ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

前往频道在 Telegram

ይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው። በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ! @noahtoael for anything https://telega.io/c/Noahtoaels_Idea I blog about marketing and sales Buy ads: https://telega.io/c/Noahtoaels_Idea

显示更多
3 410
订阅者
无数据24 小时
+237 天
+4230 天
帖子存档
እቺን ቃል ንገሯት ተፈርዶብኝ እንጂ መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል ሀገሬው ምድር ላይ እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል ዞር ባለች ቁጥር አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት ልቻለው ብዬ እንጂ : ምሳሌ ከምሆን አፍቅሮ ከማጣት። ገደል ግቢ በሏት ይሄው ደግሞ ዛሬ ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው የእጇን አይበሉባ በቄንጥ አኮናትራ ሰአቷን አየችው ገናነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው መንቀር አለችና መስታወት ፊት ቆመች ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና። : ማርያምን ታምራለች ዘከርኳት በወዳጅ መከርኳት በዘመድ ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ ገደል ግቢ በሏት ልቤን ከጋረደው ወዳጅ እንደ እደማ/በት ከከለላት ስውር አይነጥላ እንዲ እዳማረባት ገደል ግቢ በሏት : ልቤን ከጋረደው ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነጥላ መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰውጥላ ልክ እደገላዋ ይለስልስ መንገዱ ፍፁም አይጎርብጣት አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት እንደ ጥርሷ ንጣት እያልኩኝ ፎክሬ እንደ ገጣሚ ቃል ልቤ አልጀነጅን የት አባቷን እና በፀበል ካልወጣች ትረሳለች በጅን። : ገደል ግቢ በሏት የት አባቷን እና እንዲህ የሚያምርባት የት እናቷን እና እንዲህ የሚደምቅባት ገደል ግቢ በሏት እስከ መቼ ድረስ ስቀባ እኖራለው ጉድፍ ልቧን ስኩል ገደል ግቢ በሏት እኔ ገደል ስር ነኝ ድንገት ከወደቀች እንድቀበላት። ✍️ አስታወሰኝ ረጋሳ

语音消息02:01

ሄራን-10- "ተመለከት አሁን ራሴን ያስቀመጥኩበትን ቦታ!ዛሬ ላለሁበት ቦታ ራሴም ትልቅ ድርሻ ነበረኝ።ከስህተቷ የማትማር ሴት መሆኔ ለሌላ ክህደት አጋልጦኛል።በህይወት ውስጥ በተለይም በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ተቋርጦ ለቆየ ፍቅር ሁለተኛ እድል መስጠት ሪስክ አለው።በመለያየት ውስጥ ሁለቱም ወገኖች ለጊዜውም ቢሆን ሌላ ግንኙነት ጀምረው መቆየታቸው አይቀርም።ታድያ ደግመው ሲገናኙ እንደመጀመሪያው ሊሆኑ አይችሉም።የሁለቱም አይን ሌላ አይቷል።ሌላ ገላ፣ሌላ ማንነት፣ሌላ ሰው ምናምን•••   እኔን ውሰድ።ጥሩ ህይወት መኖር ስጀምር ለመጀመሪያው ፍቅረኛየ ማድላቴ ባሌን እንድክድ አደረገኝ።አሳዘንኩት።ልቡን ሰበርኩት።ለበፊቱ ሁለተኛ እድል ስሰጥ ብዙ ነገር አበላሸሁ።ከዛስ ክህደቴ አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ ዋጋ አስከፈለኝ።ይሄው መጨረሻየ እዚህ ሆነ" መሬቱን እየደበደበች በቁጭት ነው የምታወራው። "እባክሽ አትማረሪ" "ሌላ የሚያሳፍር የህይወቴን ክፍል ልንገርህ?ግን ይቺ ቀሽም እንዳትለኝ" "በጭራሽ አልልሽም ንገሪኝ" "ሁሉ ነገር ተበለሻሽቶ ስራም ትቼ ቤት በተቀመጥኩበት ሰአት የማይሆን ነገር ውስጥ ልገባ ውሳኔ ላይ ደረስኩ።ቂ ጤን ሲያዩ ምራቃቸዎን የሚውጡ ወንዶችን እያስከፈልኩ ተኝቻቸው ለምን ዳሌየን አልመነዝረውም ስል የሞኝ ሀሳብ አሰብኩ።ተቸግሮ ከመኖር ይሻላል ሲል ሰይጣን በጆሮየ ሹክ አለኝ።ከማከክ መሸር ሞጥ ይቀላል አለኝ።እሺ አልኩት።ተጣጠብኩ፤ልብሴን ቀያይሬ ቦሌ ሄጄ መንገድ ላይ ራሴን ለሽያጭ አቀረብኩ።ምን የመሰለች መኪና የያዘ ሸበቶ ሰውየ ከሁሉ ቀድሞ ስንት እንደማወጣ ጠየቀኝ።አምስት ሺ አልኩት።ጀማሪ መሆኔ ገብቶታል ሳይከራከረኝ መኪናው ውስጥ አስገብቶኝ አንድ ቆንጆ ሆቴል ወሰደኝ።ውስኪ ጋበዘኝ።ተጎነጨሁ፤እራት በላን።የታሸገ ባለ ሃምሳ ብር አቀበለኝ።የኔ ቦርሳ ጡት ማስያዣየ ነው።ብሩን ጡቶቼ መካከል አስቀመጥኩት።   በመጨረሻ ውብ ወደሆነ መኝታ ክፍል ይዞኝ ገባ።ቀድሜ ወደ መታጠቢያ ቤት መግባት እንደምፈልግ ነግሬው መታጠቢያ ቤት ገባሁ።ልብሶቼን አወላልቄበረጅሙ መስታወት ውስጥ ራሴን አየሁት።ጡቶቼ ያምራሉ፤ዳሌየ ያምራል፤ለራሴ ሳሳሁላት።አንቺ ሴት ያንቺ ዋጋ አምስት ሺ ብር አይደለም አልኳት።አንቺ ውድና የከበርሽ ሴት ነሽ አልኳት።ተቀየርኩ።ልብሴን መልሼ ለብሼ ወደ ሼባው ተመለስኩ።የሰጠኝን ገንዘብ ፊቱ ላይ ወርውሬ በጥድፊያ ከዛ ስፍራ ተሰወርኩ።ደግሜ እራሴን ለእርድ አላቀረብኩም" "ውሳኔሽ ትክክለኛ ነበር" "ድህነትን የሚያክል አዋራጅ ነገር የለም።ሆኖም ራስን ከመሸጥ በላይ አያዋርድም።እኔ ብዙ ቅንጦት የምፈልግ ሴት አይደለሁም።በቀን አንዴ ከበላሁና በቀን የምቅማትን ብቻ ነው ምፈልገው" "እስከ መቼ?" "እስከምሞት ልበልህ?የተሻለ ነገ ቢኖረኝ፣ብማር፣ብሰራ እኮ አልጠላም።ግን እነዚህ ነገሮች ለኔ ርቀውብኛል።ስለዚህ ከድህነት ጋር ተስማምቼ አንተ ትብስ አንቺ ትብስ እየተባባልን እንኖራለን።አንዳንዴ በጣም ሲቸግረኝ በድህነቴ ላይ አጉረመርማለሁ" "ያንቺ ቦታ እዚህ አይመስለኝም" "እና የት ነው የኔ ቦታ?ቤተመንግስት?" "እየቀለድኩ አይደለም።በምንም አይነት ከድህነት ጋር ተዳብሎ መኖር ጤነኝነት አይደለም" "ኦኦ አንተ ስትወጣ አብሮኝ ከሚቀረው ደባሌ ጋር አታጣላኝ" "ሌላ ስራ ብፈልግልሽ አትሰሪም?" "ባክህ እንደዚህ የሚሉ ሰዎች ውለታቸው እንዲመለስላቸው የሚፈልጉት አልጋ ላይ ነው።እኔ ደግሞ ደክሞኛል። "እባክሽ ቁምነገር መሀል አትቀልጂ።ስራ ልፈልግልሽና ስራ ስሪ" "ውለታህን መመለስ ግን አልችልም" "አልገባኝም!" "እንጋደም ብትለኝ አልስማማ!በውለታ መታሰር አልፈልግም" "እውነት እልሻለሁ በጭራሽ እንደዚህ ያለ ነገር አላስብም!" "እንደዛ ከሆነ እሺ ፈልግልኝና እሰራለሁ" •••ደስ ብሎኛል።ይቺን የመሰለች ንፁህ ሴት ትንሽ ደግፎ ወደ አልሆነ አቅጣጫ እንዳትጓዝ መሞከር እርካታ ይሰጣል።ልለያት ስል የተወሰኑ ድፍን ብሮች አጠገቧ አስቀመጥኩ።አልቀበልህም ብላ ተከራከረችኝ።ያደረክልኝ ነገር ከአቅሜ በላይ ሆኗል አለች።በመጨረሻ የመጀመሪያ ደሞዟን ስትወስድ የሚመለስ እዳ ሆኖ እንዲመዘገብ ተስማምተን ገንዘቡን ወደ ቦርሳዋ(ጡት ማስያዣዋ)ከተተች••• ይቀጥላል•••          ዮሓቶኤል!

“እንዴት ፍቅርን ትፈራለህ?” ብላ ጠየቀችኝ። “ፍቅርን አልፈራም…” አልኳት። “እንግዲህ ምን ትፈራለህ?” “አንድን ሰው ከልብ መውደድን… ከዚያም እሱ ሲሄድ ያለኝን ሁሉ ማጣትን ነው የምፈራው።” ትን
“እንዴት ፍቅርን ትፈራለህ?” ብላ ጠየቀችኝ። “ፍቅርን አልፈራም…” አልኳት። “እንግዲህ ምን ትፈራለህ?” “አንድን ሰው ከልብ መውደድን… ከዚያም እሱ ሲሄድ ያለኝን ሁሉ ማጣትን ነው የምፈራው።” ትንሽ ዝም አለችና፣ “እኔ ብሄድስ?” አለችኝ። እኔም ፈገግ ብዬ፣ “ለዚህ ነው እንግዲህ እንዳልወድሽ ራሴን ሳሳምን የነበረው…” አልኳት። እሷ ግን ዝም ብላ እጄን ያዘችኝ። ያኔ ነው የተረዳሁት፤ አንዳንዴ ፍቅርን መፍራት ሳይሆን፣ የምትወደውን ሰው ማጣትን መፍራት ነው።
🤎

ግዜ የማይፈታው ችግር የለም የሚባለው እውነት አይደለም። አንዳንድ ነገሮችን ውሳኔ እንጂ ግዜ አይፈታቸውም ለመወሰን የፈራችሁት ነገር ምናልባት ትክክለኛው ውሳኔ ሊሆን ይችላል።😇
ግዜ የማይፈታው ችግር የለም የሚባለው እውነት አይደለም። አንዳንድ ነገሮችን ውሳኔ እንጂ ግዜ አይፈታቸውም ለመወሰን የፈራችሁት ነገር ምናልባት ትክክለኛው ውሳኔ ሊሆን ይችላል።😇

እግዚአብሔር ዝም ካላችሁ ያላችሁበትን ሁኔታ ታልፉታላችሁ ማለት ነው።አንዳንዴ እግዚአብሔር፦ እየጸለይን መልስ እየፈለግን እንኳን ዝም ይለናል። የጸለይነው ስለማይጠቅመን ወይም የመመለሻው ግዜ ገና ስለሆነ አይደለም!። እንደሚያልፍ እና እንደምናልፈው እርሱ ስለሚያውቅ ነው። ካለፍነው በኋላ የነበርንበት ሁኔታ ምን ያክል ትንሽ እንደሆነ እና ለዛ ነበረንዴ እንደዛ የሆንኩት እንደምንል ስለሚያውቅ ነው። አልፋችሁ ታዩት የለ ብሎ ዝም ይለናል። እግዚአብሔር ሁሌም ቢሆን አዋቂና መልካም ነው ዝም ካላችሁ ደስ ይበላችሁ አልፋችሁ ስለምታዩት ነው።🤍

1 Yr 365 Days On Oct 5 my life totally Shifted into Something I can't even Know

ሮማን ከፊቱ ፤ የፊያሚታ ጊላይ መቃብር ከኋላው ፤ በመካከላቸው ቆሞ ቀረ ። በመጨረሻ ሰው ብቻውን ነው ፤ብቸኛ ነው ። ብቸኛነት ተሰማው ። ልቡ የኃዘን አንጉርጉሮ አንጎራጎረ ። ልቡ የኃዘን አንጉርጉሮ የማያንጎራጉር ሰው አለ ይሆን? ግን ልናዳምጠው አንፈልግም ። ለምን ? ደስተኞች መሆን እንፈልጋለን ። ተስፋ ከመቁረጥ ተስፋ ማድረግ ይሻላልና ባናገኘውም ቅሉ ዘላለም እንሻዋለን ። ዘላላማዊ ተስፋ ፤ የኃዘንና የእንጉርጉሮ። ሰው ያለትስፋ ምንድነው? ተስፋ በልባችን ማሳደር አለብን ፤ ተስፋ በሌለበት ቦታም ቢሆን ። ኦሮማይ፦ ገጽ 371

በርግጥ ምን እንደምፈልግ ታውቂያለሽ? ሰላም ነው የምፈልገው፣ ሰላም ስጡኝ፣ ማንም እንዳይረብሸኝ ስል መላዋን ዓለም ላንድ ሳንቲም ብሽጣት ቅር አይለኝም፡፡ ሻይ መጠጣቴን በመተው የሰውን ዘር ሁሉ ከኩነኔ ማዳን ቢቻለኝ እንኳን ሻይዬን አግኝቼ ፍጡር ገሃነም ሲገባ ማየት እንደምመርጥ ታውቂያለሽ???   📖 :~ The notes from under ground

ካነበብኩት
ካነበብኩት

"መቼ ነው እዚህ ደረጃ የደረስነው? እንዴት እንደዚህ ሆንን?ምኑ ጋር ነው የተሳሳትኩት?ምኑ ጋር ነው ልክ የሆንከው? የትኛው መንገዳችን ላይ ነው መንታ መንገድ የገጠመንና ሌላ አቅጣጫ መርጠህ የሄድክብኝ? ምን የተሻለ አጋጠመህ? ደስተኛ ሆንክ? " "ምንም የምልሽ ነገር የለም በቃ እዚህ ላይ ይብቃን።ለሁለታችንም የሚሻለው ይሄ ነው።" "ለምን ምንድነው የተፈጠረውን የማትነግረኝ?ለምን በዝምታ ትቀጣኛለህ? አትወደኝም?ፍቅርህ አለቀ?እንዲህ በድንገት የሁለት አመት የህይወት ጉዞ ይቋጫል? ቀልድ ነው ሰውን ሜዳ ላይ ጥሎ መሄድ? ዝም አትበል ንገረኝ" እንዴት ነው ከጓደኛሽ ጋር አድሬ በአንድ ቀን ስህተት እምነትሽን አጉድያለሁ ብዬ የምነግራት? እንዴት ተብሎ ነው አንችን በያዝኩበት እጄ ሌላ ሴት ለዛውም ጓደኛሽን ያዝኩ አቀፍኩ ብዬ አይኗን እያየሁ የምነግራት?የሷን ምህረት ለመጠየቅ ከአፌ እንዴት የይቅርታ ቃል ማውጣት ይቻለኛል? ይህን እውነት ነግሬያት ከምትሰባበር "ለአንች ያለኝ ስሜት ቀንሷል"ብላት ይሻላል አዎ አንዳንድ እውነቶች ለተናጋሪው እረፍት ለሰሚው ህመም ከመሆን በቀር ሌላ ትርፍ የለውም....          ዮሓቶኤል

ክፋትም፡በልባቸው፡እያለ፡ከባልንጀራቸው፡ ጋራ፡ሰላም፡ከሚናገሩት፡ጋራ፡አትጣለኝ። መዝ፦27፥3
ቸር ዋሉ ።

የደማስቆ ምርኮኛ ነኝ የተሸነፍኩ፤ ፍቅሩ ሰብሮ የጠገነኝ የተፈወስኩ፤ ማሳደጃ ደብዳቤዬን ከእጄ ጥሎ፤ ዳሶኝ ሄደ በልቤ ላይ ወንጌል ተክሎ። ኀጢአተኛዎችን፡ሊያድን፡ክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ወደ፡ዓለም፡መጣ፡የሚለው፡ቃል፡የታመነና፡ዅሉ፡ እንዲቀበሉት፡የተገባ ነው፤ከኀጢአተኛዎችም፡ዋና፡እኔ፡ነኝ፤ ስለዚህ፡ግን፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡ለማግኘት፡በርሱ፡ያምኑ፡ዘንድ፡ላላቸው፡ሰዎች፡ምሳሌ፡ እንድኾን፥ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ዋና፡በምኾን፡በእኔ፡ላይ፡ትዕግሥቱን፡ዅሉ፡ያሳይ፡ዘንድ፥ምሕረትን፡አገኘኹ። ብቻውን፡አምላክ፡ለሚኾን፡ለማይጠፋው፡ለማይታየውም፡ለዘመናት፡ንጉሥ፡ምስጋናና፡ክብር፡እስከ፡ ዘለዓለም፡ድረስ፡ይኹን፤አሜን።🤍 1ኛ ጢሞቲዮስ፦1፥15-17

አንዳንዴ . . . ያለ ነው! አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም! አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም! አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም! አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም! አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም! አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዝም! አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አያቅተንም! አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም! አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም! አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!!!

ሄራን -9- •••ጭካኔ የሚመነጨው ከየትኛው የሰውነታችን ክፍል ነው?ፍቅርስ?ቀናነትስ የሚጠነሰሰው ምናችን ውስጥ ነው?ሰዎች ሲወለዱ ንፁህ ናቸው።ታድያ ሲያድጉ ክፉ ወይም ደግ የሚሆኑት ከየት ተምረውት ነው?በእርግጥ የሁላችንም የመጀመሪያ መምህራኖቻችን ወላጆቻችን ናቸው።ከእነሱ የምንወርሰው በርካታ ነገር መኖሩ እሙን ነው።በተቃራኒው ደግሞ ከመጥፎ ቤተሰብ ጥሩ ከጥሩ ቤተሰብ መጥፎ መፈጠሩም የተለመደ ነው••• •••እኔም ስልኩን ይዤልሽ እመጣለሁ ባልኳት ማግስት ጨካኝ ሆንኩ።ራስወዳድነት አጠቃኝና ቀርቼባት ስለ እኔ እንድታስብ ላደርጋት ፈለግኩ።ስለዚህም ተኝቼ እኩለ ቀን ድረስ አረፈድኩ።ምሳ ሰአት ሲደርስ ግን ጭካኔየ ቅጥ ማጣቱ ተሰማኝ።ከመኝታየ ተነስቼ በቀጥታ ወደ ቤቷ አመራሁ።ስደርስ ረከቦት ስር የሚቀመጥ የእጅ ስራ ይዛ ስትወጣ አገኘኋት••• "ወዴት ነው?" እየጠበቅኩህ ነበር።አርፍደሃል ስለዚህ እነዚህን ልሸጥ እየወጣሁ ነው" •••ቅር ብሏታል።ተከፍታለች።በሀዘን ውስጥ ሆና አየችኝ።ያመጣሁላትን ስልክ አቀበልኳት።በቸልተኝነት ተቀበለችኝና••• "እስከምመለስ እዚሁ ትጠብቀኛለህ?" "አትሂጂ!" "ምን እበላለሁ?" እንዳዘንሽብኝ አውቃለሁ።በጣም ስላረፈድኩብሽም ይቅርታ።አሁን ስልክሽን አብሪውና አብረን እንውጣ።እነሱን ነገ ትሸጫቸዋለሽ" •••ቅሬታዋ በአንዴ ተገፎ ወደ ቀድሞ ሁኔታዋ ተመለሰች።እቃዎቹን አስገባች።ተያይዘን ወደተለመደው ቦታ ስናመራ••• "አናደኸኝ ነበር።ከቤት እንዳልወጣ ያስጠነቀቅከኝ ራስህ ነህ።መጥተህ እንዳታጣኝ ብዬ ትእዛዝህን አከበርኩ።ስትቀር ከፋኝ" "ይቅርታ ብየሽ የለ?" "ሚስትህ ናት ያዘገየችህ?" "ሚስት እንደሌለኝ ነግሬሽ ነበርኮ" "አላመንኩህማ!" "ቁጥርሽን መውሰድ እችላለሁ?" "ከባሌ ጋር ስሆን መደወል ግን አይቻልም" እየቀለደች መሆኑ ገብቶኛል። "ቀሪ ታሪክሽን ቀጥይልኛ?" "ቁርስ ሳልበላ ነው ስጠብቅህ የዋልኩት።በአጭሩ ሆዴ ባዶ ሆኖ አቅም አንሶኛል" *** •••ከሰዓት በኋላ የለመደችውን ገዛዝተን ቤቷ ተመለስን።ታሪኳን ቀጠለች••• "ከመምህሩ ባሌ ጋር አንድ አመት በጥሩ እንክብካቤ ሰራተኛ ተቀጥሮልኝ እየኖርኩኝ ያለፈ ታሪኬን በረሳሁበት ሰአት ስህተት ሰራሁ።ሲያቀብጠኝ አረብ ሃገር የሄደውን ፍቅረኛየን ፈለግኩትና አገኘሁት።ድጋሚ ስላገኘኝ ተደሰተ።ስልኬን ተቀብሎ ደወለልኝ።ድሬዳዋ ተመልሶ ነበር።ነገር ተበላሸ።ባሌ ስራ ሲሆን ቀን ቀን ማውራት ጀመርን።ማግባቴን ብነግረውም እሱ ወደ ኋላ ሊመልሰኝ ፈለገ።ሊያግባባኝ ጣረ።በድየሻለሁ አለኝ።በጣም መቀጣቱን ነገረኝ።ረስቼሽ አላውቅም አለኝ።ፍቅሩ በነበረበት እንዳለ ሊያሳምነኝ ሞከረ።ሴት አይደለሁ?በመጨረሻ በቃላቶቹ ልቤ ቀለጠች የበፊቱ ነገር ውል አለብኝ።ይሄኛውን ባሌን ችላ ብየ ወደዛኛው አዘነበልኩ።    ከዛ አዲስ አበባ ሳይነግረኝ መጣ።ላግኝሽ አለኝ።አገኘሁት።ሳገኘው የተሰማኝን ስሜት በቃላት ልገልፅልህ አልችልም።ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን።ወደ ቤቴ ስመለስ ቤቴ ደበረኝ።ባሌን መጥላት ጀመርኩ። ስንተኛ የማስበው ያኛውን ሆነ።አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ።ከዛኛው ጋር አብሬ ለመሆን ተነሳሳሁ።ባሌን ለመለያየት እንደምፈልግ ነገርኩት።ሳይበድለኝ፣ሳያስከፋኝ በክህደት ጎድቼው ወደ ድሮ ፍቅረኛየ ተመለስኩ።    ሌላ ህይወት ተጀመረ።በተገናኘን ሰሞን ካሳ በሚመስል መልኩ አነገሰኝ።እየሰነበተ ሲሄድ ግን ሰይጣናዊ ማንነቱ ተገለጠ።ለበቀል ነበር አመጣጡ።አጉል ሊያረገኝ ነበር አመጣጡ።አንድ ቀን ሰክሮ•••" ይቀጥላል•••        ዮሓቶኤል!

የንባብ ጥምዎን እያያረኩ ከክፍል ወደ ክፍል የሚያሻግሩ ተከታታይ ታሪኮችን ይፈልጋሉ? በታሪኮቹ መሳጭነት ተመስጠው ሰዓታት ቢያልፉብዎ፣ እንቅልፍ ቢረሱ፣ ንባብ ማቆም ቢያቅትዎ… እኛ ተጠያቂ አይደለንም! 😄 የምርጥ ተከታታይ ታሪኮች መገኛ የሆነውን ቻናላችንን በ መቀላቀል በምናብ አለም አለሞን ይርሱ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Fiction_123

ባሻዬ! ሆስፒታል ሄጄ ዶክተሩ ሁለት መድኃኒቶችን አዘዘልኝ። ሁለተኛውን መድሃኒት ወዲያውኑ አገኘሁት። መጀመሪያ ላይ የተጻፈውን አንደኛውን መድኃኒት ግን 13 ፋርማሲዎች ዞሬ አጣሁት። ድራጊስቶቹ ያሉኝን ልንገርህ፣ አንዱ "መድኃኒቱ ዛሬ የለም። ነገ ላምጣልህ" አለኝ፣ ሌላው "ይህንን መድኃኒት የሚያመርተው ካምፓኒ ተዘግቷል። ሌላ ካምፓኒ ያመረተውን ተመሳሳዩን ልስጥህ?" አለኝ፣ ሌላው ደግሞ "ይሄንን መድኃኒት ብዙ ሰው ይፈልገዋል። አሁን ከተማ ውስጥ አይገኝም። በብላክ ላምጣልህ?" ብሎ አስደነገጠኝ። አንዱ ግን "ይሄ መድኃኒት ለካንሠር ህሙማን የሚሰጥ መድኃኒት ነው። ካንሠር የያዘው ቤተሰብ አለህ?" ሲለኝ በጀርባዬ ልወድቅ ስል ግድግዳውን ተደግፌ ተረፍኩ። በመጨረሻም ያዘዘልኝ ዶክተር ጋ ሄጄ  "መጀመሪያ ላይ የጻፍከውን መድኃኒት ፈልጌ አጣሁት" ስለው፣ ወረቀቱን ተቀበለኝና እንዲህ አለኝ "አቶ ተሰፋዬ! ይሄ እኮ የመድኃኒት ስም አይደለም።  እስክሪብቶዬ አዲስ ስለሆነ እንዲጽፍልኝ የሞከርኩበት ነው" ብሎ ወረቀቱን ቀዶ ጣለው። ባሻዬ! . . ባልተጻፈ ህግ ሰው በሚሞትበት አገር በተጻፈ ወረቀት ብሞትብህ እንዳይደንቅህ። ፋርማሲስቶቻችን ለዘላለም ይኑሩ!!!🤍🙌

እንዳንድ ምሽቶች ስለ እግዜር መኖር መጠየቅ አቆምና ከናካቴው የነገሮች መኖር በራሱ ምን ማለት እንደሆነ ማሰብ እጀምራለሁ፤ ለዚች አጭር ሕይወት ለምን እንደተፈጠርኩ፤ ለምን እንዳውቅ እንደተፈረደብኝ.
እንዳንድ ምሽቶች ስለ እግዜር መኖር መጠየቅ አቆምና ከናካቴው የነገሮች መኖር በራሱ ምን ማለት እንደሆነ ማሰብ እጀምራለሁ፤ ለዚች አጭር ሕይወት ለምን እንደተፈጠርኩ፤ ለምን እንዳውቅ እንደተፈረደብኝ... ምንአልባት ዩኒቨርስ መልስ የለው ይሆናል። ምናልባት ከዝምታው ጀርባ ምንም ድምጽ የለም፣ ምንም የሚገኝ ትርጉም የለም። እና ግን አሁንም አለሁ። እንደነቃሁ ነኝ። እየተነፈስኩ ነው። ጨለማው ላይ አፍጥጫለሁ። ምንአልባት ህልውና ይሄው ይሆናል... ...አላፊ እንደሆንክ እያወቅክ መኖር...🌘