ch
Feedback
Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
1 743
订阅者
+224 小时
+37
-130
帖子存档
#ዜና| በፀሐይ ሀይል እየተገኘ ያለው ለውጥ እና ስኬት ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ #DireTvአማርኛ | መጋቢት 25 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአድራ (ADRA) ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በሶላር (በፀሐይ ሀይል )የሚሰሩ የተለያዩ የምርት ውጤቶችን የሚያስገኙ መሳሪያዎችን በመስራት በይፋ አስመርቆ ሥራ አስጀምሯል። በወቅቱም ከጀርመን እና ከኢትዮጵያ አድራ የመጡ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ፤ የኮሌጁ አመራሮች እና ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመጡ ኃላፊዎች የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑት በማህበር የተደራጁ ሰራተኞችም ተገኝተዋል። በምርቃት መርኃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ወደ ኮሌጁ ከመጣ በኋላ መጀመሪያ ላይ በፀሐይ ኃይል ( በሶላር ) የሚሰራ ወፍጮ በመስራት ይፋ ማድረጉን አስታውሰው አሁን ደግሞ ለኮሌጁ እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሚጠቅም በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የውሃ መሳቢያ ፓንፕ ፣ የዘይት መጭመቂያ መሳሪያ እና የተለያየ አካል ጉዳት ያለባቸው በማኅበር ተደራጅተው የሚጠቀሙበት የመኪና ማጠቢያ (ላቪያጆ ) በመስራት ርክክብ እንዳደረጉ ገለፀዋል። ዲኑ አያይዘውም በተለይ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፀሐይ ኃይል የወጣው ውሃ ኮሌጁ የነበረበትን ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት ችግር ቀርፏል ነው ያሉት። ውሃውም ከኮሌጁ አልፎ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ብሎም በግቢው ውስጥ በመኪና አጠባ ሥራ ለተደራጁት ማኅበራት የስራ እድል መፍጠር የተቻለበት አቅም ፈጥሯልም ብለዋል። ዲኑ አድራ ኢትዮጵያም ድጋፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። የአድራ ኢትዮጵያ ዳሬክተር ዶ/ር ዘሪሁን አዋኖ በወቅቱ እንደገለፁት የድሬዳዋ ኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፀሐይ ኃይል አጠቃቀም በኩል በገጠርም በኮሌጁም እየደረገ ያለው ስራ እጅግ በጣም የሚበረታታ ነው ብለዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘውም የፀሐይ ኃይል ማመንጫውን በዘላቂነት ለመጠቀም ኮሌጁ በአጫጭር ስልጠና ያስተማራቸውን የሶላር ጥገናና ተከላ ባለሞያዎችንም በማፍራት በማህበር በማደራጀት ወደስራ ማስገባቱ የሚደነቅና ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ብለዋል። ይህም በፀሐይ ሓይል የሚሰራ ስራ መቀጠል አለበት በማለት ጨምረው ገልፀዋል። የጀርመኑ አድራ ዳሬክተር አቶ ዳዊት መሐሪ በድሬዳዋ ኢትዮጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያየነው ተጨባጭ ተግባር ተደስተናል። በቀጣይም በሌላ ፕሮጀክት አብሮነታችን ይቀጥላል ብለ፥ ይህ ስራም ኮሌጁ ከራሱ አልፎ አሁንም ለሌሎች መትረፍ አለበት በማለት አሳስበዋል። በመርኃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይም በፀሐይ ኃይል የሚሰሩት መሳሪዎች ርክክብና ስራ ማስጀመሪያ ፊርማ የተከናወነ ሲሆን እንዲሁም በመኪና አጠባ ለተደራጁት አካል ጉዳተኞች የስራ ማስጀመሪያ የሚሆን አጫጭር ስልጠና ስልጥነው ያጠናቀቁበት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ለድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የባዮሜዲካል ሰልጣኝ ተማሪዎች በቀዝቃዛ ሰንሰለት የሚሠሩ የህክምና መሣሪያዎች (ColdChain equipment management) ቅድመ-ሥራ ላይ ሰልጠና ተሰጠ። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በቀዝቃዛ ሰንሰለት የሚሠሩ የህክምና መሣሪያዎች (ColdChain equipment management) ቅድመ-ሥራ ላይ ሰልጠና ለባዮሜዲካል ሰልጣኝ ተማሪዎች ሰልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ የተገኙት በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፈውስ ህክምና ተሃድሶ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዶ ሙሜ ስልጠናውን በአብሮነት ለሰልጣኞች እንዲሰጥ ያደረጉትን ጤና ሚ/ርን እና ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክን በማመስገን የባዮሜዲካል ዘርፍ ባለሞያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ አነስተኛ በመሆናቸውና የባለሞያ እጥረት በመኖሩ ሰልጣኞች በዚህ በየጊዜው እራሱን እያዘመነ ባለው የሞያ ዘርፍ ስልጠና መውሰዳችሁ ላለው የባለሞያ እጥረት በጥቂቱም ቢሆን መፍትሄ የሚሰጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ አብዶ ጨምረውም ሰልጣኞች ከወሰዳችሁት ስልጠና ባሻገር በግላችሁም በየጊዜው ከወቅቱ ጋር እራሳችሁን በማናበብና በዘርፉ ለአዳዲስ ነገሮች በማዘጋጀት የጤና ተቋማትን የባለሞያ ችግር በመፍታት በስነ-ምግባር የተቃኘ ሙያዊ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባችኋል ያሉ ሲሆን ቢሮውም በሚያስፈልጓችሁ ሞያዊ እገዛዎች ከጎናችሁ ይሆናል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው የምንሰጠውን ትምህርትና ስልጠናዎችን የሚደግፍ እንደ ጤና ቢሮ ያለ ተቋም ማግኘታችን እጅግ ዕድለኝነት ነው ያሉ ሲሆን ሰልጣኞች የባዮሜዲካል ስልጠናን ከጤና ቢሮ በመጡና በቀጥታ የሞያው ባለቤት በሆኑ ስልጠናውን ማግኘት ለሰልጣኞች የበለጠ አቅም የሚሰጥ መሆኑንና ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና መሰረት በማድረግ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድና ተከታታይነት ያለው አገልግሎት በመስጠት እራሳቸውን ሊያበቁ እንደሚገባም ተናግረዋል አቶ ታደለ። በስልጠናው የተሳተፉ ተማሪዎች በበኩላቸው በተሰጣቸው ስልጠና ደስተኞች መሆናቸውንና በተለይ በጤና ተቋማት በተማሩበትና ጤና ቢሮ ባመቻቸላቸው ዕድል በሰለጠኑበት የሞያ ዘርፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ለተገባላቸው ቃል በማመስገን በቀጣይም ጤና ቢሮና ኮሌጃችን መሰል ስልጠናዎችን የምናገኝበትን ሁኔታዎች እንዲያመቻቹልን እንጠይቃለን ብለዋል። ስልጠናው ከክፍል ባሻገር በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንደነበር የስልጠናው አስተባባሪዎች ተናግረዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን 21/07/2018 ዓ.ም

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና ሰራተኞች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚፆመውን የአብይ ፆም ምክንያት በማድረግ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ተገኝተው ከቅዳሴ ለሚወጡ ምእመናን ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ ከወዲሁ መልካም ምኞቴን መግለፅ እወዳለሁ። አ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ ከወዲሁ መልካም ምኞቴን መግለፅ እወዳለሁ። አቶ ታደለ አሰፋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን     #ኢድ_ሙባረክ!!

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ስራ ሂደቶች ክፍሎች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር አጠናቀቀ:: የ2018 የመጀመርያ ግማሽ አመት የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ በድጋፍና ክትትል ቡድኑ አማካኝነት ባለፉት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዚህም አጠቃላይ በኮሌጁ የሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎችን ተደራሽ በማድረግ በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል:: በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ ወቅት በኮሌጁ የሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶች፣ ደጋፊ ስራ ሂደቶች፣ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችን ጨምሮ አጠቃላይ የስራ ክፍሎችን ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በድጋፍና ክትትል ቼክሊስት መሰረት የተለዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እንዲሁም የተስተዋሉ ውስነቶችንም ለማሻሻል የሚያግዝ ግብረ-መልስ ለስራ ሂደቶችና ክፍሎች ተሰጥቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 9/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የታላቁ ረመዳን ወር ፆምን ምክንያት በማድረግ የኮሌጁ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት የተካፈሉበት የኢፍጣር መርሃ-ግብር በተቋሙ አካሄደ::  ይህን መሰል የኢፍጣር መርሃ-ግብር እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር አብሮነት እና እንድነት የሚፀባረቁበት ልዩ ትዕይንት መሆኑን የተገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም ይህን መደጋገፍና በህብረት መቆምን በሁሉም መስኮች ላይ ጠብቆ ማስቀጠል ይገባል ያሉ ሲሆን ይህን ልዩ የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላዘጋጁ እንዲሁም ለተሳተፉ የኮሌጁ ማህበረሰብና አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል።  በኢፍጣር መርሃ-ግብሩ ላይ የስራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጃችን አመራርና ሰራተኞችን ጨምሮ ሰልጣኝ ተማሪዎችም የተሳተፉበት የአብሮነት መርሃ-ግብርም ነበር ። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 8/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተዳደሩ ከአራቱም ክላስተሮች ለተወጣጡ ወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ:: ስልጠናውን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ከአራቱም የገጠር ክላስተሮች ለተወጣጡ 20 ለሚሆኑ ሰልጣኞች በህይወት ክህሎት፣ በመሰረታዊ ቢዝነስ አያያዝ እንዲሁ በካይዘን ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ሰልጣኞችም ላለፉት ሳምንታት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ የተሰጣቸው ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ማጠናቀቅም ችለዋል:: በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ለሰልጣኞች መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ ይህ ስልጠና ወጣቶቹ ከዚህ በፊት በኮሌጁ የወሰዱትን የMarketing based sanitation concrete slab training በአግባቡ ስራ ላይ እንዲያውሉ የሚያግዛቸው መሆኑን ገልፀው ወጣቶች እዚህ ያገኟቸውን ክህሎቶች በየአካባቢያቸው የሚስተዋሉትን መሰረታዊ ችግሮች በመቅረፍ የሚፈጠርላቸውን የስራ እድል በእግባቡ መጠቀም ይገባቸዋልም ብለዋል:: በአስተዳደሩ የጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዩሱፍ ሰኢድ በበኩላቸው መሰል ስልጠናዎችን ለአስተዳደሩ ወጣቶች አዘጋጅተው ወደ ኮሌጁ ሲመጡ ምንግዜም ፈጣን ምላሽ ከኮሌጁ እንደሚያገኙ አስታውሰው ለዚህ ስልጠና መሳካት ጉልህ ሚና ለተወጡ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን እና አመራሮችም ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለወጣቶቹም የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል:: በመድረኩ ማጠቃለያም ስልጠናውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ወጣቶች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 3/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ