ar
Feedback
Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 746
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+67 أيام
-230 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+9

photo content
+9

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ዋሂል ክላስተር በSolar PV Installation & Maintenance ስልጠናዋን ተከታትላ ላጠናቀቀች ወጣት በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) ድጋፍ አደረገ:: ድጋፉ በዋናነት በBMZ ADRA, Germany አማካኝነት የተገኘ ሲሆን ይህም 1.1 KW የሚያመነጭ የSolar PV System ዝርጋታ እና በሶላር የሚሰራ ማብሰያ ምድጃ(Solar Cooker) ያካተተ እንደሆነም ተገልፇል:: በፕሮጀክቱ ድጋፍ የተደረገላት ወጣት ፎዚያ ባጋጠማት የአካል ጉዳት ሳትበገር ከምትኖርበት ከዋሂል ክላስተር ጁጁማ ወረዳ ተነስታ ኮሌጅ ድረስ ለስድስት ወራት 20 ኪሎ ሜትሮችን እየተመላለሰች ስትሰለጥን የቆየች ብርቱ ሴት ስትሆን የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክትም የዚህችን ወጣት ድካም በመረዳት በአካባቢዋ የራሷን ቢዝነስ ሰርታ ገቢ ምታገኝበትን የSolar PV System ዝርጋታ እንዲሁም በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) በድጋፍ መልክ አበርክቷል:: የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በSolar PV Installation Maintenance ወጣቶችን አሰልጥኖ የሙያ ባለቤት ከማድረግም ባሻገር ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊ ድጋፎችን ሁሉ በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ያስታወሱት የADRA Germany ዋና ሀላፊ አቶ ዳዊት መሀሪ ሲሆኑ በድሬዳዋ ገጠር ክላስተር ላይ ለእህታችን ፎዚያ የተደረገው ድጋፍም ፕሮጀክቱ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽና አካታች መሆኑን ማሳያ ከመሆኑም በተጨማሪም የፕሮጀክቱ ከላይ እስከታች የሚገኙ ሀላፊዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ የመስራት ድምር ውጤት እንደሆነም ገልፀዋል:: ወጣት ፎዚያ በበኩሏ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከብዙ ድካም እንግልት እንዳሳረፋት በመግለፅ በተደረገላት ድጋፍም የተለያዩ ገቢዎችን በማመንጨት የራሷንም ሆነ የቤተሰቦቿን ህይወት እንደምታሻሽል የገለፀች ሲሆን በአጠቃላይ ይህ ድጋፍ እውን እንዲሆን ያደረጉ ለADRA ፕሮጀክት ሀላፊዎችንና አስተባባሪዎች በሙሉ ምስጋናዋን አቅርባለች:: በእለቱ በነበረው የድጋፍ ርክክብ ላይ የADRA Germany, የADRA Ethiopia ሀላፊዎች እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና የኮሌጁ አመራሮች በቦታው ተገኝተው የተደረገውን ድጋፍ ውጤታማነት የተመለከቱ ሲሆን ወጣቷንም አበረታተዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

photo content
+9

#ዜና| በፀሐይ ሀይል እየተገኘ ያለው ለውጥ እና ስኬት ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ #DireTvአማርኛ | መጋቢት 25 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከአድራ (ADRA) ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በሶላር (በፀሐይ ሀይል )የሚሰሩ የተለያዩ የምርት ውጤቶችን የሚያስገኙ መሳሪያዎችን በመስራት በይፋ አስመርቆ ሥራ አስጀምሯል። በወቅቱም ከጀርመን እና ከኢትዮጵያ አድራ የመጡ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ፤ የኮሌጁ አመራሮች እና ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመጡ ኃላፊዎች የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑት በማህበር የተደራጁ ሰራተኞችም ተገኝተዋል። በምርቃት መርኃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ወደ ኮሌጁ ከመጣ በኋላ መጀመሪያ ላይ በፀሐይ ኃይል ( በሶላር ) የሚሰራ ወፍጮ በመስራት ይፋ ማድረጉን አስታውሰው አሁን ደግሞ ለኮሌጁ እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሚጠቅም በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የውሃ መሳቢያ ፓንፕ ፣ የዘይት መጭመቂያ መሳሪያ እና የተለያየ አካል ጉዳት ያለባቸው በማኅበር ተደራጅተው የሚጠቀሙበት የመኪና ማጠቢያ (ላቪያጆ ) በመስራት ርክክብ እንዳደረጉ ገለፀዋል። ዲኑ አያይዘውም በተለይ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፀሐይ ኃይል የወጣው ውሃ ኮሌጁ የነበረበትን ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት ችግር ቀርፏል ነው ያሉት። ውሃውም ከኮሌጁ አልፎ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ብሎም በግቢው ውስጥ በመኪና አጠባ ሥራ ለተደራጁት ማኅበራት የስራ እድል መፍጠር የተቻለበት አቅም ፈጥሯልም ብለዋል። ዲኑ አድራ ኢትዮጵያም ድጋፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። የአድራ ኢትዮጵያ ዳሬክተር ዶ/ር ዘሪሁን አዋኖ በወቅቱ እንደገለፁት የድሬዳዋ ኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፀሐይ ኃይል አጠቃቀም በኩል በገጠርም በኮሌጁም እየደረገ ያለው ስራ እጅግ በጣም የሚበረታታ ነው ብለዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘውም የፀሐይ ኃይል ማመንጫውን በዘላቂነት ለመጠቀም ኮሌጁ በአጫጭር ስልጠና ያስተማራቸውን የሶላር ጥገናና ተከላ ባለሞያዎችንም በማፍራት በማህበር በማደራጀት ወደስራ ማስገባቱ የሚደነቅና ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ብለዋል። ይህም በፀሐይ ሓይል የሚሰራ ስራ መቀጠል አለበት በማለት ጨምረው ገልፀዋል። የጀርመኑ አድራ ዳሬክተር አቶ ዳዊት መሐሪ በድሬዳዋ ኢትዮጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያየነው ተጨባጭ ተግባር ተደስተናል። በቀጣይም በሌላ ፕሮጀክት አብሮነታችን ይቀጥላል ብለ፥ ይህ ስራም ኮሌጁ ከራሱ አልፎ አሁንም ለሌሎች መትረፍ አለበት በማለት አሳስበዋል። በመርኃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይም በፀሐይ ኃይል የሚሰሩት መሳሪዎች ርክክብና ስራ ማስጀመሪያ ፊርማ የተከናወነ ሲሆን እንዲሁም በመኪና አጠባ ለተደራጁት አካል ጉዳተኞች የስራ ማስጀመሪያ የሚሆን አጫጭር ስልጠና ስልጥነው ያጠናቀቁበት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

photo content
+9

photo content
+9

ለድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የባዮሜዲካል ሰልጣኝ ተማሪዎች በቀዝቃዛ ሰንሰለት የሚሠሩ የህክምና መሣሪያዎች (ColdChain equipment management) ቅድመ-ሥራ ላይ ሰልጠና ተሰጠ። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በቀዝቃዛ ሰንሰለት የሚሠሩ የህክምና መሣሪያዎች (ColdChain equipment management) ቅድመ-ሥራ ላይ ሰልጠና ለባዮሜዲካል ሰልጣኝ ተማሪዎች ሰልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ የተገኙት በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፈውስ ህክምና ተሃድሶ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዶ ሙሜ ስልጠናውን በአብሮነት ለሰልጣኞች እንዲሰጥ ያደረጉትን ጤና ሚ/ርን እና ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክን በማመስገን የባዮሜዲካል ዘርፍ ባለሞያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ አነስተኛ በመሆናቸውና የባለሞያ እጥረት በመኖሩ ሰልጣኞች በዚህ በየጊዜው እራሱን እያዘመነ ባለው የሞያ ዘርፍ ስልጠና መውሰዳችሁ ላለው የባለሞያ እጥረት በጥቂቱም ቢሆን መፍትሄ የሚሰጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ አብዶ ጨምረውም ሰልጣኞች ከወሰዳችሁት ስልጠና ባሻገር በግላችሁም በየጊዜው ከወቅቱ ጋር እራሳችሁን በማናበብና በዘርፉ ለአዳዲስ ነገሮች በማዘጋጀት የጤና ተቋማትን የባለሞያ ችግር በመፍታት በስነ-ምግባር የተቃኘ ሙያዊ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባችኋል ያሉ ሲሆን ቢሮውም በሚያስፈልጓችሁ ሞያዊ እገዛዎች ከጎናችሁ ይሆናል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው የምንሰጠውን ትምህርትና ስልጠናዎችን የሚደግፍ እንደ ጤና ቢሮ ያለ ተቋም ማግኘታችን እጅግ ዕድለኝነት ነው ያሉ ሲሆን ሰልጣኞች የባዮሜዲካል ስልጠናን ከጤና ቢሮ በመጡና በቀጥታ የሞያው ባለቤት በሆኑ ስልጠናውን ማግኘት ለሰልጣኞች የበለጠ አቅም የሚሰጥ መሆኑንና ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና መሰረት በማድረግ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድና ተከታታይነት ያለው አገልግሎት በመስጠት እራሳቸውን ሊያበቁ እንደሚገባም ተናግረዋል አቶ ታደለ። በስልጠናው የተሳተፉ ተማሪዎች በበኩላቸው በተሰጣቸው ስልጠና ደስተኞች መሆናቸውንና በተለይ በጤና ተቋማት በተማሩበትና ጤና ቢሮ ባመቻቸላቸው ዕድል በሰለጠኑበት የሞያ ዘርፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ለተገባላቸው ቃል በማመስገን በቀጣይም ጤና ቢሮና ኮሌጃችን መሰል ስልጠናዎችን የምናገኝበትን ሁኔታዎች እንዲያመቻቹልን እንጠይቃለን ብለዋል። ስልጠናው ከክፍል ባሻገር በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንደነበር የስልጠናው አስተባባሪዎች ተናግረዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን 21/07/2018 ዓ.ም

photo content
+9

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና ሰራተኞች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚፆመውን የአብይ ፆም ምክንያት በማድረግ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ተገኝተው ከቅዳሴ ለሚወጡ ምእመናን ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ ከወዲሁ መልካም ምኞቴን መግለፅ እወዳለሁ። አ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ ከወዲሁ መልካም ምኞቴን መግለፅ እወዳለሁ። አቶ ታደለ አሰፋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን     #ኢድ_ሙባረክ!!

photo content
+7

photo content
+9

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ስራ ሂደቶች ክፍሎች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር አጠናቀቀ:: የ2018 የመጀመርያ ግማሽ አመት የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ በድጋፍና ክትትል ቡድኑ አማካኝነት ባለፉት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዚህም አጠቃላይ በኮሌጁ የሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎችን ተደራሽ በማድረግ በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል:: በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ ወቅት በኮሌጁ የሚገኙ ዋና ስራ ሂደቶች፣ ደጋፊ ስራ ሂደቶች፣ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችን ጨምሮ አጠቃላይ የስራ ክፍሎችን ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በድጋፍና ክትትል ቼክሊስት መሰረት የተለዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እንዲሁም የተስተዋሉ ውስነቶችንም ለማሻሻል የሚያግዝ ግብረ-መልስ ለስራ ሂደቶችና ክፍሎች ተሰጥቷል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 9/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7