዎች እየሰራባቸው ከሚገኙ ስራዎች ውስጥ የስራ ቦታን ለሰራተኛው ምቹ የማድረግ ስራ የሚገኝበት ሲሆን ዛሬ ተመርቆ ስራ የጀመረው የኮሌጁ የግዢና ፋይናንስ ስራ ሂደት ቢሮም የዚህ ማሳያ ነው::
ይህ የስራ ክፍሎችን የማዘመና ምቹ የማድረግ ስራ በሌሎች የስራ ክፍሎችም ጭምር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ወደተቋሙ የሚመጡ ተገልጋዮችን ምቹ በሆነና በተቀላጠፈ መንገድ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ታቅዶ እየተሰራ የሚገኝ ተግባር ነው::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም
Repost from N/a
" እያመረትን እናሰለጥናለን እያሰለጠንን እናመርታለን " በሚል አዲስ ዕሳቤ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ስር የሚገኙ ሁለቱን የመንግስት ኮሌጆች ከስልጠና በተጨማሪ አምራችነታቸውን የሚያጠናክር የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በዛሬው ዕለት ተካሄደ።
" እያመረትን እናሰለጥናለን እያሰለጠንን እናመርታለን " ስንል ምን ማለታችን ነው?
ማሰልጠንና ማምረት ፣ማምረትና ማሰልጠን በአንድ ቦታ ማለትም በድሬዳዋ እና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆቻችን በተመሳሳይ ወቅት በማከናወን የማምረቻና የማሰልጠኛ መሣሪያዎች፣ አምራችና አሰልጣኝ ባለሙያ ፣ቦታና ጊዜ ተቀናጅተው የሚገኙበት ሲሆን በዚህም ቁሳዊና ሰብዓዊ ሃብቶችን በማቀናጀት እሴት በመጨመር ሃብት ማፍራት ምንም የሚባክን ጊዜና ሃብት እንዳይኖር በማድረግ ድርብ ኃላፊነትን በማቀናጀት ምርት በማምረት/አገልግሎት በማቅረብ ገቢ ማግኘት የሚያስችል ነው፡፡
በዚህም መርሃ ግብር ላይ የየድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፤ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋን ጨምሮ የአስተዳደሩና የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፤ የኮሌጅ ዲኖች፤ አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Endi mavjud! Telegram Tadqiqoti 2025 — yilning asosiy insaytlari 
